አማራ ባንክን የበላ ጅብ አልጮኸ አለ! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Amhara Bank

“እኔውም ዕብድ ነኝ ከወፍ የገበየሁ፤ መቀመጧን እንጂ መብረሯን የት አየሁ” ይሉ ነበር የቀድሞ ሰዎች – እንደኔው ያለ የቀባጭ ምቸውን ሲቀምሱ (‹ሣ›ን አጥብቁልኝ ታዲያ)፡፡ ውጣ ያለው ገንዘብ ግድግዳ ሲቆፍር ማደሩ የሚነገረውም ብዙውን ጊዜ እውነት ነው፡፡ የኔንማ ነገር ተውት – ዕርሟን ቡና አፍልታ ጀበናውን ሙሉ አተላ እንዳደረገችው አላዋቂ ሴት ዕርሜን አክሲዮን ብገባ ሹዋሹዋ ተሠራሁ፤ ጠጠቱ በማይለቅ ንዴት እየተንጨረጨርኩ አለሁ፡፡

ኧረ ይሄ የጉግማንጉጎች የላቦራቷር ፍጡር ኮርዬ ጉድ እያፈላ ነው! ዛሬ ብቻ 142 ሰው በቫይረሱ መያዙ ሲረጋገጥ 3 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ ፡፡ ደረጃችንም ወደ 103ኛ ወጣ፡፡ ይሄኔ በሀብት በሥልጣኔ ምናምን ቢሆን ኖሮ ወደ ውራነት በወረደ ነበር፡፡ በዚህችም የቀናብንን እንጃ ከደህና ደረጃ ወደ መጥፎ – ወደ ደህና መጥፎ ደረጃ እያዘቀዘቅን ነው፡፡ በቃችሁ ይበለን፡፡ ለነገሩ ኮሮና እንኳን ጊዜያዊ ጫጫታ ፈጥራ ለሌላ የባሰ ውርጅብኝ አጋፍጣን ነው የምትበርደው – (እየተባለ ሲወራ ሰማሁ ልበል?)፡፡ ባለፈው አንድ ጦማሬ ኮሮና ወደ ኢትዮጵያ እንደማይገባ በጥቅስ ቢጤ ጠቆም ማድረጌ ይታወሳል፡፡ እርግጥ ነው – የመንደር ሌባ “ቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ይላሉ” እንደሚለው በቂ ጥንቃቄ ካልተደረገና ኅሊናቸውን ለገንዘብ የሸጡ ሆዳም ዜጎች ታማሚን ሳይቀር ከማቆያ ቦታዎች በጉቦ እያስወጡ ከለቀቁ እኛ እንጨት ወይም ድንጋይ አይደለንምና መያዛችን አይቀርም፡፡ ይህም ሆኖ ጥቂት ሽዎች ያሏት ሀገር ብዙ ሽዎችን በቫይረሱ ስታጣ 115 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ 17 ብቻ ማጣቷ እንደማነጻጸሪያ የነገር ማዋዣ አድርጌም ቢሆን እንደዋዛ የተናገርኩት ነገር እውነትነት የሚያጣ አይመስለኝም፡፡ (አሁን ይህን ደብዳቤ ልልክ ስል ደግሞ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዘው ሰው ቁጥር ከምንጊዜውም በልጦ 150 ሲሆን የሟቹ ቁጥርም በአንድ ጨምሮ 18 ደርሷል – ደረጃችንም 101ኛ ሆኗል፡፡ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ቡሃ ላይ ቆረቆር፡፡ በዚህ ድህነታችንና በዚህ የሙስና ዘመን ይህ ክስተት ትልቅ አደጋ ነው፡፡)

በሌላ በኩልም ቢናገሩት ለሚያሳፍር አንድ ጥያቄ እማሆይ የሰጡትን መልስ ማስታወስ ተገቢ ነው – “ሲያጎርሱት የማያላምጥ የለም” ብለዋል አሉ በአሽሙር መልክ፡፡ ኤርትራ እንኳን በአቅሟ ነፍስ አውቃ አልቀበልም ያለችውን የ666 ፊታውራሪዎች እነጃክማ በህክምና መሣሪያዎችና በፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በዓለም ዙሪያ የሚያዛምቱትን ቫይረስ ከነኮተቱ አቢይና ግብረ አበሮቹ እየተቀባበሉ አፍሪካንና መላዋን ኢትዮጵያ ለማዳረስ ቆርጠው ከተነሱ ለአንድዬ ከመጮኽ ውጪ ለጊዜው ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ የሀገራችን 65 ሀኪሞች በቫይረሱ የተያዙት ከጥንቃቄ ጉድለት ሳይሆን በህክምና አልባሳት ሆን ተብሎ በነቢልጌትስ በሚሰራጭ ኮሮና ቫይረስ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ ምሥጢራውያኑ ድርጅቶች ጦርነቶችንና ፍብርክ በሽታዎችን ጨምሮ በተለያዩ ዘዴዎች ከሲሶ በላይ የሚሆነውን የዓለምን ሕዝብ ፈጅተው የራሳቸውን የሰይጣን መንግሥት ለመመሥረት ቅድመ ሁኔታዎችን ጨርሰው ወደ ትግበራው መግባታቸውን ካነበብነውም ከሰማነውም እያጣቀስን አንዳንዶቻችን ሰሚ አጣን እንጂ ብዙ ለፍልፈናል፡፡ ሰይጣን በተፈጥሮው ሰዎችን ማዘናጋትና ማደደብ ዋና ሥራው ስለሆነ ብዙው የሀገራችንና የዓለማችን ጎጋ ዜጋ አልገባውም፤ እንደስካሁኑ ሁኔታ ከሆነ ደግሞ አይገባውምም፡፡ ከመጋረጃ በስተጀርባና አሁን አሁን ደግሞ በማን አለብኝነት በግልጥ እየተሠራ ያለውን ለሚገነዘብ የዓለም ፍጻሜ መቃረቡን ብቻ ሳይሆን በውስጡም እንዳለን መገንዘብ አይሳነውም፡፡ “ኢትዮጵያዊ አባት አ(ስ)ምጦ የወለዳትን ልጁን ደፈረ”፣ “እናት የገዛ ልጇን አፍቅራ አባቱንና ባሏን በመግደል/በማስገደል ከልጇ ጋር ተጋባች”፣ “ወይንሸትና ጫልቱ 50ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ጠ/ሚኒስትሩና የካቢኔ አባሎቻቸው በተገኙበት በጁፒተር ሆቴል በድምቀት አከበሩ” … መባልን የሚሰማ ጤነኛ ሰው “በዚያን ዘመን ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ወሬ ከያቅጣጫው ትሰሙ ዘንድ ግድ ነው” የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢት ትዝ ሊለው እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ እንደዚህ ያለ ሀገር ውስጥ  “አባት ወንድ ልጁን አግብቶ መኖር ጀመረ”፣ “ጆንሰን ከሚወዳት ፈረሱ ጋር ህጋዊ ጋብቻ መሠረተ”፣ “ቤኪ ከልቧ ከምታፈቅረው ውሻዋ ጋር ዘመድ አዝማድ በተገኘበት በተክሊል ተጋባች”፣ “የትናንትና ማታው የቡድን ወሲብ (orgy) ግሩም እንደነበር ተሳታፊ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ሳይቀሩ መሰከሩ” … ልቀጥል? የዐዋጁን በጆሮ እኮ ነው፡፡ እናስ እነአቢይ ትሰማላችሁ? የጌዮችና የሌዝቢያኖች መብትም መከበር ያለበት መብት ሆኖ ልክስክሱና ለዲያብሎስ አጎብዳጁ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሽርፍራፊ ገንዘብ ኅሊናውን በመሸጥ ምን እየሠራ እንደሆነ በተለይ ከመምህር ደረጀ ነጋሽ የዘወትር ልፋትና ድካም እየተገነዘብን ነው – መምህር ደሬ እግዚአብሔር በሰማይም በምድርም ዋጋህን እንዲከፍልህ እጸልያለሁ፡፡ እነአቢይ ግን በሩ ሳይዘጋ ቶሎ ይመለሱ – የቀራቸው እኮ ቤተ መንግሥት መግቢያ በር ላይ የሦዶማውያንን ዓርማ መስቀልና ህገ መንግሥቱን በማሻሻል የተመሳሳይ ፆታን ጋብቻ ማጽደቅ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን በገንዘቡ ኢትዮጵያን እንደልቡ እየፏለለባት ነው፡፡ መጨረሻውን ላዬ! የዚህ ጦርነት ውጤት በጣም ግልጽ ቢሆንም ጉዳቱ ግን ቀላል እንዳልሆነ እየታዘብን ነው፡፡

በዚህ በዶክተር አቢይ ላይ ደግሞ እነጌታቸው ጅጌ ሲዘምቱበት በሶሻል ሚዲያ አየሁ – ምድረ ሥልጣን ወዳድና ምድረ የግብጽ ዘሕወሓት ቅጥረኛ የሰማውን እንጃለት ሰሞኑን ዕረፍት አጥቷል – እንደቀትር እባብ መቅነዝነዝ አብዝቷል፤ አንዱ ሲያርፍ ሌላው እየተነሳ መወሻከቱንና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያባላ ዲስኩሩን በሚዲያ ማቀርሸቱን ተያይዞታል – በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካባ ተጀቡኖ “ስለአባይ ግድብ አያገባኝም” እስከማለት የደረሰ ፕሮፓጋንዳ መስማት በርግጥም የት እንዳለንና ወዴት እየሄድንም እንዳለን ያስጨንቃል፡፡ … አቶ ዶክተር ጌታቸው ራሱ ማይም ሆኖ ሰውን አልተማረም ሲል አያፍርም፡፡ ልንገርህ – ይሄ ጀዝባ ዶክተር ነኝ ባይ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ሸሽቶ በኤርትራ ቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ በማያውቀው እንግሊዝኛ በተደጋጋሚ “In generally…” እያለ ከአንድ ዶክተር በጭራሽ በማይጠበቅ ሁኔታ እንግሊዝኛውን በእግሩ ሲያስኬደው እየሰማን እንኳን ስለርሱ ዶክትሬት አልተመራመርንም፡፡ (ይህን ስል ግን አቢይ ዶክተር ይሁን አይሁን የሚያገባኝ ሆኖ ወይም ለርሱ ጥብቅና ለመቆም ፈልጌ አይደለም) – እንግሊዝኛን ካነሳሁ ዘንዳ ደግሞ ይህ ቋንቋ ከዘመኑ ምሁራን ከአብዛኛዎቹ ጋር ኩርፍ ነው መሰለኝ አብዛኛው ሳይማር የተማረ ምሁር ሲሞላፈጥበት ነው የምናይ፡፡ ግን የራስን ጉድ በክርታስ ወረቀት ሸፍኖ ስለሌላ ሰው ገመና ማውራት ስለሚደብር ነው የጌች ነቀፋ የሚያስጠላኝ፡፡ አያስጠላም ጓዶች? ደግሞስ አቢይ ኦሮሞ ሆነ አልሆነ ከጠ/ሚኒስትርነቱ ጋር ምን ያገናኘዋል? አቢይ ካዝኪስታናዊ ወይም የመናዊ ቢሆን እርግጥ ነው ለምን ብሎ መጠየቅ ይቻላል  – ካለሀገሩና ካለዜግነቱ በህገ ወጥ መንገድ ተሾሞ ከሆነ፡፡ አንድን ኢትዮጵያዊ “ኦሮሞ አይደለምና ከቤተ መንግሥት ይውጣልን” ማለት ግን በትንሹ ዕብደት ከፍ ሲል ደግሞ የቁም ተዝካር የሚያስወጣ የቁም ሞት ነው – ስሰማው  በኢትዮጵዊነቴ ብቻ ሳይሆን በሰውነቴ እንዴት በሀፍረት እንደተሸማቀቅሁ አትጠይቁኝ – ደግሞም ያን የፈረደበት “ዶክተር” የሚል ቅጥያ መያዙ ይበልጥ ያናድዳል፡፡ ይህ ሰው ሚስት ካለችው አፍራበት ልክ እንደጆርጅ ፍሎይድ ሚስት ወዲያውኑ ነበር መፍታት ያለባት – አሁንም ትፍታው! እንዲህ ያለ ሙትቻ ምን ይሠራላታል? (ፐ! በሰው መፍረድ ግን እንዴት ቀላል ነው?)  ግን ግን ፖለቲካና ዘረኝነት እስከዚህን ያከረፋል – ማነው ያደነቁራል ልበል? ግዴላችሁም የአቢይ ስም ከመቶም ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ አንዱ ራሽያዊ ደግሞ ነገ ይነሣና “የአቢይ ትክክለኛ ስም ዶስቶቪስኪ ሮማኖቪስኪ ሮማኖቪች ነበር፡፡ አባቱም አቢይ ልጅ እያለ ከሶቭዬት አሰውጥተው ወደ ጋምቤላ ልከውት ነው ስሙ ‹ኡጅሉ ኢቦንግ ቱምክ› የተባለው፤ አሁን ደግሞ አብዮት ካሳዬ በላይነህ አስባሉት” ማለቱ አይቀርም፡፡ አሁንስ ይሄ አቢይ ያሳዝነኝ ገባ! አንዴ በስም፣ አንዴ በአምባገነንነት፣ አንዴ በአስመሳይነት፣ አንዴ በገዳይ-አስገዳይነት፣ አንዴ በሥልጣን አፍቃሪነት፣ አንዴ በውሸታምነት፣ አንዴ በታሪክ በራዥነት፣ አንዴ በጴንጤ ወጋኝነት፣ አንዴ በኦሮሞነት፣ አንዴ በአማራነት፣ አንዴ በትግሬነት … ብቻ የማይከሰስበት ወንጀልና ጥፋት የለም፡፡ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ምናልባት እንደመንጌ ዓይነት ኮምጨጭ ያለ አመራር ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ለማስደሰት ፈልገህ የአመራር ቅኝትህን ካስተካከልክ አንዱንም ሳታስደስት ከሁሉም ጋር እንደተላተምህ ትኖራለህ፡፡ ሁሉንም ለማስደሰት የሚጥር ሰው ደግሞ አንደበቱ ከሀሰት ንግግርና ግብሩ ከባዶ ተስፋ ጋር የቆረቡ ስለመሆናቸው ጥርጥር አይግባህ፡፡ የመቀሌውን ወያኔ ተመልከት፤ አቢይንም እይ፡፡ ብዙ እምናገረው ነበረኝ፡፡ ግን አንድዬ ዕድሜ ከሰጠኝ በሌላ ጊዜ ልመለስበት ቀጠሮ ልያዝና ወደገደለው ልግባ፡፡ …

በዚያን ሰሞን በምሥረታ ላይ እንደሚገኝ ሲነገር ሰማሁና ከነበረኝ መናኛ አንጡራ ገንዘብ ለፓናዶል መግዣ ብቻ ትንሽዬ ሣንቲም አስቀርቼ በቀረው ወደ 30 የሚጠጉ አክስዮኖችን ገዛሁ – በምሥረታ ላይ እንደሚገኝ በተገለጸው አማራ ባንክ፡፡ በወቅቱ የአክሲዮን ግዢው አራት ቢሊዮን አምስት ቢሊዮን ገባ እየተባለ ሲነገር ስለነበር ከገንዘቡ ይልቅ ቁጭቱ ከንክኖኝ እኔም ወጉ ደርሶኝ አክሲዮን ብገዛም እስካሁን ድረስ በመንግሥት ይሁን በአስተዳደር ችግር ባንኩ ሊመሠረት አልቻለም፡፡ የገንዘብ ችግር እንዳይባል ከማንም ሌላ ባንክ የምሥረታ ታሪክ የገንዘብ መጠን ቢበልጥ እንጂ አያንስም (እየተባለ ነው)፡፡ የአማራ ነገር አያሳዝንም? የት ይሂድላቸው?

እናስ ታዲያ ችግሩ ምንድን ነው? አማራ ጋ ሲደርስ ሁሉም ነገር እረብ እሚለው ለምን ይሆን? ኮከቡ ነው ወይንስ የ40 ቀን ዕድሉ? ሙስና ነው ወይንስ የመንግሥት ተፅዕኖ? የባንኩ አመራር ችሎታና ብቃት ማነስ ነው ወይንስ ሌላ የማናውቀው ችግር አለ? በአሁኑ ወቅት እርግጥ ነው ይሄን የፈረደበትን ኮሮና እንደምክንያት ሊጠቀሙበት ይችሉ ይሆናል፡፡ ኮሮና ከመጣ ግን ጥቂት ወራትን ነው ያስቆጠረው፡፡ ችግሩ የጀመረው ከኮሮና በፊት በመሆኑ ይህን ምክንያት መስጠት ውኃ አያነሳም፡፡ ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ መሆኑን ማንም ይረዳዋል፡፡

ለምን በሕዝብ ገንዘብ ይጫወታሉ? ያጋጠማቸው ነገር ካለ ለምን አይገልጹልንምና ቁርጣችንን አያሳውቁንም? ቁርጥ ያጠግባል፡፡ የሚመለከተው አካል በዚህ ጉዳይ ዙሪያ መልስ እንዲሰጥበት መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ ያንን ባንክ ለማቋቋም እኔን መሰል ዜጎች ያለንን ብቻ ሳይሆን የሌለንንም ጭምር ከየትም ቧጥጠን የከፈልነው ተመችቶን አይደለም ተናደን እንጂ  – ሰፊው የአማራ ሕዝብ በጠላቶቹ ሤራ ሳቢያ ያለበትን ድቅድቅ ጨለማ ስለምናውቅ ያንን የዘመናት አፈና “የተበቀልን” መስሎን፡፡ እንደ አካሄድ ደግሞ አንድ ሰው ሁለት ነገር ሊኖረው አይችልም – በሙስና ላይ መናደድ ከዚያም መጻፍና ማጋለጥ በአንድ በኩል ሙስና ውስጥ ተዘፍቆ ያልደከሙበትን ገንዘብ ማካበትና በየካምፓኒው አክሲዮን በመግዛት በሀብት መንበሽበሽ በሌላ በኩል፡፡ ንጹሕ ኅሊናና ሀብታምነት ለየቅል ናቸው፤ ኅብረት የላቸውም፡፡ የድሃን ገንዘብ ቀምቶ እንዳይንቀሳቀስና ጥቅም ላይ እንዳይውል ማሰር ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ለማንኛውም ምሥጢሩን ለሚያውቅና አንዳች ተስፋ ያለው ነገር ሹክ ለሚለኝ ወገኔ አድራሻዬ ይሄውና –

13 Comments

 1. Dagmawi Gudu Kassa
  You know share holders of Amahara Bank are around 140,000. Amhara Bank is to be established as a share company. According to Ethiopian laws, to establish a share company shareholders shall hold founders meeting. Where can Amahara Bank call its 140k shareholders Meeting? Please suggest where it can find such a place. May be amending the law is an option. Or there could be some other alternative. I call upon lawyers and other professionals to recommend a solution to this deadlock. (sorry for writing in English. It is because my computer has no Amharic fonts).

  • Basli, it is okay to use any language you speak as long as your audience understands it.
   I have some worries regarding the obstacles that could come from the incumbent government to impede the free walk of the Amhara. You know, many of us have become suspicious of every move by the so called federal government and we are always afraid of what happens next.
   Therefore, to a lay person like me, the delay might create some inconvenience which could lead to various interpretations.
   The problem you mentioned is convincing but should be communicated properly in time. As you said it, it is practically impossible to have a meeting of 140k people in a hall unless at Meskel Square which is unimaginable. I think this huge number of shareholders is unmanagable. Anywaya, thank you dear for your prompt response and brotherly concern.

   • What I do not understand is the organizers unlimited appetite to attract more new capital and shareholders. The intake appears more than their capacity and is not advisable from business, operation and management point of view.

 2. ጉዱ ካሳ ለቅሶ የማንደርስበት ነገር ነዉ የነገርከን። የአክሲዮኑ ግዢ አመለጠኝ ብዬ ስጸጸት ይህን ነገር አመጣህብኝ? በፈረንጂ አፍ የጻፈልህ ሰዉ ስለ ነገሩ ሳያዉቅ አይቀርም ትንሺ ጠብቅ። ደብቀህን ነዉ እንጂ ግማሹ ያንተ ሳይሆን አልቀረም። ለማንኛዉም እነ በረከትም እስር ቤት ስለሆኑ ግሪሳዎቹም ሌቦቹም በሙሉ ሀይላቸዉ ወደ ሌብነት ለመግባት ትንሺ ጊዜ ሳያስፈልጋቸዉ ስለማይቀር ዋናህን አታጣዉም በትእግስት ጠብቅ።

  ዶክተሩ ያልከዉ ሰዉ አባቱ ዶክተር ተብለዉ እንዲጠሩ ያወጡለት ስም እንዳይሆን እንደ ሻምበል በላይነህ። አንድ በመደበኛዉ አካሄድ የተማረ ዶክተር እንዲህ መንግስት በተገለበጠ ቁጥር አብሮ እየተገለባበጠ የሚኖር አይመስለኝም። አንዴ እየሰለመ አንዴ እየከረስተነ እንዴት ይችለዋል? ከግሪሳዎቹ(ዲጂታል ወያኔ) አንዱ ይሆን እንዴ?

 3. Dagmawi Gudu Kassa I like your articles and about the Amara Bank they know you have invested and you will become rich and you will forget to write about the poor so we want you to write about injustice, fraud, embezzlement and the conspiracy of the COVID 19 that the government is using to promote his agenda for power and control.
  By the way the wife Of George Floyd is not the one who divorced her husband it is the wife of the criminal police Derek Chauvin who put his knees on the victim’s neck until he dies. This was another conspiracy even the Ambulance came and told the police he was dead and still he knees were on victim’s neck they did it on purpose the African Americans will protest and more blacks contract COVID 19 and the want more blacks to die.
  Pray Stay safe and healthy and May God bless and protect Ethiopia.
  Muchfun
  Yegomoraw Lij
  Canada.

  • MUCHFUN A KASSA እግዜር ይባርክህ! ሥንተዜ አንብቤው ያተገለጠልኝን ስህተት ካንተ አሥተያየት ሥረዳ እንዴት እንደተገረምኩ ብታይ! የስህተቱን መንሥኤ ልንገርህ? በሰውዬው ሞት አንጀቴ ከመጨሱ የተነሣ ከአእምሮየ ሊወጣልኝ አልቻለም። ለዚያ ይመሥለኛል የሞተውን ሰው ሚሥት ካልፈታችው ብዬ ድትቅ ያልኩት። አንዳንድ ስህተት እንዲህ ነው፤ የሚገርምህ ከተለጠፈም በኋላ አንብቤው አልተከሠተልኝም። ተባረክልኝ ለማንኛውም – የኔን ቀሪ አስተካክላለሁ።
   Derek Chauvin ባልከው ወንጀለኛ ግን ለካንሥ “ሥም ይቀድሞ ለነገር” እንዲሉ ሥሙ አሥቀድሞ ሰውዬውን (ፖሊሱን) ‘ትምክህተኛ’ ሲል ፈርጆታል! chauvinist ትምክህተኛ ይባል ነበር ዱሮ በኢሃባ ዘመን።
   ሠምሩ ባልከኝ ግን ቅዋሜ አለኝ። ሀብታም ነው ተብዬ ጠላት እንዳታበዛብኝ ሠጋሁ። ወላሂ እውነቴን ነው ሙልጭ ያልኩ የድሃ ባለጠጋ ነኝ። እመብርሃን ምሥክሬ ናት ያልኩት ሃቅ ነው። ግን ወጉ ይድረሠኝ ብሌ ብገባልህ ጉድ ሆንኩ። ያማራምላክ ይክሠኛል ግዴለም አንተው! ገንዘብ እንደሁ ጠፊ ነው።

 4. The great Gudu Kassa,

  Thanks again for this great article. Just a little correction. George Floyd`s wife did not file a divorce. In fact, I heard George had a girl friend, not a wife. I think you mistook the wife of the police, who was accused of murdering George, for George`s wife. Anyways, it is not a big deal; just for the record.

  • አመሠግናለሁ መሡ! ከፍ ሲል ለብዙ ደሥታ (MUCHFUN) የሰጠሁትን አሥተያየት እዚህ ላለመድገም ፈልጌ ነውና ያን እይልኝ። አየህ(ሽ)! “ታፍ ተወጣ አፋፍ” እሚባለው ለዝህ ነው! ስለዝህ ሰዎች በሚሠሩት ሥራ መጠንቀቅ አለባቸው። ፍሎይድን የጠቀምኩ መሥሎኝ (through my subconscious, of course) ለካንሥ ሞኝነቴን ገልጫለሁ። እናም በዚህ ይሥተካከልልኝ ፥ “የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ የዴሬክ ቾቪን ሚሥት ባሏን በወንጀሉ ምክንያት ወዲያውኑ እንደፈታችው ሁሉ የዚህ ገልቱ ዶክተር ተብዬ ሚሥትም ትፍታው…” ። ደግሞ እሱን ብሎ ባለሚሥት! ቱ! የሰው ልክ አያቅማ፤ ይህ ንገሩኝ ባይ።

 5. “በህክምና አልባሳት ሆን ተብሎ በነቢልጌትስ በሚሰራጭ ኮሮና ቫይረስ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ ምሥጢራውያኑ ድርጅቶች ጦርነቶችንና ፍብርክ በሽታዎችን ጨምሮ በተለያዩ ዘዴዎች ከሲሶ በላይ የሚሆነውን የዓለምን ሕዝብ ፈጅተው የራሳቸውን የሰይጣን መንግሥት ለመመሥረት ቅድመ ሁኔታዎችን ጨርሰው ወደ ትግበራው መግባታቸውን ካነበብነውም ከሰማነውም እያጣቀስን አንዳንዶቻችን ሰሚ አጣን እንጂ ብዙ ለፍልፈናል፡፡“

  የጠላ ቤት ጋዜጠኝነትህ እንደተጠበቀ ሆኖ I honestly never thought you are that stupid. A little man like you will never tarnish the good work of Bill Gates. Ethiopians are generally smart people . They are not fooled by your trash .

  • እውነቱ፥ ሠውን ከምትሣደብ አንቀልባ ገዝተህ ወዳጆችህን እነቡል ጌትስን አዝለሃቸው ብትዞር አይቀልህም? ወንድማችን ጉዱ ካሳ ጠላ ይጠጣ ይሆን እንድሆን እንጅ የጠላ ቤት ጋዜጠኛ እንኩዋንብ እይመሥልም፣ አይን አይቶ ልብ ይፈርዳል ይባላል እኮ አውዬ። ይልቁን ወሬውንና ሥድቡን ገታ አድርግና ንባብ ላይ አተኩር። እሱ አያመልጥህም ትደርሥበታለህ፣ የት ይሄድብሃል? በዚያሥ ላይ ደግሞ የዘመኑ አበሻ አይደለህ? ለሥድብ እናንተን ማን ደርሦባችሁ? አሉላ ሠሎሞንን አታየውም? ምላሡ ለሥድብና ዛቻ ሢሆን እንዝርት እኮ ነው።በል ከምሥኪኑ አዝናኝ ጦማሪያችን ራሥ ወረድ በል አንት ወረትህና ሃያትህ ያለቀ ወያኔ!

  • Ewnetu, it is fine that you have quoted some sentences that fit and substantiate your position. But I am also obligated to remind you of the sentences found next to your quotation. “…ሰይጣን በተፈጥሮው ሰዎችን ማዘናጋትና ማደደብ ዋና ሥራው ስለሆነ ብዙው የሀገራችንና የዓለማችን ጎጋ ዜጋ አልገባውም፤ እንደስካሁኑ ሁኔታ ከሆነ ደግሞ አይገባውምም፡፡…”
   And it would have been didactic if your tone of opposition had had a little bit touch of modesty or decence. Badmouthing doesn’t help us teach each other; it could rather exacerbate relations and lead them to become poorer and poorer.

 6. እውነቱ፥ ሠውን ከምትሣደብ አንቀልባ ገዝተህ ወዳጆችህን እነቡል ጌትስን አዝለሃቸው ብትዞር አይቀልህም? ወንድማችን ጉዱ ካሳ ጠላ ይጠጣ ይሆን እንድሆን እንጅ የጠላ ቤት ጋዜጠኛ እንኩዋን እይመሥልም፣ አይን አይቶ ልብ ይፈርዳል ይባላል እኮ ሠውዬ። ይልቁን ወሬውንና ሥድቡን ገታ አድርግና ንባብ ላይ አተኩር። እሱ አያመልጥህም ትደርሥበታለህ፣ የት ይሄድብሃል? በዚያሥ ላይ ደግሞ የዘመኑ አበሻ አይደለህ? ለሥድብ እናንተን ማን ደርሦባችሁ? አሉላ ሠሎሞንን አታየውም? ምላሡ ለሥድብና ዛቻ ሢሆን እንዝርት እኮ ነው።በል ከምሥኪኑ አዝናኝ ጦማሪያችን ራሥ ወረድ በል አንት ወረትህና ሃያትህ ያለቀ አዲሥ ግልብጥ ወያኔ!

 7. Why should we have a bank with an ethnic tag? Amhara has become Ethiopian over hundreds of years of fighting, expansion, contraction, assimilation, integration etc. Why do you need to go back in history and dig for a ‘dead’ tribe from the grave? Over hundred years of intermingling with its Ethiopian brothers and sisters from all walks of life and each corner of the country , this social,cultural and and linguistic group has already transformed itself to a much broader and bigger entity, Ethiopia. The only remnant of this group is the language Amharic, which is no more Amhara, but Ethiopian and widely spoken in every corner of the country. Why don’t you call this new bank Queen of Sheba, Emperor Tewodros, Emperor Yohannes, Emperor Menilik, Empress Taitu, Emperor Haile Selassie, Ras Alula Abanega, Bitwoded Ali Mirah , Dej. Omar Semeter, Ras Abebe Aregay ,General Jagama Kello , Dej.Belay Zeleke, Abdisa Aga or Zeray Asgedom & Abrha Deboch Bank etc?. In so doing, you will have a colorful and inspiring history of unity in diversity to write, on the walls of a bank with such glorious and diverse names behind.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.