/

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ በበሽታው የተጨማሪ 1 ሰው ሕይወት አለፈ

healthበኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5141 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ።

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1636 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 94 ወንድ እና 56 ሴቶች ሲሆኑ ዕድሜያቸውም ከ3 እስከ 72 ዓመት መሆኑ ተገልጿል። በዜግነት 147 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3ቱ የውጭ ዜጎች መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በቦታ ሲለዩ፣

* ከአዲስ አበባ – 123 ሰዎች
* ከአፋር ክልል – 1 ሰው
* ከትግራይ ክልል – 2 ሰዎች
* ከደቡብ ክልል – 3 ሰዎች
* ከኦሮሚያ ክልል – 2 ሰዎች
* ከአማራ ክልል – 13 ሰዎች እና
* ከሶማሊ ክልል – 6 ሰዎች ናቸው።

የላቦራቶሪ ውጤቶች እንደሚያሳዩት በኅብረተሰቡ ውስጥ ባለው የስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለዚህም ማሳያ የመጀመሪያው ሰው በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉ ሁለት ወራት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ300 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ ማሳየቱን አመልክቷል።

በዚህም ምክንያት የታካሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንደ ሚሌኒየም አዳራሽ ዓይነት የለይቶ ማከሚያዎች ታካሚዎችን እንዲቀበሉ ማድረግ መጀመሩን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በኢትዮጵያ እስካሁን በአጠቃላይ 125 ሺህ 570 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.