“የሠራዊቱን መልካም ስም በማጠልሸት በህዝብ ዘንድ ያለውን አመኔታ ለማሳጣት የሚሞክሩ አካላት ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው” የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን

በመሃመድ አህመድ

103361226 898746987310711 6968704237244895948 nየመከላከያ ሠራዊቱን መልካም ስም በማጠልሸት በህዝብ ዘንድ ያለውን አመኔታ ለማሳጣት የመሞከር ስራ ላይ የተጠመዱ አካላት ከድርጊታቸው መታቀብ እንደሚገባቸው የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን አስታወቁ::

ዋና አዛዡ በሰሜን እዝ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ቪድዮ ኮንፈረንስ በተካሄደበት ወቅት የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነትና አመለካከት ነፃ በመሆን ተልዕኮውን ያለምንም ውግንና በአስተማማኝ ሁኔታ እየፈፀመ ያለ የሰላም ሃይል መሆኑን አብራርተዋል::

ሌ/ጄኔራል ድሪባ አሁን ላይ የራሳቸውን ፍላጎት ማሳካት የሚፈልጉ ሃይሎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰራዊቱን ለማደናገር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዋና አዛዡ አያይዘውም የሰራዊት አመራር እና አባላት የስነ-ልቦና ዝግጅት በማድረግ ውስጣዊ አንድነቱ የጠነከረ አሃድ ለመገንባት ተግተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

የሰራዊቱ አመራሮች በበኩላቸው እዙ በተሰማራበት ቀጠና ተልእኮውን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

ሰራዊቱ የተገነባበትን ህዝባዊ ባህሪ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አጠናክሮ መቀጠሉንና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚነዙ አሉቧልታዎች ለመስማት ዝግጁ ያለመሆኑንም አመራሮቹ አረጋግጠዋል፡፡

በቪድዮ ኮንፈረንሱ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት

1 Comment

  1. The current military doesn’t have a good name, it let the innocent Military General Kinfe Dagnew rot in jail . It holds Badme illegally.
    The current military killed Military General Asaminew Tsige and Military General Saere Mekonnen.
    The current military sat and watched without lifting a finger while the Debre Berhan and Ataye got attacked by genocidal terrorists .
    The current military constantly kills so many innocent people in various parts of Ethiopia including in Addis Ababa , Western Wollega and Ogaden. The current military is weak to defend the country from external enemies .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.