የወሰን ተሻጋሪ ወንዝ የውሃ ክፍፍል፣ አጠቃቀም፣ አለም አቀፍ ህግጋት እይታዎች – በቀለ

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የውዳሴ ግድብ የማንንም አገር አሉንታዊ ፍቃድ የማይጠይቅ እንደሆነ ብዙ ተብሎለታል ሁላችንም የምናምንበት ነው።

water distribution

በዚህ ዙርያ ለማለት የምፈልገው አንድ አገር የውሃ ሃብቷን ለምን ተግባር ትጠቀምበታለች ተብሎ የሚታሰበው የመጀመርያ የሃብት ክፍፍል ሲነሳ የሚመጣ መሰረታዊ ሃሳብ ነው።ይህም ሃብቱ ለተፈትሮ ተጋላጭ ሆኖ ለልማት ሲውል የሚባክን ከሆነ የተሻሉ አማራጭ ያሉበትን አካባቤ መምረጥ ይጠይቃል። እንዲሁም የውንዙን ውሃ ቀጣይነት ስንመለከት ተመሳሳይነት ያለው የሃይድሮሎጂ ዑደት መፍጠር ይኖርበታል። ሆኖም ግን ተፋሰሱ በአግባቡ ካልተያዘ ሊባክን የሚችል የውሃ ሃብት ማስከተል ስለሚችል በቀጣይ አመታት የስርጭቱን መጠን ችግር መፍጠሩ ታሳቢ ይሆናል። የሃድሮሎጂ ዑደት ስርአት የሚጠብቁ የውሃ አካል ትነት ፣ከዛፎች የሚወጡ ትነቶች፣ ወደመሪት የሚሰርጉ ፣ የውሃ ሃብት ልማት ፍጆታዎች እና በወንዝነት የሚፈሰው በአንድነት ተደምረው እግዜአብሄር ከለገሰን የዝናብ መጠን ጋር ተስማሚነታቸው ሊኖራቸው ግድ ይላል። ተስማሚነታቸውን በአንፅሩ በአመታት የሚታዩትን የፍሰት መጠን ስርጭት ተቀራራቢ ያደርገዋል ። የዚህም ውጤቶች ባለቤት ያልተፋለሱ የተፋሰሱ የቶፖግራፊ አቀማመጥ ዋንያው ማሳያዎች ናቸው።ይህ ሳይሆን ሲቀር ማለት በደን እና በቁጣቋጦ የተሸፈኑ ተራራዎችን ስናጠፋ ፈጣን የሆኑ ወንዞች መፍጠር እንችላለን ። በትንሽ ስአታት የሚያልፉ ከፍተኛ የፈሰት መጠን  (peak flow) ያላቸው ወንዞች ማለት ነው።

ተፋሰሶችን በማርቆታችን ወደመሬት የሚሰርገውን የዝናብ መጠን እንቀንሳለን። ከደን የተራቆቱ አካባቤዎች መፍጠራችን  በተፈትሮ የውሃ አካሎች ይጠራቀሙ የነበረ የወንዝ ወይም የዝናብ ውሃን እንቀንሳለን።

የተፈጥሮ የወንዙን የሃድሮሎጂ ስርአት በማበላሸታችን ለተወሰኑ ግዜያት ከፍተኛ ፍሰት በወንዙ ውስጥ ይኖርና የአማካኝ ፍሰቱ በአብዛኛው ወራቶች በጣም ዝቅ ሲል ።ይህም የተፈጥሮ የወንዙን ዝቅተኛ ፍሰት ለማውቅ ያስቸግራል።በአባይ ዙርያ ለተነሳው የግድቡን የመሙላት ግዜና የግድቡን የመያዝ አቅም ለንትርክ የዳረገው በአባይ ወንዝ የሚፈሰው የአመቱ አማካኝ የፍሰት መጠን ስምምነት ላይ መድረስ አለማስቻሉ ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የአባይ ወንዝ ታሪካዊ ፍሰቱ የተዛባ ሆኖል።  የአባይ ወንዝ ላይ በአመት ሲሰላ የሚገኘው የውሃ መጠን ከ 75% በላይ በ3 ወር ባነሰ የክረምት ወቅት ነው የሚፈሰው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕገ መንግሥቱ ይሻሻል ወይስ ይቀየር?   (ለውይይት መነሻ እንዲሆን የተዘጋጀ) - ባይሳ ዋቅ-ወያ

ሰው ሰራሽ በሆኑ ሁኔታዎች ያጣናቸው የተፈጥሮ የሃይድሮሎጂ ዑደት (hydrology water balance) ሄደቶች መስተካከል የሁሉም ተጠቃሚ ሃገራት በድርድር የሚቀበሉት ሃስብ መሆን አለባቸው ። በአባይ ተፋሰሱ ሃገራት መካከል የጠነከ የመተማመን  ስምምነቶች መፈጠር ተገቢ ነው። በተለይ የውሃ ፍጆታ የሚፈልጉ ፕሮጀክቶች በአገራችን በኩል በዝርዝር መቅረብ ይኖርባቸዋል። እስከዛሪ መገንባት ያልቻልናቸው በአባይ ተፋሰስ ላይ ያሉን እምቅ ፖቴንሽያልንም ያካትታል። ትኩረታችንም በሁለት አይነት መንገድ በማደራጀት መዘጋጀት ይጠብቅብናል። የውሃ ፍጆታ የሚያስፈልጋቸው ጥቅም ላይ ከዋሉ በሃላ ተመልሶ የማናገኘውን የውሃ አጠቃቀምን እና  የውሃ ፍጆታ የማያስፈልጋቸው ፕሮጀክቶች፣ የውሃ ሃብቱን ሳይቀንስ መገልገል የሚያስችሉን ልማቶችን በጎላ ሁኔታ ለድርድር መቅረብ ላያስፈልገን ይችላል። የውዳሴው ግድብ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል በስተግርጌ ላሉት ሃገራት የሚፈልጉት ብቻ ስይሆን  የማያስፈልጋቸውን የውሃ ሃብት ስለሚሰጥ ከግድቡ የሃይል ማምረት እስትራቴጂ ጋር የሚገናዘብ መሆን አለበት ። ለአገራችን የሚሰጠው ጥቅም በንፅፅር ከበስተግርጌ ካሉት አገራት አነስተኛ ነው። በተደጋጋሚ የሚገኘውን ጥቅም በጋራ እንጠቀም የሚሉ የመግባብያ ሃሳቦችም በአግባቡ መታየት ይኖርባቸውል።በውዳሴው የምናመነጨው የሃይድሮ ፓወር ግብይት አለም አቀፍ ካልሆነ አትራፊነቱ ጥያቄ ያስነስል።በጎረቤቶ አገራት ላይ ጥገኝነት ካለው አገራቱ ሃይል የሚያመነጩባቸው አማራጭ እንዳላቸው ግምት ውስጥ አስገብቶ መሆንን ይጠይቃል። ለአገር ፍጆታ ብሎ የተካሄደ ፕሮጀክት ከሆነ ሃይልን ለማመንጨት የሚያስገድዱ የሃይል አቅርቦት ስራቶች ስለማይኖሩ በአገራችን ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደርገዋል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

በዚህ ዙርያ የሃድሮ ፓወር ፣ የአሳ እርባት እና ለትራንስፖርት   የውሃ ሃብትን ስናውል የውሃ ፍጆታ የማያስፈልጋቸው ስለሆነ በነፃነት አገራችን ስታለማ ቆይታለች። አሁንም ልብ ማለት ያለብን የውዳሴው ተግባር ቀደም ብሎ ከአከናወናቸው የሃይል ማምረት ፕሮጀክቶች ጋር ተመሳሳይ ያለው ሲሆን። ሃይል በማምረት ፣ለምሳሌ የጢስ አባይ እና የፊንጫን ሃድርሮ ፓወር መመልከት ይቻላል። አሁን ለምን የተለየ ጥያቄ አስነሳ ብሎ ሌሎችንም መመርመር የሚያስፈልገን ይሆናል። አንዳንድ ሙሁራን በጣና ሃይቅ ላይ ስለደረሰው የደለል መሙላት ያስረዱናል ለእኔ ግን የሚሰማኝ የፕሮጀክቱ ፅንሰ ሃሳብ ማን አመጣው ብሎ ከማሰብ ይጀምራል። ወደ ላይ ከፍ ስል ደግሞ ደለል በራሱ አይፈጠር እንደ ወርቅ ፍለጋ ያለ ፕሮጀክት ችፍርግን ፣ አጋም እና ቀጋውን አጥፍቶብን ቢሆንስ።  ዛፎቻችን ጥቅማቸው ሁለት ነው ብዬ ነው ባስብ ፣አንድም ለማገዶ እና ለቤት ግንባታው ነው። ጠለቅ ብለን ስናስብ ለሃድሮሎጂ ባላንስ ከዚያም ከአለፈ ለአፈር መጠረግና መከላከልም ይሆናል። ሆነም ግን የዝናቡን ሃይል አርግበው ወደ ገፅ ምድር የሚወሰዱልን እና የወንዙ base flow የሚያስተካክሉልን እንደአካባቢው ቢለያዩም ተመሳሳይነት ያላቸው ችፍርግ ፣ አጋም እና ቀጋው ናቸው ብዬ አምናለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  " የጥለዛ ፓለቲካ " ፣ሥለ ፍትህ ፣ ሥለ ሠላም ሥለ ዴሞክራሲ ወዘተ ደንታ የለውም  - መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ 

ሌላው የውሃ ፍጆታ የሚያስፈልጋቸው ፕሮጀክትን መመልከት ያስፈልጋል የመጠጥ ውሃ፣ የመስኖ ልማት በቂ ምሳሌዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ማብራራትም አያስፈልጋቸው። የተጠራቀመ ውሃ ይፈልጋሉ ለልማት ለማዋል፣ ይህም የተፈጥሮ ሃይቆችን ፣ ረግረግ ቦታዎች እና ትንንሽ እና ትልልቅ ግድቦች ያካትታል። በአገራችን በክረምት ዝናብ ብቻ አብቅለን ህዝባችንን መመገብ አንችልም በተግባርም አይተነዋል፣ የክረምቱን ጎርፍ አጠራቅመን ብንችል ትላልቅ እርሻዎችን ፈጥረን ብልፅግናን መጥራት ያስፈልገናል።

የውዳሴው ግድብ የግብፅም ሆነ የሱዳን የውሃ ፍጆታ የማይቀንስ ነው ብለን ስንረዳ። ከፍታው ይቀነስ፣ የሚሞላበት እድሜ ይርዘም እና ሌሎችም ቴክኒካዊ የሆኑ ማደናጋገርያ ሃሳቦች እየተሰጠ የሚያደነጋግሩን መስማት የለብንም። ተደራዳሪዎቻችን በጥልቀት የሚያስቧቸው የውሃ ሃብት የይገባናል አካሄዶች እንዳሉ ሆነው የሚደራደሩበት ይሆናል። እስካሁንም በውሃው ሃብት ዙርያ የተደረሰበት የውሃ ክፍፍል አለመኖሩ ቀጣይ የጠነከሩ ድርድሮች እንደሚጠብቃቸው ያሳያል። የአባይ ወንዝ ለሌሎችም አገር አቋራጭ ወንዞቻችን ትምህርት ስለሚሆን የተለያዩ በለሙያተኖች ተሳታፊ ማድረጉ ከግዳቱ ጥቅሙ ከፍ ይላል እላለሁ።

ሆኖም ግን እንደኔ አይነቱ በደፈናው  የውዳሴን ግድብ ብቻ እየተመለከተ ያለውን ባለሙያ የሚሰጠው ሃስብ አጉልቶ የሚናገረውን  እና በግድቡ ላይ ባለ መብት መሆናችንን የሚመለከተውን ማስተማሩ ተገቢ ሲሆን አውቆም የሚቀባጥረውንም ማረም ተገቢ ነው እላለሁ። ወንዙን እና ግድቡን ለምንፈለገው ሃይል ማመንጨት ማዋላችንን ብቻ የምናወድስ መሆን የለብንም። የውዳሴው ግድብ የተሻለ እድል ሊፈጥርልን እንደሚችል ማስብ አለብን የውሃው ባለቤቶች ነን፣   በለስልጣናቶቻችን የሚሉንን በአንክሮ ማዳመጥ ይገባል እላለሁ፣ በግድቡ ዝርያ ማንም ይሁን ማን ሊለን አይችልም በራሳችን አቅም እና ባለሙያዎች የምነገነባው ስለሆነ ማንንም መስማት አንችልም እኛን የሚጠቅመን እስካልሆነ ድረስ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከ “ናስ ማሰር - አፍ ማሰር”   - ይገረም አለሙ

 

የአገር ተሻጋሪ ወንዞችን የሚጋሩ ሃገራት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ወንዙን  በስምምነት እና በትብብር ለሚፈልጉት ልማት ከግጭት ውጪ በሆነ ሁኔታ መገልገል የሚደገፍ ሲሆን። በጋራ ለሚያዘጋጅዋቸው የመግባብያ ሰነዶች ትብብር ማድረግ ቢችሉ የተሻለ ይሆናል እላለሁ ። የአባይ ወንዝ ተጠቃሚ የሆኑት የታች አገራት የአትንኩብን ባይነት መፈክራቸው በማውረድ ስምምነት መፍጠር ብልህነት ነው። አንዱ ከአንዱ አገር በብልጥነትም ይሁን በአጋጣሚዎች ተጠቃሚ መሆኑ የሌላውን ባለመብትነት ሊገታው አይችልም።

እውነት ነው የወንዝ ተሻጋሪ ወንዞች ለሚያካልሏቸው አገራት ብቻ ሳይሆን የአለም ህዝብ የጋራ ሃብቶች ናቸው ።ሆኖም ግን የባለመብትነት መብት ሙሉ በሙሉ ተቆጠጥረው በያዙአቸው አገራት የሚያቀርቡልን የቀደሙ ስምምነቶች ትርክት ወይም የታሪክ ተጠቃሚነታቸው ቦታ አይኖራቸውም። አለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረታቸው በአገሮች እንዲሁም በህዝቦች መካከል ሊከሰቱ የሚችሉ ቅራኔዎችን በማስወገድ ሃገራት የውሃ ሃብቱን በቁጠባ እና ተተኪ ሃይላትን ባማቀናጀት ለጋራ ጥቅም ማዋል የሚያስችሉ ስምምነቶችን ለመተግበር የሚረዱ ህግጋት እና ደንቦች አካል ናቸውና።

በአባይ ወንዞች ተጠቃሚ የሆኑ ሃገራት መካከል የሚደረገው ንትርክ ፣ ውይይቶች እና ድርድሮች መደምደሚያቸው በተፋሰሱ በተደረሱ ስምምነቶች ሲዳኙ ወይም የአለም አቀፍ ስምምነቶችን አገራቱ በማክበር ተገዥ ሲሆኑ ነው። ለዚህም ነው በአባይ ወንዝ ላይ የተገነቡት ሊሎች የሃይል የማመንጫ ግድቦች ወደታች ባሉ ሃገራት አሉንታዊ ችግር የማይፈጥር መሆኑ በባለስልጣኖቻችን የሚገለፁልን። በአገራችን በኩል እየተከናወነ የሚገኘው ወይም ቀድመው የተከናውኑ የአባይ ወንዝ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የታችዮቹ አገራት ሲያሸኛቸው የሚቀበሉአቸው ወይም የሚቃወሙአቸው መሆን የለበትም።

 

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

በቀለ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.