ኮረና በኢትዮጵያ ከባድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሁሉም ያስብበት – ሰርፀ ደስታ

አንዳንድ የሚወጡ ዜናዎች በበሽታው የተነሳ ትልቅ መደናገጥ እንዳለና የሞቱ ሰዎችን እንኳን ለመቅበር እጅግ አሳዛኝ የሚመስሉ ዜናዎች እወጡ ነው፡፡ ከበፊቱም ከሰጋሁት ነገሮች አንዱ ይሄ ነው፡፡ መጠንቀቅ መልካም ነው፡፡ ሆኖም አላስፈላጊ ፍራቻ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ እጅግ ስለሚደነግጡ የመከላከል አቅማቸው ይወርዳል፡፡ በዚህ የተነሳ መዳን ላይችሉ ይችላለሁ፡፡ አስታማሚዎች ከፍራቻቸው የተነሳ መዳን የሚችልን ሰው ባለመርዳታቸው ምክነያት መዳን የሚችሉትም ይሞታሉ፡፡ ይሄ በኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ የሆነ ችግር የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ እንዳልኩት ነው መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሆኖም አላስፈላጊ ፍራቻ ብዙ ጥፋት ሊያመጣ እንደሚችል ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መረዳት የሚገባቸው ሰዎች በአግባቡ እርዳታ ማግኘት አለባቸው፡፡ የሞቱትንም ለመቅበር እንደበፊት በብዛት ባይወጣም ወዳጅ ዘመዶች ርቀታቸውን ጠብቀው መቅበር የዛን ያህል አደጋ የለውም፡፡ የተያዘ ሁሉ ደግሞ ይሞታልም አልተባለም፡፡ ማንኛውም በሽታ የመግደል እድል ሊኖረው ይችላል፡፡ በምዕራብ አፍሪካዊያኖቹ አገራት ተነስቶ የነበረው ኢቦላ ከያዘ የመግደል አቅሙ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ይሄ ግን 3 በመቶም ነው ተብሎ አይታሰብም፡፡ በእርግጥ የመዛመት አቅሙ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ይሄንን ደግሞ ርቀትን በመጠበቅ የፊት ማስክና እጅ ጓንት በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዘጎች የተያዙባቸው አገራት በሽታውን እጅግ በመፍራት ሳይሆን የሚፈለገውን ጥንቃቄ በማድረግ ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ አሁን እንደውም የበሽታውን ባሕሪ እያወቁት ሲመጡ ዘግተውት የነበረውን ሥራም እየከፈቱ ነው ጥንቃቆዎቹን በማድረግ፡፡ በእኛ አገር አሁን ያለው የፍራቻ ሁኔታ እንደሚሰማው ከሆነ አደጋው ብዙ ነው፡፡

ሌላው ሕዝቡ ለጉንፋን ይጠቀምባቸው የነበሩ የሚያውቃቸውን ሁሉ ቢጠቀም ጥሩ ነው፡፡ በእኛ አገር ሻይ ኮረንቲ የሚባል አለ፡፡ አልኮል የመከላከል አቅምን ይቀንሳል ሆኖም በጥንቃቄ በመጠኑ በሻይ ኮረንቲ መልክ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፡፡  ግን ደጋግሞ መውሰድ የአልኮል መጠንን ከፍ ካረገ የመከላከል አቅምን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ግን መረጃውን ከሌሎች አገራት ቢወሰድ ጥሩ ነው፡፡ በአውሮባ እንዳየንው ጀርመን ከአገራት ሁሉ አነስተኛ ሞት ከተመዘገበባቸው አንዷ ናት፡፡ ጀርመኖር በብርድ ወራት ማለትም ኮረና አይሎ በነበረባቸው ወራቶች የፈላ ወይን የመጠጣታ ባህል አላቸው፡፡ ይሄ ባሕላቸው ረድቷቸው እንደሆነ የእኛም ሻይ ኮረንቲ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ የጀርመን የፈላ ወይን በብርድ ወራቶች የመጠጣት ባህል በኦስትሪያም ያለ መሰለኝ በዛም እንዲሁ አነስተኛ ሞት እናያለን፡፡ ይሄን ሀሳብ የምሰጠው እን ባለሙያ ሆኜ አደለም፡፡ ግን ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ እንድንመለከት እንጂ፡፡  ሌሎች የባሕል መድሀኒቶች ማለት ዝንጅብል፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አሪቲ የመሳሰሉትን ያለአንዳች ንቀት መጠቀም ይጠቅማል፡፡ ለዚህ በሽታ ከአዋቂ ባለሙያዎች ብዙ አንጠብቅ ግን ሁላችንም በራሳችን የምናውን እናድርግ፡፡ ግን ቫይረስ ይገድላል በሚል የሚያቃጥል ነገር ሁሉ መድሀኒት ነው ብሎ መውሰድ አደጋ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የሚታወቁትን የባህል መድሀኒቶች ግን እኔ ቢወሰዱ እላለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጴጥሮስ አንተ አለት ነህ! - አሰፋ በዱሉ

ሌላው የአሜሪካው ፕሬዘደንት የጫወታው ቀያሪ (ጌም ቼንጀር) ያሉትን የወባ መድሀኒት አብዛኞቹ ሚዲያዎች ከፕሬዘዳንቱ ጋር የተቃረኑ መስሏቻ በተለይ በአሜሪካ ብዙ በሽተኞች መድሀኒቱ እያለ ባለመጠቀማቸው ለጉዳት ሳይዳረጉ አልቀሩም፡፡ በትክክል ግን ሳይንሳዊ ምርምሮች በአብዛኞቹ ያለ ማፋለስ የወባ መድሀኒት የሆነው ሀደሮክሲልክሎሮከዊን  ውጤታማ እንደሆነ ያሳያሉ፡፡ በተለይ ከዚንክ ጋር ዜተሮማይሲን መሰለኝ የሚሉት የበለጠ ውጤት ያሳያል፡፡ ለከፍተኛ አደጋ ተቃልጠው የነበሩ በሽተኞች ሳይቀሩ በእነዚህ መድሀኒቶች ለመዳን ችለዋል፡፡ በጀርመን ይሄ መድሀኒት በስፋት ጥቅም ላይ እንደነበር የሚጠቁሙ ሪፖረቶች አሉ፡፡ በሌሎች አገሮችም፡፡ የሀይደሮክሰከሎሮኪዊን እህት የሆነው ክሎሮኪዊን ትንሽ   የጎንዮሽ ጉዳት ስላለው እንጂ እሱም ጥሩ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ የኤች አይቪ መድሀኒትም እንደሚረዳ ይነገርለታል፡፡ ምን አልባት በእኛው አገር የወባው መድሀኒት በስፋት ሊኖር ስለሚችል ከሌለም ከሌለም ከሌሎች አገራት በእርዳታም በመጠየቅ በማስገባት ብዙ ወገኖችን መታደግ እንደሚቻል ይሰማኛል፡፡ እኔ ባለሙያ አደለሁም ሆኖም የሳይንሳዊ ጥናት ሪፖርቶችን አያለሁ፡፡ የሌሎች አገራትንም ተሞክሮ በተወሰነ እከታተላለሁ፡፡ ከማያቸው ሪፖረትቶች ተነስቼ ባለሙያዎች እንዲያስተውሉትና የሚያሳምን ምክነያት ከሆነ እንዲጠቀሙበት ነው፡፡ አመክንዮው ቀላል ነው፡፡ የወባው መድሀኒት የሚቀመመው ኪኒን በመባል ከሚታወቀው የደቡብ አሜሪካ ዛፎች ነው፡፡ ከወባ ውጭ ለብዙ ሌሎች በሽታዎችም ይውላል፡፡ እንደሚባኝ መድሀኒቱ መልቲ ስፔክትረም የሚባለው አይነት ነው፡፡ የእኛዎቹም የባህል መድሀኒቶች እንደዛ ያለ ባሕሪ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ፌጦ ከተገኘ መጠቀሙ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ መታጠኑን ጨምሮ፡፡ ምክነያቱም የትንፋሽ ስለሆን መታጠን ውጤታማ ሊሆን ስለሚችል፡፡ እንግዲህ እጃችን ላይ ያለን ነገር ሁሉ መጠቀም ነው፡፡ ለማስተዋል እንዲረዳ ጥቆማ እየሰጠሁ ነው፡፡ መረጃው ሁሉም ጋር ቢደርስ መልካም ነው፡፡ ነገሮችን እንርዳ እንጂ ማድነቅም መኮነንም አሁን አንችልም፡፡ በቃ ገብተንበታል!

ተጨማሪ ያንብቡ:  አጭር ግልጽ መልዕክት ለክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ - መስፍን አረጋ  

ሌላው አሁንም የመረጃ አሰጣጡ አልተስተካከለም፡፡ ትላንት የሆነ ዌብሳይት የተከፈተ መስሎኝ ነበር፡፡ ዛሬ ተመልሶ እዛው የተለመደው ሰንጠረዥ ውስጥ ገብቷል፡፡ መረጃው ከክልል በዘለቀ ቢያንስ በዞን ደረጃ ያለውን ስርጭት በሚያሳይ መልክ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ የከተሞች በተለይ በርከት ያለ ሕዝብ የሚኖርባቸውን መረጃም ለሕዝብ ቢለቀቅ በጣም ይረዳል፡፡ ታች ደግሞ ወረዳዎች በወረዳቸው ላለው ሕዝብ ለአካባቢ የኤፍ ኤም ሬድዮኖች ቢያሳውቅ ለሕዝቡ ማድረስ ይቻላል፡፡ የጂኦ ሪፍረንሲነግ የሚሰሩት ባለሙያዎች መረጃው ከተገኘ እስከ ወረዳ ያለውን ማሳየት ቢችሉ ጥሩ ነው፡፡ መረጃው በደንብ ካለ ለመከላከልም ይረዳል፡፡ በእኛ የምርመራው አቅም አነስተኛ ስለሚሆን በአካባቢ ባሉ የርቀት ሙቀት መለኪያ ኢንፍራ ሬድ ቴርሞ ሜትር በመጠቀም ሙቀት የጨመሩ ወይም ሌላ ምልክት ያሳዩ በሚል ተጨማሪ የመረጃ ደረጃ ቢኖር እላለሁ፡፡ ምርመራ እስከሚደርስ ሕዝቡን ከሚታዩ ምልክቶች አንጻር ጥንቃቄ እንዲያረግ ስለሚረዳው፡፡ ስለዚህ የተረጋገጠ የተያዙና ምልክት ያሳዩ በሚል በሁለት መልክ መረጃው ቢቀርብ ይረዳል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ሆኖም ምልክት የሚታይባቸውን መረጃ ጥንቃቄ ሊኖረው ይገባል በአልተረጋገጠ ነገር ሰዎች እንዳይደነግጡ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን  ይታደግ! ለዓለሙ ሁሉ ምህረቱን ይላክ! አሜን!

– ሰርፀ ደስታ

1 Comment

  1. IN JUNE 2020 ETHIOPIA’S HUMANITARIAN SUPPORT REQUIREMENT REVISED TO US$ 1.65 BILLION USD DOLLARS TARGETING 16 MILLUON PEOPLE, MORE THAN DOUBLE THE APPEAL MADE IN JANUARY 2020. SO FAR ONLY US$284 MILLION USD DOLLARS IS RAISED .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share