በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከሐረሪ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 1 ትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1412 ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንዶች እና 138 ሴቶች ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸውም ከ3 ወር ህጻን እስከ 80 ዓመት እንደሚገኙም ተገልጿል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል እና 1 ሰው ከትግራይ ክልል መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3 ሺህ 359 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 38 በፀና የታመሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 223 ሺህ 341 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል

105632021 1677114545773220 6061844665424092655 o e1592964819461 በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል

(ኢፕድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.