“አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአንድ ወገን ሪፖርትን ከማንጸባረቅ ሚዛናዊና ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ መጠቀም ነበረበት” . የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ

Amnesty 1“አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአንድ ወገን ሪፖርትን ከማንጸባረቅ ሚዛናዊና ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ መጠቀም ነበረበት” ሰል . የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው እንዳለው “አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በመንግስት ኃይሎች የተፈጸመ የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ” ብሏል።

ይሁን እንጂ ሪፖርቱ ሚዛናዊነት የጎደለውና የተሳሳተ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

“ሪፖርቱ የአንድ ወገን መረጃን ብቻ የያዘ፣ ሚዛኑን ያልጠበቀና የተሳሳተ በመሆኑ ሊታረም ይገባል” ብለዋል።

ሪፖርቱ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው በተለይ ነፍጥ ያነገቡ ታጣቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብና በመንግስት ኃይሎች ላይ የሚፈፅሙትን ወንጀል መካዱን አስታውቀዋል።

ለዚህም ድርጅቱ በሪፖርቱ ላይ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ አካባቢ 38 ሰዎች መገደላቸውንና ከእነዚህ ውስጥ 16 ሰዎች በመንግስት ኃይሎች የተገደሉ መሆኑን ከገለጸ በኋላ ስለሌሎቹ ሰዎች ምንም ሳይል ማለፉን ለአብነት ጠቅሰዋል።

“ሪፖርቱ ሚዛናዊ ያልሆነና በተቃዋሚ ጎራ ያሉ ግለሰቦች የራሳቸውን ሀሳብ ያንጸባረቁበት በመሆኑ በመንግስት በኩል ተቀባይነት የለውም ብለዋል አቶ ጌታቸው።

በክልሉ ውስጥ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉበት፣ የታገቱበትና የት እንደደረሱ የማይታወቅበት ሁኔታ ቢኖርም ሪፖርቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ያለማለቱንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

ድርጅቱ ከመንግስት የወሰደው መረጃ አለመኖሩን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፣ ያወጣው ሪፖርት መንግስት የሰራቸውን ሥራዎች የሚያንቋሽሽ በመሆኑ እንደገና ሪፖርቱን ማጤን እንዳለበት ተናግረዋል።

“ሪፖርቱ መንግስትን ለመጉዳትና ሌላውን ወገን አጉልቶ ለማሳየት የተደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ ሊስተካከል ይገባል” ሲሉም ገልጸዋል።

“አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ከሆነ ሁሉንም ማካተት ነበረበት’ ያሉት ሃላፊው፤፣ ያወጣው ሪፖርት ግን የአንድ ወገን ወገንተኝነት የታየበት መሆኑን አመልክተዋል።

“ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰራ በመሆኑ ሁሉንም ያከተተ ሪፖርት ማውጣት ሲገባው በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚፈልጉ ኃይሎችን ፍላጎት ያበረታታ ሪፖርት ነው” ብለዋል።

የክልሉም ሆነ የአገሪቱ ህዝብ በሪፖርቱ የተሳሳተ ግንዛቤ ሊይዙ አይገባም ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ድርጅቱ ከክልሉ መንግስት ተጨባጭ መረጃን ተጠቅሞ ሪፖርት የማድርግ ፍላጎት ካለው የክልሉ መንግስት ያለውን መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ መሆኑንም ነው ያረጋገጡት ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

(ኢፕድ)

2 Comments

  1. ጃዋርና ተከታዮቹ በማስፈራራት እጅ መጠምዘዝና ፍላጎትን ማሳካት ችለው እንደነበር አንዘንጋ፡፡ ለዚህም የ12ና ክፍል ፈተና ውጤት፣ የት/ት ፍኖተ ካርታ፣ እና ሌሎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ሁሌ ይህን የማታደርጉ ከሆነ እናሳምጻለን፣ ጥሪ እናደርጋለን፣ አመጽ እናስነሳለን ይሉናል፡፡ ይህም የልብ ልብ ሰጥቷቸው መንግስት አቋሙን በገለጸ ቁጥር ያስፈራሩናል፡፡
    እስከዛሬ የጠመዘዙን ይበቃል እንበላቸው፡፡ አገራችን የኮረና ችግር ላይ ነች፡፡ ፖለቲከኞች ዛሬም የስልጣን ጥማችሁን ለማርካት ብቻ ከመሄድ እስቲ ስለወረርሽኙ ህዝቡን አስተምሩት፣ ደጋፊዎቻችሁን ርዳታ ሰብስቡለትና ደሃውን እርዱ፤ ስለአባይ ግድብ ስራ ስሩ፡፡
    እጅግ በሚያስገርም ደረጃ ስራ እንኳን የሌላቸው ወጣቶች ደሃውን ለመርዳት እርዳታ ሲያሰባስቡና ሲረዱ ሚሊየኖች ደጋፊ አለን የሚሉት ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች/አክቲቪስቶች ዝምታን መምረጥ የሚያመለክተው መንግስት በመከላከሉና መቆጣጠሩ ረገድ እንዳይሳካለት በማሰብ የመነጨ እንጂ መሥራት ከብዷቸው አይደለም፡፡ አመናችሁም አላመናችሁም አብይና ህዝቡ ኮረናን አሸንፈን ያደፈጣችሁ ፖለቲከኞችን እንደምናሳፍር ፍቃደኛ ከሆናችሁም እንደምትማሩበት አትጠራጠሩ

  2. Ato Getachew, you raised a fair point here. But as a communication head of the regional state, I think it is your duty to avail information to everyone including Amnesty International, on the human rights atrocities Jawar, Jal-Mero, Gerba, and their herds are committing by causing and celebrating the killings of government officials, foreign and local investors in broad daylight as well as the kidnapping of university girls whose whereabouts are still unknown. You better be proactive and tell the true story on the ground to Ethiopians and to the world, before crooks like JA-WAR make up the stories for you. Look how he is making ‘good’ use of the Amnesty report, with all due respect to the good work they do by the way, for his own narrow political gains to discredit your government day in and day out on his extremely tribal TV station you guys ‘ironically’ have allowed him to operate. I think you need a better organization in managing your communications, as he is beating you on that front, not because he is telling the truth, but he is a master spinner who makes a living out of it. You can catch him red-handed any time, if you wish, and charge him legally on the hate propaganda and inciting violence among Ethiopians, he is engaged in sleeplessly 24/7. I don’t really understand why he is being allowed to continue sowing seeds of hatred and violence among Ethiopians. Democracy? I doubt it, as I am not even sure if democracy comes before survival as a nation.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.