የገዳ ስርዓት እና የአረብ ነጋዴዎች፣ (ከ ደረጀ ተፈራ – የግል ምልከታ)

Geda

   መግቢያ፣

ዙሪያዋን ተብትቦ ከያዛት እሾክና አሜኬላ የሚያላቅቃት አዳኝ መሲህ አጥታ ስትሰቃይ የኖረች ኢትዮጵያ ሃገራችን በመጨረሻም በህይወት የመኖር አለመኖር የህልውና ትግል ውስት የገባችው ለረጅም ጊዜ በደረሰባት ያልተቋረጠ ጥቃትና ለተሰነዘረባት ጥቃት በሁሉም አቅጣጫ ተመጣጣኝ ምላሽ ባለመሰጠቱ ነው የፋሽስት ተልእኮ አስፈፃሚ የሆኑ የባንዳ ልጆች፣ በሚሲዮናውያን ስብከት የነሆለሉ ጽንፈኛ ብሔርተኞች ምንም ዓይነት ጥናትና ምርምር ሳያደርጉ፣ የሰሙትን ሁሉ አምነው ተቀብለው በሆይሆይታና በአመጽ በሃገራቸውና ባባቶቻቸው ላይ የተነሱት 60ዎቹ ጥራዝ ነጠቅ፣ ግልብ ተማሪዎች የተከተሉት መንገድ ሃገራችንን ብዙ ዋጋ አስከፍሏታል።  

2.    ዝርፊያና የአረብ ነጋዴዎች፣

እንደሚታወቀው በጥንት የሃገራችን ታሪክ በሰሜን ሶማሌ በቀይ ባህር ዳርቻ የሚገኘው የዘይላ ወደብ በአክሱም መንግስት ስር የሚተዳደር የኢትዮጵያ አካል ነበር። ምንም እንኳን የዘይላ ወደብ የሚገኝበት በወቅቱ አዳል ተብሎ በሚጠራው ግዛት ለኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የሚገብር የኢትዮጵያ አውራጃ ቢሆንም በአካባቢው የአረቦች ተጽዕኖ እየበርታ በመጣበት በመካከለኛው ዘመን አዳልን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም ነበር። በመካከለኛው ዘመን (Medieval Period) ከአረብ ሃገራት በየመን የኤደን የባህር ወደብ በኩል ወደ ምስራቅ አፍሪካ ባህሩን አቋርጠው በመምጣት በዘይላ፣ በሞምባሳ፣ በሞቃድሾ እስከ ታንዛኒያ እና ሞዛምቢክ ድገስ የባሪያ ንግድ የሚያከናውኑ የአረብ ነጋዴዎች ነበሩ። በወቅቱ ለአረቦች በባርነት የሚሸጡ አፍሪካውያን ደግሞ ክርስቲያኖች እና ሙስሊም ያልሆኑ የአካባቢው ነዋሪ ህዝቦች ናቸው። ለምሳሌ በአዳል ግዛት ውስጥ ከእነዚህ የአረብ ነጋዴዎች ጋር ግንኙነት የነበረው አሚር ማህፉዝ ኢብን መሐመድ የተባለ የዘይላ አስተዳዳሪ ነበር። ማህፉዝ ወደ ደጋማው የኢትዮጵያ አውራጃ ወደነበረው ዳዋሮ አድብቶ በመሄድ መኖሪያ መንደሮችን በመወረር የባላገሩን የቤት እንሣት፣ የቤተክርስቲያናትን ወርቅ፣ ብርና አልባሳት፣ እንዲሁም ሴቶችንና ህጻናትን አፍነው ይወስዱ ነበር፣ እራሳቸውን ሲከላከሉ የሚማረኩ ወንዶችን ባሪያ አድርገው ለአረብ የባሪያ ነጋዴዎች ገበያ አውጥተው ይሸጧቸዋልዋል። የማህፉዝ አሟሟት ለወረራ በዘመተበት ወቅት በተፈጠረ ጦርነት ነው። አሚር ማህፉዝ ከሞተ በኋላ ባቲ ድል ወምበራ የተባለች ልጁን ያገባው በተለምዶ ግራኝ አህመድ እየተባለ የሚጠራ ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ (1507 እስክ 1543 ..) ከአረብ ነጋዴዎች ጋር አማቹ ማህፉዝ ጀምሮት የነበረውን ግንኙነት ቀጠለ። በኢትዮጵያ ውድቀትና ኪሳራ መበለጽግ የፈለጉ ኑሯቸውን ሃረር ያደረጉ የአረብ ነጋዴዎች ግራኝ አህመድ የክርስቲያኑን መንግስት እንዲወጋ ይገፋፉት ነበር። በተለይ ሼህ መሐመድ አል መግራቢ እና ሳድ ቢን የኑስ የተባሉ አረቦች ለግራኝ አህመድ ህልም አየንልህ በማለት ለጦርነት ያነሳሱት ነበር። “አንድ ቀን ተኝቼ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ሁለት ቅዱሳን አየሁ . . ሱልጣን አትበሉት፣ አሚርም አትበሉት ነገር ግን የሙስሊሞች ኢማም በሉት . . . በዚህ ሰው አማካኝነት አላህ የሃበሻን ሃገግ ይገዛል . . ።“The conquest of Abyssinia” . . page 18 and 19. አየን የሚሉትን ህልም ለግራኝ አህመድ ደጋግመው ይነግሩት ነበር። ይህ ህልም ሳይሆን የጦርነት ቅስቀሳ ነው። እነዚህ የአረብ ሼኮች በሃረር ከተማ እየተዟዟሩ ግራኝ አህመድን በተመለከተ አየነው ስለሚሉት ህልም (ፕሮፓጋንዳ) በመንገር ህዝቡን ለጦርነት ይቀሰቅሱ ነበር። ግራኝ አህመድ በሼኮቹ ህልም በመበረታትት ተዋጊ ሰራዊት አደራጅቶ የንጉሱን ግዛት የነበረውን ዳዋሮን በመውረር የተለያዩ ንብረቶች፣ በርካታ ከብት፣ ፈረስ፣ በቅሎ ዘርፎ፣ የሃገሩን ሰዎች በባርነት ይዞ ተመለሰ። “He organized his army, . . he set forth against the country of the infidels (Christians) finally arriving . . a place called Dawaro where they amassed vast booty: horses and mules, slaves and livestock.” “The conquest of Abyssinia” . . page 20. በድል እንደተመለሰ በሃረር ከተማ፣ በትውልድ ሃገሩ በሆባት፣ በቅርብ ወደሚገኙ የሶማሌ መንደሮች በመሄድ የጎሳ መሪዎችን እየሰበሰበ የዘረፈውን በማሳየት ከእሱጋ ቢቀላቀሉ እነሱም እንደሱ እንደሚከብሩ ያማልላቸው (ይቀሰቅስ) ነበር።      

በመሆኑም ግራኝ አህመድ በየቦታው እየተዟዟሩ ተዋጊ ሰራዊቱን በመመልመል፣ ከሞሮኮ፣ ከየመን፣ ከግብጽ እና ከተለያዩ የአረብ ሃገራት ዘርፈው ለመክበር በመጡ “የጂሃድ” ተዋጊዎች ሃይሉን በማጠናከር፣ የኦቶማን ቱርክ ገዢዎች ያስታጠቁትን በወቅቱ ዘመናዊ የተባለ ቱርክ ሰራሽ ጠመንጃ (Matchlock) እና መድፍ በማስታጠቅ መቀመጫውን ሸዋ በረራ ላይ ባደረገው የደጋው የክርስቲያን መንግስት ላይ ጦርነት አወጀ። በኢትዮጵያ ኪሳራ ማትረፍ ለሚፈልጉ አረቦች ገፋፊነት ላወጀው ጦርነት ጀሃድ የሚል ስም” በመስጠት ዘረፋውን ቅዱስ ለማስመሰል ሞከረ። በ1521 ዓ/ም በምስራቅ ሸዋ ለሞጆ እና ደብረዘይት ከተሞች ቅርብ በሆነ “ሽምብራ ኩሬ” በተባለ ቦታ ላይ ከአጼ ልብነ ድንግል ጦር ጋር ከፍተኛ ጦርነት አድርገው በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የንጉሱ ተዋጊዎች በቱርክ ሰራሽ ነፍጥና መድፍ በተተኮሱ አረሮችና የመድፍ ሼሎች ደማቸው ፈሰሰ። ሽምብራ ኩሬ ሃገራቸውን ከወራሪና ዘራፊዎች ሲከላከሉ በተሰዉ ሰማዕታት የደም ጎርፍ ጨቀየች። በዛ ባልተባረከ ክፉ ቀን ድሉ ለግራኝ አህመድ ሆነ። በመቀጠል ግራኝ አህመድ ከተማ ለከተማ፣ በየገዳማቱና ቤተክርስቲያኑ እየዞረ የሃገሪቱን ሃብትና ታሪካዊ ቅርስ መዝብሮ ሲያበቃ ቤተ መንግስቱንና ቤተክርስቲያናቱን አቃጠላቸው፣ የበረራን ከተማ ጨምሮ በደብረዘይት፣ በዱከም፣ በየረርና አካባቢው ይገኙ የነበሩ እንደ ዘመኑ የቤት አሰራር ጥበብ በሳር ክዳን የተሰሩ የክርስቲያን መንደሮችን ሰዎቹን አሰማርቶ ያለ ርህራሄ እንደ ጧፍ አነደዳቸው፣ እምነታችንን አንቀይርም ያሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን (የንጉሱን ልጅ ልዑል ሚናስን ጨምሮ) ወደ ዘይላ ወደብ በማሻገር ለአረቦች በባርነት ሸጣቸው ቀድሞም ቢሆን በኢትዮጵያ ኪሳራ ከመክር ውጪ ሌላ አላማ ያልነበራቸው የአረብ ነጋዴዎች ከሃገሪቱ የተዘረፉ ቅርሶችን እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን በመላው የአረብ ሃገራት በተለይም በደቡብ አረቢያ ለጅዳ ቅርብ በሆነች Zahid በምትባል ቦታ እንዲህም Gujarat (ጉጅራት) በሚባል የህንድ ግዛት ድረስ እያሻገሩ ሸጧቸው። ይህንን በሃገር እና በህዝብ ላይ የደረሰ አጠቃላይ ውድመት ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግስቴ በመጽሃፋቸው ገጽ 190 እንዲህ በማለት ይገልጹታል፡ “እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ በራራም በግራኝ አህመድ ወታደሮች ተዘርፋ ተቃጠለች። . . . የግራኝ አህመድ ወረራ ኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድን ባጠቃላይ ከስልጣኔ ማማ አውርዶ ወደድንጋይ ዘመን የእድገተ ደረጃ መለሳቸው”።  

   

3.    የጥንቱ የገዳ ስርዓት፣

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች የገናሌ (ጁባ) እና የዋቢ ሸበሌ ወንዞች በሚፈሱበት ሰፊ አካባቢ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀርሱ ይኖሩ ነበር። ይልማ ደሬሳ የተባሉ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዘመን ሚኒስቴርነት የነበሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ከአባቶቼ በቃል ሲወርድ የሰማሁት እና ከታማኝ ምንጮች ያነበብኩት ነው በማለት “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” በተባለ መጽሐፋቸውኦሮሞዎች ወደ ደጋ ኢትዮጵያ መውጣት” በሚል ምዕራፍ ስር ስለ ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ወደ መሃል አገር እንዴት እንደተስፋፉ ይገልጻሉ። በመሆኑም የገናሌን ወንዝ በመሻገር መጀመሪያ በባሊ ቆላማ አካባቢዎ በመቀጠልም ቀስ በቀስ ወደ ደጋማው የባሊ ተራራማ አካባቢዎች እና ለአባያ ሃይቅ ቅርብ በሆነ ለከብቶች በቂ ውሃና የግጦሽ መሬት በሚያገኙበት ለምለም አካባቢ በመፍለስ ሰፈሩ። የሰፈሩበትንም አካባቢ በኦሮምኛ  ቋንቋ “መደ ወላቦ” ብለው ጠሩት። የአካባቢው የተፈጥሮ ልምላሜ እየተስማማቸው ስለመጣ ከብቶቻቸው እጅግረቡላቸው፣ የህዝቡም ቁጥር እየጨመረመምጣቱ ለከብቶቻቸው የግጦሽ መሬት ጥበት አጋጠማቸው በማለት ይልማ ደሬሳ ታሪኩን ይቀጥላሉ እንግዲህ በዚህ ወቅት ነበር ግራኝ አህመድ መቀመጫውን ሸዋ በረራ ላይ ባደረገው የደጋው የክርስቲያን መንግስት ላይ ጦርነት ያወጀው። በመሆኑም ግራኝ አህመድ ዘርፎና አቃጥሎ ያለ ጠባቂ ያስቀራትን ሃገር እና ይህንን መከረኛ ህዝብ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች ጎረቤቶቻቸውን በመንጋ በመውረር  እያፈናቀሉ በመሬታቸው ላይ መስፈር የጀመሩት።

በተለይ 16ኛው እስከ 17ኛው / ባሉት ጊዜያት የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች በአባ ገዳዎች (ሉባዎች) እየተመሩ ነባሩን የሃገሩን ህዝብ ከቀዬው እያፈናቀሉ በመሬቱ ላይ ሰፈሩ፣ በየመደሩ እየገቡ ወንዱን ገድለው ሴቱን ሚስት፣ ህፃናቱን ደግሞ ለዘረፉት ከብቶች በጉድፈቻ ልጅነት እረኛ አደረጓቸው። ህዝቡንም ሞጋሳና ሚቲቻ በሚባል ባህላቸው ባርያ (ገርባ/ Serfs) በማድረግ የህዝቡን ቋንቋ፣ ባህሉንየሃገሩን መጠሪያ ስም ሳይቀር በመለወጥ ማህበረሰቡን ከራሱ ማንነት እና ታሪክ ጋር በመለያየት Cultural genocide ፈጸሙበት። የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች ነባሩን የሃገሩን ተወላጅ ህዝብ በሃይልና በተፅዕኖ ቋንቋ፣ ባህልና ማንነቱን አስገድደው እንዲቀይር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ በየጎሳውና ነገዱ የነበረውን የቆየና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲዳብር የመጣን የማህበረሰቡን ባህላዊ አደረጃጀት በጥቂት ጊዜ ውስጥ በማፍረስ የማያውቀውንና የእሱ ያልሆነውን የኦሮሞ ባህልና ቋንቋ ጫኑበት። ለምሳሌ በጅማ ማለትም በጊቤና አካባቢው የነበሩ ጥንታዊ የጊቤ መንግስታትን ጨምሮ፣ በደቡብም ሆነ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍሎች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የነበሩመንግስት መዋቅሮችን በማፍረስ የህዝቡን የማንነት መገለጫዎች ከምድረ ገጽ አጠፉት።

  

ይሁን እንጂ የኦሮሞ ፅንፈኛ ብሔርተኛ ልሂቃን በኦሮሞ ወረራና መስፋፋት ምክንያት በኢትዮጵያ ነባር ህዝቦች ላይ የተፈጸመን የባህል፣ የቋንቋና የማንነት ድምሰሳን እንደ ተራና ቀላል ነገር ሸፋፍነው በማለፍ የችግሩ ምንጭ የሆነውን የገዳን (የሞጋሳን) ሥርዓት ሲያሞግሱ፣ በቃላት በማሰማመርሃሰት ያለባህሪው አቃፊና ዲሞክራሲያዊ በማስመሰል በባዶ የሚመጻደቁ ናቸው። ምናልባት ፈረንጅን ማታለለ ይቻል ይሆናል፣ እኛ ግን ፈረንጅ ሳንሆን ለዘመናት አብረን የኖርን ቤተሰብ በመሆናችን የገዳ ስርዓት ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን። የገዳ ሥርዓት ከሰማይ የወረደ የቅዱሳን ማህበር ሳይሆን ስልጣኔ ባልተስፋፋበት ወቅትነበሩ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች ያጋጠማቸውን የግጦሽ መሬት ጥበት እና የውሃ እጥረት ችግር በወቅቱ በነበራቸው የእውቀት ደረጃና የህይወት ልምድ መሰረት ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይከተሉት የነበረ ባህላዊ አሰራር ነው። ቋንቋዬ፣ ባህሌ እንዲከበርልኝ ነው ወደትግል የገባሁት ሲሉ የሚሰሙት የኦሮሞ የዘውግ ፖለቲከኞችና ልሂቃን በራሳቸው ላይ ሊደረግ የማይፈልጉትን በደል፣ ጭቆና እና ሰብአዊ ጥሰት ያውም እነሱ ባልነበሩበት ከዘመናት በፊት የተፈጸመን ኋላቀር ድርጊት እንዳልተፈጸመ ያህል ዓይኔን ግምባር ያድርገው በማለት መካዳቸው ለህሊናቸውም ሆነ ለሞያ ስነምግባር የማይገዙ ግብዞች (Hypocrite) ወይም ልዝብ ሴጣን መሆናቸውን ያሳያል። ለዚህ ነው የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኞች እውነትን የመጋፈጥ ወኔ (ሃሞት) የላቸውም ሲባል የሚሰማው ሃቅን በመሸሽ፣ በክህደት የሃሰት ትርክት ፈጥሮ በማድበስበስ ታሪክን ማቃናት የሚቻል ስለሚመስላቸው ብዙ ጊዜ ከታሪክም ሆነ ከራሳቸው ጋር ሲላተሙ ይታያሉ በተለያየ ጊዜ እራሳቸው ከጻፉትና ከተናገሩት አንጻር አምባሳደር ሱሌማንን፣ ህዝቅኤል ገቢሳን እና መሃመድ ሃሰንን እዚህ ላይ እንደ ጥሩ ምሳሌ  ማንሳት ይቻላል።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፣ ድሮ ዓለም ባልሰለጠነበት ጊዜ የነበሩት ጥንታዊ የኦሮሞ ከብት አርቢ ጎሳዎች Primitive Oromo Nomadic Pastoral tribes እና አሁን በዘመናችን ሚገኘው የኦሮሞህበረሰብ Contemporary Oromo መሃል ብዙ ልዩነት እንዳለ መገንዘብ ተገቢ ነው።ጥንቱ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች ወደ መሃል ሃገር ሳይንቀሳቀሱ በፊት የነበራቸው ባህል፣ አኗኗር፣ እምነት፣ አስተሳሰብ፣ ስነልቦና፣ የህዝቡ ስብጥር፣ ብዛት እና የመሳሰለው አሁኑ በዘመናችን ካለው የተለየ ነው እምነትን ብንመለከት ቀድሞ ይከተሉት የነበረውን ባህላዊ እምነት ወይም አምልኮት (Traditional belief) በጊዜ ሂደት በመተው እስልምናን፣ የኦርቶዶክስን የአውሮፓ ሚስዮናውያኑን የክርስትና እምነትን ተቀብለዋል። አሁንም እንደ ድሮው ባህላዊ እምነት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ከክርስትናው እና ከእስልምናው ጋር እየቀላቀሉ የሚያመልኩም አሉ። ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ በመነሳት ወደ መሃል ሃገር በመንቀሳቀስ ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ይናገሩት የነበረው የኦሮምኛ ቋንቋ ባህልና የመሳሰሉት አሁኑ ካለው የተለየ አሁን ያለው የኦሮምኛ ቋንቋና ባህል በአንድ ጊዜ የተገኘ ሳይሆን ለዘመናት ከሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ቋንቋዎች እና ባህሎች ጋር በተፈጠረ መስተጋብር ሲዳብር፣ ሲሻሻል፣ ሲቀየጥ እዚህ የደረሰ ነው። እንደሚታወቀው የግራኝ አህመድን ወረራ ተከትሎ 16ኛው እስከ 17ኛው / ባሉት ሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች የሃገሩን ነባር ህዝብ በመውረር የተስፋፉበት፣ ህዝቡን ያወረሙበትና በመላ ሃገሪቱ በሚያስብል ደረጃ የተሰራጩበት ወቅት ነው። ከዛም በመቀጠል ባሉት ተከታታይ ዘመናት በተለይም በዘመነ መሳፍንት ተጠናክረው በመንግስት መዋቅር ውስጥ እስከ ላኛው የመንግስት የስልጣን ማማ ድረስ መቆጣጠር ችለዋል። በመሆኑም ይህ የኦሮሞ ትውልድ ማንነቱን ወደ ኋላ ሄዶ ቢመረምር የዘር ሃረጉ ከአማራ፣ ከጉራጌ፣ ከጋፋት፣ ከሃድያ እና ከመሳሰሉት የኢትዮጵያ ወገኖቹ መሆኑን በተረዳ ነበር።

 

እንደ እውነቱ ከሆነ ከዛሬ አራት እና አምስት መቶ ዓመታት በፊት ዘመናዊ ትምህርትም ባልነበረበት፣ ስለ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና ሰብአባዊ መብት በማይታወቅበት፣ ዓለም ባልሰለጠነበት ወቅት የመንግስትነት አደረጃጀት ያልነበራቸው በጎሳ ደረጃ ተሰባስበው ህይወታቸውን በከብት አርቢነት ይገፉ በነበሩ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ አርብቶ አደሮች የተፈጸመ ጥሩም ሆነ መጥፎ እንደ አንድ የሃገራችን ታሪክ እውነቱን ተቀብለን ማለፍ ሲገባን አንዳንድ የኦሮሞ ልሂቃን ታሪክን ገልብጠው ኦሮሞ ተወቀሰ በማለት ህዝብን በማነሳሳት የፖለትሪካ ቁማር መጫወቻ ሲያደርጉት ይታያል። እውነቱ ግን በወቅቱ የነበረው የገዳ ስርዓት ከኦሮሞ ውጪ የሆነን ህዝብ አፈናቅሎ ወይም ወግቶ በማጥፋት መሬቱ ላይ የሚሰፍር እንጂ ፈፅሞ አቃፊ አልነበረም። ይህ ፀሃይ የሞቀው፣ የዓለም ምሁራን የመሰከሩት ነው። ለምሳሌ / ነጋሶ ጊዳዳ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክብለው በጻፉት መፅሐፍሰዮ (ቄለም) ወለጋ አካባቢ የነበሩ ቀድሞ ኦሮሞ ያልነበሩ የሃገራችን ነባር ህዝቦች እንዴት በአባ ገዳዎች ወረራ ቋንቋና ባህላቸው እንደጠፋ ገልጸዋል። / ነጋሶሰዮ (ቄለም) ወለጋ አካባቢ ብዛታቸው ከአስር በላይ የሆኑ የተለያዩ ነባር (Native) ማህበረሰቦች በሞጋሳ ተገደው ኦሮሞ እንደሆኑ እስከ ስማቸው ዘርዝረው ገልፀዋል። ይህ የመሬት ወረራና የባህል ጭፍለቃ የተፈፀመው በወለጋ ውስጥ ብቻ ሳይሆን አሁን ስማቸው በተቀየረ ጥንታዊ የኢትዮጵያ አውራጃዎች በሚባሉት በደዋሮ፣ በፈጠጋር፣ በወጅ፣ በማያ፣ በሸዋ፣ በዳሞት፣ በቢዛሞ፣ በገኝበእናርያ፣ ባሌሊና በመሳሰሉት ተፈፅሟል። በነዚሁ ጥንታዊ የኢትዮጵያ አውራጃዎች ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው 20 በላይ የሆኑ የራሳቸው ቋንቋ፣ ባህልና ማንነት የነበራቸው ነባር ማህበረሰቦች በኦሮሞ አርብቶ አደሮች የመንጋ ወረራ ከምድረ ገፅ ጠፍተዋል። በነገራችን ላይ የጅማው አባ ጅፋር እና የኦሮሞ የባሪያ ነጋዴ ባላባቶች በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠር የጅማ እና የአካባቢው ነባር ጥንታዊ ህዝቦችን እንደ እንስሳ መንደሩ እያደኑ አሮጊትና ህፃናትን እያስቀሩ ህዝቡን በባርነት በዘይላ (ሰሜን ሶማሌ) በኩል ወደ የመኗ የኤደን ወደብ እያሻገሩ ኢትዮጵያውያንን ለአረብ ሸጠዋል በአሁኑ ጊዜ በአረብ ሃገር የሚገኙ ጠይም (ጥቁር) የሃገሩ ዜጎችኢትዮጵያን ጨምሮ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በተለይም ከአፍሪካ ቀንድ በአረብ የባሪያ ንግድ (Arab Slave Trade) አባቶቻቸው ተሽጠው እዚያው የተዋለዱ ናቸው 

እንደሚታወቀው የገዳ ስርዓትን የሚመሩት አባ ገዳዎች (ሉባዎች) በየስምንት አመቱ ይቀየራሉ። ከስልጣናቸው የወረዱትም ሆነ አዲስ የሚሾሙት አባ ገዳዎች የአመራር ብቃታቸው የሚመዘነው በማህበረሰቡ ዘንድ ዝናና ሞገስ የሚያስገኝላቸው በስልጣን ዘመናቸው ኦሮሞ ባልሆኑ ጎረቤቶቻቸው ላይ ወረራ በመፈጸም ለጎሳቸው በሚያስገኙት ተጨማሪ የግጦሽ መሬት፣ በነዱት (በዘረፉት) የከብት መጠን፣ በሞጋሳና በጉድፈቻ ባወረሙት የህዝብ ብዛት፣ ባላቸው የግል አሽከር፣ ባርያ (ገርባ/ Serfs) መጠንና በመሳሰለው ነው። ለአባ ገዳዎች “ገርባ” የጎረቤቶቻቸውን መውረር በፈለጉ ጊዜ እንደ ወታደር የሚያዋጉት፣ በእርሻ ወቅት እንደ ጭሰኛ ገበሬ በነጻ ያለክፍያ የሚያሳርሱት፣ ሲፈልጉ ገበያ አውጥተው እንደ ባሪያ የሚሸጡ የሚለውጡት ከሰው በታች የሆነ ከእንሣት ያልተሻለ የግል ንብረታቸው ነው። በመሆኑም አንድ አባ ገዳ ይህንን ዝና እና ክብር በመህበረሰቡ ዘንድ ለማግኘት ከሌሎች አባ ገዳዎች የተሻለ ሆኖ ለመታየት ፉክክር ውስጥ ይገባል። ስለዚህ በተከታታይ ስምንት ዓመታት ያለማቋረጥ በሚፈጽሙት ወረራ የተነሳ ኦሮሞና ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ፣ መኖሪያ ሃገሩም እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ተወራሪዎቹ ማህበረሰቦች ነፍሳቸውን ለማዳን በመሸሽ በአነስተኛና በተጣበቡ አካባቢዎች፣ በየገደላገደሉና በየተራራው አናት ላይ ተጨናንቀው ለመኖር ይገደዳሉ እንግዲህ ይህንን በየስምንት ዓመቱ አባ ገዳዎች የሚፈጽሙትን አስነዋሪና ኢሰባዊ ድርጊት ነው ኦነጋውያን አይናቸውን በጨው አጥበው ገዳ “ዲሞክራሲያዊ” ነው ሲሉ የሚሰማው። ነገር ግን ለተወራሪው፣ ከርስቱ ከመሬቱ ላይ ለተነቀለው፣ ለተገደለው፣ ዘሩን፣ ማንነቱን፣ ቋንቋና ባህሉን በኦሮሞ ወረራ፣ በሞጋሳና በጉዲፈቻ ለውተነጠቀው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ግን የገዳ ስርዓት “ዲሞክራሲያዊና አቃፊ” ሳይሆን ጨቋኝ፣ ጨፍላቂና ማንነትን ደምሳሽ ነው።

 

ስለዚህ የገዳ ሥርዓትዲሞክራሲም ሆነ ከአቃፊነት ጋር ምንም ዓይነት ዝምድናም ሆነ ግንኙነት የሌለው የሰው ልጅ መፈጠሪያ ከሆነችው ከኢትዮጵያ ምድር የተገኙ ነባር ህዝቦችን እስከ ባህል፣ ቋንቋና ማንነታቸው ጠራርጎ ያጠፋ፣ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የአካባቢ መንግስታትን የደመሰሰ፣ በየጎሳውና ነገዱ የነበሩ ባህላዊ አደረጃጀቶችን ያፈራረሰ፣ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ ስደት መፈናቀል ምክንያት የሆነ፣ ይህ የገዳ ስርዓት ኦሮሞ ባልሆነው በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መጫን ከጀመረበት ከዛሬ አምስት መቶ አመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው። ስለዚህ ይህ ከዘመኑ ስልጣኔና አስተሳሰብ ጋር የማይሄድ፣ ጸረ ዲሞክራሲ የሆነ ስርዓትና አስተሳሰብ ለብዝሃነት የማይበጅ በመሆኑ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ሙዚየም መቀመጥ አለበት–//–

ገለቶማ”

ምንጭ፣

1.      “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ (/ ነጋሶ ጊዳዳ) – 2008 ዓ/ም

2.     በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 1887) እድገት ውድመት እና ዳግም ልደት 2020

 ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግስቴ ተገኝ

3.     “The conquest of Abyssinia” Futuh al-Habasa (Arab Faqih) 2003

4.     የብሔሮች ጠላት ማነው? ሞጋሳ ወይስ ምኒሊክ? ርዕዮት ሚድያ

2 Comments

  1. “Beekaan wanna dubbatu beeka; gowwaan waanuma beeku dubbata” goes an Oromo proverb! ትርጉም> አዋቂ የሚናገረውን ያውቃል፣ ሞኝ የሚያውቀውን ያወራል። “እኔ የማውቀው ይህቺኑ ብቻ ነው” ለማለት በዝባዝንኬ ገጾችን ከመሙላት፣ አንዳንድ የእውነተኛ ታሪክ ገጾችን ብታገላብጥ የበለጠ በጠቀመህ ነበር። አስሬ ብትደርተው ያረጀ ተረት ያው ተረት ነው። ግን ተረትን ከታሪክ ለመለየትም ችሎታና ዙሪያገብ ምልከታ ይጠይቃልና አይፈረድብህም።

  2. ሰሞኑን ሳተናውና ዘሃበሻን ገጾች ስመለከት ነበር። ጎልቶ የሚወጣው አንድ መልእክት ነው። ምንሊክ ብቻ ልክ ናቸው፤ አማራ ብቻ ነው ኢትዮጵያዊ። ሌላው በተለይ ኦሮሞ መጤ ነው (በ15ኛና 16ኛ ምእተ ዓመት)። ዋነኛ ጸሐፊዎቻቸው ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ ሰርፀ፣ አቻምየለህ፣ ወዘተ። አንዳቸውም በሚጽፉት ፖለቲካ ወይም ታሪክ ላይ የተለየ ብቃት የላቸውም። ኦሮሞ ነባሮቹን ገድሎ ዘርፎ መሬታቸውን ቀምቶ ይላሉ! ይኸ ትርክት አሳፋሪ፣ ደንቆሮ ብቻ ሳይሆን ዘረኛ ነው። የሚያቀርቡት የሚደግፋቸውን መረጃ ብቻ ነው። ጠባብ ከመሆናቸው የተነሳ፣ በዓለም ሁሉ ላይ ከታየው የሕዝቦች አሠፋፈር፣ የኢትዮጵያው ብቻ የተለየ ነው ብለው ሊያሳምኑን ይጥራሉ! የሚያሳዝነው፣ ኦሮሞ ምሑራንም በተራቸው አማራ ቅኝ ገዥ ነፍጠኛ ገድሎና ዘርፎ እንጂ ከቅድመ ኦሪት መሬቱ የኛ ነው ይላሉ። በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን ላይ ሆነን አስተሳሰባችን ገና በጨለማ ዘመን ውስጥ ነው! አገራችንስ እንዴትና መቸ ትረፍ? እረፍት የነሳናት እኛው ነን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.