“ያትውልድ ተቋም” እነሆ 8ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በቴሌ/ቪድዮ ኮንፈረንስ ያከብራል

ያ ትውልድያ ትውልድ

ቀን ፡  ሰኔ ፲፬ ቀን ፪ ሺህ ፲፪ ዓ.ም. (June 21, 2020)

ለ፦

ከ፦ ያ ትውልድ ተቋም

በቅድሚያ ሁሉንም ማድረግ የማይሳነው እግዚአብሔር በዓለማችን የተከሰተውን የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ጉም በትኖና አጥፍቶ ምህረቱን ሰጥቶን እስከ ፍቅራችን፣ ጸባችን ለመተቃቀፍ ያብቃን፡፡ አሜን!!!

ሰኔ 28 ቀን 2004 ዓ.ም. (July 5, 2012) የተመሠረተው “ያ ትውልድ ተቋም” እነሆ 8ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን በቴሌ/ቪድዮ ኮንፈረንስ ያከብራል፡፡

ያ ትውልድ ተቋም” በዚህ 8 ዓመት ጉዞው ምን ሰራ? ምን አበረከተ? ጠቀሜታውስ ከምን ድረስ? በሚሉት ላይ በመነጋገር በቀጣይነት ይህንን ተቋም በማስፋት ለማንቀሳቀስ ያለውን ዕቅድ ያስተዋውቃል፡፡

ያ ትውልድ ተቋም” ዋልታ ምሰሶ አድርጎ የቆመበትን የያ ትውልድን መረጃ ማሰባሰብና በደርግ ቀይ ሽብር የተጨፈጨፉ ወገኖች መታሰቢያነቱን በስፋት ለመቀጠል አሁንም በርካታ ሥራዎች ከፊታችን ተደቅኗል እንላለን፡፡ የያ ትውልድ ታሪክ የሕዝብና የሀገር ታሪክ ነው ስንል ሕዝብና ልጆቹ ስለተሳተፉበት በመሆኑ ነው፡፡ በጎውም፣ ጎጂውም፤ አዎንታዊ፣ አሉታዊ ጎኑም፤ ትክክለኛነቱ፣ ስህተቱም ሁሉም እንደ ታሪክነቱ ለትውልድ አስተማሪነቱ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በመሆኑም ይህንን የትውልድ ታሪክ ዋልታ ያደረገው የ“ያ ትውልድ ተቋም” ድረ ገጽ (http://www.yatewlid.org/http://www.yatewlid.com/ ) ይበልጥ ይዳብር ዘንድ ስምንተኛ ዓመታችንን ስናከብር ቀዳሚ ርዕሳችን ይሆናል፡፡

በዚህና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ድርጅትዎን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ በመሆኑም ዕሁድ ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. (Sunday July 5, 2020) ከቀኑ 11፡00 AM Eastern Daylight Time ጀምሮ በምናከብረው 8ኛ ዓመት የ“ያ ትውልድ ተቋም” የቴሌ/ቪድዮ ኮንፈረንስ ዝግጅታችን ላይ ወኪላችሁን ትልኩልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ የወኪሎቻችሁን ስምና ዝርዝር ሁኔታም እስከ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. (June 30, 2020) ታሳውቁን ዘንድ በትህትና እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦ ሰዓቱ ከኢትዮጵያና ከሌላው ዓለም ለሚገቡ ወገኖቻችን ያመች ዘንድ ለማጣጣም ሲባል የተመረጠ ነው፡፡

የያ ትውልድ ታሪክ ህያው ነው!!!

ነሲቡ ስብሐት (703)3004302 [email protected]

ያ ትውልድ ተቋም ቦርድ ሊቀመንበር

አባሪ፦ የቴሌ/ቪድዮ ኮንፈረንስ መግቢያ

 

You are invited to a scheduled “Ya Tewlid Tequam” Zoom meeting.

July 5, 2020 11:00 am EDT

Join Zoom Meeting

https://us02web.zoom.us/j/85231486692?pwd=dmtGSkpHRTdENzRGa2pqZVYxTEJWZz09

Meeting ID: 852 3148 6692

Password: 786202

One tap mobile

+13462487799,,85231486692#,,,,0#,,786202# US (Houston)

+12532158782,,85231486692#,,,,0#,,786202# US (Tacoma)

Dial by your location

+1 346 248 7799 US (Houston)

+1 253 215 8782 US (Tacoma)

+1 669 900 6833 US (San Jose)

+1 301 715 8592 US (Germantown)

+1 312 626 6799 US (Chicago)

+1 929 205 6099 US (New York)

Meeting ID: 852 3148 6692

Password: 786202

Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kdcg33aHuG

 

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.