የምክር ቤት አባላት የትግራይ ክልልን በተመለከተ ላነሱት ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰጡት ምላሽ

Abiy የትግራይ ህዝብ የተከበረ የበላይም የበታችም ያልሆነ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት የተዋደቀና ዋጋ የከፈለ፤ ለኢትዮጵያ ጋሻ የሆነ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ተራራን ቆፍሮ፣ ጥሮ ግሮ ሰርቶ የሚበላ ኩሩና ሚያኮራ ህዝብ ነው፡፡

የትግራይን ህዝብ የምናቀው በወሬ አይደለም አብረን ኖረን፣ ከእጁ በልተን ኖርንበት ነው፣ አብሮ መኖርን የሚያውቅበት ህዝብ ነው።

ችግር እየሆነ ያለው የትግራይን ህዝብና ፓርቲዎችን መቀላቀል ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ የዛሬ አርባ ዓመት ፀረ-ደርግ ትግል ሲጀምር አንድ ሃሳብ አንድ ፓርቲ ይዞ አልተነሳም፡፡ ብዙ ፓርቲዎችንና የተለያዩ ሃሳቦችን ነበሩ።

ዛሬም አረና የሚባል ህጋዊ ድርጅት አለ፡፡ የራሱ የሆነ አስተሳሰብ፤ አመለካካት፣ የራሱ አደረጃጀት ያለው የትግራይን ህዝብ መለወጥ የሚፈልግ ፕሮግራም ያለው ፓርቲ፡፡ ህውሃት አለ፤ የራሱ ሃሳብና ፍልስፍና ያለው፡፡ እንደዚሁም ብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ሆነው የሚታገሉ የትግራይ ተወላጆች አሉ፡፡

ይህን ትልቅ ህዝብ በአንድ ሃሳብና በአንድ መንገድ በአንድ ፓርቲ ማየት ጥሩ አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ህውሓትና ብልፅግና የቃላት ጨዋታ ሲጀምሩ በጥቅሉ የትግራይ ህዝብ ተነካ ተብሎ ይነገራል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፤

የትግራይን ክልል መንግስት እንደ መንግስት አጥፊ ፣ሌባ፣ ክፉ፣ የማይሰራ አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው፡፡ በትግራይ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከላይ እስከ ታች የህዝባቸውን ሕይውት ለመቀየር የሚፈልጉ፣ ሌብነትን የሚጠሉ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና የሚጥሩ ሰዎች በሺህ የሚቆጠሩ አሉበት፡፡

ህውሓትም ቢሆን ብዙ ሺህ አባላት ያሉት ፓርቲ ነው፡፡ ከሊቀ መንበሩ አንስቶ እስከ ታች ተራ አባሉ ድረሱ ያሉ ጥፋተኛ ናቸው የሚል እሳቤ እኛ ዘንድ የለንም፡፡

ለኢትዮጵያ ህዝብ ልማትና ዲሞክራሲ ህይወታቸውን የሰው፤ ለአካል ጉዳት የተዳረጉ አሁንም መቀሌ አሉ ክብር የሚገባቸው፡፡ በህውሓት ጥላ ስር የታገሉ፡፡ ራሱ የክልሉ ዋነኛ አመራር የኢትዮጵያን ሰላምና ልማት የሚፈልግ ነው፡፡ ክልሉ እየመራው ያለው ዋነኛው ኃይል ከላይ ከጫፍ ያለው አመራር እዚህ ካለው አመራር የማይለዩ ቀን ከሌሊት ለትግራ ህዝብ ልማትና ሰላም የሚሰራ ናቸው፡፡

ይህ ማለት ግን ትግራይ ክልል ውስጥ ወንጀለኞች የሉም ማለት አይደለም፤ ጥፋተኞች፣ የሚሳደቡ ሰዎች የሉም ማላት አይደለም፡፡ አንድ ሰው ሲወቀስ፣ ሁለት ሰው ሲወቀስ የትግራይ ህዝብ ተወቀስ ወደሚል ድምዳሜ አንውሰደው፡፡

የትግራይ ህዝብ በሚሊየን የሚቆጠር ትልቅ ህዝብ ነው፡፡ በሁለት ሶስት ሰዎች የሚወከል አይደለም፤ በአንድ ፓርቲም የሚወከልም አይደለም፡፡

የትግራይ ህዝብ ከለውጡ በኋላ ተጎድቷል ለሚለው የክልሎችን በጀት የሚያፀድቀወ ይህ ምክር ቤት ነው፡፡ እኔ ወደ ስልጣን ስመጣ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በጀት ሰባት ቢሊየን ብር ገደማ ነበር፡፡

ትግራይ ክልል ሆኖ ከተጀመረበት እስከ ለውጡ ድረስ የትግራይ ክልል ያደገው በጀት ሰባት ቢሊየን ብር ድረስ ነው፡፡ አሁን ከቢኔው ያፀደቀው ከሰሞኑ የሚቀርብላችሁ በጀት ሲመጣ ትግራይ 10 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገብቷል፡፡

በፊት ከነበረው ምከር ቤቱ ከሚያውቀወ በጀት በለውጡ 42 በመቶ አድጓል፡፡ ይህ በጀት ፕሮጀትን፣ መንገድን፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን አይመለከትም፤ ለክልለ የሚመደብ በጀት ብቻ ነው እያነሳው ያለሁት፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ በሚመለከት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ለትግራይ ከልል 46 ሚሊዮን ብር በጥሬ የገንዘብና በቁሳቁን ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ለኮሮናን በተመለከተ ለትግራይ ድጋፍ አልተደረገለትም የሚል ሰው ካለ ጤና ሚኒስትርን ጠርታቹህ ብታረጋግጡ ጥሩ ነው፤ የክልሉን ጤና ቢሮም ብትጠይቁ ይነግራቹሃል፡፤ ከበጀት ባሻገር በቁሳቁስም በገንዘብም ድጋፉ ተደርጓል፡፡

ከማዳበሪያ አቅርቦት ጋርም ተያይዞ ደቡብና ትግራይ ክልሎች ከዚህ በፊት የነበረባቸውን እዳ አልከፈሉም፡፡ ሌሎች ክልሎች ከፍለዋል፡፡ ዘንድሮ ትግራይ ስለላልከፈለ ማዳበሪያ አይመጣለትም ሲባል የፌዴራል መንግስት 445 ሚሊየን ብር ተበድሮ ትግራይ ማዳበሪያ ማጣት የለበትም ወደፊት ይከፍለዋል ብሎ ያቀረበው የፌዴራል መንግስት ነው፡፡

ለመቀሌ ውኃ ከቻይና መንግስት ጋር የተደረገው ስምምነት ዘጠኝ ቢሊየን ብር ነው፡፡ ለመቀሌ ከተማ የመጠጥ ውኃ እያወጣን ያለነው ገንዘብ አምስት ስድስት ከተማ ሊሰራ ይችላል፡፡ ከቻይና መንግስት ጋር ከተፈራረምን በኋላ መንግስት ዘንድሮ መክፈል የሚገባው ገንዘብ ካለከፈለ አልጀምርም ስላሉ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊየን ብር ክፍያ ተፈፅሟል፡፡ ምክንያቱም የመቀሌ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ስለሚያሰፈልገው፡፤ ተርፎን ሳይሆን መደረግ ስላለበት ነው፡፡ ይህ ሃሳብ መቀሌ ውስጥ ላለ ሰው በትክክል ተነገጸል ወይ እሱን አላውቅም፡፡

የወልዲያ መቀሌ የባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ትልቅ ችግር አለበት፡፡ አንደኛው ችግር ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ያለው የባቡር መንገድ በኪሎ ሜትር አራት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከአዋሽ ወልዲያ የተሰራው በአንድ ኪሎ ሜትር አራት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከወልዲያ መቀሌ የሚሰራው ግን በአንድ ኪሎሜትር ሰባት ነጥብ ሶሰት ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ በጣም ውድ ነው፡፡ መንገዱ ስለማይመች፤ ብዙ ዋሻና ድልድይ ስላለው ግንባታውን ውድ አድርጎታል፡፡

ከመጀመሪያው ፕሮጀክቱ ሲቀረፅ አርባ በመቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ቀሪውን 60 በመቶ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ሊያበድር ነበር፤ የቻይና ባንክ ፕሮጀክቱ አዋጪ ስላልሆነ አላበድርም፤ አያዋጣኝም አለ፡፡ ሁሉም ባንኮች አናበድርም ነው ያሉት፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ አምቦ፣ ከአምቦ ፣ ጅማ.፣ በደሌ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አብሮ የተቀመጠ ነው፡፡ ከዚህ አምቦ ያለውን ጨረታው አልወጣም፡፡ ከወልዲ መቀሌ ያለው ዘንድሮ ለቻይና ኩባንያ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር ስራው እንዳይቋረጥ ተከፍሏል፡፡ አሁን ፕሮጀክቱ 55 በመቶ ደርሷል፡፡

በሁለተኛው የእድትና ትራንስፎርሜ እቅድ በትግራይ ውስጥ 23 የመንገድ ፕሮጀክቶች ነው የታቀዱት፡፡ ከዚህ ውስጥ 16ቱ አልቀው ስራ ጀምረዋል፡፡ ሶስቱ እየተገነቡ ሲሆን ቀሪ ሶስቱ በጨረታ ሂደት ላይ ናቸው፡፡ ወደፊትም አቅም በፈቀደ መጠን የትግራይን ህዝብ መስረታዊ ልማት ለማፋጠን የፌዴራል መንግስት አበክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

2 Comments

 1. Good job Dr.Abiy !!
  የትግራይ ህዝብ ባንድ ኣቅጣጫ ብቻ በሚፈስ ፕሮፓጋንዳ ታውሮ መቀጠል ኣይኖርበትም።
  በማስ ሜዲያው የተደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ ለመሆኑ የት ህነግ መሪዎች መንጨርጨር በቂ ምስክር ነው።
  Keep it up !
  የዶክተር ኣብይ ንግ ግር በትግሪኛ ተተርጉሞ በተደጋጋሚ ለትግራይ ህዝብ እንዲቀርብ መደረግ ይኖርበታል።
  Information is power !!

 2. “ዛሬም አረና የሚባል ህጋዊ ድርጅት አለ፡፡ የራሱ የሆነ አስተሳሰብ፤ አመለካካት፣ የራሱ አደረጃጀት ያለው የትግራይን ህዝብ መለወጥ የሚፈልግ ፕሮግራም ያለው ፓርቲ፡፡ ህውሃት አለ፤ የራሱ ሃሳብና ፍልስፍና ያለው፡፡ እንደዚሁም ብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ሆነው የሚታገሉ የትግራይ ተወላጆች አሉ፡፡”

  ችግሩ ማንኛቸውም ከ’Prinzip እና Charisma ጋራ አንዳችም ግንኙነት ስላሌላቸው፣ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን ነገሮች ናቸውና፣ ከያሉበት “ፓርቲያቸው” ዘንዳም ሆነው ጥሬ ለወረወረላቸው ሌላ ግለ ሰብም ሆነ ሃይል ከመሽመድመድ ወድኋላ የማይሉ መሆናቸው ነው!
  ህወሓት እና ፍልስፍና የሚባሉ ነገሮች ደግሞ ባንድ መስመር አብረው ባይመዘገቡ የተሻለም ይሆናል! ፍልስፍና ያለው ሃይል ቢሆን ኖሮ፣ ገና ትግል ከመጀመሩ አለም ለትግራይ ህዝብ የለገሰውን እህል በጎን ሸጦ ወደ ግል ኪሱ ባላስገባ ነበር፣ አንዲት እና ብቸኛዋ የህወሓት በጎ ውጤት ያንን ገና ስልጣን ከመቀበሉ፣ ታሪኩን ወጣት የትግራይ ፖለቲካል አክቲቪስቶን እነ መለስ ተኽለንና ግደይ ገብረዋህድን በመግደል የጀመረውን የተራ ጋኔኖች ጥርቃሞ ደርግን ማባረሩ እንደሆነ ይቀራል፣ በተረፈ ግን የትግራይን ህዝብ ለ45 ዓመታትና ጠቅላላን የኢትዮጵያን ህዝብ ደግሞ ለ30 አመታት እንደ ሆስተጅ ይዞ ከመዝረፍ በስተቀር ሌላ በጎ ነው የሚባል ተግባር ስለሌለው፣ ከማፊዮዚነት በስተቀር ከፍልስፍናም ሆነ ሌላ በጎ Prinzip ጋራ የሚያገናኝ ጉዳይ የለዉም!

  “ከመጀመሪያው ፕሮጀክቱ ሲቀረፅ አርባ በመቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ቀሪውን 60 በመቶ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ሊያበድር ነበር፤ የቻይና ባንክ ፕሮጀክቱ አዋጪ ስላልሆነ አላበድርም፤ አያዋጣኝም አለ፡፡”

  ወያነ በግለሰብ ስምም ሆነ በሆነ ሃይል ስም በእነ ቻይና አካባቢ ከደበቀችው የኢትዮጵያ ንብረት፣ ምናልባትም የስብሓት ቤተሰቦች ወደ አውስትራሊያ አካባቢ በባንክ መልክም ይሁን በፈለገው ሌላ መልኩ ከሚያንቀሳቅስዋቸው የኢትዮጵያ ሃብቶች፣ ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ሃብት ሃብታሞች ከሆኑት እነ የስብሓት ወንድም ልጆች ከወደ ኩዌት አካባቢ፣ ወይንም የኢትዮጵያ ሃብት ተዘርፎ የዓለም ሃብታሞች ከሆኑት እነ አላሙዲዎችስ አካባቢ የተደረገ አስተዋፅኦ የለምን?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.