አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርቱን እንዲያጤነው የአማራ ማሕበር በአሜሪካ አሳሰበ

101113523 1301160676756992 7380342291002556416 o አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርቱን እንዲያጤነው የአማራ ማሕበር በአሜሪካ አሳሰበግንቦት 22/2012 ዓ/ም

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግንቦት 21/2012 ዓ/ም ያወጣው ሪፖርት በርካታ ክፍተቶች ያሉበትና የተዛቡ የአንድ ወገን መረጃዎችን ያካተተ በመሆኑ የመረጃ ምንጮቹን እና አሰራሩን እንዲያጤን የአማራ ማሕበር በአሜሪካ ጠይቋል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለተጎዱና ድምፅ ላጡ ዜጎች ድምፅ ሆኖ መቆየቱን ያወሳው የአማራ ማሕበር በአሜሪካ፤ ይሁን እንጅ ትናንት በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ላይ ያወጣው ሪፖርት በርካታ ክፍተትና ስህተቶች ያሉበት እንደሆነ የአማራ ማሕበር በአሜሪካ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡ አምነስቲ በአማራ ክልል በተለይም ሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው ችግር ላይ ያቀረበው ሪፖርት ላይ የታለፉና የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ ትኩረት ያደረገው የአማራ ማሕበር በአሜሪካ ሪፖርቱ ከግጭቱ መነሻ ምክንያት ጀምሮ በተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በዝርዝር አስረድቷል፡፡ የአምነስቲ ሪፖርት የግጭት መነሻ አድርጎ የወሰደው አማራ ተወላጅ ሾፌር ጭልጋ ላይ መገደሉ ጋር ተያይዞ እንደሆነ የሚገልፅ ሲሆን የአማራ ማሕበር በአሜሪካ ሪፖርቱ ከዚህ የግጭት መነሻ ብሎ ካቀረበው ጀምሮ ትክክል አለመሆኑን ገልፆአል፡፡ በአንጻሩም ችግሩ የተባባሰው በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ጉላግ በተባለ ቦታ ያደረሰው ጥቃት፣ ሾፌሮችን ጨምሮ በርካታ የአማራ ንፁሃን ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የአማራ ማሕበር ሪፖርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ የአምነስቲ ሪፖርት ችግሩ የተስፋፋበት መንገድ ላይ ያስቀመጠው ምክንያትና መረጃዎችም ላይ የአማራ ማሕበር በአሜሪካ ቅሬታውን በመግለፅ ችግሩ የተስፋፋበትን ምክንያት በዝርዝር ጠቅሷል፡፡ በተለይ በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በጎንደር ከተማና አካባቢው በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈፀም ያደረሱትን ጉዳት በሪፖርቱ መታለፉን ተችቷል፡፡ በተጨማሪም በአምነስቲ ሪፖርት የተካተቱት አብዛኛዎቹ ታሪኮችና ተፈፅመዋል የተባሉ ጉዳዮች የአማራ ተፈናቃዮችን መረጃ ያላካተተ መሆኑም ጠቅሷል፡፡ የአምነስቲ ሪፖርት ለፋኖ የሰጠው ስም ትክክል አለመሆኑን፣ በመንግስት የፀጥታ ኃይልና ፋኖ ጉዳይ መረጃዎችን አለማገናዘቡን በዝርዝር ያስረዳው የአማራ ማሕበር ሪፖርት በአንፃሩ በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ከባድ መሳርያ የታጠቀ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀመ መሆኑ በመረጃ የተደረገፈ፣ ሌሎች በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ያመኑት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የዘገቡት ሆኖ እያለ በአምነስቲ ሪፖርት መታለፉን ነቅፏል፡፡ ችግሩን በማባባስ ትልቅ ሚና የተወጣውን የትህነግ/ሕወሓት ጉዳይ በአምነስቲ ሪፖርት መታለፉን አግባብ ትክክል አለመሆኑ ተገልፆአል። አምነስቲ በተሳሳተና በአንድ ወገን መረጃ ያቀረበው ሪፖርት የአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ዘርፈ ብዙ የመብት ጥሰትም ያላካተተ መሆኑን የአማራ ማሕበር በአሜሪካ በመግለጫው በዝርዝር አጠናቅሯል።

በተጨማሪም የቅማንት ተብለው ስለተጠቀሱት ቀበሌዎች፣ ሕዝብ ውሳኔ፣ የሕዝብ ግጭት ተብሎ የተጠወሰው ላይ በሚዛናው መረጃ ያልተደገፈ፣ እውነታውን የማያሳይ መሆኑ እንዲሁም መፍትሔ ተብለው በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት የተጠቀሱት የመረጃና የጥናት ችግር ያለባቸው፣ የአንድ ወገንን መረጃና ፍላጎት ይዘው የተሰሩ በመሆናቸው አምነስቲ ያለውን ስም እንዳያጠለሹ የመረጃ ምንጮቹንና የጥናት ሂደቱን እንዲያጤነው የአማራ ማሕበር በአሜሪካ ዛሬ ግንቦት 22/2012 ዓ/ም ባወጣው መግለጫው አሳስቧል፡፡

አሥራት

https://www.amharic.zehabesha.com/statement-on-the-gaps-and-omissions-in-the-latest-amnesty-international-report/

 

1 Comment

  1. አምንስቲ ያወጣው ሪፖርት በድርጅቱ የስነ-ምግባር ደንብ መሰረት የወጣ አለመሆኑን፣ በስህተት የታጨቀ ታአማኒነቱን ጥርጣሬ ውስጥ የከተተው መሆኑን እንረዳለን፡፡ በሌላ በኩል የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ከአማራ ክልል በስተቀር፣ ለተቋሙ ሲጠየቁ መረጃ አለመስጠትም ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ለማንኛውም
    1. በአማራ ክልል አማራ ሆነው የሞቱ፣ የቆሰሉ እና የተፈናቀሉ በሙሉ የተፈጸመባቸው የመብት ጥሰት በመንግስት መዋቅር ያልተፈጸመባቸው አድርጎ መውሰዱ ተገቢ አይደለም፡፡ መዋቅሩ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ወይም ክልልና ፌዴራል መ፣ንግስት አካላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ታዲያ ለምን የሌሎች ሲወሳ የአማራው ቀረ
    2. በክልል መንግስት ተገቢው ከለላ አለመደረጉ በቅማንት ማ/ሰብ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ሪፖርቱ ያወሳል፡፡ በትግራይ ክልል ጣልቃ ገብነት የተፈጸመ ጥሰት ሪፖርት ከማንም አልደረሰንም እያላችሁ ነውን፡፡ ያሳዝናል
    3. ሪፖርቱ ስለኢትዮጵያ እያቀረበ ስለ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ድሬደዋ እና ሌሎች ክልሎች ምንም አለማለቱ ተአማኒነቱን ብንጠረጥርስ፡፡ የመደራጀት፣ የመንቀሳቀስ፣ እና የመሳሰሉት አፈናዎች በብዙ ቦታዎች ቢታዩም አማራና ኦሮሚያ ጉጂና ም/ወለጋ ላይ ማነጣጠሩ ሚስጥር ግልጽ ነው፡፡
    በአጠቃላይ ሪፖርቱ ቀደም ሲል በጃ-ዋር፣ በድምጸ ወያኔ ሲነገሩ የነበሩ በትንሽ እውነት ብዙ ውሸት የታጨቁበት እንዲሁም ምሉዕነት የጎደለው የተቋሙ ሳይሆን የግለሰቦች ስብቀት ነው ብንል አልተጋነነም፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.