የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣና ሀይቅን ከእንቦጭ ለመከላከል 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

Tana 3“ጣናን እንታደግ” በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ድንበር የለሽ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት በተከናወነ መርሃግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ የገንዘብ ድጋፉን ለአማራ ክልል አስረክበዋል ።

ኢንጅነር እንዳወቅ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ጣና ሃይቅ ለአማራ ክልሉ ብቻ ሳይሆን የአገር ሀብት ነው ብለዋል።

ጣና ላይ የተጋረጠውን አደጋ በዘላቂነት ለማስወገድ እና
የእንቦጭ መጤ አረሙን ለማስወገድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ከመንግሥት በተጨማሪ መላው ህብረተሰብ ርብርብ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ኢንጅነር እንዳወቅ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በጣና ሐይቅ ላይ የተጋረጠውን የእንቦጭ አረምን ለመከላከል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢንጅነር እንዳወቅ ገልፀዋል ።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ
በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የጣና ሀይቅን ከእንቦጭ አረም ለመከላከል እና በደንበር የለሽ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የከተማዋ ወጣቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ በክልሉ ስም አመስግነዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.