የፕ/ር ብርሀኑ እና የመስከረም ቆይታ በአጭሩ በእኔ እይታ – ደሱ አሰፋ

meskermመስከረም፡ የአማራ ብሄረተኝነት የተፈጠረው ኢትዮጵያዊ ብሄረተኛ ነኝ የሚለው ደህንነቱን ስላላስጠበቀለት ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ በብዛት በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት የማውቃቸው ሰዎች ዛሬ በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ተስፋ ስለቆረጡ ነው የአማራን ብሄረተኝነት የሄዱት?

ፕ/ር ብርሀኑ፡ እንደኔ እምነት አሁን ያሉት የኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ሀይሎች በቂ አይደሉም የሚል ሰው ካለ ነገርግን በምንም ተአምር እምነቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሰረተ የሆነ ሰው ማድረግ ያለበት የአማራ ብሄረተኛ ድርጅት መመስረት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት እምነቱ ላይ ሆኖ ሌላ ደህነነቴን ያስጠብቅልኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ብሄረተኛ ድርጅት መመስረት ነው፡፡

አቋረጠቸው

መስከረም፡ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እኮ እንዲሁ አይመጣም በእድሜ፤ በማንበብ በምንም ነው፡

ፕ/ር ብርሀኑ፡ አይደለም ወዴት ነገሩን ሺፍት የምታደርጊው ሁለቱንም ነገር ይዘሽ እኮ መሄድ አትችይም፡ ህብረ ብሄራዊነት ነው የጎዳን ነው የሚል የአማራም ይሁን ማንም ብሄረተኛ ወደ ብሄሩ መሄድ ይችላል፤ ነገርግን የአማራ ብሄረተኝነት ለሀገር ይጠቅማል አንቺ እንደምትይው የምንል ከሆነ

አቋረጠችው፡

መስከረም፡ ለመሆኑ በብሄር ተደራጅቶ ለሀገር የሚጠቅም አለ እንዴ?

ፕ/ር ብርሀኑ፡ እንዴ መስከረም ለምን ነገሩን ትደበላልቂዋለሽ፤ ያልሽኝን በደንብ ስሚ፤ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊቱ ያምናል

አቋረጠችው፡

መስከረም፡ ያምን ነበር

ፕ/ር ብርሀኑ፤ ቆይ አሁንም አያምንም ነው የምትይኝ?

መስከረም፤ አያምንም ማለት አልችልም ምክያቱም አሁን ስለህዝብ ማውራት አንችልም

ፕ/ር ብርሀኑ፤ ቆይ ቆይ እስኪ፤ የአማራ ማህበረስብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ከሆነ እኔ ያምናል የሚል በሙሉ እምነት አለኝ፤ በኢትዮጵያዊነት የሚያምን ማህበረሰብ ሀገሩ፤ ይሄ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር፤ በእነዚህ በብሄር በመጡ ሀይሎች የምትናጥበት እና እንደ ሀገር መኖሩ ጥያቄ ውስጥ በሚገባበት ግዜ፤ አሁን አንቺ እንደምትይው ወይ ኢትዮጵያ የራሷ ጉዳይ እኔ ወደ ራሴ ብሄር እገባለው ብሎ ከገባ፤ ያኔ ለእኔ በኢትዮጵያዊነት ላይ ተስፋ ቆርጠሀል ማለት ነው፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ! (የመጨረሻ ‹መጣጥፍ›)

አቋረጠቸው፤

መስከረም፤ እኔ የበለጠ ሪ ፍሬዝ ላድርገው ኢትዮጵያ የምትባለዋ ሀገር አማራውን የበለጠ ዋጋ አስከፈለችው

ፕ/ር ብርሀኑ፤ አማራ ብቻ አይደለም መስዋእትነት የከፈለው፤ በመረጃ እና በዳታ የምናወራ ከሆነ በወያኔ ግዜ ከሆነ እና ማነው የተፈናቀለው በቁጥር ብዙ የሚለውን ለመወያየት አንቺ እንደ ጋዜጠኛ ማድረግ የነበረብሽ ቁጥር ሰርተሽ ማን ነው በዚህ ግዜ የተፈናቀለው፤ ወይንም ማንው ብዙ በደል የደረሰበት የሚለውን በዴታ እንጂ

አቋረጠቸው፤

መስከረም፤ መፈናቀል ብቻ እኮ አይደልም ሎስ ያደረገው የስነ ልቦና የሊሎችም ተጠቂ የሆነው እንደ አማራ የለም

ፕ/ር ብርሀኑ፡ ቆይ ውይይቱን እኮ ሺፍት እያደረግሽው ነው፤ቆይኝ፤ የመፈናቀል፤ የመበደል፤ ጉዳይ ከሆነ አንዱ ልታወሪ የምትችይው በዴታ ነው፤ እኔ የማውቀው በትክክል ይሄ ነው የሚል የለኝም ነገርግን ያልተፈናቀለ የኢትዮጵያ ማህበርሰብ አለ ብዬ አላምንም፤ ሶማሊያ ክልል የተፈጠረውን በደል የትም ቦታ አልተፈጠረም፤

አቋረጠቸው፤

መስከረም፤ አውቃለው እሱን

ፕ/ር ብርሀኑ፤ እይው የትም አልተፈጠረም ፤ የሱማሌ ማህበረሰብ የተገደለውን የተረገጠውን የተደፈረውን ያህል የትም አልተደረገም፤ የአማራም ክልል እንደዛ አልሆነም፤ በመፈናቀል ቁጥር የተፈናቀለውን ኦሮሞ ያህል የአማራ ክልል እንደዛ አልሆነም፤ በአንድ ግጭት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነው የተፈናቀለው ፤ አየሽ አሁን መከራከሪያው ማን የበለጠ ተበድሏል ከሆነ ችግር አለ

አቋረጠቸው፤

መስከረም፤ እኔ አንተ አትረዳውም ብዬ አይደለም እንደው ጭቅጭቅ ጭቅጭቅን እየወለደ ስለመጣ እንጂ፤ አሁን በሱማሌ አንድ ሰውዬ ርእሰ መስተዳድር ሆነ ያመጣው ችግር እና ከ1966 ጀምሮ ስልጣን የያዘ አካል ጠላቴ ብሎ የተነሳበት የአማራው ብሄረሰብ እኩል ነው ብለን ካሰብን ይሄ ስህተት ነው፤ አማራው የተባለው ማህበረሰብ እንደ ጠላት እየታየ ለትግራይ ሴቶች ድህነት ሳይቀር ተጠያቂ ነው እየተባለ የኖረ ማህበርሰብ እና እነዚህ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚደረጉ መፈናቅሎች እኩል ናቸው ብዬ አላስብም፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃብታሙና ሳዲቅ: ሕወሓት | የአዜብ መተንፈስ | የሳሞራ የኑስ እጣና ሌሎችም

ከዚህ በኋላ መስከረም ብርሀኑ እንዲመልስ እድል አልሰጠችውም አቋረጠቸው፤ ከዚያም በመቀጠል እንደውም ይሄ ነገር ግዜያችንን ስላባከነ ጊዜያችንን አናቃጥል በማለት መልስ እንዲመልስና የሷን ዝባዝንኬ ውሸት በድጋሚ በመረጃ እና በሎጂክ አፈር ድሜ እንዳያበላባት አፉን አዘግታ የውይይቱን አቅጣጫ እንደገና መንገድ አሳተቸው፤

በነገራችን ላይ መስከረም በጣም ችኩል፤ ደረቅ፤ ስሜታዊ፤ እና በጥራዝ ነጠቅ እውቀት የምትመራ ከመሆኗም ባሻገር ለመማር ፈቃደኛ ያልሆነች ሁሉን አውቃለው ባይ ናት፤ ግና ምን ዋጋ አለው በዚህ ሁሉ እንግዳዋን ግራ የማጋባት እና ከአንዱ ቅጠል ወደ አንዱ እንደ አበደ ፌንጣ እየዘለለች ብትዘባርቅም፤ እንግዳዋ ፕ/ር ብርሀን ነጋ እንደምንም የታሰረችበትን የድንቁርና ገመድ በስሜት ከሚወዛወዝበት ንፋስ እያስጣለ በእግሯ እንድትቆምና መፈጠሯን እስክትጠላ ድረስ እና የቆመችበት መሬት ውስጥ ተቆፍራ መቀበር እስክትመኝ ድረስ ተራ የአሉባልታ እና የተረት ተረት ድሪቶዋን በመረጃ፤ በእውቀት እና በሰከነ ሳይንሳዊ ውይይት እፊቷ ላይ እየቀዳደደ እርቅኗን አስቀርቷቷል፤

መቼም የዚህ ውይይት ዋናው ማሰረጊያው ያለው ይሄ በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ ያለ አንዴ እራሱን ፓለቲካኛ፤ አክቲቪስት፤ ጋዜጠኛ፤ የፓለቲካ ተንታኝ እያደረገ በተራ አሉባልታ እና በጥራዝ ነጠቅ እውቀት ድንቁርናውን ሲተረተር የሚውል ሁሉ፤ እርግጠኛ ነኝ እንደ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ አይነት ግለሰቦች ጋር ቀርቦ እንኪያ ሰላምቲያ ለመግጠም አፉን አሞጥሙጦ ከመቅረቡ በፊት “የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወተም” እንደሚባለው የመንስከረምን በራሷ ሜዳ ላይ በዝረራ መውደቅ ተመልክቶ እንደ አቅሙ ሲሆን ሲሆን መረጃዎችን በቅጡ አጠናክሮ አሊያም እጁን ወደ ላይ እንደ ሰንደቅ አላማ ሰቅሎ ፕ/ር እባክሆን ያስተምሩኝ ብሎ ለመቅረብ መዘጋጀት አለበት ብዬ አምናለው፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያለማስታረቅ ጥቅም? (አሁንገና ዓለማየሁ)

መስከረምም በጣም በሳል መሆን ከፈለገች ሁለተኛ እንዲህ አይነት ድፍረት እንደማትሞክር ተስፋ አለኝ፡፡

አዎ እውቀት ይለምልም፡ ምክንያታዊነትን ያብብ፤ አሉባልታ እና ሀሜት ይውደም፤

ሀገራችንን አላህ በእውቀት እና በልምድ የምትመራ ያድርግልን

9 Comments

 1. If you base your arguments on knowledge, reason, and facts as Prof did, you can face the devil, let alone this novice young lady, which I trust is genuine inside. Let us encourage her to learn how to behave like a journalist, i.e, ask questions, without trying to ‘convince’ the interviewee. It appears she was determined to ‘change’ Dr. Birhanu in a single interview, which was an attempt in vain. I admired his patience and understanding, which is a role expected of a leader, like him. I raise my hat to both!, the student and the teacher.

 2. ውድ ደሱ አሰፋ፣
  ብዙዎች “ጋዜጠኞች” ራሳቸውን ለማስተዋወቅ እንጂ በቂ ዝግጅት አያደርጉም፣ ብቃቱም የላቸው! ፕሮፌሰር ብርሃኑን በግል ቡና እየጠጡ እንደዚያ ማነጋገር ትችል ይሆናል፤ በሆነ ጒዳይ ላይ የእርሳቸውን አሳብ ለሕዝብ ለማስተላለፍ ከሆነ ግን እርሳቸው የሚሉትን በትክክል መዘገብ ግዴታ አለባት፤

  አባይ ሚድያ እና የመሳሰሉት ዩቱብ ጋዜጠኞች በዋነኛነት አታካሮ የሚፈጥሩት ክሊክ አድርገን ፍራንክ እንዲለቅሙ ብቻ ነው። ሌላኛው ጒዳይ፣ ብዙዎቹ ውጭ አገር ከሚያዩት ቀድተው ስለሆነ፣ ድርጊታቸውን ከስነ ምግባርና ከባህል አኳያ አይመዝኑትም። መስከረም “ሃርድ ቶክ” ላይ ያየችውን በፕሮፌሰሩ ላይ መሞከሯ ይመስላል! ትርፉ ለርሷ ቅሌት፣ ለአድማጭ ደግሞ ድንቊርና ነው!

 3. ደሱና ጓደኞቹ በተለይም ደሱ የጻፍከዉንም የ ዶ/ር ብርሀኑ ቃለ መጠይቅንም ደግሜ ሰማሁት። እንደእዉነቱ ከሆነ ጽሁፍህ ኢዜማ ዉስጥ የስራ ማመልከቻ ማስገባት ነዉ የመሰለኝ።
  በመሰረቱ ብርሀኑ በማንኛዉም ቃለ ምልልስ ለህዝብ በሚያቀርበዉ መልእክቶች ማለት የፈለገዉን ሳንረዳ የግንቦት 7 አባሎቹ አጨብጭበዉ አስጨብጭበዉ ምንም ዉጤት ሳይገኝ ይበተናል። ወዳጄ ስለ ብርሀኑ የምታስበዉን ሳይሆን የሰጠዉን ቃለምልልስ ተመልከተዉ እላይ የሰጠዉን አስተያየት እታች ሲንደዉ ታያለህ። ተቆንጥጦ ሲያዝ ደግሞ ማለቴ ይልሀል ገፋ ሲል ደግሞ ጥያቄዉ መሆን የነበረበት እንዲህ ነዉ ይልሀል። ከእንደዚህ አይነት ሰዉ ምንም አይነት ምክንያታዊ ዉይይት ማድረግ አይቻልም ዘባራቂ ነዉ ብሎ ከማለፍ ባሻገር። አማራን በተመለከተ ብርሀኑ/ ነአምን/አንዳርጋቸዉ የአማራ ጥላቻቸዉን ደብቀዉት አያዉቁም። ኢሳት ያዘጋጀዉን የተለያዩ ኮነፍረንሶችን መመልከት ነዉ። እላይ ወያኔን ከሚጥል ሀይል ጋር እንሰራለን ይልሀል ኦነግን ጨምሮ እታች የአማራን ብሔረተኞች እንቃወማለን ይልሀል ይህን እንዴት ታስታርቃለህ።፡የሚያጭበረብርበት ዴታ ላይ የተመሰረተ አይለም ይልሀል እሱ ዴታን እንደጠቀሰልህ ሁሉ። ይልቅ የምትጠይቀዉ ቅርበት ካለህ ከዉጭ መጥቶ ሀገር ቤት እንደ ጥጃ ሲታሰሩ ሲፈቱ ከኖሩት በላይ ቀድሞ የኢዜማ ዋናዉ ሰዉ የሆነዉ?

  የመስከረም ስህተቷ ለጥያቄ ጋብዛዉ ብርሀኑ ጠያቂ ሁኖ ፕሮግራሟ ላይ ሲጋልብባት ማስቆም ነበረባት የዉይይቱ ስነ ስርአት መካሔድ የነበረበት የፋና ብሮድካስቲንግ ትንታግ ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን በሚባል ልጅ አይነት ስልት ብርሀኑ ተወጥሮ መያዝ ነበረበት እንደዚህ ካልሆነ ያሰበዉን ማወቅ አይቻልም አጨናግፎ ከዉይይቱ ይሰናበታል።

  ሌላዉ ሳይታወስ ሊታለፍ የማይገባዉ የመስከረም አበራ ጉዳይ ነዉ በብርሀኑ ቃለ መጠይቅ ደሱ እንዳለዉ ሳይሆን ብርሀኑ ሀሳብ እየፈራ ይሸሻል ያደናግራል እንጂ አስተማሪና ሀሳብ አመንጭ ሁና የተገኘችዉ መስከረም አበራ ነበረች። መስከረም አበራ በኢትዮጵያ የሀሳብ ልእልና ቦታዋን የያዘች ነች ከዛ ዝቅ የሚያደርጋት ነገር የለም አንተም የፈራሃት ጉዳዩ ሌላ ነዉ። እኛ እንኳን ቀደም ሲል በየዋህነት ነገርን ሳትረዳ እነ አንዳርጋቸዉን እላይ መስቀሏ ነበር ይኸዉ ጊዜዉን ጠብቆ ማን ማን እንደሆነ ታወቀ።
  ለማንኛዉም ብርሀኑ ኦሮምያም ሆነ ትግራይም ሆነ ሌሎች ክልሎች ድርሺ ማለት ስለማይችል አንዷለም አራጌን ይዞ ወደ አማራ ክልል ሂዶ አንድ የፓርላማ መቀመጫን ማትረፍ ነዉ። በተረፈ ብርሀኑ ፕሮፌሰር የሚባለዉን ቅጥያ ይዞ ደከማ ጋዜጠኞችን ታክኮ የሚያላግጥበት ሁኔታ መቆም አለበት። ስለ ትምህርቱ ነገር እንደ ግራዝማችና ደጃዝማች የህይወት ሙሉ ሹመት ነዉ ብሎ የሚያስበ ካለ ተሳስቷል።፡ብርሀኑ ከእዉቀት ከተፋታ ረጂም ጊዜ ሁኖታል ሶሻል ሳይንስ በየአመቱ 25% ስለሚቀንስ ሰዉየዉ የማንበብና የመመራመር ልምድ ስለሌለዉ ይህን ምሁር ነኝ በሚለዉ ነገር ባይታበይም መልካም ይመስለኛል።

  ደሱም የሰጠዉን መልስ ለፋና ብሮድካስት የሰጠዉን ቃለ ምልልስና በየቦታዉ የሰጠዉን ዲስኩር ሌላ ሰዉ እንዳደረገዉ አድርገህ አዳምጠዉ አእምሮህን በምክንያት ቃኘዉ። ያልተቀለደብን የለም አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ሳምንት ቀረን 500 ዶላር አምጡ እያሉ ስንቱን ነዉ ጉድ የሰሩት። ሆድ ይፍጀዉ ብርሀኑ ለሀገር መበተን አሳቢ ይመስላል እናንተ ከፖለቲካዉ ከተሰናበታችሁ አገር ተመልሶ አንድ ይሆናል ብቻ አረጋዉያኑ ዉጡልን።

 4. ሰመረ
  አሳብህን እጋራለሁ:: ባለፉት 30 አመታት በኢትዮጵያ አማራ ሆነህ ካልተፈጠርክ መገለሉና መዋረዱ እምብዛም ላይታይህ ይችላል:: ይህ ነው የዶክተር ብርሀኑም ችግር:: ሆኖም ዶክተር ብርሀኑና አንዳርጋቸው ፅጌ ለአማራ ህዝብ ክፉ ያስባሉ ብዬ በጭራሽ አላምንም:: በዚህ ወቅት ኢዜማና አብን ተባብረው ቢሰሩ አማራም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ ይሆናል::ምክንያቱም 1. የሁሉም መዳረሻ ኢትዮጵያዊነት ስለሆነ 2. የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች በኢዜማና በአብን መካከል ምንም ልዩነት አያዩም:: 3. ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ብዙ ግምት ያልተሰጠው ውህድ ብሄር ህዝብ አለ:: ይህም የሚፈልገው አንድነት ነው:: በዚህ ወቅት እርስ በርስ ከሞበጫጨቅ መተባበር ይበጃል:: መስከረም አበራ የሰከነች አዋቂ ፀሀፊና አወያይ ነች::

 5. ለፀሐፊው
  ሁለት ክፍል ያለውን (በ internet) የመስከረምን ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁ። ብርሃኑ አትኩሮ የያዘው ውይይቱን አቅጣጫ እንዲለውጥ ብዙ ጥሯል ።በቁንፅል ከላይ እንደመረጃው ያቀረበው እንኳን ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆኑን የጥያቄውን ይዘቱን ሆነ ስሜት ለመቀየር የሚያደርገው ጥረት ነው።ጠያቂው የጠየቀውን ለመመለስ ይልቅ ” ጥያቄው መሆን ያለበት ” እያለ ለማደፍረስ ይፈልጋል። እንደ ኢሳት ጋዜጠኞች ገባሪ አለመሆኗን በደንብ ወጥራ ይዛው ፣እምቢ ሲልም እይቋረጠች ሞግታዋለች ።ትክክልም ነው። የኢዜማ መሪዎች ፣ ስምም ቢለውጡ ያው ግንቦት 7 ናቸው ።

 6. እዉነቱ ለኢትዮጵያ ሃሳቢ ቢሆኑ መች ከፋኝ ነገሩ ግን እንደዛ አይደለም። መቶ አለቃ አያሌዉ ደሴና አንዳርጋቸዉ በአንዳርገቸዉ ቲቪ ኢሳት ተጋብዘዉ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እሳቸዉ በኢትዮጵያ አንድነት የማያምን ፓርቲና ግለሰብ ጋር አብሬ መስራት አልፈልግም ብለዉ በአጽንኦት ሲናገሩ አንዳርጋቸዉ ግን በኢትዮጵያ አንድነት የሚለዉን አልሳማማበትም ነዉ ያላቸዉ። ትላንት ጸረ ኢትዮጵያን ሀይሎችን ኢትዮጵያ ብለዉ ስሟን መጥራት ከሚጠየፉ ሀይሎች ጋር በታላቅ ፍቅር አብረዉ ይሰሩ ነበር ይህ በሚዲያ ላይ ጊዜ ወስዶ ጎግሎ መመልከት የሚቻል ነዉ። አንዳርጋቸዉ/ብርሀኑ/ነአምን የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስባቸዉ ሳይሆን የራሳቸዉ አጀንዳ ያላቸዉ ናቸዉ ወደሗላ ተጉዘህ ብታይም የሚያሳየዉ ያንኑ ነዉ።

 7. Write your comment…አቶ ደሱ አሰፋ!
  ምነው መስከረም እና ዶ/ር ብርሃኑን ጥየቄ እና መልስ ሳይሆን በጦርነት ላይ ያሉ ሁለት አገር ሰዋች ፕሮፌሽናል ቦክስ ሪንግ እንደገቡ አንተም የአንዱ ወገን ይሆንክ መሠልክ፡፡ እንዲህ አይነት ፍጹም ጥላቻ የተሞላበት አስተያዪት እንዲሰጥበት አይደለም የዝግጅቱ ዐላማ፡፡ ዶ/ር ብርኑም እንዲህ አይነት ድጋፍ እና ደጋፊ አይሻም፡፡ የመ/ርት መስከረምም ጥንካሬ በአንተ ስድብ የሚነካ አይደለም፡፡

 8. መስከረም ኣበራ ጎልታ እየወጣች ያለች ሀገር ወዳድ፣ ተቆርቁዋሪ እህታችን ናት።ሚናዋንም የበለጠ ለማጉላት ፣ የጊዜው ኣንጋጋሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተመልካቹ የበለጠ ግንዛቤ ፣ ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረው የጀመረችው የጥያቄ ፕሮግራም የሚበረታታ ነው ።ጉድለት ቢኖር ገንቢ ሂስ መስጠት ነው ።እርግጥ ነው የተገነዘብኩት ጥያቄዎችዋ ቀድማ ካሰበችው መንገድ እንዲመለስላት የምትፈልግ ይመስላል/ leading question type / ።ግን ይህ በቀላሉ የሚታረም ነው።በሱዋም የተጀመረ ኣይደልም ፣ተዋቂ ጋዜጠኞችም ኣልፎ ኣልፎ የሚያረግት ነው ።
  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሳያወላውል ለሀገሩ መልካም ያሰበ፣ የታገለ፣ ህዝብን ዘመናዊ ፖለቲካ በተግባር ያስተማረ፣ራእይ ያለው ሰው ነው ። ተነስተን እንዲህ ነው ፣ እንዲያ ነው ማለት ከሱ የተሻለ ሰርቶ መገኘትን ይጠይቃል። መሳደብማ ማንም ባለጌ / Any fool can insult) የሚያረገው ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.