‹‹ያልወለዱ ማህፀኖች ምንኛ የተባረኩ ናቸው፣ ያላጠቡ ጡቶች ምንኛ የታደሉ ናቸው!!! ለእራሳችሁ አልቅሱ!!!›› ስጋና ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል!!! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

236‹‹በመስከረም 2013ዓ/ም በኃላ ፣ የኦነጎች ጥያቄ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ሃዋሳ ወዘተ የኖሪና የመጤ ዘረኛ ጥያቄ ወደ ዘር ፍጅት እንዳያመራ በየከተማው የተደራጀ ሠላማዊ ህዝባዊ ጋርድ መደራጀትና መገንባት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡››

1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የሸዋ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱ ከተቆረቆረች መቶ ሃያ ሦስት አመታት ተቆጥሮል፡ የኢትዮጵያ ዜጎች በሃገሪቱ ባሉ አስራ አራት ጠቅላይ ግዛቶች በጆግራፊ፣ በኢኮኖሚና በታሪክ መስተጋብራቸው ተከፋፍለው በህግ፣ በነጻነትና ሠላም  ይተዳደሩ ነበር፡፡ 1984ዓ/ም የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት አዲስ አበባ የሃገሪቱ ዋና ከተማ በማድረግና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ በማለት የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ያጋጩበት ለሃያ ስምንት አመታት በከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ የገዙበት የፖለቲካ ሴራ ሚስጢር ነው፡፡ የዚህ ፖለቲካ ሴራ ዋና ጭንቅሎ (Master Mind) ኢሳያስ አፈወርቂ፣ መለስ ዜናዊና ሌንጮ ለታ  ነበሩ፡፡ ምሁራን ሃገሪቱን ለዘጠኝ የዘርና ልሣን ክልሎች ከፋፈሉ፡፡ Ethiopia is a federation subdivided into ethno-linguistically based Regional States and chartered cities. This system of administrative regions replaced the provinces of Ethiopia in 1992 under the Transitional Government of Ethiopia and was formalised in 1995 when the current Constitution of Ethiopia came into force. ትግራይ ከጎንደር፣ ከወሎና ከአፋር ለም መሬት ወሰደች፡፡ አማራን ለመምታት ቤተክርስቲያኖን ማዳከም፣ ብሄራዊ ስሜት፣ የሃገር ፍቅር፣ የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ኩራትን ማውደም የሃገሪቱን ቅርሶች መዝረፍ ወዘተ የሥስቱ ሴጣኖች ተግባር ነበር፡፡   መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ ነው በማለት፣ ለዘጠኙ ክልሎቹ ሰንደቅ ዓላማ  ተሠራ፡፡  አዲስ አበባና ድሬዳዋ ቻርተርድ የከተማ አስተዳደሮች ሆኑ፡፡ የደቡብ ክልል በሃምሳ ስድስት ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት አንድ ክልል ሆኑ፡፡ የደቡብ አፍሪካ የባቱስታ በዘር ላይ የተመሠረቱ ክልሎች የተነሳ የወሰን ግጭት ህዝብ ለሞት፣ አስራት፣ ስደትና መፈናቀል የዕለት ጉርሱ ሆኖል፡፡ በነጻነት ስም ባርነት፣ እራስን በእራስ ማስተዳደር ስም የኢህአዴግ/ የብልፅግና ካድሬዎች አንባገነን አስተዳደር፣ በዴሞክራሲ ስም አንድ ለአምስት የስለላ ጥርነፋ ስርዓት ተከሉብን፡፡   እንደ ህወሓት/ኢህአዴግ አብዬታዊ ዴሞክራሲ ፣ የህገመንግስት አይነኬነትን፣ የቌንቌ የፌዴራል ሥርዓተ መንግሥት፣ የቡድን/ የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች መብት፣ የመገንጠል መብት (አንቀፅ 39) የሚደግፍ፣ የቡድን መብትና ነፃነት፣ መሬት የመንግሥት ኃብት መሆን፣ የፓርቲው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፕሮግራም ስምምነት በኢህአዴግም በብልጽግናም የመሠረት ድንጊያ ሆነው ቀጥለዋል፡፡ የኢዜማ አቆም በግልፅ አይታወቅም ለህዝብ ይገለጥ እንላለን፡፡

{1} ብልፅግና/ኢህአዴግ  ዶክተር አብይ አህመድ መጋቢትአሥር ቀን 2010 ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ሁለት ሽህ አምስት መቶ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ስድሳ በመቶ የሃገሪቱ ዜጎች በመከላከያ ሠራዊት ኃይል ኮማንድ ፖስት ተጠርንፎና በኮሮናቨይረስ አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ቀሪዋ ነፃነቱን ተለጎሞ የረገኛል፡፡  በዶክተር አብይ አህመድ ዘመንም ፣ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ መሠረት በኦነግ  ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ

‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣ 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው ፣72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን፣ እንዲሁም ሃያ ሥስት ባንኮች መዘረፋቸውን የተደበቀ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል፡፡›› በዶክትር አብይ መንግሥት የሁለት አመት በትረ ሥልጣን ዘመን ኦነግ ከኤርትራ ምድር ከነበረው አምስት ሽህ ሽምቅ ተዋጊ ውስጥ አንድ ሽህ ሦስት መቶውን ብቻ ትጥቅ አስፈትቶ፣ ቀሪውን ሦስት ሽህ ሰባት መቶ ሠራዊት ከነትጥቁ አገር ውስጥ በማስገባት የወለጋ ህዝብ በኦነግ ሸኔና አባ ቶርባ ነፍሰ ገዳዬች መከራውን ያያል ይገኛል፡፡ አብዛኛዎቹ ታዳኞች የኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልፅግና ፓርቲ ሹማምንቶች በየቦታው እንደሚገደሉ፣ እንደሚቆስሉና  እንደሚታፈኑ  ታዉቆል፡፡ በኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ክልል በተለይ የወለጋ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ተይዞል፡፡ የህግ ሉዓላዊነት እስካልተከበረ፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እስኪሆን ድረስ ትግላችን ሊቀጥል ይገባል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከነእንከኑ አሰተካክሎና እርማቱን በጋራ ፈትቶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ መንግሥት ካለን ዋነኛው ስራው ይሄ መሆን ይኖርበታል እንላለን፡፡  ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይሄ ሁሉ የስብኣዊ መብቶች ጥሰት ሲከናወን ተከታትለው አለማጋለጣቸው ያሳፍራል፡፡

{2} የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ በአዋጁ ዘጠና አንድ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ተገድለዋል አለ፡፡ እንዲሁም መቶ የኦፌኮ ደጋፊዎች መታሰራቸውን የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ገልፀዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የህቡእ እስኮዶች በስውር ዜጎችን በመግደል ላይ ናቸው፡፡ የይህ የፖለቲካ ሴራ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ሰዎችን በመግደል ማስወገድ ላይ ያተኮረ ሲሆን በደርግ ወታደራዊ አስተዳደር ዘመን  በሽህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝና ሰባዎቹ አመታት ደርግ ኢሰፓ፣ መኢሶን፣ ወዝሊግ፣ ሰደድ፣ ማሌሪድ ኢጭአት ኢህአፓ  ያደረጉት የመገዳደል የፖለቲካ ስህተት  በደርግ የቀይ ሽብር መንግሥታዊ ሽብር ተጠናቀቀ፡፡  ዛሬም በ2012 ዓ/ም በኦነግ ሸኔ  የሃያ ሦስት ባንኮችን ዘርፎ፣ የወርቅና ታንታለም፣ ብረት ወዘተ የማዕድን ሥፍራዎችን በመቆጣጠር ፣ እንደ ቆያ እሳት የተስፋፋው የጦርነት ሰደድ እሳት በኦሮሚያ ክልል በምእራብና ደቡብ ወለጋ ቄለምና ጉጅ ዞን  አንድዶል፡፡ የሽምቅ ታጣቂ እንቅስቃሴ ባለበትና በሌለበት በኦዴፓ/ብልፅግናና ኦፌኮ ፓርቲዎች መኃል በሸዋ፣ በአርሲ ሃረርጌና ባሌ የሰው ህይወት እየተቀጠፈ ይገኛል፡፡  የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ሹኩቻ የፖለቲካ ስልጣን ለመጨበጥና  የኢኮኖሚ በተለይ የመሬት ኃብትን በሜትር ካሬ አዲስ አበባ እስከ 350 ሽህ ብር፣ አዲስ አበባ ኦሮሚያ ዞኖች ከመቶ እስከ 250 ሽህ በሜትር ካሬ እየቸረቸሩ ባለጸጋ የሆኑ ፖለቲከኞች በነጻነት ስም የኦሮሞን ህዝብና የኢትጵያን ዜጎች ሠርተው እንዳይበሉ ያደረገ የፖለቲከኖች ሴራ የሃብት ዘረፋ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዛሬ በቄለም ወለጋ የተጀመረው የፖለቲካ ግድያ ወደ መኃል አገር አይመጣም ብሎ ዝም ማለት ‹‹ሲቃጠል በቅጠል!››እንደማለት ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ስለዚህ ግድያ አውርቶም ለብልፅግና ፓርቲም አሳስቦ ድምጽ ለሌላቸው ድምፅ ሆኖቸው አያውቅም፡፡   ‹‹በመስከረም 2013ዓ/ም በኃላ ፣ የኦነጎች ጥያቄ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ሃዋሳ ወዘተ የኖሪና የመጤ ዘረኛ ጥያቄ ወደ ዘር ፍጅት እንዳያመራ በየከተማው የተደራጀ ሠላማዊ ህዝባዊ ጋርድ መደራጀትና መገንባት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡››ጁዋር መሃመድ ከ85ቱ ሰዎች የግፍ ግድያም በኃላ ቄሮን በሃያ አራት ሰዓት ማነቃነቅ እንችላለን ድንፋታን ነቅቶ መመከት  የአልሞት ባይ ተጋድሎ ነው እንላለን፡፡

{3}  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)  1

‹‹ኢዜማ ገዥው ፓርቲ በደቡብ ክልል የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያዘጋጀውን አወቃቀር ተቃወመ፤-በደቡብ ክልል ራስን በራስ ለማስተዳደር የቀረቡ ግልጽ ጥያቄዎችን በፍፁም መመለስ የማይችል፣ ለችግሩ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት ዓላማ ያደረገ፣ አመፅና ብጥብጥ ለማነሳሳት ለሚሞክሩ ኃይሎች ስንቅ እንደማቀበል የሚቆጠር ነው ሲል የገዥውን ፓርቲ ውሳኔ ተቃውሟል። ከምሥረታው ጀምሮ በብዙኃን ቅቡልነት ባልነበረው የደቡብ ክልል አደረጃጀት፣ ክልሉ ከተመሠረተ በኋላ ሲተገበሩ በነበሩ አግላይ ፖሊሲዎች፣ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል ኢፍትሐዊነት፣ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ዕጦት በብዙ የክልሉ ማኅበረሰብ ዘንድ የክልልነት ጥያቄዎች እንዲነሱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ኢዜማ አስታውሶ፣ ከኅብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ቀጥተኛና ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ሲገባ ጊዜያዊና የሕዝቡን ጥያቄ የማይፈቱ አማራጮችን በማቅረብ፣ የሕዝብን እውነተኛ የፍትሕና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ማፈን ተገቢ እንዳልሆነ አስታውቋል።  ‹‹ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ መሠረታዊ፣ የምንደግፈውና ተግባራዊ እንዲሆን የምንታገልለት ጥያቄ ነው፤›› ሲልም በመግለጫው አስረድቷል፡፡››

ኢዜማ፣ በህገ-መንግስትቱ ላይ ያለው አቆም፣ አንቀፅ 39 የመገንጠል መብት ጥያቄ፣ የመሬት ጥያቄ፣ የአብዬታዊ ዴሞክራሲ ጥያቄ ፣ የአዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረሪ ከተሞች ጥያቄ ላይ ኢዜማ ለህዝብ ይፋ ያላደረገው የፖለቲካ ፕሮግራም እንዲሁም በየጊዜው በህዝብ ላይ ለሚደርስ በደል አቆምና ድምጽ አለማሰማት ወዘተ ኢዜማን ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ገጥሞ ለጥቅሙ የሚሠራ ፓርቲ በመሆኑ ህዝቡ ቅሬታውን ካሰማ ቆይቶል፡፡

‹‹ገዥው ፓርቲ ይኼንን ያልታደሰና የመለወጥ ፍላጎት እያሳየ ባልሆነው የካድሬና የባለሥልጣናት መዋቅሩ በደቡብ ክልል እየቀረበ ያለውን ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለማፈን እያደረገ ያለው ሩጫ የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄ የማይመልስ ብቻ ሳይሆን፣ ፓርቲው እያሳየ ያለውን የመብት ሰጪና ነሺነት ፍላጎትንም የሚያሳይ ነው ብሏል። ይህ በየጊዜው ከለውጡ አጠቃላይ መንፈስ  እየራቀ የመጣው የገዥው ፓርቲ ፍላጎት፣ በአገሪቱ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ጭምር ነው ሲል በመግለጫው ኮንኗል።››

‹‹ገዥው ፓርቲ ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ

መንገድ በመብት ሰጪና ነሺነት የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት የሚያደርገውን ሩጫ በአስቸኳይ እንዲያቆም ኢዜማ አጥብቆ ያሳስባል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዚህ ምክንያት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ለሚደርስ እያንዳንዱ ጉዳት ቀጥተኛ ተጠያቂ በራሱ ተነሳሽነት ጉዳዩን እየገፋ ያለው ገዥው ፓርቲ እንደሚሆን በግልጽ መታወቅ አለበት፤›› ሲል አስጠንቅቋል። ‹‹ኢዜማ ከተመሠረተ ጀምሮ ለአገር መረጋጋትና ሰላም ቅድሚያ በመስጠት የፉክክር ጉዳዮችን ምርጫው ለሚደረግበት ጊዜ አቆይቶ፣ ለሁላችንም የሚበጀውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ከሚፈልጉ አካላት ሁሉ ጋር በትብብር መንፈስ ሲሠራ ቆይቷል። በኢዜማ እምነት ቀጣዩ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ያለው የሽግግር ወቅት በዋነኛነት አገርን ለማረጋጋት፣ ምርጫውን ነፃና ፍትሐዊ ለማድረግ መሠራት ያለባቸው ሥራዎች ማከናወኛ ነው። ዘላቂ ውጤት ያላቸውን ሥራዎች የሕዝብ ፈቃድ ያላገኘ አስተዳደር፣ የሕዝብ ፍላጎት ሳይታወቅ በዚህ የሽግግር ወቅት ሊተገብር እንደማይገባ በፅኑ እናምናለን፤›› ሲልም አስታውቋል።

  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከሕዝብና ቤት ቆጠራ በተያያዘ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መሠረት በኢትዮጵያ ከሕዝብና ቤት ቆጠራ ከምርጫው በኃላ እንዲካሄድ በመወሰን ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጎል፡፡ ኢዜማ እንዴት የህዝብና ቤት  ቆጠራ  ከምርጫ በኃላ እንዲሆን ተስማማ!
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ድጋፍን ለብልጽግና ፓርቲ ህገመንግሥቱን በማሻሻልና በመተርጎም በሚል ለብልጽግና ፓርቲ ድጋፉን ሰጠ፡፡ በዚህም መሠረት ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉም መሠረት የኮሮናቫይረስ ወረርሺኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል፤ እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው ውሳኔ ያሳለፈው። ኢዜማ የዶክተር አብይ መንግሥት ወደ ፍፁም አንባገነንነት መንግሥት እየተሸጋገረ መሄድ አልተገለጸላቸውም ነበር ወይስ የደቡብ ክልል ጉዳይ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ ለመሆን ያስቻለው ጉዳይ ሊገባን አልቻለም፡፡ ኢዜማ ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ በፍቃዳቸው ሲያስተላልፉት በሃገረ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ ከመቶ አስራምስት ሽህ ህዝብ ህይወቱን አጥቶ፣  በኖቨንበር 2020 አጠቃላይ ምርጫ እንደሚካሄድ ኢዜማ አልሰማ ይሆን!!!
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አንደኛ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከምርጫው በፊት እንዲደረግ መወሰን፣ ሁለተኛ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት ተበትኖ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ማድረግ፣ ሦስተኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ብልጽግና ፓርቲ የምርጫውን ጊዜ ሠሌዳ በህብረት እንዲያወጡ ማድረግ፣ አራተኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ፕሮግራማቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ በጋራ ማዘጋጀት ከወዲሁ በመገናኛ ብዙሃን ኢዜማ ኢሳት ስላለው ጥያቄው እንደማይመለከተው ሳይሆን በጋራ መወገን ለዴሞክራሲያዊ ኃይሉ ያስፈልጋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የዶክተር አብይ መንግሥት በሁለተኛ አመት በትረ ስልጣኑ በሃገራችን ህግና ሥርዓት ባለማስከበር የንፁሃን ደም በግፍ እንዲፈስ አድርጎል፣ ብዙ ህዝብ ተፈናቅሎል፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዘረመል ቤተሙከራ ተገድለዋል፡፡ በሃገሪቱን በወታደራዊ እዝ አገዛዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር ትገኛለች:: ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ወዘተ ክልሎች በኮማንድ ፖስት ሥር ወድቀዋል፣ የስብአዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲ አፋና በህዝብ ላይ ቀጥሎል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና/ ኢህአዴግ መንግስት ለአምኒስቲ ዓለም አቀፍ ድርጅት የኢትዮጵያን የስብዓዊ መብት ጥስት ሪፖርት ዶክተር አብይ አህመድ ድርሰት ነው በማለት ተሳልቆበታል፡፡  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ላቀረቡት የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ሪፖርት መረዳት የተሳናቸው፣ የፍትህ ሚኒስትሮ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሲያስተባብሉና ሲቃወሙ  ተደምጠዋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ‹‹በደቡብ ክልል የምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኢዜማ ደቡብ ክልል የሕዝቡን ፍላጎት ባሟላ መልኩ እንደገና እንዲዋቀር እንደሚፈልግ እንድትረዱና ለምታነሱት ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ትክክለኛና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት፣ አሁን ያለንበት ጊዜ እንደማይፈቅድና የእናንተን ፍላጎት የሚያስፈጽሙ በእናንተው የተመረጡ ወኪሎቻችሁ ሳይኖሩ፣ እኔ አውቅልሃለሁ በሚሉ ካድሬዎች ሊከናወን የሚቻል እንዳልሆነ በመረዳት፣ ቀጣዩ ምርጫ ተደርጎ ፍላጎቶቻችሁን የሚያስፈጽሙ ወኪሎቻችሁን እስክትመርጡና በጥያቄያችሁ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጋችሁ በሕዝበ ውሳኔ መወሰን የምትችሉበት ሁኔታ እስኪመቻች፣ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ትዕግሥት እንድትጠብቁ አበክረን እንጠይቃለን። ይህንን ተረድታችሁ ለጋራ አገራችን መረጋጋትና ሰላም በማሰብ ጥያቄዎቻችሁን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ለምታሳዩት ትዕግሥት ከወዲሁ የኢትዮጵያ የከበረ ምሥጋና ያቀርባል፤›› ሲል ኢዜማ ጥሪውን አቅርቧል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በደቡብ ክልል ሃምሳ ስድስት ብሄር ብሄረሰቦች አንዳሉና ከዚህ ውስጥ አስራ ሁለቱ የማንነት ጥያቄ በማቅረብ የክልል መንግሥት ለመሆን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት በዘጠና ዘጠኝ በመቶ ድምጽ ድጋፍ እንዳገኘ መረጃው ያሳያል ለሪፈረንደሙን ለማስፈጸም 750 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖል፡፡ከዚህ በመረዳት ለወላይታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ፣ ከንባታ፣ ጌዲዬ፣ ጎፋ፣ ወዘተ ቤሳቢስቲን ገንዘብ ወጪ ማውጣት ሃገሪቱ አያሻትም እንላለን፡፡ ምርጫ ቦርድ ምን ይስራ፣ ስራ ፍጠሩ ብላችሁ በፈጠርንው ስራ አሉ ይባላላ!!!

{4} ደኢህዴን ብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ክልልን በአዲስ መልክ በአምስት ክልልነት ለማዋቀር በአባ ዱላ የተጀመረው አዲስ የፖለቲካ መዋቅር  የወላይታ ምክር ቤት አባሎች ሰላሳ ስምንት መቀመጫ ትተው መውጣታቸው ተሰምቶል፡፡ ያለህዝብ ፍላጎት የሚደረግ ሁሉ እንደጤዛ ይረግፋል እንላለን፡፡ በህገመንግሥቱ መሠረት ኢትዮጵያ ከአስር ወደ መቶ ትናንሽ መንግስትነት መሸንሸኖ አይቀሬ ነው እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የብሄር ብሄረሰቦችን ጥናት ማድረግ በፖለቲካ ሴራ የተጫነብንን ህገመንግሥት በተለይ መንግስታዊ አወቃቀር በዘርና ልሳን ላይ በመመስረቱ የተፈጠረ ወደፊት የወሰን ግጭት ወደ ማያበራ ጦርነት  የሃገሪቱን ህዝብ ለሞት፣ እስራት፣ ድህነት፣ እርዛትና ስደት ስለሚዳርግ የኢዜማ የፖለቲካ አቆሙን መግለጽ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

{5} ህወሓት፤- በትግራይ ምርጫ ለማካሄድ ወስኖል፣ ሽማግሌ ተልኮል፡፡ ህወሓት የትግራይን ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ይዞ መደራደር ችሎል፡፡

{6} ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ  ላልተወሰነ ጊዜ ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያደረገውን ውሳኔ በመቃወም ህዝባዊ ሰላማዊ ሠል እንደሚጠራ፣ ሆኖም የኮሮናቫይረስ  ወረርሺኙ ስጋት ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ተቃውሞ ማሰማት የትግል ጥሪ አድርጎል፡፡  ባልደራስ የአዲስ አበባን ወጣቶች በየክፍለ ከተማው ወጣቶችን በማደራጀት ህዝቡን ማንቃት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ባልደራስ ወጣቶች በሞባይል በፌስቡክ ድረገፅ ግንኙነታቸውን በማዘመን በ2013ዓ/ም ሊከሰት የሚችል የዘር ፍጅት ከወዲሁ መከላከል አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡  ባልደራስ የህዝብ ደጀን ነውና ደጀን እንሁነው፡፡ ኢዜማ የትግል ስልቱ ምንድን ነው!!!

ምንጭ፡- ርእሱ የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል

  • 1- ኢዜማ ገዥው ፓርቲ በደቡብ ክልል የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያዘጋጀውን አወቃቀር ተቃወመ/ 17 June 2020/ በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.