ግንቦት 20 የቀውሶቻችን መባቻ!?

677ግንቦት 20 በግልብ ትንተናና በፈጠራ ትርክት ድቡሽት ላይ የተመሰረተ አማጺና አንጋችን ለአገዛዝነት ያበቃ ዕለት ነው። ሀገራችን ዛሬ ለምትገኝባቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች መባቻም ነው። እንደ ሀገር እንደ ሕዝብ የገባንበት ቅርቃር አሀዱ የተባለበት ቀን ነው ማለት ይቻላል። አምባገነናዊውን የጊዜያዊ ወታደራዊ አገዛዝ /ደርግ/ን ገርስሶ በሌላ አምባገነንና አፋኝ አገዛዝ በመተካት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ዕለት ነው። የተማሪዎችን አብዮት ቀምቶ ስልጣን የጨበጠ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ 70ሺህ የሚጠጉ ታጋዮች የተሰውለትን፣ ከ120ሺህ በላይ አካል ጉዳተኛ የሆኑለትን የነፃነት አብዮት ቤተሰባዊ በሆነ ቡድን ጠልፎና አግቶ ስልጣን በመዳፉ ያደረገበት ክፉ ቀን ነው። ግንቦት 20 ኤርትራንና ሕዝቡን እንድናጣ አበክሮ ሕዝበ ውሳኔ የተሰጠበት፣ የባሕር በር ያጣንበት፣ የ3ሺህ ዓመትና ከዚያ በላይ ታሪካችን ወደ 100 ዓመት የወረደበት፣ ጥንታዊው የሀገረ መንግሥት ታሪካችን የተካደበት፣ ስንቶች በዱር በገደሉ የተዋደቁለት ሰንደቅ ጨርቅ ተብሎ ዱቄት የተቋጠረበት፣ ጥላቻና ልዩነት የተቀነቀነበት፤ የጋራ ታሪክ፣ ብሔራዊ ጀግናና ምልክት /አይከን / እንዳይኖረን የታወጀበት፤ ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት የተወገዘበት ጥቁር ቀን ነው።

ግንቦት 20 የሀገር ሀብት በጥቂቶች እጅ የገባበት፣ እንደ ኤፈርት ያሉ ድርጅቶችና ቡድኖች እንዳሻቸው እንዲዘርፉ ካዘና የተከፈተበት፣ ለዘመናት የተገነቡ ተቋማትና እሴቶች እንዲወድሙ ደማሚት የተቀበረበት፣ ዜጎች እርስ በርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ የሚሰራ ተቋም የተመሰረተበት፤ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ሕዝብ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በሌሎች ማንነቶች እንዲከፋፈል የተሴረበት፣ በጎሳና በቋንቋ ብቻ የተመሰረተው የልዩነትና የጥል የባቢሎን ግንብ /ክልል/ መሰረተ ድንጋይ የተጣለበት፣ ሀገር ለብተና የታጨችበት፣ ሀገር በደም ካሳና በዕዳ የተያዘችበት፣ አናሳዎችና ህዳጣን በአፈሙዝ ብዙኃኑን ቀጥቅጠው የገዙበት፣ አንደኛና ሁለተኛ ዜጋ የተፈጠረበት፣ ወዘተረፈ የኀዘን ቀን ነው። ታሪክ የአሸናፊው ነው እንዲሉ ይህ ሁሉ ቀውስ ውድቀት መወገዝ ሲገባው እንደ ድል በዓል የሚከበረበት ቀን ነው።

ግንቦት 20 የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ተስፋ ሳይውል ሳያድር ወደ ቀቢጸ ተስፋነት የቀየረ መናጢ ቀን ነው ማለት ይቻላል። ለ17 ዓመታት በተካሄደ የእርስ በርስ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች አምራቹና ወጣቱ የሰው ኃይል በግዳጅና በወዶ ገብነት ለጦርነቱ ተማግዷል። የሀገር ሀብት፣ ጥሪት፣ ኢኮኖሚና መሠረተ ልማቶች ወድመዋል። የሀገሪቱ እድገት አሽቆልቁሏል። ድህነት፣ ኋላ ቀርነትና ማህበራዊ ቀውስ ተንሰራፍቷል። የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለለት «ትግል» ገና ከጅምሩ መጨንገፉ ነው። ነፃነትን፣ ፍትሐዊነትን፣ እኩልነትንና ዴሞክራሲያዊነትን ያዋልዳል ተብሎ የተጠበቀው ጽንስ ውርዴ ሆኖ ቀርቷል። ግንቦት 20 በተለይ ከ1987 ዓ.ም ወዲህ እስከ ለውጡ ዋዜማ በፅኑ ሕሙማን ማቆያ /አይ ሲ ዩ/ በጠመንጃ በአፈና እና በከፋፍለህ ግዛ የቅኝ ገዥዎች መርህ ቆዬ እንጂ የተነሳለትን አላማ ገና ከመነሻው የዘነጋ ስለነበር ህልው አልነበረም።

በግንቦት 20፣ ለቀደሙት 27 ዓመታት ሥልጣን ላይ የነበረው ገዥ ፓርቲ ትህነግ/ኢህአዴግ መመጻደቂያዎች ቀዳሚው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን እኩልነት አረጋግጫለሁ፤ በማንነታቸው እንዲኮሩ አድርጌያለሁ የሚል ቢሆንም የግንባሩ አስኳል የሆነው ትህነግ በሚመራው የትግራይ ክልል በዞኖች እንኳ እኩልነት አልነበረም። ሕዝቡም በአንድ ለአምስት ተጠርንፎ ዛሬ ድረስ ከኢትዮጵያውያን ተለይቶ በጭቆና ፍዳውን እየበላ ይገኛል። ልጆቹን ገብሮ ያለጧሪ ቀባሪ ቀርቶ ለሥልጣን ያበቃው ቤተሰባዊ ቡድን ዛሬም ከትክሻው የመውረድ ፍላጎት የሌለውና ይህ አልበቃ ብሎት ኢኮኖሚውን ከጅምላ ንግድ እስከ ጉልት ተቆጣጥሮ ፤ መሬቱን ፣ የተፈጥሮ ሀብቱንና ጉልበቱን እየዘረፈ ለምሬትና ለብሶት ዳርጎታል። ካለፉት ዘጠኝ ቀናት ወዲህ ግን «ፈንቅል ! » ብሎ ጭቆና ፣ አፈና፣ ዘረፋና በስሜ መነገድ ይብቃ እያለው ነው። ትጥቅ የጀመረበት ቀዬ ሳይቀር በቃ ! ብሎታል። ማጣፊያው አጥሮታል። በልጆቹ አጥንትና ደም ተረማምዶ ለሥልጣን የበቃበትን ሕዝብ በአውራጃና በጎጥ የሚከፋፍል፣ የሚያፍን፣ የቁም እስረኛ የሚያደርግ ነፃ አውጭ አስኳል የሆነበት ድርጅት በምን ተጠየቅና አመክንዮ ነው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን እኩልነት የሚያረጋግጠው ? በእርግጥ የይስሙላና በእሱ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረት አስመሳይ እኩልነት አልነበረም ማለት አይደለም። በመናጆዎቹ በእነ ደኢህዴግ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና በአጋር ፓርቲዎች መካከልና እኩልነትንና ውስጠ ድርጅታዊ ዴሞክራሲና ነፃነትን ሳያረጋግጥ በየት አልፎ ነው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን እኩልነት አረጋግጫለሁ የሚለው !?

ማለት ይቻላል። ለ17 ዓመታት በተካሄደ የእርስ በርስ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች አምራቹና ወጣቱ የሰው ኃይል በግዳጅና በወዶ ገብነት ለጦርነቱ ተማግዷል። የሀገር ሀብት፣ ጥሪት፣ ኢኮኖሚና መሠረተ ልማቶች ወድመዋል። የሀገሪቱ እድገት አሽቆልቁሏል። ድህነት፣ ኋላ ቀርነትና ማህበራዊ ቀውስ ተንሰራፍቷል። የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለለት «ትግል» ገና ከጅምሩ መጨንገፉ ነው። ነፃነትን፣ ፍትሐዊነትን፣ እኩልነትንና ዴሞክራሲያዊነትን ያዋልዳል ተብሎ የተጠበቀው ጽንስ ውርዴ ሆኖ ቀርቷል። ግንቦት 20 በተለይ ከ1987 ዓ.ም ወዲህ እስከ ለውጡ ዋዜማ በፅኑ ሕሙማን ማቆያ /አይ ሲ ዩ/ በጠመንጃ በአፈና እና በከፋፍለህ ግዛ የቅኝ ገዥዎች መርህ ቆዬ እንጂ የተነሳለትን አላማ ገና ከመነሻው የዘነጋ ስለነበር ህልው አልነበረም።

በግንቦት 20፣ ለቀደሙት 27 ዓመታት ሥልጣን ላይ የነበረው ገዥ ፓርቲ ትህነግ/ኢህአዴግ መመጻደቂያዎች ቀዳሚው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን እኩልነት አረጋግጫለሁ፤ በማንነታቸው እንዲኮሩ አድርጌያለሁ የሚል ቢሆንም የግንባሩ አስኳል የሆነው ትህነግ በሚመራው የትግራይ ክልል በዞኖች እንኳ እኩልነት አልነበረም። ሕዝቡም በአንድ ለአምስት ተጠርንፎ ዛሬ ድረስ ከኢትዮጵያውያን ተለይቶ በጭቆና ፍዳውን እየበላ ይገኛል። ልጆቹን ገብሮ ያለጧሪ ቀባሪ ቀርቶ ለሥልጣን ያበቃው ቤተሰባዊ ቡድን ዛሬም ከትክሻው የመውረድ ፍላጎት የሌለውና ይህ አልበቃ ብሎት ኢኮኖሚውን ከጅምላ ንግድ እስከ ጉልት ተቆጣጥሮ ፤ መሬቱን ፣ የተፈጥሮ ሀብቱንና ጉልበቱን እየዘረፈ ለምሬትና ለብሶት ዳርጎታል። ካለፉት ዘጠኝ ቀናት ወዲህ ግን «ፈንቅል ! » ብሎ ጭቆና ፣ አፈና፣ ዘረፋና በስሜ መነገድ ይብቃ እያለው ነው። ትጥቅ የጀመረበት ቀዬ ሳይቀር በቃ ! ብሎታል። ማጣፊያው አጥሮታል። በልጆቹ አጥንትና ደም ተረማምዶ ለሥልጣን የበቃበትን ሕዝብ በአውራጃና በጎጥ የሚከፋፍል፣ የሚያፍን፣ የቁም እስረኛ የሚያደርግ ነፃ አውጭ አስኳል የሆነበት ድርጅት በምን ተጠየቅና አመክንዮ ነው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን እኩልነት የሚያረጋግጠው ? በእርግጥ የይስሙላና በእሱ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረት አስመሳይ እኩልነት አልነበረም ማለት አይደለም። በመናጆዎቹ በእነ ደኢህዴግ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና በአጋር ፓርቲዎች መካከልና እኩልነትንና ውስጠ ድርጅታዊ ዴሞክራሲና ነፃነትን ሳያረጋግጥ በየት አልፎ ነው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን እኩልነት አረጋግጫለሁ የሚለው !?

ሌላው መመጻደቂያው በግንቦት 20 ሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ፣ ፌዴራላዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሪፐብሊካዊ በሆነ ሥርዓት እንድትመራ ጥርጊያውን ማመቻቸት ተችሏል የሚለው ነው። በቀደሙት 27 የግፍ ዓመታት ሕገ መንግሥቱ ምሰሶ ያደረጋቸው የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች መብት፣ የሕዝቡ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤት መሆኑን፣ የክልሎችን ራስን የማስተዳደር ሥልጣን፣ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶችን ፣ ወዘተረፈ የሚደነግጉ ድንጋጌዎቹም ሆነ ሌሎች አንቀጾች የኢህአዴግ አዛዥና ናዛዥ የነበረው ትህነግ በአደባባይ ሲጥሳቸው ስለነበር፤ «ሕገ መንግሥት የታተመበትን ወረቀት ያህል እንኳ ዋጋ አጣ ፤» እስከማለት ተደርሶ ነበር። በአምስቱም የይስሟላ ምርጫዎች ኮሮጆ በመገልበጥ፣ በማጭበርበርና በአፈ ሙዝ የሕዝቡ ድምጽ በጠራራ በመዘረፉ የሕዝቡን ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት በተደጋጋሚ በመጣሰ ሲከሰስ መኖሩ የአደባባይ ምስጢር ነው። ሌላው በሀገሪቱ ታሪክ ዴሞክራሲያዊ ነኝ የሚል መንግሥት በገዛ ዜጋው ላይ ዘግናኝና ተቋማዊ በሆነ አሠራር የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየረገጠ፣ እየጣሰና እየገፈፈ ከፍ ሲልም ሲገድል፣ ዘቅዝቆ ሲገርፍ፣ ጥፍር ሲነቅል፣ ወስባዊ ጥቃት ሲፈፅምና ሲያንኮላሽ የነበረ ቡድን ስለ ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት የማውራት ሕጋዊም ሞራላዊም ልዕልና የለውም።

ግንቦት 20 የራስን አስተዳደር በራስ የመወሰን መብት፣ እኩል የመልማት ዕድል የፈጠረ እና ሁሉም ክልሎች በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እኩል እንዲወስኑ ያስቻለ ስለ መሆኑን ተደጋግሞ ይነገራል። ሆኖም እኔ አውቅላችኋለሁ እያለ ክልሎች መሪያቸውን የመምረጥ መብት የገፈፈና በጀታቸውን እንዳሻው ሲሸነሽን የኖረ አሠራርና አደረጃጀት በነበረበት አግባብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት አጎናጽፏል ቢባል ከልግጫ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም። ለዚህ ነው አገዛዙ ፌዴራላዊም፣ ዴሞክራሲያዊም፣ ሪፐብሊክም አልነበረም የሚል የሰላ ትችት የሚሰነዘርበት። ለውጡ ከባተ ጀምሮ ግንቦት 20 ይከበር አይከበር የሚለው ሙግትና እሰጥ አገባ ገፍቶ የመጣው። ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን የያዘበት ፤ ሌላ አምባገነን በመንበሩ የተተካበት ሆኖ እንዴት ክብረ በዓል ይሆናል የሚል ክርክር የተነሳበት፤ መስከረም 2 በግንቦት 20 ተተካ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ እስከ ማለት የተደረሰበት። ለዚህ ይመስላል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግንቦት 20 «በዓል» አከባበርን እንደገና የበየኑት፤ ትርክቱንም ያረቁት።

አዲስ ዘመን ግንቦት 20/2012

በቁምላቸው አበበ ይማም (ሞሼ ዳያን)

[email protected]

3 Comments

 1. The amazing thing about the TPLF EPRDF is they are so fixated on Meles , even though little is known about who this Meles person is by many until this day .
  Meles’s legacy had been kept a secret and his biography never written because Legesse stole
  Meles’s identity and became Meles.

  Legesse went to school at Tikur Anbessa hospital in Addis Ababa to become a doctor same as Seye Abrahe did but were not able to complete their studies, after that Legesse joined Shabiya and Seye Abraha went to Sudan . Then that so many years Legesse joined TPLF as Shabiya’s spy.
  On the other hand the real Meles was among the few that formed TPLF never joined Shabiya, so Shabiya trained Legesse then sent him to infiltrate TPLF to kill Meles, then Legesse stole Meles’s identity so Shabiya can control TPLF by putting this puppet Legesse impersonating Meles to rule TPLF.
  The plan worked with the TPLF being Shabiya’s puppet until 1998.

  Many of the TPLF fighters were not aware that the real Meles died and another impostor Legesse who changed his name to Meles was leading TPLF until they saw his face on Ethiopian national TV after TPLF took control of Addis Ababa on ግንቦት 20 which was a shocking revelation for them, but since TPLF and EPRDF were and are till this day so
  power hungry they collaborated with Shabiya and Legesse’s scheme and kept quiet about not knowing who this impostor Legese is after he showed his face in public television , at first many EPRDF fighters assumed Meles sent this different person to go on TV to claim he is Meles to ensure that Boone gets to assasin the real Meles but as time goes by they were forced to accept the impostor as Meles, the impostor let the country be looted so they hush hush but the looting went out of control , they became doctors , PhD holders colonels Generals billionaires ..you name it they did it , all these to hush up about Shabiya ruling Ethiopia but the Ethiopian people decided to kick them all out but failed to do so they only succeeded in kicking Shabiya out, because when Meles died this Legesse took his name and became Meles with most TPLF EPRDF fighters not being notified about the death of the real Meles until they started their luxurious life in 1991 which they were too happy to have they ended up not caring about Ethiopia as long as their bellies are full , with money keep flowing to them from every which way. The least they could do now is tell who this real Meles was and how Legesse cheated his way into becoming Meles in detail to save themselves , truth shall set them free because lie is about to put them to their graves.

 2. Substantial’ን ማጥፋትና ትርከሚርኪን ግን ማስነበብ ምን ብሎ እንዲጠቅም ታስቦ ይሆን…!? እየነቃን እንጂ !

  Aufklärung ist die Befreiung des Menschen aus der selbstverschuldeten Naivität !

 3. ኣይተ/ወይዘሮ ሂሊና፣ ተግባራትም እንደ ስም ሂሊና የተሞላበት ቢሆን ይመረጣል::

  የነ መለስ ዜናዊን ስም ለማጥፋት የራሳቸው የሆነ በቂ እኩይ ተግባራት ስላላቸው፣ ያልነበረን ፊክሽን መፍጠር አስፈላጊነት የለውም::
  እንያ የፅዮኑ ልጅ ንጉስ ሃይለመለኮት ዘ-ሸዋ እግዝሄር ይይላቸውና፣ በአባታቸው በረት ውስጥ ሲልፈሰፈሱ ካደሩበት ሌሊት ጀምሮ (ወይ እንያ አፄ ቴዎድሮስ ቀደም ብለው ሃይለመለኮት ለአቅመ አዳም ከመድረሳቸው በፊት ሸዋን አልወረሩ፣) የሆኖ ሆኖ እነ ምኒልክ ሃይለመለኮት በእምነ ፅዮኑን ተደግፎ ተንደላቃቂው የበታችነት የሚባል ነገር አይሰማው ዮሃንስ ቆመና እና እነ መንግስቱ ሃይለማርያምም ምናልባትም በነፍስሃ ደስታና ሻለቃ ኪሮስ ቆመና መቅናት የተነሳ ሳይሆን አይቀርም መነሾው፣ እስከ ሃይለመለኮት ዘ-ሸዋ ድረስ የማይታወቀውን “የትግሬን ማጥፋት” ነው ደም ፍላታቸው እየገነፈለባቸው ሲያክለፈልፋቸው፣ (እዚህ ላይ ያንን ምኒልክ-ደጃዝማች ከበደ-መንግስቱ መስመርን ማስታወስ ያስፈልጋል) ደርግ ገና ለስልጣን ከመብቃቱ ወጣት ለጋ የዘብሄረ ትግራይ ፖለቲካው አክቲቪስቶችን እነ መለስ ተኽለንና ግደይ ገብረዋህድን የመሳሰሉን ለጋ ተጋሩን ይገላል::
  TPLF ትግል ሲጀምር መላ አባላቶቹን ከፀጥታ ዋስትና ጋራ በታያያዘ ጉዳይ ስማቸውን እንዲቀይሩ ስላደረገ፣ ለምሳሌ እንደ እነ ገሰሰ=ስሑል፣ ወልደስላሴ=ስብሓት፣ ኣረጋዊ=ብሪሁ ወወዘተ:: ስምን ስትይዝ ደግሞ ከሆነ ጉዳይ ተነስቶ ደስ የሚልህን ወይንም ደግሞ ለማስታወስ የምትፈልገው ሰው ስምን ትመርጣለህ፣ ስለሆነም ደርግ ገና ብቅ ከማለቱ የገደላቸውን የመለስ ተኽለ እና የግደይ ገብረዋህድ ስምም በመለስ ዜናዊና በግደይ ዘር ኣፅዮን ተወሰደ:: እነዚህ የተሰዉትን ወንድሞቻቸውን ሰም አንግተው ወደ ትግል ያመሩት ሰዎች በመልካም ልባቸው የተሰዉት ወንድሞቻቸው ስም እንዳይረሳ እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም አልነበረውም::

  የስለላ ተግባራትን በተመለከተ ደግሞ፣ እስካሁን ጊዜ ድረስ በእማኝ የሚታወቅ ጉዳይ የሃይለስላሴ መንግስት ኢሳያስን ስሙንም ሳይቀይር ተዟዙሮ በሱዳን በኩል ወደ ባርካ እንዳሰረገው ነው:: ስለ እነ መለስ ዜናዊ ለሻዕቢያ ስለላ ተግባራትም በሩቅ ከምንገኘው ሌሎቻችን ይልቅ በቅርባቸው የነበሩትን፣ ተሎ ተብሎ ጊዜ ሳያልፍ፣ የተሻለ ግምት ያላቸውን እነ ስብሓት ነጋንና ኣረጋዊ በርሀን መጠየቅ ይሻላል እንጂ፣ እንዲያው ዝም ብሎ ፍሬከርሲኪ-ከርሰመርሲን መበተን ትርፉ ራስን ማስገመት ይሆናል::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.