በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ መከላከል ተቋማዊ አሰራር በጣም ይጎድለዋል – ሰርፀ ደስታ

covid 19እስካሁን በምናየው የኮሮና ሁኔታን በኢትዮጵያ የሚቀርበው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴሯ የግል ቲዊተር ነው፡፡ ከጅምሩም እንዴት እንዲህ ያለ ሪፖረት አቀራረብ እንደተመረጠ አይገባኝም፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የመንግስት ተቋም እንጂ የሚኒስቴሯ የግል ንብረት አይደለም፡፡ ይሄ  በብዙ ቦታ የምንታዘበው ተቋማዊ ያልሆነ አሰራር ነጸብራቅ ስለሆነ ለብዙዎቻችን ስህተት መስሎ አልታየንም፡፡ ሚኒስቴሯ እንደሚኒስቴር የእለት ተእለት መረጃ ማቅረብ ይችለሉ፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ ያለው መረጃ ሲሆን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጅ ልዩ የሚኒስቴሩ መረጃ ማቀበያ ዌብ ሳይት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ካልሆነ በተቋሙ ሥም በተዘጋጀ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ መቅረብ አለበት እንጂ በሚኒስቴሯ  የቲዊተር አካውንት መሆን የለበትም፡፡ መረጃው የተቋሙ እንጂ የሚኒስቴሯ አደለምና፡፡ ከዚህ በተረፈ መረጃው በተራ ዘንጠረዥ መኆኑ ቀርቶ የሥርጭቱን የጊዜና (ሪል ታይም)ና ጂኦገራፊያዊ ስርጭት ሁኔታ በሚያሳይ መልኩ ቢሆን መረጃው ሙሉ ይሆናል፡፡ ይሄን ሊሰሩ የሚችሉ የኮምፒር ባለሙያዎችን በቦታው ማስቀመጥና የመረጃ ልውውጡን ጥራትና ፍጥነት መቀየር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ እንደሚገባኝ ሁሉም አገራት በዚህ አይነት እየሰሩ ነው፡፡ ሚኒስቴሮቹም ሆኖ ሌላው ባለስልጣን በእንዲህ ያለ ቦታ ተገቢ ሥራ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እደግመዋለሁ ይሄ መረጃ የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት እንጂ የሚኒስቴሯ አደለም፡፡ ተቋማዊ ያልሆነ አሰራር ነው፡፡ ሌላው የሚኒስቴሩን ማህተብ ማስቀመጥ ትክክል አይደለም፡፡ ይሄ በመጀመሪያዎቹ ሪፖረቶች ነበር መሰለኝ አሁን ሳይቀር አልቀረም፡፡ ራሱን የቻለ የመረጃ ቋት ወይም መረጃ ማስተላለፊያ በሚኒስቴሩ ሥም ካለ ያ በራሱ በቂ ነው፡፡ መረጃው ግን መቼ፣ የትና፣ ስንት የሚሉትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ለጥንቃቄም ይረዳልና ነው፡፡

በተረፈ ኢትዮጵያ ቀስ እያለ ችግሩ እየገዘፈ የመጣ ይመስላል፡፡ አብዛኞቹ መረጃዎች ለከተሜው እንጂ ሕዝባችን በብዛት የሚኖረባቸው ገጠሮች ምን ያህል እንደሚጠቅሙ አላውቅም፡፡ አብዛኛው ሕዝብ ኢነተርኔቱ ቀርቶ ሬዲዮም ላይኖረው ይችላል፡፡እስካሁንም እንደዛ እየቀረበ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ግን በተሻለ በሬዲዮና ቴሌቪዥን ሙሉ መረጃዎችን በየሰዓቱ ማቅረብ ጥሩ ነው፡፡ በጊዜና በቦታ የስርጭቱን ሁኔታ ገላጭ ዌብሳይት ወይም ሌላ የመረጃ መለዋወጫ ከተዘጋጀ የአካባቢ የኤፍኤም ሬዲዮኖችን ጨምሩ በአገሪቱ በሚሰሩ ሚዲያዎቹ ሁሉ በተለያየ ቋንቋ ከመረጃ ቋቱ እያዩ ለማስተላለፍ እድል ይሰጣል፡፡ የመረጃ ምንጩ ግን በተደራጀ ሁኔታ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፖለቲካ፣ ሐይማኖት፣ ዘር፣ በሰው ልቦና ውስጥ።

ሌላው ሕዝቡ በባሕላዊ መልኩ ለጉንፋን የሚጠቀምባቸውን ለዚህ በሽታ ቢጠቀምባቸው መልካም ነው፡፡ ሆኖም እነዚህ ግብዓቶች እንደልብ ላይገኙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል፡፡  ቢገኙም ገንዘብ እንደፈለጉ ለሚረጩ እንጂ ለለፍቶ አዳሪው የማይቀመሱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ እየከፋ ከመጣ ነገር ቢኖር መኖር አለመኖሩን እንኳን ሳያስብ በከፋ ስግብግብነት መበከልና እንደሰው ለሌላው አለማሰብ ነው፡፡ እነዚህ ግብዓቶች በሻይ መልክ በአነስተኛ መጠን እንጂ በኩንታልና በመጋዘን አደለም የሚፈለጉት፡፡ ሆኖም ገንዘብ ያላቸው ወይም ደግሞ እናተርፋለን የሚሉ ስግብግብ ነጋዴዎች ከገበያ ሁሉ ሊያጠፏቸው ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መንግስት እንደመንግስት እነዚህን ጨምሮ ሌሎች አቅርቦቶችን ሁሉ በስግብግቦች ከገበያ እነዳይጠፉ መቆጣጠር አለበት፡፡ ሆኖም እሰከዛሬ እንደምናየው ለእንደዚህ ያለ ውንብድና ዋና ተባባሪና ሁኔታዎችን የሚያመቻች የመንግስት መዋቅር ስለሆነ መንግስት እንዲህ ያሉ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ለማሰብ ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ ሕብረተሰቡ እርስ በእርሱ መተሳሰብን በዚህ አጋጣሚ ቢጠቀምበት ራሱን ያድናል ለሌላም ጊዜ ይረዳዋል፡፡

የባሕል ሕክምና አዋቂዎች ነን ብለው በየሚዲያው በተደጋጋሚ የታዩ ነበሩ፡፡ አሁን ምን እየሰሩ እንደሆን አላውቅም፡፡ መጀመሪያ ላይ እንደውም የሳይንስና ጤና ሚኒስቴሮች በባሕላዊ ሲሰራበት የነበረውን መድሀኒት በዘመናዊ መልክ ምርምር አደርገን ጨርሰናል ተዘጋጅተናል ብለው ነበር፡፡ እንደዛ በድፍረትና ሀላፊነት በሌለው ሁኔታ መናገር ቀላል ነው፡፡ ግን ችግርን ለማስወገድ አንድም ቦታ እየተሰራ ለመሆኑ በጣም አጠያያቂ ነው፡፡ እንግዲህ በአላስፈላጊ ተስፋ መዘናጋቱን ትቶ  ሕዘቡ እሰከዛሬ በጉንፋን ላይ ያሉት ልምዶች ቢጠቀምባቸው ጥሩ ነው፡፡ በጉንፋን ስኬታማ የሆነ ባሕላዊ ሕክምና በዚህ በሽታ ቢያንስ አስከፊነቱን ለመቀነስ ያስችላልና ነው፡፡

 

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ለዓለሙ ሁሉ ምህረቱን ያውርድ! አሜን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ሰርፀ ደስታ

3 Comments

  1. አንተ ግን ምንድን ነው የምታመሰግነው ሁሌ ቅጥ ያጣ ትችትህን እና ዘለፋህን ትጥፋለህ ጥሁፎችህ ሁሉ ሚድያ የማይመጥኑ ተራ መደዴ ናቸው በጥላቻ ክፉኛ ሰክረሀል ይህ ደግሞ ስነልቦናህን አቃውሶት የሚታይህ ሁሉ ጥቁር ነገር ነው በእውነት ለትንሽ ጊዜ አረፍ በልና እራስህን ገምግም ከዛ ሚዛናዊ የሆኑ ጥሁፎችን ፖስት አድርግ

  2. ጠሃፊው ስለኮረና መከላከል አወቃቀር ርዕስ ነው የሰጡት፡፡ የሚያወሩት በዋናነት ስለ መረጃ አሰጣጥ ነው፡፡ የመረጃ አሰጣጥ ችግር እውነት ከሆነ ይስተካከል፡፡
    ነገር ግን በመንገስት መዋቅር ኮረናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመንግስት እየተደረገ ያለው ርብርብ እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡ ሁሉም ሚኒስቴር መ/ቤቶች ሥራቸውን በዋናነት ኮረናን መከላከል አድርገዋል፤ በየቀኑ በየሚዲያው እንሰማቸዋለን፡፡ ስለዚህ በጣም ጥሩ ነው በርቱ፡፡
    ይልቅስ እኛ እነሱ የሚሰሩትን፣ ጭንቀታቸውን ብንረዳ፣ የሚሰጡትን ት/ት በተገቢው እየፈጸምን አይደለም፡፡ ስለዚህ ክፍተቱ በመንግስት ሳይሆን በዋናነት በእኛ ነውና አንተን ጨምሮ ብናስተካክል፡፡ አንዳንድ ጀሌ በብዛት አለን የሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በኮረና ዙሪያ መንግስት ድክመት ታይቶበት፣ ብዙ ህዝብም አደጋ ላይ ወድቆ እንዲገኝ አድፍጠው እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ለዚያም ነው አንድም ስራ ሲሰሩ ወይ፣ም መንግስትን ሲያግዙ የማናየቸው፡፡ በኛ ሞት ስልጣን ጥማታቸው ይሳካል ብለው አስበዋል፣ ግን አይሳካም

  3. We Ethiopians need to stop the denial and we need to face the reality. Most Ethiopians are tired of living, life is becoming unbearable for most.
    Life in Ethiopia is becoming too expensive, too competitive , too evil so we do not care if we live or if we die. Especially those of us who got no children who amount to almost two thirds of the total population got no interest in surviving this pandemic.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.