በነ ዶር አብይ ላይ አመጽ የጠራው የቀድሞ የዶር አብይ ሹመኛ – ግርማ ካሳ

Birhaneአቶ ብርሃነመስቀል አበበ በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጽ/ቤት አምባሳደር ሆኖ የሰራ ሰው ነው፡፡ እነ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከፊት ፊት በመቅደም፣ ዋና ደጋፊ ሆኖ ስልጣን ለመቆናጠጥ በቅቶም ነበር፡፡ በሂደት ፣ በተለይም ቀደም ሲል የተናገራቸው ንግግሮች በስፋት እየወጡ ሲመጡ ግን በሃላፊነቱ መቀጠል አልቻለም፡፡ በተለይም ኦህዴድ ፈርሶ ብልጽግና ሲመሰረት፣ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ከንቲባ መሆን ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው” ብሎ የተናገረው ዘረናና አፓርታይዳዊ ንግግር በሃላፊነቱ እንዳይቀጥል ትልቁና አንዱ ምክንያት ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ ብርሃነመስቀል ዶክተር አይደለም፡፡ ዶክተር የሚባለው የሕክምና ዶክትሬት ያለው ወይንም በሌሎች ፊልዶች PhD የያዘነው፡፡ ብርሃነ መስቀል አሜሩካን አገር የመጀመሪያውን የህግ ዲግሪ ነው ያለው)

ከላይ እንደጠቀስኩት ይህ ሰው የነ ዶር አብይና የብልጽግና ፓርቲ ዋና አፈቀላጤን ደጋፊ የነበረ ሰው ነው፡፡ ልክ ከሃላፊነቱ ሲነሳ ግን ፣ ሌላው ጸጋዬ አራርሳ ሆኖ አረፈው፡፡ በፊትም ለስልጣን የሚሰራ ከነበረ ሰው፣ መርህ ያለው አቋም መጠበቅ ስለማይቻል ብዙም አላስገረመኝም፡፡

ወደ ዋና ነጥቤ ስመጣ፣ ይህ ሰው በኦሮሞ ክልል የአመጽና የሰልፍ ጥሪ አስተላሏፋል፡፡ ምን አልባት እነ አቶ አዲሱ አረጋ “ሰልፍ ተጠርቷል” ያሉት የዚህ ሰው ጦማር አንበበው ሊሆን ይችላል፡፡ (አቶ አዲሱ ሰልፍን በተመለከተ በተናገረው ላይ በሌላ ጽሁፍ እመለሳለሁ)

ብርሃነ መሰቀል ከጻፈው የሚከተለውን ላጋራችሁ፡

” የኦሮሞ ህዝብ የህወሃት መራሹን ስረዓት በናደበት ጉልበት፣ ያለ፣ ያሌለ ኃይሉን በፍጥነት እንደገና አሰባስቦ (regroup አድርጎ) ፣ በካፒታልዝም ስም የጭሰኛውን ስረዓት መልሰው በህዝባችን ላይ ልጭኑበት የሚቋምጡትን አሃዳዊያን ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ ከኢትዮጵያ ስረዓተ መንግስት ውስጥ መቁረጥ ሳይሆን ከስራቸው ጨርሶ መንቀል አለበት”

እያንዳንዱ ኦሮሞ፣ እውቀቱን፣ ገንዘቡን፣ ጉልበቱን እና ጊዜውን አሰባስቦ እና አደራጅቶ፣ በከፍተኛ የበቀል እና የጥላቻ መንፈስ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ካልመከተ፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጄኖሳይድ አዋጅ ያወጅነው እኛ እንጂ፣ እነርሱ እንዳልሆኑ ማወቅ አለብን።

የኦሮሞ ህዝብ ተደራጅቶ፣ በሁለት እግሩ ከቆመ፣ አሃዳዊያኑ የኦሮሞን ህዝብ ጨፍልቀው እና አጥፍተው፣ የአፄ ምኒልክ እና የአፄ ኃይለስላሴን አማርኛ ብቻ ተናጋሪ (Assimilationist) ኢትዮጵያን የመፍጠር ህልም ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር፣ የቀን ቅዥት እንጂ የፖላቲካ ትርክት አይሆንም።”

አንድ የማይገባኝ ነገር ቢኖር ተማርን የሚሉ ሰዎች ለምን በድንቁርና እንደሚሞሉ ነው፡፡ እነ ዶር አብይ በፌዴራል ደረጃ በሕገ መንግስቱ እስኪሻሻል ድረስ፣ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤትም አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግሪኛና አፋርኛ ከአማርኛ የስራ ቋንቋ እንዲሆን አልተደረገምን ? ዶር አብይ በሚለጥፈው የሶሻል ሜዲያ ጦማር በኦሮምኛም ያውም ብዙዎች በሚደብራቸው ላቲን መልእክቱን ያስተላለፍ የለም እንዴ ? አሁንም የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ በኦሮሞ ክልል እያስተዳደረ ያለው በኦሮምኛ አይደለም እንዴ ?

ነው ወይስ በኦሮሞ ክልል ያሉ ኦሮምኛና የማይናገሩ በክሉ በአማርኛ አገልግሎት ያግኙ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች በብዛት ባሉባቸው ወረዳዎችና ዞኖች አማርኛም ከኦሮምኛ ጋር የስራ ቋንቋ ይሁን፣ በክልሉም አማርኛ ከኦሮምናኛና ከእንግሊዘኛ ጋር እንደ ትምህርት ይሰጥ መባሉን ነው ፣ “የአፄ ምኒልክ እና የአፄ ኃይለስላሴን አማርኛ ብቻ ተናጋሪ (Assimilationist) ኢትዮጵያን መፍጠር ተደርጎ የሚወሰደው ??????

 

3 Comments

  1. In the greater Los Angeles, California, USA area numerous Diaspora Ethiopians trusted this guy and formed business partnerships with him involving themselves in import and export businesses operating between USA and Ethiopia per his recommendations , only for him to end up profiting from it while each of those business partners of his loosing all they invested.

  2. አቶ ግርማ ምን ሎስ አንጀለስ ወስደህ? እዛው እራስጌው አይደል እንዴ ለማን የመሰለ ቀኝ እጅ ሸብረክ ያለበት በዶር አቢይ? አቶ ግርማም ሆንክ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ያልገባችሁ ቢኖር ለሽፍታውም፣ ለከሃዲዎቹም፣ ለአክራሪዎቹም ይሁን ለዘብተኞች አቢይ የማይገፋ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ነው የሆነባቸው። የማንንም አጀንዳ ሳይሆን ይህ ቅን ወጣት መሪ የኢትዮጵያን አጀንዳ ነው የሚያራምደው። እነ ብርሃነመስቀል አቢይ ኢትዮጵያዊ ጸጋ በመላበሱና ለፈለጉት አላማ አልመች ሲላቸው ከጀርባና ፊት ይወጉት ገባ። አንዳንድ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኛ ተብዬዎችም አቢይ ከጅምሩ ሹመት ቢሰጣቸውና ቢያቀርባቸው ኖሮ ጠላት አይሆኑትም ነበር። ጭራሽ ዖሮሞ አይደለም እስከማለት የደፈሩ ጉደኞች ናቸው። በነዚህ ደካማዎች እይታ ዖሮሞዎቹ በቀለ ገርባ፣ ጁዋር መሃመድ፣ ህዝቅኤል ገቢሣ ወይም ዶር ገመቹ ሊሆኑ ነው። ኸረ እንደውም በነ በቀለ እይታማ ወያኔ ሞር ዖሮሞ ነው ከአቢይ አህመድ። እንዲህ ነው ያለንበት ዘመን ፖለቲካ። በዚህ የኮረና ውጥረት አመት ሰልፍ የሚጠራ የዖሮሞ አክቲቪስት ወይም ፖለቲሻን ሳይሆን በዖሮሞ አናት ተፈናጦ ፣ በዖሮሞ እናትና ህጻናት መቃብር ላይ ተረማምዶ የራሱን ሰልፊሽ ኢንተረስት የሚያራምድ ወይም ሊያራምድ የሚቋምጥ ደመነፍስ ነው። በዝምታ በየቤቱ ያደፈጠው ወገን ይህ ካላነቃው ምንም አያነቃውም። የዛ የታማኝ በየነ ድምጽ ናፈቀኝ። አስቀይመወት እንጅ በኢትዮጵያ እንዲህ አንደበቱ አይያዝም ነበር። ለነገሩ እኔም ይቅርብህ ፖለቲካው ብዬው እሱም ሰምቶኝ ሰብአዊነቱ ላይ አተኩሯል። ፈጣሪ ይርዳን ።

  3. የዚህን ብርሃነ መሥቀል የተባለ ሰው ፎቶ “አንብቤ” አንድ የማይካድ እውነት ብነግራችሁ ትቀበሉኝ ይሆን? ሰውዬው ዖሮሞ አይደለም። ግን በዖሮሞ ሥም ይነግዳል – ልክ እንደጃዋር። ወዳጄን ፕሮ. ፍቅሬ ቶሎሣን አንብቡልኝ – በብዙ መቶኛ ሥሌት ዖሮሞ ነው።
    ለነገሩ ችግሩ ያለው ከዘር አይደለም አባዊርቱ እንዳለው ከጥቅምና ፍላጎት ነው። ይሄ በልቶ እማይጠረቃ ሆድና አግኝቶ እማይረካ ግላዊ ፍላጎት ሰውን አሥሬ እያፈረሰ ይሠራዋል። ሃይማኖትን ዘር የመጥፎ ሰዎች ጥቅምና ፍላጎት ማሥጠበቂያ ሰይጣናዊ መሣሪያዎች ናቸው።
    ይህ ዘመን ከማንኛውም እኔ ከማውቀው ዘመን በበለጠ የፍየል ሥጋ ሆኗል። የፍየል ሥጋ የውሥጥ በሽታን ወደ ውጭ ያወጣል ይባላል – ፍየል የማትበላው ቅጠል ስለሌላት ነው አሉ ሰውን እንዲህ ጉድ የምትሠራ፤ አሥተናግር የሚባል ቅጠልም ስለምትበላ ጭምር። …

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.