ሰላም ሰላም አየር መንገዳችን፤ አቤት! ስለ አየር መንገዳችን – ሶሎሞን ደረጄ ከአዲስ አበባ

Airline

ዳራ፡ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከሰባ በላይ አመታትን በጥንካሬ የዘለቀና ብሄራዊ ኩራት የሆነ አለማቀፋዊ የህዝብ ወ መንግስት ድርጂት ነዉ፡፡ ዘመኑን እየዋጀ ስለደረሰበት ስኬት ሁሌም የሚያወራለለት ይህ ድርጂት የጥንካሬዉና ዘመን ተሸጋሪነት ሚስጥሩ አንድም በጠንካራ ሳይንሳዊ መሰረትና አለም አቀፍ ተቋማዊ አደረጃጄት ላይ መገንባቱ ሲሆን ሌላዉ ደግሞ ድርጂቱንና የድርጂቱን ስራ በተቀጣሪነት ሳይሆን በባለቤነትና ብሄራዊ ኃላፊነት የሰሩትና የመሩት ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች መሆናቸዉ ሁሌም ልብ የሚባል ጉዳይ ነዉ፡፡

አየር መንገዳችን እንደ ተቋማዊ አብነት

አየር መንገዱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ስኬታማ ሆኖ መዝለቅ በመቻሉ ዝናዉ ከሀገር ዉሥጥ እስከ ባህር ማዶ በመናኘት የተቋም ተምሳሌት ለመሆን በቅቷል፡፡ አሁን ላይ በዘመናዊ የልማት ዕሳቤወች(Modern development Thinking) ዉስጥ የማህበረብም ሆነ የሀገር ዕድገት ቅድመ ሁኔታ እየሆነ የመጣዉ የተቋማት (Institutions) መኖር/አለመኖር ነዉ የሚል ሲሆን ተቋም ማለትም የተወሰነ አላማና ግብ ለማካሄድ በጊዜ፣ ቦታ፣ ካፒታል፣ መመሪያወችና እነዚህን አቀናጂቶ በሚያስፈጽም የሰዉ ሀይል የሚመሰረት ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ ወይንም ኢኮኖሚያዊ ድርጅት ነዉ፡፡ ታዋቂወቹ የ Why Nations Fail ፀሃፍት Daren Acemeglu እና James A. Robinson አለማችን ከእግር እስከ እራስ በዳሰሱበት የሀገራት እድገትና ብልፅግና ምልከታ የበለጸጉት ሀገራት ቁልፍ የእድገታቸዉ ሚስጥር ለህዝብ ጥቅም የተቋቋሙትና በህግና ደንብ ለህዝብ ፍላጎት የሚዘወሩት የፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ተቋሞቻቸዉ እንደሆኑ ነዉ፡፡ በተቋራኒዉ ታዳጊ ሀገሮች ደግሞ እነዚህ ተቋማት በዞሩባቸዉ አንዳልዞሩና የድህነታቸዉ ዋነኛ ምክንያትም ሆነዉ እንደቀጠሉ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያን፤ ኖጋሊስ አሪዞናና ኖጋሊስ ሜክሲኮን በማነጻፀር ያስረዳሉ፡፡ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ እስከ 1945 እንዲሁም ኖጋሊስ አሪዞናና ኖጋሊስ ሜክሲኮ እስከ 1853 ድረስ እያንዳንዳቸዉ አንድ ቋንቋ ተናጋሪና አንድ ህዝብ የነበሩ ሀገራት ቢሆኑም በጥቂት አመታት ዉስጥ በተፈጠሩ የተቋማዊ የአስተዳደር ለዉጦች ምክንያት ሰሜን ኮሪያና ኖጋሊስ ሜክሲኮ ድሮ በነበሩበት ድህነት ሲቀጥሉ ደቡብ ኮሪያና ኖጎሌዝ አሪዞና ግን ከበለጸጉት ሀገራት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ በጥቅሉ በተቋማዊ አስተዳደር የሚመራ ሀገርም ይሁን ድርጂት የፖለቲካም ይሁን የአመራር ለዉጥ ሳያሰጋዉና ሳያናጋዉ የእለት ተዕለት ስራዉን በመከወን አላማዉን ይዞ የሚቀትል ለመሆኑ ቤልጄምና ጃፓንን እንደአብነት መዉሰድ በቂ ነዉ፡፡ ሁለቱም ሀገራት ባለፉት 15 አመታት ዉስጥ መሪዎቻቸዉና ገዢ ፓርቲወቻቸዉ ከ5 ጊዜ በላይ ተቀያይረዋል፡፡ ምስጋና ለጠንካራና ህዘባዊ ተቋሞቻቸዉ ይግባና እዚህ ግባ የሚባል ችግር ሳያደናቅፋቸዉ የአመራርና ፓርቲ ቀዉሱን ታሻግረዋል፡፡

ወደኛዋ ኢትዮጲያ ስንመለስ ዘመናዊ ተቋማት ግንባት በዉል የተጀመሩት በዓፄ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት እንደነበረና ኢትዮጲያ አየር ምንገድም አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲወሳ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን በተመሳሳይ ዘመን የተፈጠሩት ሌሎች እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አንበሳ የከተማ አዉቶቡስ፣ መብራት ሃይል የመሳሰሉት ተቋማት መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር ከፍና ዝቅ ሲሉ አሊያም ሲኮሰምኑ አየር መንገዱ ግን የከፋ የሚባለዉን አምባ ገነናዊ የደርግ ስርአት እንኳን መሻገር መቻሉ ተቋማዊ ጥንካሬዉን ከማስመሰከር ባለፈ በአፍሪካና በመላዉ አለም ተምሳሌት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ይህም በመሆኑ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጲያ አየር መንገድ እንደ ቤተአምልኮት የተከበረና የታፈረ፣ በተቋሙ ዉስጥ መስራት ደግሞ የተለየ ክብርና ሞገስ የሚያሰጥ አድርጎና መልካም ገጽታን አጎናፅፎ አቆይቶታል፡፡

አየር መንገዳችን! ሰላም ነዉን?

ባለፉት ሁለትና ሶስት ሳምንታት ከማህበራዊ ሚዲያዉ እስከ መደበኛ የቴሌቪዢን ጣቢያወች አልፎም ታማኝና ሚዛናዊ በሚባሉ የህትመት ሚዲያወች የአየር መንገዱን አስተዳደር የተመለከቱ በርከት ያለ ጩኸቶች ሲሰሙ ሰንብተዋል፡፡ አሁን አሁን ጩኸቱ ከመበርከቱ የተነሳ ከአባይ ግድብና ኮረሮና ቀጥሎ አነጋጋሪም አስጨናቂም ጉዳይ በመሆን የድርጂቱን ሰራተኛና አስተዳደር እንዲሁም የሚዲያ ማህበረሰቡንና ስለጉዳዩ ያገባኛል ባይ ዜጎችን ከሁለት ጎራ ከፍሎ እያራኮተ ይገኛል፡፡

የመጀመሪያዉ ጎራ የአየር መንገዱ አስተዳደር አምባገነንና ህገወጥ አሰራርን በመዘርጋቱ የአየር መንገዱና የሰራተኞች ህልዉና አደጋ ላይ ወድቋል እናም በጊዜ ሊስተካከል ይገባዋል የሚል ሲሆን በዋነኛነት ከድርጂቱ አስተዳደር ጋር ይሰሩ ከነበሩ ግለሰብና ከሰራተኛ ማህበሩ የሚነሱ ክሶች ናቸዉ፡፡ ክሶቹ በአመዛኙ በማስረጃ የቀረቡ ሲሆን እንደ ማሳያም የመንገደኞችን ትኬት ከዕለታዊ የባንክ ምንዛሪ ይልቅ በጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ መሸጥና በጀርመን አየር ማረፊያ የተከወኑ ሌሎች እጂግ በጣም አደገኛና ህገወጥ ድርጊቶች ድርጅቱን ለተቀናቃኞቹ ብሎም ለአለም አቀፉ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አሳልፎ የሚያሰጠዉና እስካሁን ያገኘዉን ዝና ባንድ ሌሊት መቀመቅ የሚከተዉ ለመሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ከዚህም ባሻገር በለፈዉ ሳምንት በናሁ ቴሌቪዢን የተላለፈዉ የዉለታ ቢስ እጆች ዘጋቢ ፊልም መጀመሪያ ክፍል ከእድሜ ጠገብ እስከ ወጣት አብራሪወችና ሌሎች ሰራተኞች የሰጡት የብልሹ አሰራር ምስክርነት አስደንጋጭም አሳሳቢም ነዉ፡፡

ሁለተኛዉ ጎራ ደግሞ የአየር መንገዱ ስም ፈፅሞ ሊነሳ አይገባዉም ዉንጀላወቹ በሙሉ የድርጅቱን መልካም ስምና ዝና የሚያጎድፉ የሀሰት ዉንጀላወች ናቸዉና ሊደመጡ አይገባቸዉም የሚል አንድምታ ያለዉ ግን ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ ያልቀረበባቸዉና በዋነኝነት ከአስተዳደሩ የሚደመጡ መከላከያወች ናቸዉ፡፡ በርግጥ የድርጅቱ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃንን ስፖንሰር እያደረገ በአየር መንገዱ ስም የአስተዳደሩን ግለሰባዊ ገፅታ ግንባታ ስራዬ ብሎ ከተያዘዉ ዉሎ በማደሩ ገንቢ ትችቶችን እንኳን ለመስማት ፈቃደኛ ካለመሆኑ በላይ እዉነቱን ለህዝብ ለማድረስ መረጃ ለሚጠይቅ ገለልተኛ ሚዲያ ቃለ መጠይቅም ይሁን ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ላለመሆኑን ተደጋጋሚ ክሶች ቀርበዉበታል፡፡ የሆነ ሆኖ አየር መንገዱ ዉስጣዊ ሰላም ርቆት መናጥ ከጀመረ ሰነባበተ፡፡ ሰላም ሰላም ለዉዱ አየር መንገዳችን፣ የአይን ብሌናችን፣ መዉጫ መግቢያ በራችን፣ ወደባችን! ሰላም ለአየር መንገዳችን! እንዲሆን በመመኘት ለዚህ ያበቃዉ መነሾ ምንድን ሊሆን ይችላል የሚለዉን በመረጃ ማቅረብና የመፍትሄ ሃሳብ መጠቆም ስያፈልጋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለእውነት እንዳንታገል አዚም የሆነብን ምንድር ነው? - ዘጠኙ ምክንያቶችን እንሆ -(በይበልጣል ጋሹ)

የኢትዮጲያ አየር መንገድ፣ አስተዳደሩና ሰራተኞቹ

ድሮ ድሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲባል ሰራተኞቹ፣ አስተዳደሩና በመጨረሻም እነዚህ ሁለቱ እጅና ጓንት ሆነዉ አገልግሎት የሚያቀርቡበት አንድ ድርጅት እንደሆኑ ይታሰብ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም በሰራተኛዉና በአስተዳደሩ መካከል ጉልህ ልዩነቶች እየታዩ መጥተዋል፡፡ አስተዳደሩም ሆነ ሰራተኛዉ ድርጂቱን በፍጹም ስለመዉደዳቸዉ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ድርጅቱ፣ አስተዳደሩና ሰራተኛዉ በእርግጥ ሶስት የተለያዩ አካላት እንደሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ነገር ግን አንድም ሶስትም ሆነዉ የሚሰናሰሉበት ተቀዳሚ ዓላማቸዉ አየር መንገዱን ስኬታማና ተወዳዳሪ የአለም አቀፍ ድርጅት አድርጎ ማስቀጠል ሲሆን ይህ እንዲሆን የሚያስቺሉት ደግሞ በህዝብና በመንግስት የታወጁ ተቋማዊ መርሆወች፣ ህግና ፖሊሲወች ከፍ ሲል ደግሞ አለም አቀፍ ስምምነቶች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ከሰራተኛ መብትና ጤንነት እስከ የበረራ ደህንነትና የንግድ ዉድድር ድረስ የሚያትቱ ዝርዝር ህግጋት ሳይሸራረፉና ሳይድበሰበሱ በሚተገበሩበት ጊዜ ዘላቂና ስኬታማ ተቋም እዉን ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን አስተዳደሩ አሊያም ግለሰቦችና ጄሌወቻቸዉ እነዚህን ህጎችና ፖሊሲወች እንደመሰላቸዉና እንዳሻቸዉ አንዳንዴም ለግል ጥቅማቸዉ በሚቀያይሩበት ጊዜ አሁን አየር መንገዳችን ዉስጥ እንደተነሳዉ አይነት ጎታችና አክሳሪ ሁከቶች ይፈጠራሉ፡፡

 1. አየር መንገዱ እንደ ፈላጭ ቆራጭ ራስ ገዝ አስተዳደር

“አየር መንገዱ ባንድ ሀገር ዉስጥ ራሱን የቻለ ሌላ መንግስት ነዉ” የሚለዉን ሃሳብ የሰማሁት በዉለታ ቢስ እጆች ዶክመንታሪ ዉስጥ ስለ አየር መንገዱ አስተዳደር ብልሹ አሰራር ምስክርነት ሲሰጡ ከነበሩት ከካፒቴን የሽዋስ ፋንታሁን ነዉ፡፡ ሃሳቡ አደናጋሪ ከመሆኑ አንጻር እዉነትነቱ እስከምን ድረስ ነዉ ለሚለዉ መልስ ለማፈላለግ በድርጅቱ የሚሰሩ ሰወችን ማነጋገርና መረጃ ማገላበጥን አስፈልጎኛል፡፡ አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ንብረት እንደመሆኑ በሀገሪቱ ህግና ደንቦች ሊተዳደር እንደሚገባዉ እሙን ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በአስተዳደሩ የዕለት ተዕለት ስራ ጣልቃ የማይገባዉ የንግድ ስራ በመሆኑና አንጻራዊ ነጻነት እንዲሚያስፈልገዉ በመረዳት እንጂ ከህግ በላይ ይሁን ወይንም እንደፈለገ ያድርግ የሚል የፈላጭ ቆራጭ ስልጣን አልሰጡም፡፡ ነገር ግን የአየር መንገዱ አስተዳደር የሀገሪቱን ህግ ጥሶና የራሱን ፖሊሲ አርቅቆ እያስተገበረ ለመሆኑ ምስክርነቱ በአየር መንገዱ የሰዉ ሀይል አስተዳደር መመሪያና በሲቪል አቪየሽን መመሪያ መካከል ያለዉ ተቃርኖ ነዉ፡፡ ሲቪል አቪየሽን 2013 ባወጣዉ ህግ መሰረት ማንኛዉም ህጋዊ የሥልጠና ተቋም ትምህርታቸዉን በሚገባ ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የትምህርት ማስረጃ (የስልጠና የምስክር ወረቀት) መስጠት አለበት ሲል፤

3.3.4.3 GRADUATION CERTIFICATE

 • An ATO shall issue a graduation certificate to each student who completes its approved course of training.
 • The graduation certificate must be issued

በተቃራኒዉ የአየር መንገዱ የሰዉ ሀይል አስተዳደር መመሪያ (እንደ ሲቪል አቬሽኑ ህግ በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ ማግኘት ባልቺልም) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉስጥ የሚደረጉ ስልጠናወችና ተያያዥ የትምህርት ማስረጃወች ለአየር መንገዱ አገልግሎት ብቻ ይዉላል የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፤

7.11.1. Diplomas, Certificates and other training completion documents are intended to serve within Ethiopian. Diplomas and/or Certificates shall not be issued nor be transferred to employees or their proxy under any circumstances.

ይህ ማለት ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለስልጠና የሚመጣ ዜጋ እድሜ ዘመኑን አንድ ድርጂትን ብቻ ሲያገለግል ይኑር አለበለዚያ ስልጠናዉም ልምዱም ዋጋ ቢስ ነዉ የሚል የባሪያ አሳዳሪዉ ዘመን ህግ አንድምታ ያለዉ ነዉ፡፡ በርግጥ አስተዳደሩ ይህንን መመሪያ ኢንዲያወጣ ያስገደደዉ ሁኔታ እንደሚኖር ብረዳም መፍትሄዉ ግን በሀገሪቱ ህግ መሰረትና ለሰራተኛዉ መተማመኛ በሚሰጥ መልካም አስተዳደር ሊሆን ይገባዉ ነበር እንጂ የሰዉ ትምህርት መረጃን እንደ ፍልሰት መቆጣጠሪያ መጠቀም አግባብ አይደለም ፡፡

 1. የሰራተኛ ማህበርና የአስተዳደሩ ህገወጥ ጣልቃ ገብነት

በኢፌዲሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 31 መሰረት ማንኛዉም ሰዉ ለማንኛዉም ዓላማ በማህበር የመደራጄት መብት ያለዉ መሆኑን ሲገልጽ አንቀጽ 42 በበኩሉ የፋብሪካና የአገልግሎት ሰራቶኞች፣ ገበሬወች፣… የስራና የኢኮኖሚ ሁኔታወችን ለማሻሻል በማህበር የመደራጄት መብት አላቸዉ ይላል፡፡ ከዚህ አካያ በአየር መንገዱ ዉስጥ ለረጂም ዓመታት አለ ሲባል የኖረ የሰራቶኞች ማህበር በ2009ዓም አየር መንገዱና ሲቪል አቬሽን ሲቀላቀሉ ፈርሶ እንደገና እነዲቋቋም አስፈልጎታል፡፡ ነገር ግን ይህ አዲስ የሰራተኞች ማህበር በነጻነት እንዳይደራጅ ያሴረና የበረታ የአየር መንገዱ አስተዳደርን ጫና በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደራሽንና ሀገራዊ ለዉጡን በሚመራዉ መንግስት አጋዥነት ተሻግሮ የኢትዮጲ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር በሚል 2012 መጀመሪያ ላይ ለመመስረቱ የማህበሩ አመራሮች ለተለያዩ ሚዲያወች የሰጡት ቃለ ምልልስ ያስረዳል፡፡

ይህ በሰራተኛዉ ድምጽ የተመሰረተን ማህበር ህልዉና መቀበል ያልተዋጠለት አስተዳደሩ ብዙም ሳይቆይ ለራሱ ታማኝ ናቸዉ ያላቸዉን ጥቂት ሰራተኞች ሰብስቦ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ የሰራተኞች ማህበር የሚል ሌላ ማህበር በአንድ ቀን ማስታወቂያና የሚመለከታቸዉ የመንግስትም ይሁን የማህበራት ተወካዮች ባልተገኙበት ለመመስረቱ ሰራተኞች ያስረዳሉ፡፡ በርግጥ ይህ በአስተtዳዳሩ አቀናባሪነት የተመሰረተዉ ማህበር የአስተዳደሩ ሙሉ ድጋፍ እንዳለዉ የሚያመላክተዉ ኢሰማኮ በተገኘበተት የተመሰረተዉን ማህበር በጊቢ ዉስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከልክሎ ለዚህኛዉ ግን ቢሮና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶቹን ወዲያዉኑ ማቅረቡና እዉቅና መስጠቱ ነዉ፡፡ የአስተደደሩ ህገወጥነት ተጠናክሮ ቀጥሎና እጁን አሰረዝሞ ሰራተኞች ከደመወዛቸዉ የሚቆረጠዉ የአባልነት መዋጮ በድምፃቸዉ ለመሰረቱት ማህበር ገቢ እንዲደረግ በማመልከቻ ቢጠይቁም የአየር መንገዱ ፋይናንስ ግን ያልተገባ ስልጣን ተጠቅሞ ከከለከለ ወዲያ በተቋራኒዉ አስተዳደሩ እየመራ ላዋቀረዉና ቀዳማዊ ለሚባለዉ ማህበር ገቢ እያደረገ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሙማ ማኔፌስቶ! አዲስ አበባ ኬኛ! የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት!የዘገነም ያልዘገነም እኩል አዘነ! (ክፍል ሦስት) - ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

አስተዳደሩ ከዚህ ይባስ ብሎ ይፋዊ እዉቅና የምሰጠዉ 50+1 አባላት ላለዉ ቀዳማዊ የሰራተኞች ማህበር ነዉ በማለት የዝና ተጽዕኖዉን ተጠቅሞ የሰራቶኞችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሪዉን በማሳሳት በ59 ሰወች ተመሰረተ ለሚባለዉ ማህበር የእዉቅና ሰርቲፊኬት እስከማሰጠት የሄደበት ርቀት በርግጥ የአየር መንገዱ አስተዳደር ራስ ገዝና ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ለመክረሙ ከዚህ በላይ ማስረጃ አያስፈልገዉም ያስብላል፡፡ ይህንን ተከትሎ የአየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር የ50+1 ሰርቲፊኬቱ የሚገባዉ አብዛኛዉ ሰራተኛ ለተወከለበትና ለዚህም የሚሆን ተጨባጭ ማስረጃ ለቀረበለት የኛ ማህበር ሆኖ ሳለ ለምን ለቀዳማዊ ተሰጠ የሚል ህጋዊ ጥያቄ ሲነሳ የሚኒስትር መስሪያቤቱ የሰጠዉ መልስ(ቁ.አ9/አ/81/34) ሳላዉቅ በስህተት አይነት አንድምታ ያለዉና ቀዳማዊ እሰከ ታህሳስ 7፣ 2012 ድረስ የሚለዉን ያህል ሰራተኛ ድጋፍ ያለዉ ለመሆኑ ቅጽ አስሞልቶ እንዲያመጣ የሚጠይቅ ነበር፡፡ ቀዳማዊም ይህንን ሳይከዉን የጊዜ ገደቡ አላፏል፤ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትሪም ጉዳዩን ተከታትሎ ከ5500 ባላይ ቅጽ አስሞልቶ ላቀረበዉ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር እዉቅናዉን አልሰጠም፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የጉዳዩ ባለቤትና ዉሳኔ ሰጪ ሆኖ ሳለ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሩቅ ተመልካች ሆኖ መቆሙ ፍትህ ሆይ ሀገርሽ ወዴት ነዉ! አያስብልም ትላላችሁ?

 1. ሰሚ ያጣ ጩኸትና መስዋዕትነቱ

በአየር መንገዱ አስተዳደር ያልተገባ ጣልቃ ገብነትና አምባገነናዊ አስተዳደር ሰላሙ እየተናጠ ያለዉ የኢትዮጲያ አየር መንገድ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጲያ ከታወጀበት የየካቲት አጋማሽ አንስቶ አስተዳደራዊ ክንዱን በማበርታትና ወረርሽኙን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበሩን አመራሮች ሰበብና ምክንያት ፈጥሮ የማባረርና ከስራ የማገድ ህገወጥ ተግባርን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ባጠቃላይ ባለፉት ሶስት ወራት ዉስጥ ሰባት የማህበሩን አመራርና አባላት ያባረረና ከስራ ያገደ ሲሆን ይህ ጹሁፍ በሚሰናዳበት ሳምንትም አብዛኛዉ የማህበሩ መማክርት አባላትና አስፈጻሚወች የአየር መንገዱ አስተዳደር ቢሮ ድረስ እየተጠሩ የማስፈራሪያና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምክር እንደተለገሰላቸዉና ይህንን ለማይሰሙ ግን እንደ ቀደሙት የማህበሩ መሪወች ሁሉ የመባረር ትኬቱ እንደሚቆረጥለቸዉ የሚገልፅ ማስፈራሪያ ሲሰጣቸዉ እንደሰነበተ ተነግሯል፡፡ በተጨመሪም በወረርሽኙ ምክንያት እረፍት ያስወጣቸዉን በሽወች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በስልክ እየጠራ ሰሞኑን የተላለፈዉ ዶክመንታሪ ዉሸትና መታመን የሌለበት እንደሆነ ሲሰብኩም አእንደነበር መረጃወች ይጠቁማሉ ፡፡ አስተዳደሩ እንዲህ አይነት ግብታዊ ተግባራትን ለመፈጸሙ ተጠያቂ የሚያደርገዉና በጹሁፍ የሚያቀርበዉ ሰበብ ሰራተኛ ማህበሩ የአየር መንገዱን ስም በሚዲያ እያጠፋ ነዉ፤ ይህም አፍራሽ ነዉ የሚል ነዉ፡፡ በርግጥ ማንም ኢትዮጵዊ ስለሚወደዉ አየር መንገድ አንዳች ሃሜትም ይሁን ክፉ ነገር መስማት አይፈልግም፡፡ ይህ ማለት ግን የአየር መንገዱ አስተዳደር ብልሹ አሰራርና አየር መንገዱ አንድ ናቸዉ ማለት ሊሆን አይችልም፡፡ ከህግ በላይ የኖረዉና ያለዉ አስተዳደሩ ላጠፋዉ አየር መንገዱ የሚጠየቅበት ምን የሚሉት የአይጥ በበላ ዳዋ ተመታ አመክንዮ ነዉ?

የአየር መንገዱ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሳያቸዉ እኔዉ አቡክቼ እኔዉ ልጋግረዉ እናንተ አጨብጭቡልኝ አመለካከት ህልዉናዉን የሚፈታተን ነዉ፡፡ ድርጂቱ እዚህ የደረሰዉ ባለፉት ብዙ አስርት አመታት በተከወኑ ተቋማዊ ግንባታና ስርአት፣ መልካም አስተዳደርና የህዝብ ታማኝነት እንጂ ትላንት በመጣ የጥቂት ግለሰቦች ሩጫ አይደለም፡፡ በመሆኑም የሰራተኞች ጩኸት ለምን ተበሎ በጊዜ መደመጥና አፋጣኝ ሀገራዊ መፍትሄ ሊበጂለት ሲገባ በጆሮ ዳባ ልበስ የአለም አቀፍ ሰራተኞች ኮንፌደሬሽን ሁለት ደብዳቤ እስከሚጽፍና የሀገራችንን ህገ መንግስት እንድናከብር እስኪጠይቀን መጠበቁ እንደ ኢትዮጵዊ ሆኖ ለሚመለከተዉ በእጂጉ ያሳዝናል፡፡

በእርግጥ የአስተዳደሩን ክብር ለመጠበቅ ተብሎ ዝም መባሉ ብዙ ዋጋ እያስከፈለ ለመሆኑ ባለፉት አምስት አመታት ብቻ እያሻቀበ ስለመጣዉ የሰራተኛ ፍልሰትና እያሽቆለቆለ ስለሚገኘዉ የሰራተኞች የባለቤትነት ስሜትና የስራ ተነሳሽነት አያሌ ማስረጃወችን መንግስት ከድርጅቱ የሰዉሃይል አስተዳደር ማግኘት ይችላል(ማስረጃ ከጠፋም ከሰራተኞች አንደበትና ማስረጃ ይገኛል)፡፡ እናም ሰሚ ያጣዉ ጩኸት ከሰራተኞች መብት በላይ ለአየር መንገዱ ህልዉና ወሳኚና ታሪካዊ ድምጽ በመሆኑና ካፒቴን እግዜሩ እንዳለዉ አየር መንገዱ ጸጉራም ዉሻ ሆኖ አለ ስንለዉ እንዳይሞት እየተበራከተ የመጣዉን ጩኸት አቤት ብሎ በመስማት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ የይሆናል፡፡

 1. ከኔ ወዲያ ላሳር

በስራ ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስተዳደር ድርጅቱን ሲጔዝ ከቆየበት አዝጋሚ ዕድገት አሻግሬ የፈጣን ዕድገትና ስኬት ባለቤት አድርጌዋለሁ የሚል ተደጋጋሚ የሚዲያ መግለጫ ሲሰጥ አብዛኛወቻችን እሰየዉ ብለን አጨብጭበናል፣ አመስግነናል፡፡ ድርጂቱ እንደትላንትናዉ ሁሉ በስኬት ጉዞ ለመሄዱ እንዲያዉም ተቀናቃኝ አየር መንገዶችን ማስከንዳቱ ይበልጥ እንድናከብረዉና እንድንተባበረዉም አድርጎን ኖሯል፡፡ በተጨማሪም የአየር መንገዱ የስራ ዕድል አቅሙ ላላቸዉ ሁሉም ዜጎች እንዲዳረስ በየክልል ጣቢያዉ ማስታወቂ ማዉጣቱና አንጻራዊም ቢሆን ከአድልኦ ነጻ በሆነ ምልመላ ስልጠናና ቅጥር መፈጸም መጀመሩ ሌላኛዉ ጠንካራ ጎኑ ሆኖ ሲነሳለት ቆይታል፡፡ ሆኖም ግን ጠንካራ ጎኖችን አባዝቶና አስፍቶ መቀጠል፣ ደካማ ጎኖችን ደግሞ ማስተካከል ሲገባ አንድ ሰሞን የተገኘን እውቅና ተፈናጦ አኔን ብቻ ስሙኝ፣ ከኔ ወዲያ ላሳር አይነት አታካች መግለጫወችን ማበነብነብ ድርጂቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የሌለዉ እስኪመስል ድረስ ከሬዲዮ እስከ ቴሌቪዝን መስኮት በየሳምንቱ ሊባል በሚችል መልኩ ግለሰቦች ብቅ እያሉ ስለስኬታቸዉና ስለሽልማታቸዉ የሚያወሩት ነገር አድማጭ ተመልካችን ማሰልቼት ጀምራል፡፡ የበዙት የሀገሪቱ ሚዲያወችም በበሉበት የሚጮሁ በመሆናቸዉ ኑ በተባሉ ቁጥር ሄደዉና የተለፈፈላቸዉን ተቀብለዉ ከማስተጋባት ዉጭ እንዴት? መቼ? ለምን? ማን? የመሳሰሉ መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ጥያቄን አይጠይቁም፣ ዘገባዉን ሙሉ ለማድረግ ባለድርሻ አካላትን አያካትቱምም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በፈረንጅ ድጋፍ ሾልኮ የወጣውና ለአደባባይ የተሰጣው የቅዱስነታቸው ገመና - መርሓጽድቅ መኮንን አባይነህ

ይህ የራስ አምልኮ የሚመስል የተቀናበረ የሚዲያ ዘመቻ አንድም በከሰመዉ ኢህአዴግ ጥላ ስር የተዘረጋ ስዉር መረብ ዉጤት ነዉ አሊያም የረቀቀ የድርጂቱን ሀብት የሚያባክን፣ በማስታወቂያ በጀት ሽፋንም ሚዲያወችን የማስጮሂያና ማፈኛ መዘዉር ነዉ፡፡ አለበለዚያም የሁለቱ ጥምረት ነዉ፡፡ ይህም በመሆኑም አሁን አሁን አየር መንገዱንና ስራ አስፈጻሚዉን ለይቶ መለየት የማይቻልበት የግለሰብ የገጽታ ግንባታ የተፈጠረ ሲሆን ይህ አሳሳች አመለካከት ከተመልካቾች አልፎ ራሳቸዉን ስራ አስፈጻሚዉን በማነሁለል በዋልታ ቴሌቪዝን ከቀድሞ ስራ አስፈጻሚ አቶ ግርማ ዋቄ ጋር ቀርበዉ ለማን ይተካወታል? ጥያቄ የሰጡትን የፌዝ ፈገግታና ሳቅ ልብ ማለት በቂ ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ ተተኪ መሪን የማፍራት የቤት ስራዉን ያልሰራ፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አመራር ለአየር መንገዱ ይገባልን??

ያም ሆነ ይህ 2010 ላይ የመጣዉን ሀገራዊ ለዉጥ ተከትሎ የመናገርና የመጻፍ ነጻነት ሲረጋገጥ የድርጂቱ አስተዳደርና አመራሩ በመገናኛ ብዙሃን ሲባል እንደነበረዉ አልባብ አልባብ ብቻ የሚሸት ላይሆን እንደሚችል እንዲያዉም ከፍተኛ ሙስናና የመብት ጥሰት ይፈጸምበት የነበረ ደሴት ሆኖ ለመቆየቱ የሚጠቁሙ አንዳንድ ዘገባወች ብቅ ማለት ቢጀምሩም በብርሃን ፍጥነት ዝም እንዲሉ ተደርገዋል፡፡ ነገሩ ሽልም ከሆነ ይገፋል ነዉና የተቋሙና የሰራተኛዉ ህልዉና

ያሳሰባቸዉ ሀገር ወዳድ የመንግስትና ድርጂቱ ሰራተኞች ተሰባስበዉና በስራ ዋስትናቸዉ ላይ የሚደርሰዉን አደጋ ተጋፍጠዉ መጮህ በመጀመራቸዉ የአየር መንገዱ አስተዳደር ህፀፅ በጥቂቱም ቢሆን ለህዝብ እይታ ዉሏል፡፡ እዚህ ላይ አቶ ሳሙዔል የተሻወርቅ የሚባሉት ኢትዮጲዊ በተከታታይ እቀረቡት ያለዉን ስር የሰደደ የአስተዳደሩን ብልሺት ስንደምርበት አየር መንገዱ የደረሰበትን ተቋማዊ ንቅዘት ቁልጭ አድረጎ ያስመለክተናል፡፡

በመሆኑም

በመግቢዉ ላይ በስፋት እንደተመለከተዉ አየር መንገዱ ለባህር በር አልባ ሀገራችን ወደብ የሆነ የህዝብ አለኝታና የስኬታማ ተቋም(ድርጂት) ምሳሌ ሆኖ መዝለቁ ቢያስደስተንም አሁን እየተነሳበት ያለዉ ብልሹ አሰራር አራሱን እንዳቆረቁዘዉ ቆም ብሎ አቤት! ማለት ያባት ነዉ፡፡ ድርጂቱ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና፣ ፖለቲካዊ ትሩፋቶቹ መተከኪያ የማይገኝላቸዉ ሆኖ ሳለና ተቋማዊ አብነቱ ተቀምሮና ሰፍቶ እነዲሁም ሌሎች አምሳያ ድርጂቶች አነቃንቆ ከተዘፈቅንበት የድህነት አረንቋ መዉጣት ሲገባን እሱኑ ራሱን እንዲህ እስከሚንገዳገድ መመልከት ዉሃ ሲወስድ እሳሳቀ እንዳይሆንብን፡፡ በተለይ በአሁኑ ጩኸቱ በበረታበትና የአስተዳደሩ ብልሹ አሰራረር ተጨባጭ ማስረጃ ተደግፎ ይፋ በወጣበት ወቅት አንድ ለናቱ አየር መንገዳቸን ከናካቴዉ ለጥቂት ግለሰቦች አደራ በመስጠት እጂ አጣጥፎ መቀመጥ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ አይነቱን ኪሳራ እንዳያመጣብን ከተወጋነዉ ማደንዘዣ ደፍረን መነሳት ይኖርብናል፡፡ በዘላቂነትም ድርጂቱ እንደ አለም አቀፍ ተቋሞች ሁሉ የሚመራበትን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ይፋዊ አሰራር በጊዜ ማበጄyት ለነገ የማይባል የህዝብና የታሪክ አደራ ነዉ፡፡ ከዚህም ባሻገር ወደአስተዳደሩ

 • የሚዘልቁ ሰወች በትዉዉቅ፣ ዝምድናና ፖለቲካዊ ታማኝነት ሳይሆን ለስራዉ በሚመጥኑ የክህሎት፣ እዉቀትና ባህሪያዊ መስፈርቶች እንዲሁም የተጠያቂነት ሃላፊነቶች ሊሆን ይገባዋል፡፡ በተለይም የቦርድ አባላት አመራረጥና የስራ አስፈጻሚዉ ምልመላ መስፈርቶች ካሉ ለህዝብ ይፋ ይደረጉ ካለሆነ ይዘጋጁ፡፡

በተጨማሪም መረጃና ጋዜጣዊ መግለጫ ለሚመለከታቸዉ መገናኛ ብዙሃን ያለአድልኦና ወገንተኝነት መስጠት ሲገባ አስተዳደሩ መደበኛ የሚባሉትን መገናኛ ብዙሃን ተቆጣጥሮ የአንድ አቅጣጫን እይታ ማስፈን አማራጮችንና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀጭጭ በመሆኑ ሀግ ሊደረግ ይገባዋል፡፡ ከሰራተኞቹ ተደጋጋሚ ክስ የቀረበበትና ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የተነሳበት የድርጂቱ አስተዳደር ክሶቹንና ግድፈቶችን ከመከላከል ባለፈ ራሱን በሰራተኛዉና በማህበሩ በቀጥታዊ ተሳታፎ ገምግሞና ተመካክሮ የማሻሻያ እርምጃወችን የመዉሰድና በሰራተኛዉና አስተዳደሩ መካከል ትምምንና አጋርነትን እዉን ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ሰራተኛ ማህበራቱ ተቀራርበዉ እንዲሰሩ ነፃና ከወገንተኝነት የፀዳ ህጋዊ ድጋፍ ማድረግ ሲገባ ህግ በጣሰ መልኩ አንዱን ልጅ ሌላዉን በጠላትነት ፈርጆ መቀጠል ቢያስመሽ እንጂ የማያሳድር ህመም መሆኑን ተረድቶ የሰላም መድሃኒት መዉሰድና ከግለሰብ ገጽታ ግንበባታ ታቅቦ የድርጀቱን ግስጋሴ በህብረት፣ አንድነትና እጂ ለእጂ ተያይዞ ማስቀጠል ግድ ይላል፡፡

በመጨረሻ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤቱና መንግስት ጉዳዩን በጥልቅና በፍጠነት መርምሮ ግልጽና ዘላቂ መፍትሄ ካላበጄ ዉጤቱ አሳዛኘኝም የታሪክ ተወቃሽና ተጠያቂ እንደሚያደርገዉ አምኖ ስራዉን በጊዜ ቢገባ አላለሁ፡፡ ሰላም ለአየር መንገዳችን፣ ሰላም ለታታሪ ሰራተኞቹና አስተዳደሩ፣ ሰላም!

ሶሎሞን ደረጄ

 

3 Comments

 1. The key to undo all the problems EAL is going through now lies in the hands of Seye Abraha the ex board chairman of Ethiopian Airlines who planted the seeds of hatred ethnic division in Ethiopian airlines with the help of Shabiya.

  yenetatum ያልተነገረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉድ አየር መንገዱ ከማፍያ ቡድን ላይ አውሮፕላን መከራየቱ ተጋለጠ : 60%ቱ የአየር መንገዱ አውሮፕላኖች ኪራይ ናቸው::

  • Hi Mr. Solomon I like your article and as Ethio-Canadian i am proud of EAL and it’s achievement regardless the hardship on Airlines at this moment. I am not denying the issues that are surfacing on social medias and on the news.
   Leave alone in Ethiopia in Canada there were, there are and will be issues in the Airlines and AC has said can not keep all the employees unless subsided by the government and I have not heard that from EAL. The fact it is surviving the difficult era is positive, it has survived DERG and WEYANE and will survive PROSPERITY as well.
   EAL is symbolic and prestige for Ethiopia and I want it to continue that way. I am not denying the discrimination, nepotism, power abuse and other unjust practices and there will be a time for accountability, but it is not only helping Ethiopia, Africa but also far east and south American countries by delivering materials to fight COVID19 and I could not imagine the scope of Ethiopians who would be COVID19 positive.
   We do not know the value of what we have until it is taken from us the fact that I am watching the blame, defame, and degrade EAL is not helpful, the social media is adding oil to the fire and the fruitful time to grow and correct the issues is wasting.
   When there is fame, money, status and power the hands to be part of it will be too many and all kinds of evil will take place to destroy some and to benefit others.
   There are insiders and out siders who are playing, some with personal granges and blow it to revenge others and bring you down to the hole they have been digging.
   I am not siding with any one, but I do not want to see during this time of difficulties the EAL(Ethiopian Airlines) suffer from within and outside players to their evil demise.
   I would like and love to see continue the EAL growing, correcting, flying to more destinations and be part of Ethiopia’s contribution to Africa, South America to fight COVID19 in the world.
   God BLESS & Protect all that helps ETHIOPIA.
   Muchfun
   Canada

 2. Mr. Solomon I like your article and It hurts to see all the good things slip away from our honour and identity. I know EAL is symbolic and prestige to our country. Lately the social medias are blowing damaging stories for our honour and prestige. I know there are insider and outsider players, there are those who have personal granges and try to bring you down to the hole they have been digging and do not care for collective interest but their own.
  We do not know the values that we have until they are taken away from us and the way things are heating up about EAL it only pleases Ethiopian Enemies.
  I know like every Airline even here in Canada there are, there were and there will be issues and first they see the big picture and correct the individual granges. In Ethiopia it is the reverse in order to get attention you Blame, the PM, the Organization, the Church, The mosque etc. etc.
  Had it not been to the EAL the COVID 19 infection would have tripled and EAL is delivering the materials to fight the pandemic in Africa, South America as well.
  There are those who are victims and first see the problem in big picture and think first the pro and con of the issue and wait for the right time to bring it to light. There are also those who blow second and third hand information and seek attention and Ethiopia is now in chaos.
  EAL has survived DERG, WOYANE and will survive PROSPERITY it was founded on solid grounds.
  I am not siding with any one I love to see EAL grow, prosper, correct and change to a better not during chaos and COVID 19 pandemic.
  God bless and protect Ethiopia.
  Muchfun.
  Canada

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.