ከቦናፓርቲዝም ወይም ከሀገር ብልፅግና አንዱን ምረጡ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የህዝብን የልብ ትርታ መሥማት ያልቻሉ አባገነን ባለሥልጣናት ሁሉ መጨረሻቸው አያምርም።ህዝብን ሣይከፋፍሉ እንደ አንድ በማየት ምን እንደሚሻ ቀርበው ሊያዳምጡት፣ውሥጡን ልቡን ሊያውቁት ይገባል።

” ሂትለር ና ሞሶሎኒ፣ከአውሮፖ ፤ ከላቲን አሜሪካ ፖል ፐት ና ፒኖቼ ፤ ከአፍሪካ ቦካሳ ና ኢዲያሚን በጨካኝነትና በአምባገነንነታቸው ፣ ሊጠሉ ፣ሊወገዙ ና ሊኮነኑ ይገባል።” ቢባልም ፣ ታጋይ የነበሩት ሙጋቤእና ጋዳፊ ፣ሥልጣንን ዘልዘላ በማድረጋቸውና በመጨረሻ ከህዝቡ ልብ ውሥጥ በመተፋታቸው  ፍፃሚያቸው  አሥቀየሚ መሆኑ ግን ያሣዝናል።

ይህንን እውነት በማሥተዋል ነው፤  “ለአፍሪካ ያልተቀባባ ፣የአፍ በቻ ያልሆነ ፣የህዝብን ልብ ገዢ የሆነ፣ እውነተኛ ዴሞክራሲ ያሥፈልጋታል። የሚባለው።(እያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር የዴሞክራሲ ሁኔታ ብትፈትሹ የአውሮፓና አሚሪካ፣እንዲሁም የቻይና ተፅእኖ ያረፈበት እንጂ የህዝቡን ልብ ያገናዘበ አይደለም።)  እናም ሦሥተኛ አማራጭ ሁሌም እንዳለ አንዘንጋ።ያም አማራጭ ዓላማህን በሚገባ የሚያሳካልህ አማራጭ ነው። ይህንን አማራጭ በመዘንጋት ነው ፣ብዙዎቹ መሪዎች የተኮታኮቱት።ይህ አማራጭ የሰውን የልብ ትርታ መሥማት የሚባል አማራጭ ነው።ይሄ ለግለሰብም ሥኬት ይሰራል።ለመንግሥትም አሥተዳደር የሚበጅ አማራጭ ነው።የህዝብን የልብ ትርታ ማወቅ።እናም የግለሰብንና እና የቡድንን መብት ሳይሸራርፉ ማክበርና ማሥከበር።…

ህዝብ ምንድነው የሚፈልገው?የሚጠላውስ?የሚወደውስ?የሚያሥደሥተውና የሚያሣዝነው ፣የሚያኮራውናበአንድነት እንዲዘምር የሚያደርገው ምንድነወ?…የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቆ መልሱን ከራሱ ከህዝቡ ልብ ውሥጥ ማግኘትና ፍላጎቱን ለማሣካትና ጥያቄውን ለመመለሥም መፍጨርጨር ያሥፈልጋል።

ለምሳሌ

“አንድ አይነት ዘር ሆነውና ሌላው ጥቁር ህዝብ በታሪካቸው እየኮራ፣ በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች በተፈጠረ በቅዠት ልዩነት ለምን ኢትዮጵያዊያን እርስ በራሳቸው ይናናቃሉ?ይጋጫሉ ?ይገዳደላሉ?? የአብዬ መንግሥቱን “በሻ አሸብር በአሜሪካ ” የተሰኘውን ግጥም  በማንበብ እነኳ ፣ ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ አፍሪካዊያን ዘራቸው አንድ እንደሆነ ያውቁ ነበር።” እያሉ በምፀት  የሚናገሩ ሰዎችን በማዳመጥ እንኳን በቀላሉ፣ ወደእውነተኛ ለውጥ መምጣት ይቻላል። እውነት ነው፣  ኢትዮጵያዊያን የቋንቋችን ብዛት ከሰባ በላይ ቢሆንም ፣የዘራችን ግን አንድ ነው።ሁላችንም ጥቁሮች ነን ።አፍሪካዊያን ነን ።

በእውነት እንመሥክር ከተባለ፣  ይህንን ሃሳብ የመሠለ እና  ሌላም የሚገራርሙ ፣የዚች ሀገርን ዜጎች በአንድ ልብ ወደ ብልፅግና ለመውሰድ የሚችሉ ንደፈ ሃሳቦች የብልፅግና ፓርቲ እንዳለው ፣ከመሪው ከክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) አንደበት ብዙ ጊዜ ሰምተናል።

እሥቲ ደጋግመን የሰማነውን ፣ የብልፅግና ፓርቲን የለውጥ ና የዴሞክራሲ  ንድፈ ሃሰብ እንቃኘው፦

“ሀገሬ ኢትዮጵያን፣ ባለፀጋ ለማድረግ ቆርጬ ተነሥቻለሁ ። ይህንን ዓላማዬን ለማሣካት የሚችሉ እጃቸው ያላደፈ፣ ልቦናቸው  የፀዳ። ከንግግራቸው ና ከድርጊታቸው  በፊት አበክረው  የሚያሥቡ።በዕውቀት ላይ ና በጥልቅ ምርምር ላይ ተመሥርተው ና ታግዘው ሥራቸውን የሚከውኑ፣  ሰውን የሚያሥቀይም፣የሚያሳዝን ና ጥላቻን የሚያባብስ ድርጊት የማይፈፅሙ።… መልሥ ለመሆን ቢችልም፣ህዝብ ያሥቀይማል ብለው የሚያሥቡትን ከመናገር የሚቆጥቡ።…ወይም ደግሞ ‘ይሄ ሃሳብ ለሁሉም ዜጋ ጠቃሚ እንጂ ጎጂ አይደለም ።’ በማለት  በልባቸው አመዛዝነው የሚነጋሩ።እውቀት የዘለቃቸው።ጥበብ የተወዳጀቻቸው። እጃቸው ለልማት እንጂ ለጥፋት የማይተጋ። የማይሰርቁ።የማይዘርፉ።ህግን ተገን አድርገው የማይቀሙ ባለሥልጣናትን በማፍራት፣ ሰዎችና የሚሠሩበትን ተቋም  በአዲስ መልክ በመገንባት  ህዝብን
በቅንነት እና በንፅህና ማገልገል።…

” የዜጎችን ጥቅምና መብት ለማሥከበር ሌት ተቀን  የሚተጉ የፍትህ አካላትን አቅም በመጎልበት፣ ዜጎች ከቀበሌ ጀምሮ፣አገልግሎት ለማግኘት ሲጠይቁ፣በእጅ ጥምዘዛ ፣ ጉቦ እንዲከፍሉ የሚያደርጉትን አድነው በመያዝ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ  እንዲያደርጉ እናደርጋለን። ፍትህን በማሥፈን ህግ የበላይ እንዲሆን የሚተጉ እውነተኛ ህግ አሥፈፃሚዎችንም  በኃላፊነት ላይ እንመድባለን።

“መላው የፓርቲ አባላቴን ለዚህ ግልፅነት የተሞላበት አሠራር ብቁ እንዲሆኑ አሠለጥናለሁ።በአገልግሎት ሰጪ
የመንግሥት ተቋማት ሁሉ የተጠያቂነት አሠራርን ተግባራዊ በማድረግም አገልግሎት ተቀባዩ በፈጣን እና ፍትሃዊ
አገልግሎት እንዲረካ አድርጋለሁ።…
በአንዳአንድ ለመንግሥት ገቢ ፣በሚያሥገቡ  የመንግ ሥት መሥሪያ ቤቶች እና  ድርጅቶች ፣በሥልት ና ህግን
ተገን በማድረግ እየተፈፀመ ያለውንም የመንግሥት ገንዘብ ዘረፋ(መንግሥት ሀገር እንደሚያሥተዳድር እና ሀብቱ
የሀገር ሀብት መሆኑ እየታወቀ) እሥከወዲያኛው የሚያሥቆም የተጠያቂነት አዲስ አሠራርን በመዘርጋት የመንግሥት
ገንዘብ ዘረፋ በህግ ሽፈን እንዳይፈፀም አደርጋለሁ።ከሙሥና አንፃርም የማያፈናፍን ህግ እንዲወጣ እና በሙሠኛው
ላይ እንዲጨከን በማድረግ ሁሉም አገልግሎት ሰጪ እጁ እንዲፆም እና በሃቅ ህዝብ ና ሀገርን እንዲያገለግል
አደርጋለሁ ።የውስን ሀብት ዘረፋ ና ብክነትን በማሥቀረትም፣  የኢትዮጵያ ብልፅግና ባልተራዘመ አመታት ውሥጥ
እንዲረጋገጥ አበክሬ እሠራለሁ ። ”
በደምሳሳው በየአጋጣሚው የሚያንፀባርቁት የፓርቲው ቁንፅል ንድፈ  ሃሳብ ይኽ ነው።   ይህንን የተቀደሰ
ንድፈ ሃሳብ እውን ካላደረጉት  ግን……….
“በአንድ መንግሥት ውሥጥ፣ጠንካራ ፖለቲካዊ ኢኮኖማያዊ ና ማህበራዊ መዋቅራዊ ድልድይ አይኖርም። ።ጠንካራ
አሻጋሪ ድልድይ ከሌለ የውሳኔ አሠጣጦች በእጅጉ  ይዛባሉ።መንግሥት ጠንካራና ቅቡል ፖሊሲዎችን ማውጣትም
ያዳግተዋል።  ሥልጣን የያዘው የፖለቲካ ፓርቲም፣በዕውቀት እና በልምድ ከፍተኛ የመተግበር አቅም ያላቸውን በውሥጡ
ለማካተት ወይም አባላት ወይም ደግሞ ደጋፊ ማፍራት አይቻልም።  ጠንካራ እና ሃቀኛ ባለሥልጣናትን በውሥጡ ያላበዛ
እና ጠንካራ የህግ  መሠረት ያለው ድልድይ ያልገነባ መንግሥት፣ባለሥልጣኖቹ  ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚተጉ፣የሀገር
ሀብት በሚዛናዊነት ለህዝብ የማያዳርሱ ሥግብግቦች ሥለሚሆኑ በሥልጣን ላይ የህዝብ ልብ እየዘመረለት
አይሰነብትም።እየረገመው እንጂ!!
“መንግሥት የተሰኘውም  ፣ሥልጣንን በህዝብ ይሁንታ ፣በግልፅና ተአማኒ ምርጫ በመረከብ ካልሆነ እና
፣በማጭበርበር ፣በጠመንጃ  ፣በሴራ፣እና በገንዘብ ኃይል ሥልጣን ለይ በጉልበት ከወጣ፣ግብዝ ነጉሥ እንጂ አገልጋይ
መሆን አይችልም።
” በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን  አየተከታተለ ያልተራዘመ መፍትሄ ለመሥጠትም አይችልም።ግጭቶችን ለማሶገድ
የሚጠር መንግሥትም አይሆንም። በአጠቃላይ በህግ የተሰጡትን መብቶች መተግበር እና በምክርቤቱ እንዲሰራ
የተፈቀደለትን በየዓመቱ በሚያወጣው እቅድ ለመሥራት የሚሳነው ይሆናል።’መንግሥታዊ አሥተዳደሩም ‘ እንከን
የበዛበት፣ከህዝብ ልብ የራቀ ይሆናል። ”
ብልፅግና ፓርቲ  በህዝብ ልብ ቅቡልነት ያለው ሃሳብ እንዳለው ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) በሁለት
ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ደጋግመው ነግረውናል።ይሁን እንጂ ፣በአዲስ አሥተሳሰብ የቃኙት ፓርቲ እንደትናንቱ
የጥቂት ማፍያዎች መንግሥት፣ዘራፊ፣ አሰቃይ፣ አፋኝ፣ሌባ፣ ነጠቂ፣ዋሾ ፣ገዳይ ፣ወዘተ።እንዲሆን የሚፈልጉ
ዛሬምበፓርቲው ውሥጥ አድፍጠው ሊኖሩ ሥለሚችሉ ከራእዩ ሌያናጥቡት እንደሚችሉ ይታመናል።ይህ ፀረ ብልፅግና እኩይ
ድርጊት እውን እንዳይሆን ዛሬ ላይ ፓርቲው መንቃትና ተከታታይ  ራሱን የማጥራት ሥራ በመሥራት የለውጥ ጉዞው
በግል ጥቅም በሠከሩ ኃይሎች እንዳይቀለበሥ መታገል ይኖርበታል።
በውሥጡ በህቡ በመደራጀት እና በውጪ  በግልፅ ጠላትነት፣ያልሆነ ሥም ፣በመሥጠት ፣እነ
ና ውሸት በመፈብረክ እያሣጡት ያሉትን  የግል ጥቅም ያሠከራቸውን ግለሰቦች  የተቀናጀ  ሴራ፣ብልፅግና ፓርቲ
ዛሬ በቁርጠኝነት ሊገተው ካልቻለ፣የነገ ጥፋቱ በቀላሉ የማይቀለበሥ ይሆናል።…
እነዚህ ለራሳቸው በልፅገው የሌሎች  ምንዱባኖች  ብልፅግና ፀር በመሆን ፣የጦርነት ነጋሪት የሚጎሥሙ
፣ማመዛዘን የተሣናቸው ግብዞች፣ቆም ብለው ራሣቸውን እንዲገነዘቡ የማድረግ የግልፅነት ሥራ በመሥራት ገበናቸውን
ሜዳ ላይ ማሣጣት ብልፅግና ፓርቲ ይጠበቅበታል።አለባብሶ ማረሥ እንዳላዋጣ ከመቼውም ይልቅ ዛሬ የተገነዘበ
ይመሥለኛል።
እነዚህን በቃኝ የማያውቁ አልቅቶች፣  ያለአንዳች ርህራሄ ከህዝቡ ነጥሎ ብዝበዛቸውን፣የግፍ ሥራቸውን እና
አኗኗራ ቸውን ይፋ በማደረግ  ከህዝብ መነጠል ያሥፈልጋል  ።
ብልፅግና ፓርቲ በአጭር ጊዜ ውሥጥ የአብዛኛውን ደሃ ኢትዮጵያዊ ኑሮ ለመቀየር ሲል ይህን እርምጃ መውሰድ
ይጠበቅበታል።በፅሑፉ መግቢያ የተጠቀሰው የፓርታው ንደፈ ሃሳቡ ና ቅን ዓላማው  እንዲሳካ  ከእውነት ጋር ሁሉንም
ጥፋተኞች ማፋጠጥ ይጠበቅባታል ።
ከላይ የጠቀሰው  ሃሳቡ እንዲሳካለት እና የብልፅግና ራእዩ ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ፣ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
ይፈልጋሉ።እንዲህ አይነት ሀገርን እና ህዝብን ወደ ብልፅግና የሚወስድ በራሱ ብልፅግና የሚባል   ፓርቲ  መኖሩ
ብቻ በራሱ  በእውነት “አሪፍ ” የሚሰኝ ነው። ብልፅ ግናን የማይፈልግ ፣ድህነትን የሙጥኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ከቶም
የለምና!!
ሆኖም ዛሬ ላይ ቆመው፣ለነገ የህዝብ ብልፅግና በማሰብ፣ብዙዎቹ የብልፅግና አባላቶች፣ጭንብላቸውን
በማውለቅ፣ከላይ ለሠፈረው የብልፅግና ፓርቲ መነሻ ዓላማ በመቆም   የሚያሻሽላቸውን ፓሊሲዎች በተግበር ለመደገፍ
ቁርጠኛ መሆን አለባቸው።
በበኩሌ እንደ ብልፅግና ፓርቲ ፣ የሚያሥቡ፣ሌሎች ፓርቲዎችም የፖሊሲ ተመሳሳይነት ካላቸው የኢትዮጵያን ህዝብ
ድምፅ እንደሚያገኙ ተሥፋ አደርጋለሁ።
ዛሬ  የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ነቅቷል። ብልጣ፣ብልጡ ሁሉ የቋንቋ ፓርቲ አቋቁሞ ፣እርሱ፣ግብረ
አበሮቹና ቤተሰቡ ብቻ ና ብቻ፣ ተንቀባረው ና ተንፈላሰው እየኖሩ ፣ መሬት እፍ ብሎ የሚተኛውን” ነገ እንደእኔ
ተንቀባረህ እንድትኖር አደርግሃለሁ።” በማለት  ሊሸነግለው ከቶም አይችልም።
ይህ ጨዋና ኩሩ ህዝብ  ሠርቶ እንዲያልፍለት እንጂ ዘርፎ ና ቀምቶ እንዲያልፍለት በፍፁም አይፈልግም።
በድካሙ ውጤት  ኑሮው እንዲለወጥ ግን ይፈልጋል።ለዚህ ደግሞ መንግሥታዊ  ደጋፍ ይፈልጋል። መንገድ፣ንፁህ ውሃ
እና የኤሌትሪክ አገልግሎት እና የድካሙን ፍሬ የሚያገኝበት መሬት።በከተማ ያለው ደግሞ የመሥሪያ ቦታ እና ሠርቶ
የሚመልሰው ገንዘብ።ከዚህ ውጪ ፍላጎት የለውም። ፍላጎቱ ግልፅ ነው፣ እንደጥቂቶቻችን መሠረታዊ ፍላጎቶቹ
ተሞልተውለት ፣ይህቺን አጭርና ጣፋጭ ህይወቱን ዘመናይ አድርጎ ፣ለትውልዱ ብልፅግናን አውርሶ ማለፍ ነው።
ዘላለም አለሙንም ጠባቦች፣ትምክህተኞች ፣ዘረኞች፣  አዛኝ መሣይ ቂቤ አንጓቾች ወዘተ ሁሉ ፤ “ቋንቋህን፣
ባህል ህን ፣መሬትህን፣በማሥጠበቅ ሀብታም ልናደርግህ ነው ፣የፖለቲካ ትግል የምናደርገው “እያሉ፣ራሳቸው ጠበው
፣በትዕቢት ተወጥረው፣ እጅግ ግብዝ ሆነው፣ በተጨባጭ በዘረፋ በልፅገው፣እየተመለከተ  በአቀመ ቢሥነት ቁጭ ብሎ
ማየት መሮታል።(…)
እርግጥ ዛሬ ፣በቋንቋው ዕውቀትን እየገበየ ነው።ባህሉም ተከብሮለታል።ይሁን እንጂ በእርሱ ቋንቋ ሥም ሥልጣን
ከያዙት እና አካባቢውን በአለቅነት ከሚያሥተዳድሩት ውጪ መላው ህዝቡ” በሚገባው መጠን” እንዳልተጠቀመ
ይታወቃል።ከዛሬ ኑሮ ውድነት አንፃር ከተመለከትነውም  ፣የእርሱ እና የእነሱ ኑሮ  የሰማይና የምደርን ያህል
ልዩነት አለው።
ትላንት “የትምክህት ኃይሎችን አምርረን እንታገላለን!” የሚሉ፣ትላንት “ከአፍንጫ ያራቀ አሥተሣሠብ
ያላቸውን አንታገሥም!” የሚሉ፣ትላንት “የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያን ያጠፋታል፣የፍትህ፣የነፃነት፣የዴሞክራሲ ጉዳይ
፣የመኖርና ያለመኖራችን ጉዳይ ነው።” ሢሉ፣የነበሩት፣ ከአብራኩ የወጡ ወንድምና እህቶቹ እኮ ናቸው ዛሬ ሰማዩን
በእርግጫ እየመቱ ያሉት።እርሱ ግን ትላንት በሚያውቋት ዲንጋይ ላይ ቁጭ እንዳለ ነው።
ይሁን እንጂ በአንዳንዶቹ  ላይ ታሪክ ተደገመ። እንደ ደርግ  ብሶት በወለደው የኢትዮጵያ ህዝብ አመፅ  ፣
እንደ በጋ ጉም ብን በለው በቋንቋ ጥላ የመሸጉ አሉ።በዘር እንኳን ሁላችንም ጥቁር ነን። በእውነቱ ታሪክ
በራሳቸው ላይ የተደገመው በራሳቸው ሥግብግብነት ፣ አልጠገብ፣ ባይነትና ፈጣሪ ይበቃል!ባለው ጭካኔያቸው ምክንያት
ነው።
ሥግብግብነታቸው ፣ግብዝ አድርጎቸው፣   የገዢዎች ጭቆና እና ብሶት አንገፍግፎቸው ፣በረሃ በመግባት፣ለፍትህ
እና ለነፃነት የሞቱ፣የቆሰሉ እና የደሙ መኖራቸውን ዘንግተው፣”የታጋይ” መሠዋትነትን ከመጤፍ ባለመቁጠር ፣
“ለራሴ ብልፅግና ካላመጣው፣መታገሌ ምን ፋይዳ አለው?”በሚል የሥግብግብ አሥተሣሠብ  የታጋዩን ዓላማ
በመቅበራቸው፣  የትግራይ ክልል ህዝብ አዝኗል።
ጥቂት  ሃቀኞች “ተው ይህ መንገድ ያጠፋናል ይቅርብን።” ቢሉም ከመለሥ ሞት በኋላ ማንም የሚሰማ ጆሮ ሥላልነ
በረው  ለግል ሀብት ሁሉም፣ያለሃይ ባይ እጅግ በባሰ መልኩ  ሲሯሯጥ ፣ ከህዝብ ልብ በመራቁ በአጭር ጊዜ የህዝብ
አመፅ የብዝበዛ ከለለውን የሀገር የመንግሥት ሥልጣንን የህወሃት አመራር አጥቷል።
መለሥ የፓርቲ ከበርቴነትን እንጂ የግል ከበርቴነትን እብዛም የሚደግፉ አልነበሩም።ይሁን እንጂ “ሥልታዊ
የሆነ ምሥጢራዊ በዝባዥ አልነበሩም። ” በማለት የፅድቅ አክሊልን ህዝብ አያጎናፅፋቸውም።በእርግጥ ” አምሥት
ብርን እና አሥር ብርን ባይለዩ አጋሮቻቸው እየለዩ ባንክ ሊያሥቀምጡላቸወ እንደሚችሉ ይታመናል።”(እርግጥ ነው
ለወንድሞቻቸውና እና ለእህቶቻቸው በሥልጣናቸው ተጠቅመው ያደረጉት የጎላ ችሮታ የለም። መንግሥቱ ኃ/ማርያምም
እንዲሁ ነበሩ። ለግላቸው አያሌ ሚሊዮን ዶላር  ከሀገር አላሸሹም ብሎ የሚከራከርላቸው ግን አያገኙም።)
” የቀድሞውጠ/ሚ መለሥ አሥገራሚ እውነት፣ ገና በረሃ እያለ ይህቺን ሀገር  እንደካርታ በውዞ  እንደገና
ሊሠራት ማቀዱ ነው። “(ዶር አሻግሬ ከኢሣት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሥ ይፋ እንዳደረጉት)  “ይሁን እንጂ እርሱ
በአእምሮው የሣላት  ኢትዮጵያ በልቡ ብትኖርም፣እውን ሣያ ደርጋት ሞት ቀደመው።በረቀቀ ሥልት የህገመንግሥት አር
ቃቂዎችን መደቦ ፣ህገ መንግሥቱ፣እርሱ የሚያውቀው ብዙ እንቆቅልሾች እንዲኖሩት በማድረግ፣ ግን ተሣክቶለታል።”
ይላሉ ብዙ  ገለልተኛ ምሁራን።
እሥከዛሬ  ያልተገለፀልንን የትግራይን፣የኦሮሞን፣የአማራን የቋንቋ ንግሥና ያወጀ  መለሥ ነበር።መለሥ፣
የፖለቲካ መዋቅሩን ከኢኮኖሚ መዋቅሩ ጋራ በማጣበቅ፣እንደብረት አጠናከሮ የፓርቲ ከበርቴዎች እንዲፈጠሩ
አድርጓል።ይህ ማለት  እራሱ የሚያወግዘውን ” የቦናፓርቲዝም መንገድ” ሦሥቱ ፓርቲዎች እንዲከተሉ እና በቋንቋ
ሥም ጥቂት የፓርቲ አባላት የሚያዙበት ሁሉም የማትረፊያ መንገዶች በመንግሥት በኩል የተመቻቸላቸው   ፍትሃዊ
ያልሆኑ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶችንም ፈጥሯል።
ዛሬም ድረስ ከፓለቲካው ጋር እነዚሁ ድርጅቶች  የተጣበቁ ናቸው።እነዚህን ድርጅቶች ከፓለቲካው ጫወታ ገለል
ማድረግ አሥፈላጊ ነው።ያለበለዚያ ጥቂቶች የሚያዙበት የብዙሃን  ገንዘብ የሚያመጣው መዘዝ ቀላል አይሆንም ።
ከዚህ ድብቅ አጥፊ ባህሪያቸው አንፃር ለሁሉም ከፓርቲ ጋር ለተጣበቁ የንግድ ድርጅቶች ከወዲሁ መላ ሊበጅ
ላቸው  ይገባል። ወደፊት በሀገርና በህዝብ ላይ  ከባድ ችግር ከመውለዳቸው በፊት፣ (ያረገዙት መከራ ይታወቃል ና
)በአክሲዮን ወደ ህዝቡ ተመልሰው  ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች ቢሆኑ የሚወልዱት ጥፋት
ይጨናገፋል።
መቼም የታጋዩ ዓላማ ጥቂቶችን የሚያደልብ የንግድ ድርጅት መፍጠር ባይሆንም፣እሥከተፈጠሩ ጊዜ ድረስ በትግል
ላይ  የሞተው ቤተሰቡ ድርሻ ሊሰጠው ይገባል ።የቆሰለው፣የደማው በህይወት ያለ ታጋይ ሁሉ ድርሻ ሊኖረው
ይገባል።አጠቃላይ ህዝቡም ወደልማት የሚዞር ድርሻ ሊኖረው ይገባል።( ይህ ጉዳይ ፣በኦሮሞ ሥም፣
በአማራ ሥም የተቋቋሙ የልማት ድርጅቶችን ይመለከታልና  በዚህ ጉዳይ ላይ  ያላችሁን ሃሳብ ከመናገር እና ከመፃፍ ችላ አትበሉ።)

ማጠቃለያ
በተፈጠረው ብሶት  ሰበብ ፣ጥቂት የነቁ ሰዎች የተለያየ የነፃ አውጪ እና የደረግ ተቃዋሚ ሆነው፣ሥልጣንን
ፍለጋ ፣በወቅቱ በነበረው ቀዝቃዛው ጦርነት በመታገዝ ብረት ይዘው በርሃ እንደገቡ ይታወቃል።ሥንት ሆነው  በረሃ
ገቡ?በምን ሥም ይጠሩ ነበር።?እንዲት እፍኝ የማይሞሉት እልፍ ሆኑ? በመጨረሻ ማለትም በ1983 ዓ/ም ወደሥልጣን
እንዴት ሊመጡ ቻሉ?ወደሥልጣን  እንዲመጡ፣የአሜሪካ መንግሥት በረቂቅ የሥለላ መዋቅሩ ምናልባትም ከሞሳድ ጋር
ተባብሮ የኮ/ሌ መንግሥቱን መንግሥት በማዳከምና በመሥኮብለል ፣ ትልቁን የቤት ሥራ በመሥራት ኢህአዴግ ዎች
ከአንቦ በሥተቀር ፈተና እንዳይገጥማቸው በማድረግ ረግ፣መንበሩን አንዲረከቡ ትልቅ ሚና አልተጫወተምን??
ከአሜሪካ መንግሥት ባልተናነሰ መልኩ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች፣ ምርኮኞችና  ከዳተኞች ሆነው ከህወሓት
ጋር በመቀላቀል፣ህወሓት ከደፈጣ ተዋጊነት ወጥታ ዘመናዊ ና በሥልት የተደገፈ ውጊያ እንድታከናውን ፣በምርኮኛ
ታንኳች ጭምር አረዷቸውምን? (ታሪኩ “የገደልንም እኛ! የሞትነውም እኛ!” ሥለሆነ እጅግ አሳዛኝ ነበር።በህወሓት
ሰራዊት እና በኢትዮጵያ ሠራዊት ውሥጥ ያሉ ሁለት ወንድማማቾች ተታኩሰው ቢገዳደሉ ፣የሚያሥፎክር የጀብድ ሥራ
ከቶም አይሆንም።)
ታላቁ እውነት ግን በሚያሳዝን መልኩ የ17 ዓመቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣በቀጥና በተዘዋዋሪ የሰውና የሎጀሥቲክ
ድጋፍ ለሕወሓት  ማድረጉ አይካድም  ።ቀጥተኛና ግልፅ ድጋፍ ባያደርግም ፣በሙሥና እና በዘረፋ ለሕወሓት
የኢትዮጵያ ወታደር ሥንቅና ትጥቅ ይደርሳት እንደነበር አይካድም።ለሻብያም እንዲሁ።
…ታሪክ ለእነዚህ ጥያቄዎች በቂ ማብራርያ የሚሰጡ የአይን እማኞች አሉት። የፈለግነውን ያህል ታሪክን
ለማዛባት ብንጥርም፣ ህዝብ በደረሰበት ጭቆና፣የፍትህ እጦት እና የነፃነት ማጣት ፣ ኢህአዴግ ወደ ሚኒልክ
ቤተመንግሥት  ሠተት ብሎ እንዲገባ ድጋፉን ሰጥቷል ።
ታሪክ እውነትን ሳይቀባባ ይነግረናል።ታሪክ እንደሚነግረን በህወሓት ሥም ፣ የነፃ አውጪነት ትግል
ያደረጉት፣ “ብሶት የወለዳቸው ታጋዮቾ” መሥዕዋትነት   ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ  ነፃነትና ፍትህን ለማምጣት
ነበር።ሰዎች ያለህግ እንደእንሥሣ እንዳይታሰሩ፣እንዳይሰቃዩ፣ እንደይረሸኑና ንብረታቸውም እንዳይወረስ ነበር።
እነዚህ ታጋዮች አካላቸውን ያጡት ፣ብዙዎቹ የትግራይ ወጣቶች የተሰውት፣   ለሀመርም ፤ለሸካም ፤ለቦዲም ፤
ለዳውሮም፤ ለዳሰነችም፤ለክሥታኔም ፤ለከባታም ፤ለሃዲያም። ለዶርዜም ፤ለሲዳማም፤ ለወላይታም፤
ለቅማትም፤ለመዠገርም፤ለሺናሻም፤ለኩሎም ፤ለየምም።ወዘተ።ነፃነት እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሲሉ ነው።   ደሃው
አርሶ አደሩ ና አርብቶ አደሩ ኑሮው እንዲሻሻል  ና እንዲለወጥ  ነበር የተሠውት።የአጠቃላዩ ከተሜ ሠርቶ ና
ለፍቶ አደር ህይወት እንዲዘምን እንጂ የጥቂት የኢህአዴግ አባላት ህይወት ብቻ  እንዲመነደግ አልነበረም፣ መሥዋ
ትነታቸው።ይህንን እውነት ለማሥገንዘብ ነበር “ያሥተሠርያል “የተሰኘ የጥበብ ውጤቱን፣ ያልተዘመረለት ክብር
የሚገባው፣የፍቅር ሰባኪ ባለቅኔው ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሣሁን )፣
“በአሥራ ሰባት መርፌ በጠቀመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
እንደአምነው ባለጊዜ የምናውን ከቀጣ
አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ!?… ”  በማለት  በመረዋ ድምፁ በመላ ኢትዮጵያ የተወደደ ዘፈን እንካችሁ
በማለት ጉልቻዎቹ ቦታቸው ተቀያየረ እንጂ የተጣደው ድሥት ወጥ አንድ መሆኑን ያበሠረው።
ዛሬም ከተነሱበት ህዝባዊ ዓላማ አፈነግጠው፣የህዝብን ሀብት ሲመዘብሩ የነበሩ በፈፀሙት ውጉዝ ተግባር
ተፀፅተው፣ንሥሐ በመግባት  ፣የበደሉትን ህዝብ ለመካሥ የማይፈልጉትን የቀደሞው የኢህአዴግ አባላት ፣ “በሥልጣ
ናችሁ ተጠቅማችሁ በህዝብ ገንዘብ የምትኖሩት የድሎት ኑሮ ይብቃችሁ። መመፃደ ቃችሁ  ይብቃችሁ። በአጠቃላይ
የንጉሥነት ኑሮ ይብቃችሁ።እንላለን ። “አይ አይበቃንም። ፍቅር  አይገዛንም።ዛሬም ከተጠበቅንበት የህዝብ ጀርባ
ላይ፣በጥላቻ ተሞልተን እንኖራለን እንጂ፣በፍፁም አንወርድም።” የምትሉ ካላችሁ  መጨረሻቸው ጥርሥ ማፋጨት
እንደሚሆን ከወዲሁ አውቃችሁ ፣ ከቦና ፓርቲዝምና ከሀገር  ብልፅግና አንዱን ምረጡ።

2 Comments

  1. እስይ ደግ ጽሁፍ ነው። Napoleon Bonaparte ናፋቂዎች ያለፈ ነገር ዛሬም ይሁን የሚሉ ናቸው። እኔ ጠ/ሚ አብይን አላውቃቸውም። ግን በሃገሪቱ ታሪክ ከዛፍ ተከላ እስከ ቤተመንግሥት ጽዳት፤ ለህዝብ መናፈሻ ከማመቻችቸት ከሃገራቸው ውጭ የታገቱ እስከማስፈታት የሰራ በሃገሪቱ የሥልጣን ቁንጮ ላይ ኖሮ አያውቅም። ምን አልባት የንጉሱ ዘመን አድርጎት ሊሆን ይችላል። እሱን እኔ እምብዛም አላውቅም። ደርግና ወያኔ ግን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ሆነው ሌላው በኢትዮጵያዊነት ገሽልጦ ሲበላን ወያኔ ደግሞ በዘር መንዝሮ መንደርተኛ አደረገን። ታዲያ ከዚሁ ሾተላይ የወያኔ ኮሮጆ አፈትልከው የወጡት የአሁኑ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሜሪካዊው ተናጋሪና የነጻ ሃሳብ አራማጅ Robert Green Ingersol በአንድ ግጥም መሳይ ነገሩ ላይ እንዲህ ይለናል “What light is to the eyes – what air is to the lungs – what love is to the heart, liberty is to the soul of man” ዶ/ር አብይ ለሃገሪቱና ለህዝቧ He is the breath of Fresh Air. ግን የዘርና ጎሳ ፓለቲከኞች ሥጋ በሌለው አጥንት ላይ ሲጋጩ ማየት ጥቁሩ ህዝብ መቼ ነው የራሱን መብት አስጠብቆ የሌሎችን እምባ የሚገታው ብሎ ለጠየቀ መልሱ ዝምታ ብቻ ነው። የመገናኛ አውታሩ በውሸትና በፈጠራ ወሬ የተማታበት በመሆኑ ግልጽ በሆነና እውነትን በተመረኮዘ መንገድ የጠ/ሚሩ አመራርና እይታ ለህዝባችን አያደርስም። ሁሉም እኔ ተበደልኩ ኡኡ በሚልባት የሃበሻ ምድር ለጥቅል አስቦ በህብረት መኖር ከቀረ ቆየን። አማራው ለአማራው ትግራዪ ለትግራይ ሃረሬው ለሃሬረው ወዘተ በማለት ድንበር ስናበጅ ዓለም ጥሎን ሄደ። አሁን ምርጫ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ የሚሉት የተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሆነ ወደ ጎን የተደረገው ናዚና ፋሽሽቱ ወያኔ ለሃገር አስበው ሳይሆን በግርግሩ እንደሚያተርፉ ከአሁኑ በማስላት ነው። አባይን ሸጠ ይሉናል ወያኔዎች እንደ እነርሱ ሃገር የሸጠ በታሪካችንም የለም። የአባይ ግድብ ሥራ መጓተት እነርሱ የፈጠሩት የዝርፊያ መረብ የፈጠረው ጉድ ለመሆኑ ሰው ያውቃል ግን በድሎ ለሚያለቅስ ከለቅሶው ውጭ መበደሉ አይታየው። መርከብ የሚያክል ነገር ጠፋብኝ የሚሉ የበረሃና የከተማ ሌቦች ናቸው ወያኔዎች። የትግራይ ህዝብም መነገጃ ነው እንጂ በወያኔ ነጻነትን አይቶ አያውቅም። ለመሆኑ እስቲ ንገሩን የትግራይ ህዝብና ወያኔ አንድ ናቸው የምትሉ። መቼ ነው የትግራይ ህዝብ በ 45 ዓመታት ውስጥ በነጻ ድምጽን ሰጥቶ ወያኔ ይወክለን ያለው? አዎን በጦር መሳሪያ አፈሙዝና በሺህ በሚቆጠር የወያኔ ካድሬ ከሃገር እሰከ ውጭ በስለላ መረባቸው በማስገደድ ወያኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ይበሉን እንጂ ለፈፋው የፓለቲካ የውሸት ክምር እንደሆነ እናውቃለን። አሁን ያ በውሸት የቆመ የፓለቲካ ክምር እሳት ሊበላው ሲል መውጫ ማጣታቸው ደግሞ በባንክ ምንም ገንዘብ የለንም እስከማለት አድርሶአቸዋል። በየዘመዶቻቸው ስም የቆሙት ህንጻዎችና በውጭ ሃገር የተገዙ ቤቶች፤ የተከፈቱ የነዳጅ ማደያዎችን፤ የምግብ ቤቶች እና በስማቸው የተደበቀው ንዋይ ለትግራይ ህዝብ የቆመ ድርጅት የሚሰራው ሥራ አይደለም። ግን ሲጀመር ለራሳቸው ብቻ የቆሙ የአንድ መንደር ልጆች ናቸው።
    ጠ/ሚ አብይን በኦሮሞዎች እጅ ለማስገደል ያደረጉት ሙከራ አልሳካላቸው ቢልም አሁንም እንደማያርፉ የታወቀ ነው። በሱዳኑ ጊዜአዊ መሪ ላይ የተቃጣውና ሳይሳካ የቀረው የግድያ ሙከራ እንዴትና በማን እንደተቀነባበረ አሁን ቁልጭ ብሎ ታይቷል። የግብጾች እጅ እንዳለበት ተደርሶበታል። ዛሬም ነገም የሃበሻው ምድር እርስ በርሱ እንዲገዳደል የጥቁር ህዝቦች ጠላቶችና የዓረብ መንጋ ከውስጥ ባንዳዎች ጋር የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደማይኖር ጠንቅቀን እናውቃለን። ጠ/ሚሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥን መሪ ናቸው። መታወቅ ያለበት የሃበሻን ህዝብ በፍቅር ማስተዳደር ከባድ መሆኑን ነው። ለምን ቢባል 17 ዓመት በደርግ እርግጫ 27 ዓመታት በወያኔ ሾተላይ የዘር ፓለቲካ ተተብትቦ የኖረ ህዝብ ስለሆነ በዲሞክራሲና በፍቅር ተስማምተን እንኑር የሚለውን ጥሪ ገና እያጣጣመ በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ጉዳዪ ከሆድ ገብቶና አምኖበት ጠ/ሚ አብይን ለ 5 ዓመት አመራር እንደሚመርጣቸው ጥርጥር የለኝም። መረጃ በሌለው ነገር የሚኮኑኗቸው ሁሉ የወያኔና የሃገሪቱን ጠላቶች ያጎለብታል እንጂ ለማንኛውም የሃገሪቱ ህዝብ ፋይዳ አያስገኝም። ምርጫችን ብልጽግና ይሁን። ቦናፓርቲዝም እጅ እጅ የሚል እንጀራ ነው። በቃኝ

  2. ወያኔ የተቋቋመው በ ባህል እና በ ቋንቋ ከሚመሳሰሉን ወንድሞቻችን ኤርትራውያን ጋር አብረን እንሁን በማለት ነው እንጂ ለኢትዮጵያ ብሔሮች መብት ለመዋጋት ብለው አይደለም። ለ ኢትዮጵያ ብለው ቢሆን ኖሮ ለምን የ ኢትዮጵያ ከማለት ፋንታ የ ትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ብለው ተነሱ? ለምንስ ኢህአፓን ከ ትግራይ አስወጡ? ለምንስ አሁን ያላቸውን ካርታ ስለው ሲንቀሳቀሱ ነበር?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.