ሴቶችን ጅብ አስበልቶ እንደ ወንድ ችግኝ ተከላ! – በላይነህ አባተ

Denbi Delo Students ethiopian registrar..ሱሪ ቦላሌ ሆነና ቀበቶ ላልቶ በጦቢያ፣
እንደ ምስጥ አፈር ይምሳል አንጠልጥያለሁ ባይ ሁላ፣
ሴቶችን ጅብ አስበልቶ እንደ ወንድ ችግኝ ተከላ፡፡

የግዮን ፉፏቴ ሲደርቅ ጣና ሀይቅ ሲሆን ሰሃራ፣
እንደ እባብ ሲንፏቀቅ ዋለ የማይጸድቅ በለስ ተከላ!

ምሁር ነኝ ባዩ ዶክተሩ የነፍሰ-ገዳይ ቱልቱላ፣
የግድብ ጠልሰም ይጪራል እምቦጭ ሲነግስ በጣና፡፡

ኢትዮጵያ እንድትሆን ኤደንን፣ መቀነት ታጥቃ ግዮንን፣
በላ ትከላ ፍትህን፣ ቅጥፈትን ነቅለህ እውነትን!

ችግኝ ተተክሎ እንዲበቅል፣ ፀድቆ አገፍግፎ እንዲያብብ፣
ይልቅስ እውነት ተናገር፣ ንስሃ ግባ ለወንጌል፡፡

በሰእማት አጥንት ፍርስራሽ፣ ከንፁሐን ደም መስኖ ቅጅ፣
ችግኝ ተከላ ተማወጅ፣ ቅድሚያ እጅ ታጠብ ቀላማጅ፣
ተአቡነ ጴጥሮስ ተደፍተህ፣ ንስሃ ግባ ባማላጅ፡፡

ለሃያ ዓመታት እንደ ደን፣ ሕዝብ በባሩድ ጨፍጪፎ፣
አፈሩን በደም ለውሶ፣ በአጥንት አማስሎ አቡክቶ፣
አረም ዘራበት አፍልሶ፣ ተጀግኖች አገር ሰው ጠፍቶ፡፡

በጋሞ ልጆች ደም አምባ፣ በጌዶ እናቶች ልቅሶ እንባ፣
በሰበታዎች ነፍሰ-ጡር፣ በለገጣፎ እርጉዝ ጽንስ ውሀ፣
ምድር አርጥቦ ቆፈረ፣ ሸፍጥ እንደ ጉንዳን አፈላ!

በወልቃይት ምድር አበሳ፣ በራያ መሬት ጠባሳ፣
በደራ ጋራ ሰቆቃ፣ በመተከል ወንዝ መከራ፣
የችግኝ ሥሮች ሰደዳ፣ አቤት ህሊናን ሲያደማ!

በፃድቃን ገላ ተተክሎ፣ የሰማእት ደም ጠጥቶ፣
እንዴት ሥር ሰዶ ይፀድቃል፣ ችግኝ በይሁዳ ተተክሎ?

ትናንት በመርዝ ሱስ አፍዞ፣ ዛሬም በችግኝ ሸፍኖ፣
ገደል መክተቱን ቀጥሏል፣ በሬውን በሳር አታሎ፡፡

ይልቅስ ትተህ ቅፈላ፣ መንጋን ማድረጉን ተላላ፣
ቀኑ ደማምኖ ሳይጨልም፣ በጊዜ ንስሃ ግባ!

በደም በተበከሉ ጣቶች ችግኝ መትከሉን ተውና፣
ይልቅስ ሴቶቹን አትርፍ ተጅብ መንጋጋ አውጣና፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህልም አየሁ ፍቱልኝ (ዘ-ጌርሣም)

ግድብ ግደባ ተመንጉድ በፊት መተከል ተካርቱም ተራ፣
ምንጩን ተመድረቅ አትርፍ ዘመቻ ጣና ጥራና!

ችግኞች መትከል ታማረህ፣ የፅድቅ የምረት ንስሃ!
ወንጀልህን በሱባኤ እጠብ፣ ዋልድባ ገዳም ግባና፡፡

እውነት ተበቃህ ኃጥያትህ፣ ልብህ ታሰበ ንስሃ፣
ተንኮል ክፋትን ለማልበስ፣ አፈር መጫሩን ተውና፣
የእውነትን ፍሬ አፍልተህ፣ የፍትህ ችግኝ ትከላ!

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጀመርያ ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.
እንደገና ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

8 Comments

 1. የእህቶቻችን ጉዳይ ሁላችንም ቢያሳስበንም ፣ የመንግስትን ጥረት በጉያው የተሰነጉ ባንዳዎች ጥርቅም ምንኛ እንቅስቃሴውን ሊጎትቱ እንደሚችሉ ባንድ ወገን፣ በሌላው ወገን ዞረው ለማሳጣት የሚሄዱበትን ርቀት ጽሃፊው የተገነዘቡ ኣይመስልም unless you are part and parcel of them.
  ባንዳዎች ይውደሙ !!
  ዘረኝነት ይጥፋ !!
  የኣባቶቻችን ኣለም የሚመሰክረው ኣርበኝነት በኛም ይለምልም !!

 2. አይ ዜጋ ፣ አይ ተላላው ወገኔ
  አሁን ማን ይሙት ይቺን አጥተሃት እንደኔ?
  ይህ እኮ ግልጽ ነው ለሚያስተውል ለሚያየው
  ችግኝ ነቀላን እንጅ ተከላን ለሚጸየፈው
  ለባንዳ ጃንጥላ ያዥ ሁላ ድሮስ ስንኙ ምን ሊሆንልህ ነው?
  የጠፉ ቡቃያዎችን አስታኮ የመጣብን አዲስ ተምች ነው።

  ከትዝብት ጋር

 3. ግጠም ግጠም አለኝ እኔም ልገጥም ነው፤
  ለግጥሙማ ማማር አዝማሪ አለ አይደለም ወይ፤
  ሰብልዬ ተድራ አለሟን ሥታይ፤

  “እኔ እምሞት ዛሬ ማታ እህል እሚደርሥ በፍልሰታ”፤
  እንዳለችው መነኩሲት የጊዜን ባለውልነት ተረድታ፤
  የሚፈሥን ደምና እምባ ሣያቆሙ ችግኝን እንትከል ቢሉ፤
  ለሣቅ ለሥላቅ መዳረግ ነው በላም አለኝ በሰማይ ቢታበሉ።
  (ፐ!ግጥም ብሎ ዝም! የኔን ነው ታዲያ)

 4. Woyi gizzie? The TPLF bandas used to say the same thing the empty zega, and the korokoro Abaa Wirtuuu are saying. Now the time is for banda OPDO/OLF, pentes. No shame, conscience or guilt when the descendants of Bandads call the children of patriots bands? No shame in TPLF bandas, no shame in OPDO bands!

 5. @ዜጋ
  ፋይሉን ዘርዘር አድርጌ ፣ ወደሁዋላ ሄጄ ስቃኘው
  ለካንስ “በላይኛው” አዲስ ሳይሆን መርዘኛው ነባር ተምች ነው
  መርዙን ስለተላምድነው ፣ ሰንኮፉን ብቻ ነቅሎ መጣል ነው።

  ይልቅ- ቅጥረኛውን- ቅዥቢ ያልከው ከላይ የተጸዳዳብን
  እንቁላል መጣያውን ገና ያላወቀ አዲሱ አንበጣ ይሆን?:):)
  ከአክብሮት ጋር- ወንድም ዜጋ!

 6. Abaaa Wirduuuu said የተጸዳዳብን! Idiots do not know who they are! Wirtuuu you yourself is the stool and zega is the latrine. Zega the latrine holds the stool Wirtuuuuuu. GIM

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.