‹‹ኢትዮጵያና አምስቱ ሕልመኞች›› የዶ/ር ኃይሉ ኣርኣያ

Hailu Book e1590808474927‹‹ኢትዮጵያና አምስቱ ሕልመኞች››

ይሄንን ደስ የሚልና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ነገር በመጻፌ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡

ዶ/ር ኃይሉን በቅርብ የሚያውቃቸውና የሚያገኛቸው ሰው የሚጠይቃቸው አንድ ጥያቄ ነው፤ እሱም፡-

‹‹ዶክትር ለምንድን ነው መጽሐፍ የማይጽፉት?›› የሚል፡፡ የእሳቸው የትህትህና መልስ ግን ክው ያደርጋል፡፡ የእጆቻቸውን መዳፎች ገጥመው፡-
‹‹ከእኔ የተሻሉ እና ብዙ የሚያውቁ ሰዎች አሉ…›› ይላሉ፡፡

እኔ በቅርብ ከሚያውቋቸው መካከል ነኝ፡አብሬያቸውም ሰርቻለሁ፡፡ የምር ተንቀሳቃሽ ቤተ መጻሕፍት ማለት እሳቸው ናቸው፡፡ በ2004 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበሩበት ጊዜ እኔ የሳቸው ምክትል ነበርኩ፡፡ ብዙ ተማርኩ። ብዙ አወቅሁ። ለጥቆ እሳቸውን ሙሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኘ የተካኋቸው እኔው ነበርኩ፡፡

… ስማ!! አፈ ቀላጤነት ይጎድለኛል እንጂ የተዋጣልኝ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ ነኝ እሽ (አቤት ጉራ…እግዚኦ).. ኸረ ጉራ…. አይደለም፤ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የአንድነት ፓርቲን 90 ፐርሰንት መግለጫዎች ባልተዝለገለገ ቋንቋ የሚጻፉት በእኔ ነበር፡፡ ይሄን ልምድ ያገኘሁት ከዶ/ር ኃይሉ አርአያ ስር ሆኘ እንደሆነ ለመግለፅ ነው እንጂ ጉራ አይደለም፡፡

ባክህ ወደ ደለው ግባ!….

ወደ ገደለው ስገባ… ብቻ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መጽሐፍ እንደ ጻፉ የነገሩኝ እሳቸው ናቸው፡፡ በጉጉት ከሚጠብቁት መካከል ነኝ-እኔ፡፡ ከማሳተማቸው በፊት እንዳነበው ጋብዘውኝ ነበር፡፡ ያለማጋነን እስካሁን ካነበብኳቸው ምርጥ መጽሐፎች አንዱ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያና አምስቱ ሕልመኞች››
‹‹እንዴት አገኸው?›› አሉኝ፡፡
‹‹እስካሁን የት ነበሩ ዶክተር?›› ጥያቄያቸውን በጥያቄ፤ ምን ልበል?
ለማንኛውም፡፡ ደስ ብሎኛል፡፡ ይችን መጦመሬ ታላቁን ሰው፤ የቋንቋ ሊቅና ደርባባ ምሁር እንኳን ደስ አልዎት ለማለት ያሕል ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: አርሰናል ዋንጫ ይበላ ይሆን?

ጊዜውም የጥሞናና የንባብ እንዲሁም ቤታችን የምንሰበሰብበት በመሆኑ ‹‹ኢትዮጵያና አምስቱ ሕልመኞች›› ማሰላሰላችንን የሚያሰፋና የኢትዮጵያን ሌላ ገጽ የሚያሳይ ነው፡፡

ቀኝ ያውላችሁ፤ ከቁጥር አያጉድለን!!

ዳንኤል ተፈራ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.