የክልሎች ጣጣ – መስፍን ወልደ ማርያም

Mesfinወያኔ ክልሎችን አካለ ስንኩላን አድርጎ የፈጠረው ለብልሃቱ ነው፤ ዋናው ዓላማ ጎሣዎችን በማናከስ ዳኛ ሆኖ አናታቸው ላይ ለመቀመጥ ነበር፤ ይህንን ዓላማ ሳይጨብጡ የክልሎችን አወቃቀር መደገፍ ዋና ሳይችሉ ባሕር ውስጥ መግባት ነው፤ ተናግሬአለሁ ማለቱ ፋይዳ የለውም እንጂ የክልል ሀሳብ ጭንጋፍ መሆኑን ከተናገርሁ ልጆች ተወልደው አድገዋል፤ እውነት ይዘገያል እንጂ እንደጸሐይ ጊዜውን ጠብቆ ይወጣል፤ ተንኮልም ከስቶና መንምኖ መቆም የማይችልበት ጊዜ ይመጣል፡፡

ችግሩ እንደተራራ ውሀ ግልጽ ነው፤ ክልል ማለት የጎሣ ቤት ነው ከተባለ እያንዳንዱ ጎሣ ትልቅም ይሁን ትንሽ እንደትግሬ፣ እንደአማራ፣ እንደኦሮሞ፣ እንደሶማሌ፣ እንደአፋር፣ እንደአደሬ … ሌሎቹ ሁሉ የየራሳቸው አጥር ያለው ቤት ያስፈልጋቸዋል፤ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 8 ለጎሣዎች በሙሉ ለሉዓላዊነት ሰጥቷቸዋል፤ በተጨማሪም አጥሩ ከአንቀጽ 39 ጋር የተያያዘ ነው፤ አጥሩ እርስበርሳቸው እንዳይፋጁም ይረዳል፤

ዛሬ ጎሣዎች ለክልልነት እንደሚጮሁት ነገ ደግሞ ለመገንጠል ይጮሃሉ! ስለዚህ አሁኑኑ አጥሩን በውል እያጠሩ ከልሎ አንቀጽ 39 ላይ ሲደርሱ ጣጣ የለም፤ አጥራቸውን ይዘው ውልቅ! የወያኔ ሕገ መንግሥትን ይዞ ለጎሣዎች ሁሉ የክልል ደረጃ መስጠት ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ ይሆናል፡፡

በአመራር ደረጃ ቆራጥነት ጠፋ፤ ዶር. ዓቢይ መለስ ዜናዊ ባነጠፈለት ኮረኮንች መንገድ ላይ ሳይጨነቅ እየተጓዘ ነው፤ ጠጠሮችን በመልቀም ኮረኮንቹን መንገድ ለማለስለስ መሞከር የሚያዋጣ አይመስለኝም፤ የላይቢሪያዋ የቀድሞ መሪ ዶር. ዓቢይ የሰላም ሽልማቱን ሲቀበል አንድ ነገር ብላ ነበር፤ የቆራጥነት ማጣት ችግር እንደሚፈጥርበት ተናግራ ነበር፤ ምን እንዳስመለከታት አላውቅም፡፡

የወያኔን ሕገ መንግሥት በመደረት ማሻሻል የሚቻል አይመስለኝም፤ በድሪቶ አገርን መምራት በጣም ያስቸግራል፤ ድሪቶ የደሀነት አርማ ነው፤ የሀሳብ ደሀነት ሕገ መንግሥቱን ድሪቶ ያደርገዋል፡፡ ይህ ድሪቶ ለዓቢይ አህመድ የሚስማማው አይመስለኝም፤

4 Comments

 1. All previous comments were removed after Tecola was called “brother”

  ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ለኢትዮጵያ የዋሉላት ብቸኛዋ ታላቅ ተግባር ብትኖር፣ ያንን ለጠላቶቻችን የአምስተኛ መስመርን ተዋናኝ ግብፃዊ ኢትዮጵያ ስትወረር ከጠላት ጋራ አብሮ ዶላች ጳጳስን፣ “ሃገራችን ሰላም ስትሆን ልትገዙን፣ ችግር ውስጥ ስትገባ ግን ከጠላቶቻችን ጋራ ልትመሳጠሩብን አይሆንም እና፣ ና ተነስ ሂድ ወደ አገርህ” ብለው ማባረራቸውና ለኢትዮጵያ የሚታመኑ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳትን የኛ ፓትርያሪክ አድርገው መሾማቸው በከፍተኛ ደረጃ ያስመሰግናቸዋልና፣ እነ “Muluken Wodajo”ም መፅሓፍ ቅዱስንና ብዙ አባባሎቻችንን ባላግባባቸው እያዝናናችሁ የአገራችንን መብት፣ ባላቸው አለማቀፋዊ እውቀትና ልምድም ላይ በመደገፍ እየተሟጎትላት ላሉት ወንድሞቻችን እነ ተኮላን ባትረብሿቸው ይበጃችኋል………..! አለበለዚያ ግን “አባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይጓዛል” ጎርፍ ውስጥ ተወርውራችሁ የአባይ አዞ ወይ ጉማሬ ቁርስ ትሆናላችሁ…!
  ወታደራዊ ጉዳዩን በሚመለከትም ኣይተ በቀለም ብትሆን፣ በርግጥ እንዳልከው ከፍ ያለ ብቁነት ያለው መከላከያ ሃይል ያስፈልገናል፣ ግን ደግሞ ግብፅን ካንዴም ሁለቴ ራስ አሉላ ጥቂት በራሳቸው የሚተማመኑ እንደነ አያቴ የመሳሰሉ የትግራይ ገበሬዎን ይዘው ማባረራቸው መረሳት የለበትም፣ በተገኘው መድያ ሁሉም ህብረተሰብን ስላለው ህልው ሁናቴ ማስረዳትና ማንቃትም የመከላከል ተግባራት አካል መሆኑን መገንዘብ ጠቄመታ አለው….!
  “ታህዳድስያ ፍርቂ ምስዓር” እንዲለው ትግርኛው፣ አይን አውጣዋ ግብፅን አስመልክቶ፣ ፕሮፓጋንዳም የሚጫወተቅ ሚና አለው፣ ግድ የለም ::

 2. ከህዳሴ ግድብ ጋራ በተያያዘ ጉዳይ ግብፅን ሙሉለሙሉ ካሸማቀቅን በኋላ የሚኖረን ዋንኛው አቢይ አርእስት ንጥረ ሃብት እና አሜሪካ ብቅ እያሉ ጡጦ የላሱት Marionetten በሚል ይሆናል::

  ያኔ እንግዲህ ምድረ ፋጉሎ ሁሏ ምን ይውጣት………..!!?? ፓስፖርትህ ምንድነው ሳይሆን ውናው ነጥብም፣ አወናባጅ Marionette ነህ ወይንስ ጤነኛ ለህዝቡ ወገናዊ፣ ይሆናል ዋናው ምርምሩ:

 3. ምነው የሚቀጥለውን አባባል መሰረዛችሁ፣ በተደወለላችሁ ቁጥር አባባሎችን ባትቀያየሩ እንዴት ባማረባችሁ፣ በደዋዮች ወዳጆቻችሁ ጭንቅላት ሳይሆን በገዛ ራሳችሁ አስተያየት መገዛትን ተማሩ::

  ዘረ-ያዕቖብ
  says:
  June 26, 2020 at 7:41 pm
  ከህዳሴ ግድብ ጋራ በተያያዘ ጉዳይ ግብፅን ሙሉለሙሉ ካሸማቀቅን በኋላ የሚኖረን ዋንኛው አቢይ አርእስት ንጥረ ሃብት እና አሜሪካ ብቅ እያሉ ጡጦ የላሱት Marionetten በሚል ይሆናል::

  ያኔ እንግዲህ ምድረ ፋጉሎ ሁሏ ምን ይውጣት………..!!?? ፓስፖርትህ ምንድነው ሳይሆን ውናው ነጥብም፣ አወናባጅ Marionette ነህ ወይንስ ጤነኛ ለህዝቡ ወገናዊ፣ ይሆናል ዋናው ምርምሩ::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.