“የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫ ይካሄድ ብሎ መወሰኑ ህገ መንግስቱን የሚጻረር ስለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አክብሮ ያስፈጽማል

Nigusuመከላከያ ሰራዊቱ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ “የሃገርን ሉዋላዊነትና ህገመንግስቱን
እንደሚያስከብር ሁሉ ምርጫ ቦርድም የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ስልጣን ሁሉም
አካል ሊያከብር ይገባል”
– ንጉሱ ጥላሁን፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት

******************************************

ምርጫን የማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው በህግመንግስቱ አንቀፅ 102 የተቋቋመው ምርጫ ቦርድ ስለሆነ ሌላ አካል በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ልግባ ቢል ከስልጣን ገደቡ በላይ የምርጫ ቦርድን ስልጣን መጋፋት እና መዳፈር ስለሚሆን መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አክብሮ ይፈጽማል ሲሉ የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊው አስታወቁ።

ሀላፊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በህገመንግስቱ መሰረት ምርጫን የማስፈጸም ስልጣን ለአስፈጻሚው ስላልተሰጠ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ነገር ሊያደርግ የሚችለውና ህገመንግስታዊ ስልጣን ያለው ምርጫ ቦርድ ብቻ ነው፡፡
“አስፈፃሚ አካሉ በምርጫ ቦርድ ስራ እና ውሳኔ ጣልቃ በመግባት ቢፈትፍት ያለ ሀላፊነቱ መንቀሳቀስ ስለሆነ መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ያከብራል፣ይፈፅማል” ነው ያሉት አቶ ንጉሡ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ምርጫ ቦርድ የተሸለ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲቋቋምና ለእውነተኛ ዴሞክራሲ መጎልበት በር አድንዲከፍት ሆኖ ተደራጅቷል ያለት አቶ ንጉሡ፤ የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ልግባ ቢል ከስልጣን ገደቡ በላይ የምርጫ ቦርድን ስልጣን መጋፋት እና መዳፈር ይሆናል ሲሉ ነው ያብራሩት።

እንደ አቶ ንጉሡ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት ዋነኛ ትኩረቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከላከል የህዝብን ደህንነት መጠበቅ፣ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚገጥመን የማደነቃቀፍ ፈተና በማለፍ ውሀ መሙላት መጀመር እና ለጥቅም ማብቃት እንዲሁም ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊቀንሱ የሚችሉ ስልቶችን ነድፎ መረባረብ ነው፡፡

የምርጫው ጉዳይ ገለልተኛው እና በህገመንግስቱ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ ስራ ይሆናል ያሉት አቶ ንጉሡ፤ ምርጫ ቦርድ ደግሞ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚያደርገውን ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ ሲሉ አስታውቃዋል። ይህም ልክ መከላከያ ሰራዊቱ ገለልተኛ ሆኖ የሀገርን ሉዋላዊነት እና ህገመንግስቱን እንደሚያስከብር ሁሉ ምርጫ ቦርድም በህገመንግስቱ የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት ያስከብራል ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት የክልሉን ምክር ቤት ምርጫ በዘንድሮው አመት አካሂዳለሁ ብሎ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

2 Comments

 1. Prosperity doctrine creates false hope and fears .
  Abiy gave Eritrea false hope, about Eritrea getting Badme back per the Algiers agreement two years ago, but until now Badme is not returned to Eritrea and noone knows if Badme ever will be returned while Abiy is in the office of the Prime Minister of Ethiopia. Abiy gave TPLF false hope about Abiy being ready to finish the Amara genocide
  TPLF started , TPLF is still waiting for Abiy to fulfill his promise by finalizing the ethnic cleansing of Amaras. The “COUP IN AMARA REGION” was his way of fulfilling the promise but it didn’t bring the desired results both Abiy and TPLF were hoping to accomplish.

  Abiy gave both Eritrea and the Tigray region fears, with fictitious story about the two brotherly powers Shabiya and Woyane being enemies who won’t ever turn into friends which created fear on both Shabiya and Woyane about each other . Both Shabiya and Woyane trusted Abiy’s fictitious story because Abiy was INSA’s spy chief with deep contacts to Woyane until 2018 and now after 2018 Abiy having tight deep relations with Shabiya.

  Shabiya thinks Woyane might invade Eritrea because of false fear Abiy told Shabiya same as Woyane thinks Eritrea might invade Tigray because of the false fear Abiy told TPLF, Abiy made TPLF think that Woyane needs to respect Abiy otherwise Shabiya might attack Tigray , same as Shabiya thinks Eritrea needs to respect Abiy because he is holding back the Woyanes from attacking Eritrea, this creation of false fake fear even got him to win the Nobel Peace Prize but since the peace he created was founded/based on a foundation of a false fear it got the potential to crumble with the temporary peace lost then replaced with violence of biblical proportions between Tigray and Eritrea which might even involve other scandalous nations who are waiting for opportunities such as this to attack the Habeshis, all these because the Abiy government is determined in giving false hopes regardless what kind of potential disappointments with devastating consequences it brings in the future.

  EWNET TENAGRO YEMESHEBET MADER

  YALUN AYATOCHACHIN BAFEREBUN
  NEBER

  EYAYUN SINIDENEBABER

  LEWUSHET SINIDEMER

  SINIAQIRARA BEBADO NEGE LEMEDEFER

  ht › article
  Web results
  Prosperity gospel makes people have ‘false hope and fear’, says Benny …

  harticle/prosperity-gospel-makes-people-have-false-hope-and-fear-says-benny-hinns-nephew/133111.htm

 2. ሕውሃትና የትግራይ ክልል ም/ቤት የ2012 የክልል ምርጫ መካሄድ እንዳለበት ስምምነት ላይ ደርሰው ዘንድሮም እንደቀድሞ በሙሉ ድምጽ ወስነዋል፡፡ ለምን ሲባሉ ህገ-መንግስቱ ምርጫ በየአምስት አመቱ መካሄድ እንዳለበት ስለሚደነግግ ይሉናል፡፡ ግን የህገ-መንግስቱ ድንጋጌ በየአምስት አመት መካሄድ ብቻ ሳይሆን ነጻና ተአማኒነት ያለው ጭምር መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህም ከኮረና በተጨማሪ እንዲህ ቅጥአንባሩ የወጣ ፖለቲካ በአገራችን በሰፈነበት ሁኔታ እንዴት ባለ መንገድ ነው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውን ለህዝብ የሚያስተዋውቁት፣ እንዴትስ ነው ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና የሚሰጠው፣ እንዴትስ ነው ደጋፊና ተቃዋሚዎች በአደባባይ የሚገልጹት፡፡ መቼ በቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ፣ በኢሞ፣ በቴሌግራም ትሉን ከሆነ ለማያቁሽ ታጠኚ ነው የሚባው፡፡ በዚህ ምርጫ ህዝቡም፣ ፓርቲዎችም በሁሉም አማራጮች ሃሳባቸውን ገልጸው ምርጫውም ከማስመሰል ህገ-መንግስቱ ባስቀመጠው አግባብ ነጻና ተአማኒነት መሆን ግድ ይላል፡፡ አለያ ነጥዬ ብበላ እንደሚባለው 5 አመታትን ጠብቀን ብቻ ምርጫ ይካሄድ ማለት የባለፉት አምስት ምርጫዎችን በመድገም ህዝብንና አገርን ዳግም ወደአረንቋ መዶል ይሆናል፡፡
  ለማስመሰልና መንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ይህን አካሄድ በትግራይ ስም የተደራጁ ብቻ ሳይሆን በአገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ፓርቲዎችም የሚቀበሉት አይሆንም፡፡ አቧራ በማንሳት ተደማጭ ለመሆንና አጀንዳ የመፈብረክ ተግባር ከመሆን የትም አይደረስም፡፡ እርግጥ ነው ከዚህ አኳያ የትግራይ ክልልና ህውሃትን ውሳኔ በአገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ፓርቲዎች ዝምታ ፍላጎታቸውና ተቃውሟቸው የፌዴራሉ መንግስት ስልጣን ብቻ ስለመሆኑ ሰሞኑን የፌዴሬሽን ም/ቤት ውሳኔ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ ያረጋግጣል፡፡ አለበለዚያ ምርን አስመልክቶ የትግራይ ክልልና ህውሃት ያሳለፏቸውን ውሳኔዎች ለፓርቲዎቹ ስለሚሰጠው ትርጉም ሊነግሩን ይገባልን፡፡ አለበለዚያ ኢዜማ፣ አብሮነት፣ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ አብን፣ ሌላችም ትዝብት ላይ ትወድቃላችሁ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.