“የተቃውሞ ሰልፉን እያስተባበሩ ያሉ ቡድኖች ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳጣት በግብጽ የሚደገፉ ናቸው” አቶ አዲሱ አረጋ

adisuየተቃውሞ ሰልፉን እያስተባበሩ ያሉ ቡድኖች ሕዝቡን ተጠቅመው የራሳቸውን የስልጣን ፍላጎት ለማሟላት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮሮናቫይረስ መከላከልና ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካላት እየተጠሩ ያሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫውን የሰጡት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ”ሕዝቡ ከአገር ጥቅም በተቃራኒ ከቆሙት አካላት ሊጠነቀቅ ይገባል” ብለዋል።

የተቃውሞ ሰልፉን እያስተባበሩ ያሉ ቡድኖች ሕዝቡን ተጠቅመው የራሳቸውን የስልጣን ፍላጎት ለማሟላት እየተንቀሳቀሱ ያሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

”ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዱ በግብጽ የሚደገፍ ሲሆን ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳጣት የሚንቀሳቀስ ነው” ብለዋል።

አቶ አዲሱ ሁለተኛውን ቡድን ‘ወያኔ’ በማለት የገለጹት ሲሆን ”ይህ ቡድን ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያሰቃይና ሲበዘብዝ የቆየ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ይኸው ቡድን የለመደው ጥቅም ስለቀረበት ‘ስልጣን ይዞ ያለውን መንግስት ለማዳከም በተለያየ መንገድ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።

”ሶስተኛው ቡድን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ መራዘሙን መነሻ ምክንያት በማድረግ በአቋራጭ ስልጣን የሚፈልጉ አካላት ናቸው” ብለዋል።

በመሆኑም ሕዝቡ እየተጠራ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ እነዚህ ሶስት ቡድኖች ተሰባስበው የጠሩት መሆኑን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።

”የክልሉ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄ ካለው በትክክለኛው መንገድ ያቅርብ” ያሉት አቶ አዲሱ፤ ከዚህ ውጪ ባሉት ጉዳዮች ላይ መንግስት ሕግን ለማስከበር ‘አቅሙም፤ ችሎታውም’ አለው ብለዋል።

በክልሉ እስካሁን የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የተሰራውን ስራ በተመለከተም በመግለጫቸው አካተዋል።

በዚህ ረገድ እስካሁን በክልሉ ሰፋ ያሉ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎች ቢከናወኑም የሚፈለገውን ያህል የባህሪ ለውጥ እንዳልመጣ ጠቁመዋል።

አሁንም የገበያ ቦታዎች፣ ሰርግ መሰረግ፣ ለቅሶ ማከናወንና በትራንስፖርት አጠቃቀም በኩል አሳሳቢ ሁኔታ እየተስተዋለ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሆኖም የክልሉ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው የተገኙ 3 ሺህ 700 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ተገቢውን ቅጣት ማሰጠቱን ተናግረዋል።

”በተጨማሪም ከ27 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ክልከላዎችን ተላልፈው በመገኘታቸው በጥቅሉ 19 ሚሊዮን ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል” ብለዋል።

ቫይረሱን ከመመርመር አንጻርም ሰባት የምርምራ ጣቢያዎች በስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን ስምንቱ ደግሞ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል።

በክልሉ 10 ሺህ ሰዎችን በለይቶ ማቆያነት የሚያገለግሉ ቦታዎች፣ 22 ሆስፒታሎች የተዘጋጁ ሲሆን 5ቱ ስራ መጀመራቸው ተመልክቷል።

በክልሉ እስከ ዛሬ ድረስ 83 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 15 ሰዎች አገግመዋል።

68 ሰዎች ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

(ኢፕድ)

5 Comments

 1. አቶ አዲሱ ያሉት ሁሉ ትክክል ነዉ በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣን ነዎት እነዚህን ወስላቶች እነዚህን የጠላት ሰላዮች በጽሁፍ መግለጽ ነዉ አገርን ወደ ምስቅልቅል ከማዉጣታቸዉ በፊት እግር ተወርች አስሮ ማቆየት ነዉ? ሀገር ወዳዱ ከዚህ ሱዳን መጣ ይላል ከዛ ግብጽ አለምን ሲያሳክር በያለበት ያቅሙን ያህል ይመክታል አጠገባችሁ ቁጭ ብለዉ እየተዋወቃችሁ እነዚህን ወንጀለኞች ባግድሞት መናገር ምን ማለት ነዉ? ያዉቋቸዋል እናዉቃቸዋለን ሰሜን የመሸጉት የትግሬ ወኪል ነን ባዮች፤ ዳዉድ ኢብሳ፤መራራ ጉዲና፤በቀለ ገርባ፤ ጁዋር መሀመድ፤ ዲማ ነገዎ፤ኦነግ ሸኔ፤ ኦነጋዉያን፤አረጋዊ በርሄን የመሳሰሉ ያደፈጡ ወንጀለኞች ናቸዉ።
  እነዚህ ወንጀለኞች ድጋፍ ያላቸዉ አይምሰሎት ቄሮ ከ2 ቀን በላይ አይጮህላቸዉም። እንዲህ ያለ ነገር በትግሬዎች ወይም በመንግስቱ ሐይለ ማርያም ጊዜ ይሞከር ነበር? ሀገር ወዳዱና አማራ ላይ ፈጣን እርምጃ ከመዉሰድ እነዚህን ወንጀለኞች ጠፍራችሁ ብታስገቡ አገርም ሰላም ያገኛል እናንተም እፎይ ትላላችሁ ድምበርም ይከበራል አባይም ይገነባል ግብጽም ልመና ይገባል።

 2. መሪዎቹ ያለ አንዳች ማመንታት ከሃዲዎቹ ላይ ፈጣን እርምጃ መውሰድ አለባቸው ። ከ ጠላት ጋር ከ ማበር የበለጠ ምን ወንጀል ይኖራል ? ይህን ከ አላደረጉ እራሳቸው ተባባሪዎች ናቸው ።

 3. ይሄ “ካላረፋችሁ እርምጃ እንወስዳለን” ብሎ ልክ እንደ ወያኔ እልፍ የመግለጫ ማስፈራርያ ነው እስካሁንም አዳሜን በኢትዮጵያ አናት ላይ ፊጥ ያደረጋቸው። እስቲ ምን ተደረገ በግልጽ የሲናይን ልማት በተመኘው ሰውዬ? የመናገር መብቱ ነው እንዳልል የግብጽ ጦር በግልጽ አባይን ሊያደባይ እየዛተ ነው። እናም ለጠላት አልወገነም ይህ ሰውዬ? በኢትዮጵያ አምላክ ካሁን በሁዋላ ሬዲ ስትሆኑ፣ እርምጃ ከወሰዳችሁ በሁዋላ ብቻ ውጤቱን ንገሩን አቶ አዲሱ። ታዬ ደንደአን እዛች መንበር ላይ ብታስቀምጡት እስካሁን ባልተቀለደብን ነበር። ሰዎቹ ምን ያድርጉ በሽፍታና ወያኔ ሴራ የሚያልቀው ድሃውና አቅመደካማው ነው በዖሮምያ ምድር። የዴሞክራሲያችን ምጥቀት በዚሁ ምድር ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ነው የቀረው ያውም በዘመነ ኮረና። እናም ከመንግስት ጋር በሚፈጠረው ግብግብ አሁንም እንደከርሞው ዖሮምያ የጦርነት ቀጠና ትሆናለች። የፈለጉትም ይህንኑ ነው። አስቀልዱበት በህዝባችን። ፈጣሪ ይፍረደው።

 4. Dear Addisu
  I am 100% believe that your PM and government is the one compromising Ethiopia National Interest to foreign adversary serving as a banda for Egypt as well western and arab countries. Your accusation no more than Yee Abbiyeen La Emmiyee.

 5. It’s a shame you don’t have a donate button! I’d definitely donate
  to this brilliant blog! I suppose for now i’ll settle for bookmarking and adding your RSS feed to my Google account.
  I look forward to new updates and will share this website with my
  Facebook group. Chat soon!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.