ይበቃል !! ማለት ይበቃል ነው – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

102427552 1334889813567261 4952768521442755798 nእኛ ጥቁሮች ዛሬም የቦብን “ተነሱ፣ !ታገሉ፣ !ለመብታችሁ ከመፋለም አታፈግፍጉ ! “የሚለውን መዝሙር
፣በህብረት እንዘምራለን።ብዙሃኑ ነጮችም አብረውን ይዘምራሉ።
የቦብንም ግጥም መረቅሁላችሁ። “አበጀህ !” አትሉኝም።

   ይብቃል ማለት ይበቃል ነው።

መጀመሪያ ቃል ነበር ፣ቃልም እግዛብሔር
ተተከል፣ ተነቀል ፣ሁን እያለ ፣በቃል የሚፈጥር።
አንተም የእጁ ሥራ ነህ፣ሰው የምትባል
የተበጀህ ከአፈር፣ከጭቃ በመድቦልቦል።
ይሄንን ተረዳ፣ሳትሞት አፈር ሳትሆን
ቆዳ በማዋደድ ፣የምትለይ ዘርን።
……………………………..

ይብቃ!እንልሃለን ይበቃ!
ይበቃል! ማለት ነውና ይበቃል!
ይብቃ! ይብቃ!ይብቃ!…
ነጭ፣ጥቁር፣ቢጫና ክልሥነህ ማለት
በሰዎች መካከል(በዜጎች መካከል) ማድረግ ልዩነት።
……………………………………
ከእንግዲህ እንዳይደገም፣የዘረኛ ጭካኔ
በጆርጅ ፍሎይድ የተፈፀመው በጥቁር ወገኔ።
ይብቃ! ብለን ተነሥተናል፣ ሁላችን በአንድነት
ይብቃ! ቆዳ ማዋደድ ፣ መወገን በዘረኝነት።
ይብቃ !ይብቃ! የመብት ጥሰት…
ይሥፈን በዓለም የሰው ሁሉ እኩልነት።
ይብቃ ! ይብቃ!ጥቁርና ነጭ ማበላለጥ
ሰው ሁላ ይመዘን በህሊናው ግዝፈት።
በህሊናው አበርክቶ ነውና …
አንደኛው ከሌላው በልጦ የሚታይበት።
በፈጠራ ሰዎች፣በአርቆ አሳቢዎች ነውና
ይህ ዓለም እንዲህ የተራቀቀበት።
ለዚህ ውብ እና ቅንጡ ዘመንም የበቃበት።
ይብቃ! ብዝበዛ እንላለን ፣የታጀበው በዘረኝነት
እንዳይላቀቅ ያደረገው አፍሪካዊውን ከድህነት።
ከእንግዲህ ይብቃ! ይብቃ! እንላለን፣ቆዳ ማዋደድ
በየአደባባዩ በነጭ ዘረኞች ጥቁርን ማዋረድ።
…………………………
ይብቃ!በፕሮፓጋንዳ እውነትን መሸፈን
እናውቃለን ና…
የአውሮፓ ፣የአሜሪካ፣የኢሲያ ማደግ !
የእነግሊዝ፣የፈረንሣይ ፣የአሜሪካ መመንደግ!
በምን ምክንያት እንደሆነ ታሪክ እያወቀ
ታሪክ እያሥረዳ፣ታሪክ እየመሠከረ
እምሮና ጉልበት ከአፍሪካ እንደተሠረቀ።
ዓለም “የለጥቁር ቆዳው፣ ወርቃማ ጭንቅላት”
እንደማትደርስ እያወቅን ከዛሬው የሥልጣኔ አናት…
ብናሳብብ የአፍሪካን ብልፅጋና፣በድንቁርና
ዶሮን ሲያታልሏት፣በመጫኛ እንደጣሏት
ሰንጋ ይመሥል አሥተኝተው እንዳረዷት
…………………………………
እነሱ ትላንት፣የእማማ አፍሪካን…
ወርቅ፣አልማዝ፣ማአድኗን፣
የተፈጥሮ ሀብቷን
ሰብአዊ ጉልበቷን
በሥልጣኔ ሥም በዝብዘው ሲከብሩ
ሥልጣኔን አሥተማርናቸው እያሉ ያወራሉ።
…………………………………

ይብቃችሁ ይበቃል !መቀላመዱ…
ይታያችሁ የትላንት የሥልጣኔያችን መንገዱ።
የአክሱምን ሐውልት ፣የላሊበላን ህንፃ ተመልከቱ
የአፍሪካን ቀደምት ሥልጣኔ ፣ይተርካል ፔራሚዱ።
እናም እንላለን ፣በቆዳ ቀለም መመፃደቅ ይብቃ!
ከእንግዲህ ጥቁር አይሞትም ተረግጦ እንደዕቃ ።
ከእንግዲህ፣ይብቃ! እንላለን ጭካኔና ግፍ፣ ይብቃ!
……………………………………….
ዘረኞች ተረዱ ፣ከእንግዲህ ይበቃል!ይበቃል!
ሰው የሆንን ሁሉ ዘረኞችን ለመዋጋት በአንድነት ቆመናል።
መገዛታችን  ለህግ  ብቻ ነው፣የምንቆመውም ለእግዜር ቃል
እውነተኛ ፍትህ እሥከሚሰፍን  ትግላችን መች ይቆማል!!!
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
26/9/2012 ዓ/ም
አዳማ(ናዝሬት)
Get Up, Stand Up lyrics

Get up, stand up: stand up for your rights!
Get up, stand up: stand up for your rights!
Get up, stand up: stand up for your rights!
Get up, stand up: don’t give up the fight!
Preacher man, don’t tell me,
Heaven is under the earth.
I know you don’t know
What life is really worth.
It’s not all that glitters is gold;
‘Alf the story has never been told:
So now you see the light, eh!
Stand up for your rights. Come on!
Get up, stand up: stand up for your rights!
Get up, stand up: don’t give up the fight!
Get up, stand up: stand up for your rights!
Get up, stand up: don’t give up the fight!
Most people think,
Great God will come from the skies,
Take away everything
And make everybody feel high.
But if you know what life is worth,
You will look for yours on earth:
And now you see the light,
You stand up for your rights. Jah!
Get up, stand up! (Jah, Jah!)
Stand up for your rights! (Oh-hoo!)
Get up, stand up! (Get up, stand up!)
Don’t give up the fight! (Life is your right!)
Get up, stand up! (So we can’t give up the fight!)
Stand up for your rights! (Lord, Lord!)
Get up, stand up! (Keep on struggling on!)
Don’t give up the fight! (Yeah!)
We sick an’ tired of-a your ism-skism game –
Dyin’ ‘n’ goin’ to heaven in-a Jesus’ name, Lord.
We know when we understand:
Almighty God is a living man.
You can fool some people sometimes,
But you can’t fool all the people all the time.
So now we see the light (What you gonna do?),
We gonna stand up for our rights! (Yeah, yeah, yeah!)
So you better:
Get up, stand up! (In the morning! Git it up!)
Stand up for your rights! (Stand up for our rights!)
Get up, stand up!
Don’t give up the fight! (Don’t give it up, don’t give it up!)
Get up, stand up! (Get up, stand up!)
Stand up for your rights! (Get up, stand up!)
Get up, stand up! ( … )
Don’t give up the fight! (Get up, stand up!)
Get up, stand up! ( … )
Stand up for your rights!
Get up, stand up!
Don’t give up the fight!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.