የትግራይ ሪፐብሊክ ህልም !! – ተድላ አስፋው

የትግራይ ሪፐብሊክ ለመመስረት በሚቀጥሉት ጥቂት ወራቶች የክልሉ ነዋሪዎች ድምፅ እንደሚሰጡ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ይህ የትግራይ መንግሥት የዛሬ29 አመት የ ሶማሌ ላንድ በመባል የተመሰረተው ነገር ግን እስካሁን በዐለም ነፃነቱ ያልታወቀው መንግሥት ተመሳሳይ መሆኑን ጌታቸው ረዳ ነግሮናል።

Tigrayይህ አዲስ መንግሥት ተቅዋማትን እየገነባ ከ ሌላው የኢትዮጵያ መንግሥት ተነጥሎ እንደሚደራጅም ጌታቸው ረዳ በመተማመን ይናገራል።

የትግራይ ሪፐብሊክ ከ ጎንደር ና ወሎ የቀማዉን መሬት ይዞ ነፃነት ማወጅ ተዳፍኖ የነበረውን ግጭት እንደሚያቀጣጥለው አይቀሬ ነው። ወያኔም ይህን ጦርነት ህዝብ ለማሰባሰቢያ ይጠቀምበታል።

አዲሱ ትግራይ ሪፐብሊክ ከሶማሌ ላንድ የሚለየው ዋናው የምስረታ ልዩነት የተቀረው ሶማሊያ እርስ በርስ የጎሣ ጦርነት ላይ በነበረበት ሰዐት ሶማሌ ላንድ ሀገር ግንባታ ላይ በማተኮሩ ነው።

በተቃራኒው የተቀረዉ ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዐት የጎሣ ጦርነት ላይ ባለመሆኑ ማዕከላዊ መንግሥት የ ትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እንደማያሳስበው ነው። ጦርነትም ማንሳት አይጠቅመዉም።

ሰሞኑን ወደ ትግራይ የተላከው ሽማግሌዎች ቡድን የማዕከላዊ መንግሥት ሊመጣ የሚችለው የትግራይ ነፃ መንግሥት ምስረታ የሽፍታ መንግሥት መሆኑን በቅድሚያ ለማሳወቅ ብቻ ነው።

የትግራይ ነፃ ሪፐብሊክ ከማወጁ በፊት በተቀረው ኢትዮጵያ ቀዉስ ለመፍጠር ያደረገው ሙከራዎች ሁሉ በመክሸፉ የቀረው አማራጭ ትግራይን መገንጠልን ብቻ ይሆናል።

ማዕከላዊ መንግሥትን የሚቃወሙ የጎሣም ሆነ ያልሆኑ ድርጅቶች ትግራይ እራሱን ከገነጠለ በኋላ ከ ወያኔ ትግራይ ሪፐብሊክ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት መቀየሩ አይቀሬ ነው።

የሽግግር መንግሥት እናቅዋቁም የሚለዉ ጥያቄአቸው ወያኔን ስለማይጨምር አንዳንዶቹ ያስፈራሩበትና ይመኩበት የነበረው የወያኔ ታጣቂ በሰርጎገብነት መተጋገዙም ይቀንሳል።

የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ተለይቶ ያለ ባህር መገናኛ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ መገመት ቢከብድም እንደ ሶማሌ ላንድ 29 አመት እንደማይቆይ መናገር ይቻላል።

ነፃው የትግራይ ሪፐብሊክ በዐለም የሚያዉቀው አንድም መንግሥት እንደማይኖር ጌታቸው ረዳ ቢረዳም እንዴት አድርጎ መንግሥታዊ ተቅዋም እንደሚገነባ ያቀረበው ፕላን የለም።

የትግራይ ሪፐብሊክ ዋናው ኢኮኖሚ ምንጩ በዉጭ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ይህን ሪፐብሊክ ለማጠናከር ገንዘባቸዉን ለመለገስ አቅሙ ፍላጎቱ ይኖራቸው ይሆን ??

መጪው 2013 ከቻይና የተነሳው ተውሀሲ ከሚያመጣው የህይወትና ኢኮኖሚ ጉዳት ተጨማሪ የአንበጣ መንጋ ጥቃትና ረሀብ አደጋ አዲሱ የትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ ሚሊዮኖችን አደጋ ላይ መጣሉ አይቀሬ ነው።

የኦሮሞ ታጣቂዎች ከ ትግራይ ሪፐብሊክ ጋር የጋራ ድንበር ስለሌላቸዉ የተቀረዉን ኢትዮጵያ በጎሣ ጦርነት የማተራመስ አቅም አይኖራቸዉም።

በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትም ሆነ ሌሎች ተቃዋሚዎች ከ ኮሮና በኋላ ለሚመጣው ምርጫ ከመዘጋጀት ዉጭ አላስፈላጊ ጉንጭ አልፋ የህገ መንግሥት ንትርክ ዉስጥ መግባት በህዝብ መቀለድ ይሆናል።

ያለ ህግ ምርጫ 29 አመት የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መጪዉን አንድ ዐመት ለመኖር አይቸገርም። ጥያቄው በድምፄ መንግስት ልመስርት ብቻ ነው። ሳንመርጣችሁ በስማችን አታበጣብጡን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.