ተጨማሪ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 5 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

healthበኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

በዚህም በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2ሺህ 670 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 163 ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 1 ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑ ታውቋል።

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል 117 ወንድና 47 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስክ 92 አመት ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 104 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 26 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 22 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል እና 1 ሰው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 5 ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያለፈ ሲሆን 2ቱ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው፣ 3ቱ ደግሞ በሕክምና ማዕከል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህም አጠቃላይ በአገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች ( 32ቱ ከአዲስ አበባና 1 ሰው ከአማራ ክልል ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 መድረሱን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

እስካሁን አጠቃላይ 165 ሺህ 151 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

2 Comments

 1. ምንም እንኳ ስርጭቱ የሰፋ ቢሆንም ንክኪውን ቶሎ ለይቶ የማስቀረትና ወደ ሌላ ቦታ እንዳይሰራጭ የማድረግ ስራ አሁንም መቀጠል አለበት፡፡

  የተለየውንም አካባቢ በመዝጋት ለመቆጣጠር መሞከር፡፡

 2. ኮቪድን በማስመለከት በመንግስት ላይ የውንጀላ እና የማጥላላት ዘመቻ የፖለቲካ ተልዕኮ ባላቸው ግለሰቦች እየተሰራጨ ነው፡፡ ይህን በሚከተላው መንገድ መረዳት ችያለሁ
  1. በ04/10/12 በቪኦኤ አማርኛው ፕሮገራም በአንድ ቀን የተሰሩ ሶስት ዘገባዎች በዚህና ከአንድ አካባቢ መሆናቸው
  2. ኦፌኮ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተንተርሰው ችግር ደርሰውብኛል 90 ሰዎች ተገለውብኛል ማለቱ፣
  3. በገርመን አማርኛው ፕሮግራም የወጣቶች ፕሮግራም በደቡብ ክልል በይርጋለም ለይቶ ማቆያ ችግርች አስመልክቶ ሰፊ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተጠቃሽ ናቸው
  አሁን ኮቪድ -19 ለመከላከል መንግስት የሰራቸውን ስራዎች አንድም ሳይሉ በሽታው እየጨመረ ስለመጣ የመንግስት ውድቀት አድርጎ ለማስመሰል እየተጠቀሙበት ስለመሆኑ፣ ካቢኔው ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር የገባውን ትንሽ ክፍተት ሊጠቀሙበት ያሰቡ አካላት እንቅልፍ አጥተዋል፡፡ መንግስት ሆይ ክትትል ቢያደርግ መልካም ነው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.