ግብጾች ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የአባይን ውሃ ለመጠቀም የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ዑስታዝ አቡበከር አህመድ ተናገሩ

ustazዑስታዝ አቡበከር አህመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ ውሃው የሚነሳበትና የሚመነጭበት አካል ቅድሚያ መጠቀም አለበት።

ዑስታዝ አቡበከር የግብጽን የእኔ ብቻ ልጠቀም አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለው ሲያብራሩ፤ “ከ ቅዱስ ቁርዓን ቀጥሎ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሐዲስ ምንጭ በሆነው ‹ሰሂህ ቡኃሪ ሐዲስ› ላይ እንደተገለጸው ሁለት ሰዎች አትክልት በሚያጠጡበት ውሃ ተጋጭተው፣ ከታች ያለው ሰው ከላይ ያለውን ቅድሚያ ለእኔ ይልቀቅልኝ በሚል ይከስሰውና ፍትህ በመፈለግ ከነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ፊት ይቀርባሉ፡፡

“ነብዩ መሐመድ (ሱ.ዐ.ወ) ም ጥያቄህ ፍትሃዊ አይደለም፡፡ ከምንጩ አጠገብ ያለው ቅድሚያ ሊጠቀም ይገባዋል፡፡ አጠጥተህ ሲበቃህ ልቀቅለት፡፡ ከምንጩ መነሻ ያለው ሳያገኝ እንዴት እሱን አልፎ ከእኔ ይድረስ ትላለህ? በሚል ተቆጥተውና ገስጸው በፍትሃዊ መንገድ መፍትሄ ሰጥተዋቸዋል” ሲሉም ኡስታዝ አቡበከር በአባይ ጉዳይ የግብጽ አቋም ከእስልምና እምነት አስተምሮና መርህ አንጻር ፍጹም ስህተትና ስግብግብነት የተሞላበት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ያለአግባብና ፍትሃዊ ባልሆነ ሁኔታ በኢትዮጵያ ላይ እየተሰራ ያለውን ደባ ለአለም ማህበረሰብ ማሳወቅ ይገባል ያሉት ኡስታዝ አቡበከር፤ በአባይ ወንዝ እንደ ባለቤት ያጣነውን መብት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአልሲሲ መንግስት እየተፈጸመ ያለውን ደባና ‹‹አባይ የግብጽ የተፈጥሮ (የአላህ) ስጦታ ነው›› የሚለውን የውሸት ትርክት እስልምናን ለሚወክሉ አለም አቀፍ ተቋሞች መናገርና ማቅረብ የዜግነት ግዴታቸው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በመሀመድ ሁሴን (ኢ ፕ ድ)

1 Comment

  1. ኡስታዝ አቡበከር፣ ልክ ብለዋል። ኢትዮጵያ እያለች ያለችው በእኩልነት እንጠቀም እንጂ እኛ ብቻ እንጠቀም አይደለም። በአንጻሩ እነሱ ግን እኛ ብቻ መጠቀም አለብን ይላሉ። ምን አይነት ህሊናቢስነት ነው?
    እነሱ ከራሳቸው አልፈው ለውጭ ንግድ ጥጥ፣ ሽንኩርት፣ ሩዝ፣ ፍራፍሬ ወዘተ ያመርታሉ። አዲስ ከተሞችም ይገነባሉ። እኛ በቂ የምንበላው ስለሌን ከውጭ አገሮች እንገዛለን። እንግዲህ ውሃው ለማን ነው የበለጠ የሚያስፈልገው? የፍርድ ያለህ ያሰኛል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.