/

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዝ መድኃኒት እየሠራሁ ነው አለ

101662266 1656344434516898 9141141048272093184 nመድኃኒቱ በአፍና አፍንጫ አካባቢ ያለውን ጀርምና ባክቴሪያ የሚገድል ነው ተብሏል
****************************
አዲስ አበባ፡- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የአፍ መጉመጥመጫና ለአፍንጫ የሚሆን መድሃኒት እየሠራ መሆኑን ገለፀ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሕክምና መምህር የሆኑትና ምርምሩን በበላይነት የሚመሩት ጠቅላላ ሐኪም ዶክተር መስፍን በኃይሉ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚጠቅም ለአፍ መጉመጥመጫና ለአፍንጫ የሚሆን መድሃኒት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ምርምር በማድረግ እየሠራ ይገኛል።

እየተሠራ ያለው መድኃኒት በአፍና በአፍንጫ አካባቢ ያለውን ጀርምና ባክቴሪያ እንደሚገድልና ለኮቪድ 19 መከላከያም መፍትሄ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር መስፍን፤ የምርምር ሥራው በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማለቁንና በቀጣይ ለጤና ሚኒስቴር ለማስረከብ በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ዶክተር መስፍን ገለፃ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ለቫይረሱ ሕክምናም ሆነ አስተማማኝ ክትባት አልተገኘም የሚሉት ዶክተር መስፍን፤ በዋናነት መከላከልን መሠረት ያደረጉ እርምጃዎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

እንደ ዶክተር መስፍን ገለፃ፤ በዚህ መነሻ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ኮቪድ 19 አስመልክቶ መከላከል የሚቻልበት አማራጭ መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት ይዞ እየተንቀሳቀስ ይገኛል።በዓለም አቀፍ ደረጃ በመከላከያ መርህ ከሚታወቁ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ የተረሳና አጥጋቢ ሊሆን የሚችል የመከላከያ መንገድን ለማስተዋወቅም በምርምር የተደገፈ መድኃኒት እየሠራ ነው።በዚህም አዲስ ፀረ ጀርም ኬሚካል ከባህላዊ ህክምና ጋር በማጣመር አገር በቀል ከሆኑ ተክሎች በመሥራት የላብራቶሪ ፍተሻ እየተደረገበት ይገኛል።

መድኃኒቱ የሚሠራው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሠሩ የጥናት ውጤቶችን እንደ ማስረጃ በመያዝ ነው ያሉት ዶክተር መስፍን፤ ሰዎች ምንም ምልክት ሳያሳዩ ኮሮና ቫይረስ እየተገኘባቸው ስለሆነ እየተጋጀ ያለው መድኃኒት የፀ ጀርም ኬሚካል ምራቅን ማካም እንዲያስችል ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚኒሶታ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ህክምናው በምራቅ አማካኝነት ወደ ውጭ የሚወጡ ጥቃቅን ነጠብጣቦችን የማከም አቅም እንደሚኖረውና ከዚህ በተጨማሪም ሰው እንዳያስነጥስ በማድረግ ወደ ውጭ የሚወጣውን ቫይረስ መቀነስ እንደሚያስችልና ቅቡልነትን ካገኘና ጥቅሙ ከታወቀ በኋላ አገልግሎት ላይ እንዲውል መንግሥት በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት የሚከናወን መሆኑንም ገልፀዋል።

በደብረ ብርሃን ዪኒቨርሲቲ የአንኮበር መድኃኒት ቅመማና ብዝኃ ህይወት ክብካቤ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶክተር አማረ አያሌው በበኩላቸው፤ ለአፍ መጉመጥመጫና ለአፍንጫ የሚሆን መድሃኒት የምርምር ሥራው በተመራማሪ ዶክተር መስፍን በኃይሉ ተነሳሽነት የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለያዩ ሀሳቦች ታግዞ እየተሠራ እንደሆነና በዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ማኅበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪነት እንዲሁም በአንኮበር መድኃኒት ቅመማና ብዝኃ ህይወት ክብካቤ ፕሮጀክት አማካኝነት እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም መሰል ተሞክሮዎችን በማድረጉ ውጤታማ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ዶክተር አማረ፤ የአሁኑም የምርምር ውጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይንሳዊ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው የባህል ህክምና ላይ እውቀቱ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች በማሳተፍ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንና፤ ቀጣይነት ባለው መልኩ አገርን ሊያግዙ የሚችሉ መሰል የምርምር ሥራዎችን ለማበርከት እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር አማረ፤ ተመራማሪዎችን ለማበረታታትና ዩኒቨርሲቲውንና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግም የባህል ህክምናውን ከሳይንሱ ጋር የማጠመር ሂደትን በስፋት እንደሚያከናውንም ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012
አዲሱ ገረመው

 

1 Comment

  1. It is greatly encouraging and appreciable ! But it is necessary to be very careful not to give a wrong impression that this is a medication that serves to cure the virus or to totally prevent the virus . The phrase “medhanit tresera “is very misleading . To my understanding , the the result of the research is something that greatly helps to reduce the seriousness of the virus by trying to either weaken or kill before it goes into our respiratory organs .
    So , the news is great! But it should not send a wrong message to the people who are lvulnerable to wrong perception and expectation due to lack of literacy and accurate information . Both traditional and social media need to be careful about how they select words and phrases before they publish or broadcast their news and and news analysis . Once again, to tell the people that “medhanit tegegne or testera “ Is not only wrong but dangerously misleading!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.