የሕዳሴ ግድብን የውኃ ሙሌት ጊዜ እንደተራዘመ የሚገልፁ ዘገባዎች ሐሰት ናቸው ተባለ

106130661 3699719330057371 506901847750790851 n

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን በተመለከተ አል አህራም፣ አልጀዚራና ሮይተርስ እያሠራጩ ያለው ዘገባ ትክክል አለመሆኑን አስታውቋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የውኃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይከናወናል፡፡

‘‘የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም ግልጽ ነው፤ ዓለማቀፍ ሕግጋትንም እናከብራለን’’ ያሉት አምባሳደር ዲና ግድቡን ለመገንባት የማንም ፈቃድ እንዳልተጠየቀው ሁሉ ለውኃ ሙሌቱም ፈቃድ እንደማያስፈልግና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ አል አህራም፣ ሮይተርስ እና አልጀዚራ የተሰኙ የመገናኛ ብዙኃን የውኃ ሙሌቱ ሦስቱ ሀገራት ስምምነት እስኪደርሱ እንደተራዘመ አስመስለው የዘገቡት ዘገባ የተሳሳተና የጋራ አቋም ያልተያዘበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ – አብመድ

1 Comment

  1. አባቶቻችን ” ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” ይሉ ነበር። ይህን የአሉበት ምክንያት ልክ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን ከ ግብፅ በመነጨ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንደተደናገጥንው
    ማለት ነው። የ ኢትዮጵያ መንግሥት፣ የ ህዝቦችን ጉጉት በመገንዘብ፣ በአስቸኳይ መረጃዎችን ቢያቀርብልን ኖሮ የብዙ ሰዎችን የጨጓራ መቃጠል ይታደግ ነበር። ለወደፊቱ ቢታሰብበት መልካም ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.