በኮቪድ-19ና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ ሀገር-በቀል የባህላዊ ህክምና በሚል ርዕስ በተዘጋጀ በኦንላይን በሚካሔድ ሳምንታዊ የምሁራን ውይይት መድረክ -ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

covid 19

 • ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች
 • ለሁሉም የግል ዩኒቨርስቲዎች
 • ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጤና ቢሮዎች
 • ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች
 • ለብሔራዊ የCOVID-19 ምርምር ግብረ-ሀይል አባል ተቋማ
 • ለፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጄንሲ
 • ለፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት
 • ለከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጄንሲ
 • ለከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል
 • ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ምክር ቤት አባላት
 • ለሳይንስ ሙያ ማህበራት

ባሉበት

ጉዳዩ፡– “በኮቪድ-19ና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ ሀገር-በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሄዎች”  በሚል ርዕስ በተዘጋጀ  በኦንላይን በሚካሔድ ሳምንታዊ የምሁራ ውይይት መድረክ ላይ እንድትሳተፉ መጋበዝን መለከታል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር “በኮቪድ-19ና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ ሀገር-በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ሳምንታዊ የምሁራንምክክር መድረክ ሰኔ 3 ቀን 2012 ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡30 በዙም ቴክኖሎጂ ኦንላይን (Virtually) ያካሂዳል፡፡

የምሁራን ውይይቱ ዓላማ በባህላዊ ህክምና እዉቀቶችና በኮቪድ-19 ዙሪያ እየተሰሩ የሚገኙ ጉዳዮች ላይ ምሁራዊ ገለፃና ምክክር በማድረግ  ግንዛቤዎችን ለማስጨበጥና ተሞክሮዎችን ወስዶ ለመጠቀም የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር ነዉ፡፡  የዉይይቱተሳታፊዎችበዋናነት ከላይ በተገለፁ ተቋማትየሚሰሩ የስራኃላፊዎችናለዉይይትርዕሶቹየሙያቅርበትያላቸዉባለሙያዎችእንዲሆኑ ስለሚፈለግ በዚሁ አግባብ እንዲሳተፉ እንዲደረግ በአክብሮት እየጋበዝን ኮንፈረንሱን ለመታደም የሚከተለዉን የዙም አድራሻ https://zoom.us/j/95430140049 እንዲጠቀሙ እንገልፃለን፡፡

ሰዓትተግባርፈጻሚ አካላት
7፡15 – 7፡30ተሳታፊዎች ቨርቹዋሊ በተሰጣቸዉ የዙም አድራሻ ይገባሉተሳታፊዎች
7፡30-7፡35የእለቱን መርሀግብር ማስተዋወቅና መምራትክቡር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ
7፡35 – 8፡00የመክፈቻ መልዕክትክብርት ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር

ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳዉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

8:00 – 9፡00በኮቪድ-19ና በሌሎች ወረርሽኞች ዙሪያ ሀገር-በቀል የባህላዊ ህክምና እውቀቶች ሊያመጡ የሚችሉት መፍትሄዎች
 1. ዶ/ር አባተ ጌታሁን (የሀገር-በቀል እውቀቶችምርምሮች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት – የወሎ ዩኒቨርስቲ ተሞክሮ)
 2. ዶ/ር ማሪያማዊት ዮናታን (የኮቪድ-19ኝን ወረርሽኝን ለመቋቋም የኢትዮጵያ የባህል  ህክምና ሊያበረክት የሚችለውአሰተዋፅኦ – አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ)
 3. ዶ/ር አስፋዉ ደበላ (ሀገራዊ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና  ትግበራበባህላዊ ህክምና-የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት))
 4. ሎሬት አለሙ መኮንን (የባህል ህክምናን ባህላዊነቱን ሳይለቅ ማዘመን – የኢትዮጵያ ባሀላዊ መድሐኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር)
 5. ዶ/ር ፍቃዱ ፉላስ እና ፕ/ር ብስራት ሀይለመስቀል (አለምአቀፍ ተሞክሮዎች በባህላዊ ህክምና እና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ፡ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ – USA)
 6. ፕ/ር ፅጌ ገብረማሪያም (አወያይ) – የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት
9፡00 – 10፡20ውይይት ፕ/ር ፅጌ ገብረማሪያም (አወያይ)
10፡20 – 10፡30ማጠቃለያና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ

 

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ

ለክብርት ሚኒስትር

ለክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች (X3)

ለሚኒስትር ጽ/ቤት

ለሳይንስና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

ለኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ለፋይናንስ ዳይሬክቶሬት

ሳይንስና  ከፍተኛ  ትምህርት  ሚኒስቴር

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.