ሱሌይመን ደደፎ የግብጽ ወይስ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት! – ሰርፀ ደስታ

sulemanሱሌይመን ደደፎ ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ትንሽ ተስፋ የጣልንበት ነበር፡፡ ያው የተለመደው የኦሮሞ ፖለቲከኛ ማንነት ሲገለጥ በእሱም የቱንም ያህል ለመደበቅ ቢሞክርም አልቻለም፡፡ አዝናለሁ፡፡ አብረሀም ሊንከንና ሚኒሊክ መወዳደራቸው እንዲህ አብድ ያደረገው ሱሌይመን ሚኒሊክ ምድር ላይ ባለፉት 1000 ዓመት ከተነሱ መሪዎች የሚተካከላቸው እንደሌለ ብንነግረው ምን ሊሆን ይሆን፡፡ እውነት ነው፡፡ ሚኒሊክን ብዙ ጊዜ ጸሐፊዎች የሚያወዳድሩት ጀርመንን አንድ ካደረገው ኦቶ ቢስማርክ ጋር ነው፡፡ ቢስማርክ ጀርመንን ከማዋሀድ ያለፈ ነገር ግን ከሌሎች በተለየ የሰራውን አናውቅም፡፡ ሚኒሊክ በደሀዋ የአፍሪካ አገር፣ አገር አንድ ማድረግ ብቻም ሳይሆን ምድር ላይ አለ የተባለ የዘመኑን ቴክኖሎጂ ወደ አገር ማስገባትና በተጠቃሚነት በአህጉሩ ብቻም ሳይሆን ከብዙ ዛሬ አደጉ ከምንላቸውም ቀድመው ብዙ ቴክኖሎጂዎችን እንዳስገቡ ታሪካቸውን ያዩ ፅፈውላቸዋል፡፡ ሚኒሊክን ያዋረደ እየመሰለ እየተዋረደ ያለው በራሱ ጊዜ ወዶ በአስተሳሰብ ባርነት ሥር የወደቀው የዛሬው የኦሮሞ ተማርኩ የሚለው ቡድን ይሄው በሚኒሊክ ታሪክ እውነታነት እየማቀቀ ይኖራል፡፡ አዝናለሁ፡፡

ሱሌይመን ደደፎ ሚኒሊክን ጭራቅ አስመስሎ ለማሳየት በዘመናት ነውረኛ ትርክት የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ የከተታውን የራሱን ቡድን አልፎ ጭራሽ በብሔረሰብ ደረጃ ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ሌሎች የደቡብ ምናምን በሚኒሊክ የተጨፈጨፉ የተረገጡ እያለ ያንኑ የባርነት ማላዘን ትርክት ሲያወራ እንደ አንድ ያገር ዲፕሎማት አልቀፈፈውም፡፡ ያለው ሁሉ እውነት ቢሆን አንኳን ሊያውም ከ150 ዓመት በፊት በክብር ለዓለም የተገፉ ሕዝቦች ሁሉ የልዕልና ምልክት ሆነው ያረፉትን ሚኒሊክን ጭራቅ አድርጎ ለማሳየት የሄደባቸው ንግግሮቹ አሳዛኝ ናቸው፡፡

የሱሌመን ደደፎ አስገራሚው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ጽ/ቤቱ ለግብጽ ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ አልቀፈፈውም፡፡ ይሄ ነው እንግዲህ የተደበቀ ማንነት ሲባርቅ፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚሉት ማለት ነው፡፡ አዝናለሁ! ሲጀምር ምኒሊክ በእሱ መስፈርት የሚለኩ ሰው አደሉም፡፡ የሚኒሊክ ልዕልና መስሎኝ ዛሬ ድረስ እያባነነው ያለው፡፡ አሁን 50 ዓመት የሆነው የኦሮሞ ፖለቲካ በጥላቻና ዘረኝነት ስብከቱ ይሄው ትውልዱን ሁሉ ባዶ አድርጎት እያየን ነው፡፡ አሁን ጊዜው የእኛ ነው በሚል እጅግ በሚያሳዝን ስግብግብነትና እኩይ ሴራ እየሸመቀም ይገኛል፡፡ አገርን ለማፍረስ፡፡ አዝናለሁ፡፡ የተንኮልንና የክፋትን ጉድጓድ ማራቅ ማን እንደሚወድቅበት ለማይገነዘብ፡፡ የኮቪድ አዋጅ አውጀው እነሱ ግን አሁንም በጥፋት ሥራ ቀን ከሌሊት እየሰሩ ነው፡፡ ሱሌይመን ደደፎንም ሆነ ጠ/ሚኒሰቴሩን ብዙ ሕዝብ ደግፏቸው እንደነበር እኔን ጨምሮ ሳሰብ ስለእነሱ እኔ አዝናለሁ፡፡ ምን የሚሉት እርግማን እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ግን ወጤቱ ጥሩ አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ሱሌይመን ደደፎ የሚኒሊክን ከኢነግሊዝ ጋር የተዋዋሉትን አስደናቂ ውል ነበር በግብጾች ተሞልቶ በግብጽ የፀረ-ኢትዮጵያ ዘመቻ ተሳታፊ የሆነው፡፡ ግብጽ ብዙ የኦሮሞ ሙስሊሞች ከጎኗ እንደሆኑ ታውቃለች፡፡ ኦኤም ኤን ግብጽ ማሰራጫ ከፍቶ የነበረው ይሄንኑ የግብጽን ሴራ ለመደገፍና ዳረጎት ለመቀበል ነበር፡፡ ዛሬ ግን እነዛው ግለሰቦች አገር ቤት ገብተው ጭራሽ በፖለቲካ ፓርቲ ተደራጅተው ይሄው አገር እናፈርሳለን እያሉ እየፎከሩ ይኖራሉ፡፡ ማንም አገር ይሄን አይነት ድርጊት ያደረግን በትግስት አያየውም፡፡ እንግዲህ ግብጽ እየተማመነች የለቸው ሰራዊቷን ሳይሆን የኦሮሞ ሙስሊም ተባባሪዎቿን እንደሆነ ላፍታም አንዘነጋም፡፡

ዛሬ ግብጽ ሙስሊሙን ለማሰለፍ የምታደርገውን ጥረት ታቁም የሚል መግለጫ ከዛችው ከጉድ አገር ኢትዮጵያ ሰምተናል፡፡ ሲጀምር ለግብጽ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ምን የሚሉት ቀልድ እንደሆን አልገባኝም፡፡ እግረ መንገዱን ግን ምን ያህል ሥር የሰደደ የግብጽ በሙስሊም ማህበረሰቡ እየታገዘች እንደሆነ ያሳየን ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ ይሄ እንግዲህ ኢትዮጵያዊ ነን ለምትሉ ሙስሊሙች ምን ማለት እንደሆነ እወቁት፡፡ ኢትዮጵያ እንጂ ግብጽ አደለችም በእስልምና እምነት በበጎ የተገለጽች አገር፡፡ ብዙዎች ለአገራቸው እየተዋጉ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ቀላል የማይባል የኦሮሞ ሙስሊም በጸረ-ኢትዮጵያ መስመር እንዳለ እናውቀለን፡፡ ያሳዝናል፡፡

ለማንኛውም ሱሌይመን ደደፎም የዚሁ አንድ አካል እንደሆነ በመጨረሻው ቅን ነግሮናል፡፡ የሚኒሊክ ውል ሲጀምር ከኢነግሊዝ መንግስት ጋር እንጂ ከግብጽ ጋር አልነበረም፡፡ በመሆኑም የኢንግሊዝ አስተዳደር በቀጣናው ሲያበቃ አብሮ አብቅቷል፡፡ ሲቀጥል ግን ያ ውል በዛን ወቅት ምን ያህል ሚኒሊክን ይፈሯቸው እንደነበር በግልጽ ያሳየ ነበር፡፡ እንደዛሬው ጠብታ ወሀ ወደ ግድብ አትሞላም ለማለት ማን ደፍሯቸው? የውሉ አስገራሚ ንባብ በወቅቱ ኢነግሊዞች ጠብታ ውሀ እንዳያልፍ ሚኒሊክ ሊዘጉት ይችላሉ የሚል ስጋት እንደነበራቸው የሚያሳይና አብክዎን ሙሉ በሙሉ እንዳይዘጉብን ቢያንስ ጠብታ ውሀ ልቀቁልን ነበር፡፡ ለሱሌይመን ደደፎ ቀድም ብለው ብዙዎች መልስ ሰጥተውታል፡፡ በድጋሜ የዛንው ውል ንባብ እዚህ ጋር ትቼዋለሁ፡፡ ምንጩ አቻምየለህ ታምሩ ነው፡፡ እናመሰግናለን አቻምየለህ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ጠላቶቿን ይጣል! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

17 Comments

 1. አንድ ዲፕሎማት የሀገሩ ተወካይ ሁኖ የሚያንጸባርቀዉ የላከዉን መንግስት አቋም ይሆናል በዚህ ሴንሲቲቭ ጊዜ ሱሌይማን የተናገረዉ የግሉን ነዉ ወይስ የመንግስቱን አቋም ብሎ መመርመር ይገባል? አቋሙ ከመንግስት አቋም የሚጋጭ ከሆነ ባስቸኳይ ተጠርቶ በክህደት ወንጀል ሊጠየቅ ይገባል (treason) ትላንት የትግሬ ወንጀለኛ እንዳልተጠየቀ ሁሉ ዛሬ የኦሮሞ ሰላይ አይጠየቅም ከተባለ ሌላ ነገር ነዉ።

  አቶ ገዱ እናዝናለን ዲፕሎማቶችን ኦነጎች ሹመዉ ከጨረሱ በሗላ እርሶን እንደሾሙ ምን ያህል እንደገባዎት አላዉቅም። ለጊዜዉ ሌላዉን ሁሉ ትተን የመጀመሪያዉ የአባይ የድርድር አካሄድ ልክ ባይሆንም መጨረሻ በወገን ዉትወታ ያሳዩት ቆራጥነት በተባራሪ እንደምንሰማዉ እዉነት ከሆነ ልናመስገን እንወዳለን “ስንት ጊዜ ልኖር ነዉ ይህን አሳፋሪ ዉል የምፈርመዉ” ማለትዎን ሰምተን ልባችን ለስልሷል።በተረፈ ይህ የዲፕሎማሲ ሀሁ ያልቆጠረ ለሚኒስተሩም ሆነ ለሀገር ረብ ስለሌለዉ ተመልሶ አጠና ይዞ ሰብአዊ ፍጡርን በደቦ የሚደበድብበት ሁኔታ እንዲዘጋጅለት ቢያመቻቹለት ደህና መሰለኝ። ሰርጸ ደስታ እናመሰግናለን።

 2. Ambassoder Suleyaman has spoken the truth. Menilik II had two images:: For Amhara elites Ase Menililik II is a king, but Oromo and other anions and nationalities of Ethiopia considered Ase Menililik II as a root cause of the problems the contemporary Ethiopia. Hence Menelik II is the root cause of the current problem the county faced be it domestically and regionally. The big mistake is comparing such beast colonizer man with he great leader like Pr Abraham LinkedIn. so back off Ambassoder and support truths. Otherwise this.empire soon will break away, since we could not live in one country.

  • Mohammed Abdi , Please come into your mind. You are totally brain washed with fictitious narratives that are told by mercenary activists who are assigned by certain politicians who want to grab power by all means.
   The truth about the great leader of Emperor Menilek II is totally different from what you knew.
   Emperor Menilek II reunited the territory of Ethiopia that has been vandalized by Mohammad Eben ( Gragne Mohammed) and occupied by heinous migrant Oromos until present day.
   What is the mistake and error of Emperor Menilek II?
   Should he leave the country as it was before?
   He has made one great mistake. He should have driven out the heinous migrant Oromos who occupied our territory by shading the blood of our ancestors.
   You and your likes, the descendant of then heinous occupant Oromos are claiming diametrically the opposite.
   Yes, you are right that Emperor Menilek II is the root cause of problems.
   That problem is the resurrection of your political agenda to reassert our land and country after your ancestors occupied it with brutal vandalism.
   A time will come to liberate our territory and assert our freedom.

  • Mohammed Abdi you have voluntarily given your brain for less inferior people I dont think you will be healed from this inferior complex. Can you give me one example how Menelik Favorited the Amharas? It is really hard to have rational discussion with people like you, you will never heal from the disease which you were infected by Fernjis. you have voluntarily taken the pills. The reality is the north have fought with each other for centuries but they don’t moan like you that is past history.

 3. አምባሳደር ሱሌማን እንደዚህ ይወርዳል ብሎ ማን አሰበ:: ምኒልክ እንኳን በኢትዮጵያ በምእራቡ ሀገር ተበትኖ በባርነት ይኖር የነበረ ህዝብ የመሰብሰብ እቅድ ነበረው:: የሚኒልክን ታላቅነት ትናንሽ ጭንቅላቶች አይታያቸውም ይህ ያሳዝናል:: ሰርፀ ግሩም ፅሁፍ ነው::

 4. መልእክት ለአማሀረ ሊሂቃንና ጠቅላያችን
  በመሰረቱ ለዚህ አገራችን ለምንላት ኢትዮጵያችንን ቀሥፎ ከያዘት የውስጥና የውጭ ችግሮች ውስጥ ከቶንም አላለውሥ የለን አጺ ሚኒሊክ የፈፀቸው ግፎችና ውሎች መሆናቸውን ፈጽሞ ማንም መካድ አይቻልም፤፤ በመሆኑም አጸ ሚኒሊክ ስም ለምን በክፉ ተነሳ ተብሎ አባራ ማስነሳት ተገቢነት የለውም፡፡ አጸ ሚኒሊክ በአማረ ሊሂቃን ዘንድ ታላቅ ንጉስ ሆኖ ሊታይ ይችላል ደግሞም እየታየም ነው ጥሩ፡፡ በሰማኑ የእትዮፒያ ጫፍ ባሉና በመኃልና ደቡብ አገራችን ባሉ ኀዝቦች ዘንድ ደግሞ አጸ ሚኒሊክ በጨፍጫፊነት፡ ፋሽስትነታቸው እና ሀገር ሻጭና የባሪያ ነጋዲነት ቢታዩ አይገርምም ደግሞም ነውና፡፡ ዋናው ነገር አንዱ ወገን እኛ ባየኘው መነጥር ለምን አላየም ወይም አያይም ተብሎ የሀሳብም ሆነ የአካል ግጭት ውስጥ መግባት መሞከር ተገቢ አይሆንም፤፤
  አጸ ሚኒሊክ ከአጎራባች አገሮች ቅኝ ገዢዎች ጋር በድነበር ጉዳይም ሆነ በአባይ ውሃ አጠቃቀምን አስመልክቶ የተዋወሉት ውሎች አሁን ከገብጽና ሱዳን ጋር ለገባነው አታካሮ ዋንኛ መንሲ መሆናቸው መካድ ፈጽሞ አይቻልም፤፤ በተመሣሣይ ግዛታቸውን ለማስፋፋትና ለጦር መሳሪያ መግዠ ሀብት ለመፈለግ ባካሂዱት ወረራ በኦሮሞ እና ህዝቦች ላይ አላካሂዱም፤ ባሪያ ነጋዲ አልነበሩም ብሎ መከራከር ጉነጭ አልፋ ክርክር ይሆናል፡፤ ለዝህ ደግሞየዝህ ሥርአት ናፋቂዎች ካልሆኑ የአሁኑ ትውልድ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፤፡ አማራ ሊሂቃን አንድ መሰረታዊ ችግር አለባቸው። አማራነትንና ኢትዮጵያዊነትን እና ለይተው ማየት አለመቻልል። በተለይ አሮጌው ትውልድ በፍጹም ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ፡ አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት ለያይቶ ማየት የማይችል የአስተሳሰብ መካኖችን መሆናቸው ነው ችግሮቻችንን እያወሳሰበ የለው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤፤ እኛ ብቻ ትክክል፡፡ እኛ ብቻ ያልነው ካልሆነ የሚሉት ደግሞ ለላ ተግዳሮትን መደቀኑ ነው፡፡
  የአማራ ዐሊቶች ‘አንድነት’ ስሉ ‘አንድ አይነትነት’ ማለታችን መሆኑ የተነቃባቸው መሆኑን መገንዘብ ተስኖአቸዋል። ዛረም ቢሆን የአማራ እሊቶች ያልተላቀቃቸው በሽጻ ያቺው አጸ ሚኒሊክ እና አጺ ኃይለስላሲን አሀዳዊት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን መልሶ ማዋቀርና ማንገስ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ህገመንግስቱን በመቅዳድ የክልል አወቃቀርና አስተዳደር ማፍረስና፡ በክፍላተሃገር መልሶ መዋቀር አለበተት እያሉ ነው፡፡ የሚሉት የክፍላተሃገር አወቃቀር ደግሞ ቋንቋንና ጎሳን መሠረት ያደረገ ሳይሆን መልክዓምድርን፣የሕዝብን መስተጋብር፣ ስነልቦና፣ ምጣኔ ሃብታዊ (የኤኮኖሚ) እና የባህል እንዲሁም የታሪክ ትስስርን የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ማድረረግ። ይሁን እንጂ ያልተረዱት ቢኖር አሃዳዊት ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ያልጠቀመች ኢትዮጵያ ነበረች። አሁን ብዝሃዊት ኢትዮጵያ ተገንብታ ነግሳለች። ብዙአዊት ኢትዮጵያ የዋለልኝ መኮንን ኢትዮጵያ ናት።ብዙአዊት ኢትዮጵያ የባሮ ቱምሳ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ብዝሃዊት ኢትዮጵያ የሰለሞን ዋደ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ብዝሃዊት ኢትዮጵያ የመለስ ተክሊ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በመሆኑ ኢትዮጲያ ትፈርሳለች እንጂ ብዝሃዊት ኢትዮጵያ በቀድሞ ኢትዮጵያዊነትን ማለትም አማራዊነት በተላበሰ መልኩ መልሶ ማዋቀር ፈጺሞ አይቻልም፤፤ አይታሰብም፡፡ ስለዝህ የዋሁ ጠቅላያችንን ጨምሮ እርማችሁን አውጡ፤፤

  • ሰላም አቶ/ዶር/ጓድ ሙሐመድ አብዲ፤ በጽሑፍዎ ከሌላው በተለየ የሚከተለው አስተያየትዎ ቀልቤን ሳበ፤ ይኸውም፣ “”በሰማ[ሜ]ኑ የእትዮጵያ ጫፍ ባሉና በመኃ [ኻ]ልና ደቡብ አገራችን ባሉ ኀዝቦች [ሕዝብ] ዘንድ ደግሞ አጸ [አፄ] ሚኒሊክ [ምኒልክ] በጨፍጫፊነት፡ ፋሽስት[ታዊ]ነታቸው[እ]ና ሀገር ሻጭና የባሪያ ነጋዲ [ዴ]ነት ቢታዩ አይገርምም ደግሞም ነውና፡፡ ዋናው ነገር አንዱ ወገን እኛ ባየኘው መነጥር ለምን አላየም ወይም አያይም ተብሎ የሀሳብም ሆነ የአካል ግጭት ውስጥ መግባት መሞከር ተገቢ አይሆንም።” [በቅንፉ ውስጥ የራሴን እርማት አስቀምጫለሁና ምነው ደፈርኸኝ እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ]።
   ጽሑፍዎ ስሜታዊነትና አሉባልታነት የተሞላበት መሆኑ የሚካድ አይመስለኝም። እርስዎ ከአስተሳስብዎ ጋር የማይጣጣሙትን በግል መነጥራቸው እንጂ በሌላ መነጥር ለማየት የማይጥሩ ሲሉ ይከሷቸዋል። ይኸም ማለት በቀጥታ ባይሉትም፣ የሌላውንም አሳብ ስሙ፣ የኔንም ጭምር ማለትዎ መሰለኝ። ጥሩ ምክር ነው። እንደመደማመጥ ያለ ነገር የለም። ይልቁንም አሁን ኢትዮጵያችን ባለችበት ሁናቴ። ግን በአንድ ነገር ከርስዎ ጋር ከቶዉኑ አልስማማም። ይኸውም ታሪክ መፈረድ ያለበት በራሱ መስፈርትና መነጥር እንጂ በኔና፣ በርስዎ፣ ወይንም ሌሎች በሚሉት መሆን የለበትም። የታሪክ መስፈርት በጊዜው ድርጊቱን ያዩት በሚሰጡን ተጨባጭና አስተማማኝ ማስረጃ ነው። አለበለዚያም፣ ብዙና የተለያዩ ምንጮችን አመሳክረው በወገንተኝነት የማይጠረጠሩ በመስካቸው ምርጥ የሆኑ ተመራማሪዎች በሚሰጡን ምስክርነት ነው። እርስዎ የሚነግሩን ትርክት ይኸንን መስፈርት ያሟላል ብዬ በፍጹም አላምንም። እያንዳንዱ ያሰፈሩት ነጥብ ከላይ እንዳልሁት የአሉባልታና የተረት ወሬ ውጤት ከመሆን አያልፍም ለማለት እደፍራለሁ። እኔ ርስዎ ባነሡት ነጥቦች በያንዳንዳቸው ላይ ለመተቸትና አስተያየቴን ለመግለጥ ጊዜም ትዕግሥትም የለኝም [የዐውድማ እህልህን የሚወቃውን በሬ አፉን አትሰር” የሚለውን መርህ ተከትለው ጥረቴን ለመካሥ ዝግጁ ከሆኑ ግን ለማድረግ መፈተኔ አይቀርም ይሆናል!!!] አሁን የማተኩረው የባሮችን ፍንገላና ንግድን በተመለከተ ብቻ ይሆናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ፍንገላውና ንግዱ በማንና በየት ይፈጸም እንደነበረ፣ የባሮቹ ምንጮች ከየት አካባቢ እንደሆኑ ሰፊ ጥናት ተደርጓል ብቻ ሳይሆን በእጃችን ያሉትም ተጨባጭ ማስረጃዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። እኔ ራሴ በቅርቡ ባካሄድሁት ጥናት ተመሥርቼ በድረ ገጼ ከለጠፍሁት ጥቂቶቹ እነሆ። የጋዳን ሥርዐት አድናቂዎች፣ ሩቅም ሳይሄዱ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ አቈጥቊጠው የነበሩትን የጂማ አባጅፋርን፣ የሊሙ እናርያን፣ የጐማንና የጉማን፣ እንዲሁም የለቃ-ነቀምቴንና የለቃ-ቄለምን መንግሥታት ሊያዩ ይገባል። እነዚህ መንግሥታት አካባቢውን የያዙት፣ ነባሩን ሕዝብ በማፈናቀል፣ ወይንም በመግደልና ለባርነት በመዳረግ መሆኑ መረሳት የለበትም። ኦሮሞቹ ከእረኝነታቸው ወደግብርና የኑሮ መደብ እንደተሻገሩ፣ የጉልበት ሠራተኛ የማግኘት ፍላጐታቸው እያሻቀበ ሄደ። ከዚህም የተነሣ ከብቶቻቸውን ለመዝረፍና ሰዎቻቸውን ባሮች ለማድረግ ሲሉ አካባቢያቸውንና ጐረቤቶቻቸውን መውረርን እንደዋና ሙያቸው አድርገው ተያያዙበት። ለነሱ የባርያ ጥቅሙ ሁለገብ ነበር። የጋማ ከብት መቸርቸርያቸው፣ የጠመንጃ መሸመቻቸው፣ የመድኀኒትና የክት ልብስ መግዣቸው፣ የስጦታም ዕቃቸው እሱ ስለነበረ፣ ከማንኛውም ሀብት በላይ ይፈለግ የነበረው ባርያ ነበር። በጐጃም፣ በበጌምድር፣ በምፅዋና በቀይባሕር ዙርያና እንዲሁም በሸዋና በሐረር፣ ከዚያም በዘለል፣ በባሕር ማዶ ባሉት አገሮች የሚሸጡት ባሮች ዋናው ምንጫቸው ከነዚሁ አካባቢ መሆኑ በሁሉም ዘንድ ይታወቃል። (Mohammed Hassen, The Oromo of Ethiopia: A History, 1570-1860 (Cambridge: Cambridge University Press, 1990): 124-125.
   Herbert S. Lewis, A Galla Monarchy: Jimma Abba jifar, Ethiopia, 1830-1932, (Madison & Milwaukee: University of Wisconsin Press, 1965): 66።
   በባርያ ፈንጋይነትና ንግድ የመጀመርያውን ቦታ የያዘው የእነዚህ አካባቢዎች ገዢው ክፍል ራሱ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ የጅማውን አባ ጅፋር መንግሥት ብንወስድ ንጉሡ ብቻ ከዐሥር ሺ የሚበልጥ ባርያ እንደነበረው፣ ባለሟሎቹ ደግሞ እያንዳንዳቸው ከአንድ ሺ በላይ፣ ተራው ገበሬ ደግሞ በበኩሉ ቢያንስ ቢያንስ አንድ፣ አለበለዚያም ሁለት ባሮች እንደነበሯቸው በጊዜው ያዩትና፣ በኋላም በአካባቢው ጥናት ያካሄዱ ተመርማሪዎች ይናገራሉ ። በሩሲያ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው እንደመጡ ወደአካባቢው ለአደን ሄደው በአባ ጅፋር መስተንግዶ ተደርጎላቸው የነበሩት በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ወልደማርያም፣ ስለራሳቸው ሕይወት በጻፉት መጽሐፍ ውስጥ አፄ ምኒልክ ጅማን፣ ጠቅላላውን ደቡብና ሊባ አስገብረው ወደጥንታዊት እናት አገራቸው መልሰው ቀላቅለው ሲያበቃ፣ የባርያን ንግድ በአዋጅ እስካቆሙበት ጊዜ ድረስ፣ በአባ ጅፋር ባላባቶች እጅ ብቻ እየተሸጠ ወደዐረብ አገር የሄደ [የኢትዮጵያ] ሰው ብዛት ከአንድ ሚሊዮን እንደሚበልጥና፣ በጂማም ዙርያ የሚኖረውን ሕዝብ ሽጠው የጨረሱት እነዚህ ባለሥልጣኖች መሆናቸውን ይገልጣሉ (ፊታውራሪ ተከለሐዋርያት ተክለማርያም፣ ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)፣ ፪ኛ እትም (አአ፣ አዲስ አበባ ማተሚያ ቤት ፲፱፻፺፱)፣ 162)። እግረመንገዴንም ቢሆን በመጨረሻ ላገናዝብዎት የምፈልገው ነገር ቢኖር ታሪክን ለፖለቲካ ቁማር መጫወት የትም አያደርስም። የፖለቲካ ክርክር ትኩረቱ ባለፉት ስሕተቶችና መብቶች ከሆነ ደግሞ ምንም ዐይነት ፋይዳ አይኖረውም ብቻ ሳይሆን የትም አያደርስምም። ክርክሩ መሆን ያለበት እፊታችን ስላለው ስለወደፊት ዕድልና ዕጣ ፋንታ፣ እነሱንም እንዴት በተሻለ መንገድና ሁናቴ መጠቀም እንዳለብን፣ እንደምንችልና እንደሚገባን እንጂ ባለፈው ታሪክ ላይ አይደለም።ታሪክ መማርያ እንጂ መዳኛ መሆን የለበትም። በተቀረ ስለሌሎቹ ነጥቦች ግንዛቤ እንዲኖርዎት ከፈለጉ የሚከተሉትን ጽሑፎች ቢያዩ መልካም ነው ባይ ነኝ።

 5. በመስከረም አበራ እና ባጠቃላዩ ቀኝ(ቅኝ) አክራሪ ሃበሻ ዘንድ፣ ምንሊክን ያላሞገሰ “ኢትዮጵያዊ” አይደለም! ያ ከሆነ “ኢትዮጵያዊነት” ባፍንጫችን ይዉጣ! ደግሞም የምንሊክን የዘር ፍጅትና ባሪያ ፍንገላ ወንጀሎች እውነቱን መግለጥ “ግብጻዊ” ካሰኘን አይጨንቀንም። ግን ዖሮሞአዊነት በቅርቡ እውን ይሆናልና የሌላ ሃገር ዜግነት አትለጥፉብን!
  የእነ ክርስቶፎር ኮሎምበስ ሃውልት ሲፈርስ፣ ቅኝ ግዛትና ጭቆናን እስከዛሬ ያከናነበን ምንሊክ፣ ከ ሲዳ ደበሌ የቀማው ፈረስ ላይ ተኮፍሶ ብርብርሳ ጎሮ ላይ ከማየት የከፋ *ሮሮ የለም! የነፍጠኛ ልጆች ጥጋብ መረን አጣ!

 6. Oh! Currently, no country in the world is infested by zillions of problems like Ethiopia. She seems to be on the verge of disintegration and total collapse of an historic proportion in a manner the former Yugoslavia ( et al) had faced.
  But I don’t think Ethiopia’s enemies would succeed to whatever extent they seem to be fruitfull (and happy) now. This nation is a nation of God’s promises. You have the right to disbelieve this allegation of millions of people such as me, of course, whether you are atheist or otherwise.
  Anyhow, as to me, it is time that Ethiopia needs another Menelik. You can name him Menelik III or Theodore II, I care less for the nomenclature. And believe me that would be realized soon.HE WILL COME! Never be disbeliever of this divine intervention in Ethiopia. It is repeatedly proved in her long history. Do some astral visits to know what happened when in the history of this nation in the past. You may wonder with those facts. A people that had won fighter jets with sticks and stones cannot be disdained as a nonentity.
  You know, if a house does not have an owner, everyone is an owner. If everyone in or around a house claims to be the owner of that house, the house is likely to get burned or dismantled or even sold with or without an auction. That is the fate of something disowned by a proper owner and owned by many self-destructing antagonistic forces. No one cares about the house. Ethiopia is by now ownerless. Or perhaps she is owned by those who care for the milk rather than the cow. What a pity!
  By the time Menelik III comes, all the commotion and the “ፉከራ” (boasting) we observe now here and there will soon wither away dramatically. Little temper clears away the dust. It is common that we see such condition when rules and regulations stop functioning properly. But as soon as they are fairly in place, the abracadabraic dumbfounding chaos such as what we observe in Ethiopia will automatically give way to order and established system.
  Abiy’s crew is not lucky enough to assume the role of the aforementioned unifier. He is a man to rather exacerbate problems and exasperate sane citizens. Yes men can’t fit testing times such as ours. We need strong men full of stamina and unwavering gut to take actions whenever situations demand. Abiy seemed to be so in the beginning, but time itself proved it that it was in vain. He wants to be a friend of both the Devil and God, which is practically impossible. You can’ t please two opposing sides at a time.
  These people of good for nothing such as Dedefo and Jawar and Gerba and Hizkeal or Gemechu … no problem… their graves are ready to voraciously swallow them like their friends in the north who are partly in their graves already. You will see Ethiopia resurrecting soon. Ethiopia has never been won by her external enemies. And that is why she’s fighting a proxy war with her own muttonheaded childern especially in the past 45 yrs. Ethiopia will also win this multilateral war, including the famine ahead.
  But we need to come back to the Almighty! We have to come back to our little god, the conscience. We have to abandon our sins and evil doings. We have to start acting like a human being instead of like an insane animal and EuroAmerican who have gone astray from the path of truth and joined the broad path through which the majority of Luciferians are stumbling towards the darkest end of their eternal residence, the Hell. Yea, there is no free lunch guys!

  • You can not for a single moment stop and think that the root cause for the incurable sickness of Ethiopia stems from those people who think that Ethiopia is only for those who praise Minilik, those who think like you that people “such as Dedefo and Jawar and Gerba and Hizkeal or Gemechu …” or Abdallah or Ujulu or zebarga or Xona, .., “are good for nothing ” !! It won’t strike your little mind that everyone who is indigenous to that geographical region now known as Ethiopia, from Moyale to Zalanbessa, from Shogale to Wocale must have a say in the affairs of that God foresaken country?
   If you want “to start acting like a human being”, know that others too have a stake in the affairs of that country and hear and listen to their side of the story! “All the commotion and the “ፉከራ” (boasting)” you Habeshas perform 24/7 to bring back Minilik’s colonial system will surely disband that empire for good. Think of Derg and Eritrea! This is not ፉከራ!

 7. I am so sorry About Amb/ Suleyman Dedefo!!! b/c I do not think so that he talks in this way abou Minilik II, anyways, he starts to loose his mental integrity!

 8. የነ’Mohammed Abdi አባባልን በመጋራት፣ ምኒልክን አስመልክቶ ካሁን በፊት ያልነውን በጥቅስ መልኩ ለመድገም ያህል፣ እነሆ፣

  “… አትናገሩኝ፣ እኔ ማግኘትን እፈልጋለሁኝ ማለትን ብቻም ሳይሆን፣ ሶሻል መሆንንና ማጋራትንም መማርም ያስፈልጋል:: የምኒልክ ልጆች ስትባሉ፣ ወልድያም ተገኛችሁ ወይንም ካሊፎርኒያም ይሁን ማደርያችሁ፣ መማር ያለባችሁ ጉዳይ አለ:: ምኒልክ እና ተክለሃይማኖት፣ የጎንደር 44 አድባራት በሚጋዩበት ጊዜ ላይ ከመከላከል ይልቅ ዝም ብለው ጥለው ባይሸሹ ኖሮና፣ ከዚያም ምኒልክ የወሎን እስላም በስተጀርባ ልኮ ዮሃንስን ባያስገድል ኖሮ፣ ሱዳን በገዛ የራሳችን ከዳተኞች እየተመካች ባልለመደችን ነበር:: አሁን ደግሞ የነ ስዩም መስፍን የደላላነት መክለፍለፍ ተደምሮበት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተን ባልተገኘንም ነበር:: ከዚህ ችግር ለመላቀቅ ግን እኔ የምፈልገው ይሄ ነው ብሎ መንተክተክ ወይንም ከእንደነ አትላንታ ሆኖ የዓድዋን ፉከራ ማብዛት ሳይሆን፣ መደረግ ያለበት ጊዝያዊው አንገብጋቢ ተግባር፣ በፈረስም ሆነ በታንክ ታጥቆ ወደ መተማ ብቅ ማለት ብቻ ነው:: Hic Rhodus, hic salta እንዳለው ጥንታዊው!
  በስር መሰረቱ ለመገንዘብ ግን ምንና እንዴት መሆን አለባችሁ? ትፈወሱና ሶሻልም ትሆኑ ዘንዳ፣ eat that your despotic Menelik, at least symbollicaly.
  የሰው ልጆችን ህብረተሰባዊ እድገትን አስመልክቶ፣ የሰው ልጆች ተመራማሪ ሊቃውንቶች፣ በ’Ethnologie’ው እና በ’Psychologie’ው ምርመራቸው እንደደረሱበት፣ ማለትም Ontogenese እና Phylogenese በሚለው የምርምር አርእስት ዘንዳ፣ ስለ አንተ አይነቱ ባለ ድፍን ጭንቅላት እና ስጡኝ እንጂ ማለትን ብቻ የሚያውቀውን፣ ይሄንን ጠባዩን ትቶ እንዴት ተደርጎ ሶሻል መሆን እንደሚችል አብራርተውልናልና ከዚያ መቅሰም ሊያስፈልግ ነው:: በዚህ ምርምር መሰረት እንደተደረሰበት ምኒልክን ካልበላችሁ ከእፈልጋለሁ እያሉ መስገብገብ በስተቀር መፈወስን አትደርሱበትም:: እንግዴህ Vulgär ስግብግብ እንደሆናችሁ ለዘላለማችሁን እንዳትቀሩ despotic አባታችሁን ጋጡት ቀርጥሙትም:: ዲስፖቲኩ የ’Urhorden Gesellschaften አባትዮው፣ እድሜውን በሙሉ ብቻውን በስግብግብነት መብላት፣ መጠጣት እና መደሰት ስለነበረ ተግባሩ፣ በተለይ ወንዶች ልጆቹ ችግር ውስጥ ስለገቡ፣ በተባበረ ክንዳቸው ይገሉትና ስጋና አጥንቱን የጅብን ያክል በሆነው ጥርሳቸው መንጭተውና ቆርጥመው ይበሉታል:: በዚህ ተግባር የሱን ሀይልና ጉልበትን ወደነሱ ያስተላልፋሉ፣ የእህቶቻቸው ባሎችም ይሆናሉ:: ግን አባት ነበርና በመግደላቸውም ፀፀት ይሰማቸዋል፣ ስለሆነም ህሊና ያድርባቸዋል፣ እንዲህ አይነት አገዳደል እንዳይደገምም የህብረተሰብ ህግን ይመሰርታሉ፣ ማህበራዊ ህብረተሰብም ይመሰረታል፣ የብቸኝነት ስግብግብነትም አጥር ይደረግለታል፣ ሶሊዳሪትም ተጀመረ::
  እናንተ እነ “አሹ”ም ወልድያም ሆናችሁ ካሊፎርንያ ይሄንን መንገድ ተከተሉና ሶሻል መሆንንና ማጋራትንም ተማሩ፣ እንዲህ ከሆነ ውጤቱ አለመጥቀም ሳይሆን ለሁላችንም ጠቄሜታን ያስከትላልና፣ ዲስፖቲኩን የገዛ ልጆቹ ሲበሉት እሳትም ቢላም ስላልነበረ ያው በጥሬ ስጋነቱ እስከነ አጥንቱ ነው በጥርሳቸው የጋጡትና የቆረጠሙትም:: አሁን ግን ቢላም አለ ከዚያም ደግሞ የናንተ ዲስፖት መቃብር ውስጥ የምድር ትል በልቶ ስለጨረሰው፣ ያው ተግባራችሁ symbollicaly ነውና፣ ከዲስፖታችሁ የምትገላገሉት ትንሽ ስራ ይቀልላችኋል፣ ያው እንግዲህ ቡርንዶአችሁን በአዋዜ በየምሽቱ እንደምታደርጉት መከስከስ ነው፣ የብርንዶው ክስከሳ በዲስፖታችሁ ስም መሆኑን ብቻ ያው ቃል መግባት ያለባችሁ! የብሩንዶ እየበሉ ጦርነት ማሸነፍ ልምድም ኮርያ ጦርነት ላይ ተስመስክሯል:: አባቶቻችሁ በሰማይ በኩል የአሜሪካ ቦምብ እየጠረገላቸው፣ ከምድር በኩል ደግሞ ብርንዶን በቢላ እየገመጡና ካኒባልስተን ነን የሚለውን መንፈስ ለኮርያዎቹ እያስተላለፉ ድል ተሳክቶ የለ እንዴ!? ኮርያዎቹ የሸሹት፣ እነዚህ እጅ ውስጥ ከገባን ምርኮኞች መሆን ሳይሆን የሚጠብቀን፣ ወድያው መበላትን ነው በሚል ስጋት እኮ ነው የሸሹት:: ታድያ ምነው መተማ ላይ አይደገም?”

 9. መቼም ቢሆን በጥላቻ በፈጠራ ትርክት የተሞላ አእምሮን መለወጥ ስውን መለወጥ እንኩዋን ለእኛ ለፈጣሪም እየሱስ ክርስቶስ ፅሃፍት ፈርሳውያን ካህናት በሃስት ክስና ምስክር እየከስሱ እንደስቀሉት በመፅሐፍ ቅዱስ ተጠሶል ዛሬም ድረስ አለሙ ያነበዋል::የዛሬ ፀለምት አክራሪ ኦሮሞዎች ተማርን ብለው ባልተፃፈ ያውምፊደልም የራሳቸው የሌላቸው በጨካኙ ግራኝ መሀመድ ወረራ ስማቸውንና እምነታቸውን የቀየሩ አልፎም በገዳ ስርአት በወረራ ከውጭ የወንድ ብልት እየስለቡና አንገት እየቀሉ ቀምተው የይዙትን መሬት በዘላንነት ይኖሩ ስልጣኔ አልባ ድር አደር ጨካኝ እምነት የሌልቸው ዱር አደር ህብረተስብ የነበሩ መሆናቸው የተፃፈ ታሪክ ያስረዳል ::
  ያንን ፊደል አልባ የዘለን ታሪክ የለውን ህዝብ እምዬ ምንልክ አለምን በአስደመመ ድንቅ የመሪነት ችሎታ እንዳይስልብ እንደ ባርያ እንዳይሽጥ
  ልብስ እንዲለብስ ፈትል አስተምረው እርሻ ማረስን እምነት እንዲኖረው የአለም ልጣኔ እኩል ተቆዳሽ ማድረግ የሚያስመስግን ነበር!በእየሱስ ክርስቶስ የሆነውም ይህ ነው::
  በዚህም ክፋታችን የኛ የሆነውን ፊደል ጠልተን የሌላውን ላቲን የመረጥን ምትሩ ደናቁርት ጭንጋፍ እንደ እዝቄል የመስሉ ቅል እራሶች በዚህ ዘመን ግራ የተጋቡ ፈርሳውያን መፍላት የክፉ መንፈስ ስዋች ባህርይ ነውና እነ መሀመድ ቢዘላብዱ ምንልክ አማራ አማራ ጠል ቢሆን በዚህ አለም የፈጠሩ አረሞች ናቸውና እንደ ባህር ላይ እንደሚንሳፈፍ ቅሎች ናቸው!!!!

  • እንደ የሙዚቃ ሸክላ አንዴ ከታተመበት የደናቁርት ተረት የማይላቀቅ አዕምሮ ይዘህ|ሽ 50ሚሊዮን ህዝብ መሳደብ አይገርምም! ስድብ ያውም የኢትዮጵያን ግማሽ ህዝብ መስደብ ከድንቁርናም የባሰ ነው! የማይድን በሽታ ስለሆነ ይማርህ|ሽ አይባልም!

 10. ዳግማዊ እምዬ ምኒልክ ከአማራው ህዝብ የበለጠ ለሸዋ ኦሮሞ ይቀርባሉ:: እናታቸው በዘር ኦሮሞ ናቸው:: ወጣቱ ምኒልክ ጎንደር በእፄ ቴዎድሮስ እጅ ታስሮ ነበር:: ወደሸዋ እንዲያመልጥ 12 ኦሮሞ ወገኖቹ ህይወታቸውን ገብረዋል:: እነዚህ ተማርን ተመራመርን የሚሉ ጠባብ የኦሮሞ ልሂቃን ተብዬዎች ምንም ቢዳክሩ የሚኒልክን መልካም ስብእና ሊያቆሽሹ አይችሉም:: የበታችነት ስለሚሰማቸው ሚኒልክን ባወረዱ ጊዜ ከፍ የሚል ስሜት የሚሰጣቸው የሚመስሉ ትናንሽ ጭንቅላቶች ናቸው:: ቋንቋም ቢሆን ለአፋን ኦሮሞ ከግእዝ ፊደል የተሻለ የለም :: ይህ ሀቅ ነው:: የሚኒልክ ጥላቻ ስላደነቆራቸው በእውቀትም ህዝባቸውን እያሳወሩ ነው:: ማፈሪያዎች:: ለምኒልክ እጅግ ብዙ ሚሊዮን ይሰለፋል::

 11. Before you start arguments for or against a cause, you need to read, and read the treaty close: First the treaty was written in both Amharic and English. There is a big difference between the two texts, just like the Wuchale treaty. It is a known fact that scholars repeatedly wrote about. The Amharic version only agreed to to entirely block the rivers. Ethiopia had no intention of blocking the rivers in the past or it has interest to do it now. For us, it is the Amharic version that matters, Read your history as much as you can. Here is the relevant link:
  pt_in_Legal_History_of_Ethiopia’s_Diplomatic_Confront_1900-1956

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.