የህወሃት ቅጣት – ከአንተነህ መርዕድ

ማይ 20202

በግሪኮች አፈ ታሪክ የተንኮለኝነት ቅጣት ተምሳሌት የሆነው የሲስፉስ ታሪክ ነው። ወደ ዝርዝሩ ሳልገባ ባጭሩ ላስቀምጠው። በጥንታዊቷ ግሪክ ሲስፉስ (SISYPHUS) የሚባል ንጉስ ነበር። በሸረኛነቱ የሚታወቅና በሌሎች ስቃይ መደሰት የሚወድ ተወዳዳሪ የሌለው የሰው ክፉ ነው። በቤተሰቦቹ፣ በባላንጣዎቹ፣ በእኩዮቹና በተወዳዳሪዎቹ ማንም ከሚያስበው በላይ ተንኮል ብዙ ግፎች በመስራቱ የግሪክ አማልዕክት ተቆጥተው ለዘለዓለሙ ግዙፍ ቋጥኝ ወደተራራ እየገፋ እንዲኖር ፈርደውበት ያለእረፍት ሲገፋ ይኖራል።

woyaneየኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ እንደሌሎች አገሮች ሁሉ ብዙ አስቀያሚ ገጽታ አለው። እኛ ዘንድ አስቀያሚነቱ የበረታ በመሆኑ አሁን ላለንበት በሁሉም መስክ የዓለም ጭራነት በቅተናል። በተለይም ባለፉት አምሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቅ ካሉት ድርጅቶች የህወሃትን ያህል የከፋና አገርና ህዝብን የበደለ የለም ማለቱ ማጋነን አይሆንም። ሲጸነስ ለትግል የወጡ የትግራይ ወጣት አመራሮችን እንታረቅ ብሎ በአንድ ለሊት ሲያርዳቸው አሁን አለበትይ አስከፊ ሁኔታ ይደርሳል ብለው ያሰቡ ባለመኖራቸው እየቀረቡት ተጎድተዋል።

በህዝብ ትግል የተዳከመውን ደርግ ገርስሶ አገሪቷን በዘር ሸንሽኖ በቀላሉ ወደማይሽር የዘር አረንቋ ውስጥ ከተተን።

ከሻዕብያ በበለጠ የባህር በር እንዳይኖራት ታላቋን አገር ወደብ አልባና ትንሽ አደረጋት ።

ተሸክሞ ቤተመንግስት ያስገባውን ሻዕብያ ክዶ ኤርትራ ለሃያ አምስት ዓመታት ከዓለም እንድትገለልና በከፋ ድህነት ውስጥ እንድትኖር ዓለምን አስተባበረ። በባድሜውም ጦርነት ከሁለቱም ወገን ወደ መቶ ሺህ ወጣት እንዲረግፍ አደረገ።

አጅቦት የመጣውን ኦነግን መሪዎቹን በቦሌ ሸኝቶ ሰራዊቱን ለነጋሪ እስኪጠፋ ፈጅቶ ሺዎችን በዕስር አማቀቀ።

በ1997 ዓ ም ምርጫ የህዝቡን ድምጽ ገፍፎ መሪዎቹን አስሮ፣ ሁለት መቶ ወጣቶችን አዲስ አበባ ላይ በጠራራ ጸሃይ ገድሎ ሰላሳ ሺዎችን አስሮ አሰቃየ።

ኦጋዴን፣ ጎንደር፣ ጋምቤላ፣ አርባጉጉ፣ ወላይታ፣ አዋሳ በአጠቃላይ በአገሪቱ በርካጣ ጭፍጨፋዎችን አካሄደ።

የአገሪቱን ሃብት በጥቂት ቤተሰቦች ቁጥጥር ስር አድርጎ ከሰላሳ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከህዝቡ ጉሮሮ ነጥቆ ውጭ አሸሸ።

ህዝባዊ አመጹ በየቦታው ተቀጣጥሎ የአጋዚ ጥይት ያልበገራቸው ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ በሚል የተደራጁ ወጣቶችና መላው ህዝብ ሲያምጽ በአምሳሉ ጠፍጥፎ የሰራቸውና በአገልጋይነት የተጠቀመባቸው አባል ድርጅቶቹ (ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ) በአጋርነት ስም ቆመው እንዲያበሉት ዳር ለዳር ያደራጃቸው ሁሉ ህወሃት በድሮ ጉልበቱ እንደማይቆይ መገንዘብ በመቻላቸው ሲሸሹት ሳያስበው ህዝባዊ ማዕበሉ መቀሌ ወርውሮት ራሱን አገኘ። ትናንት ዞር ብለው ያላዩትና በስሙ የተነገደበት የትግራይ ህዝብ “ልጆቼን የገበርኩበት ትግል ለእኔ ድህነት ለእናንተ ጌትነት ሊሆንማ አይችልም” ብሎ ፈንቅሎ ሊጥለው “ፈንቅል” ብሎ ተነስቷል። የህወሃት የወደፊቱ እጣ ለሰራው ሸርና ተንኮል እንደግሪኩ ሲስፉስ አማልክት ሳይሆን ህዝብ የሚጭንበትን መርግ ሲገፋ መኖር ነው። እንደሰሜን ኮርያ በጨለማ እንዲገዛ የፈረዱበት የትግራይ ህዝብ ጸሃይ ስትወጣለት የህወሃት ጀንበር እየጠለቀች ነው።

6 Comments

 1. May of1991 was the funeral of Ethiopia , hopefully Ethiopia will be resurrected when the reneissance dam starts operation in the year of 2025 as expected by many Ethiopians .

  TPLF should be completely dismantled now because by the year 2025 if the TPLF business empire and TPLF military is not dismantled completely TPLF can come back to life by 2025.

  Our neighbors in Eritrea are capable and willing to dismantle TPLF as a show of goodwill towards Ethiopians, to make right what Eritreans shabiya did to Ethiopians by bringing TPLF to power in May of 1991.

  • ባንድ በኩል “በህዝብ ትግል የተዳከመውን ደርግ ገርስሶ አገሪቷን በዘር ሸንሽኖ በቀላሉ ወደማይሽር የዘር አረንቋ ውስጥ ከተተን እያልክ

   ቀጥሎ ደግሞ “ተሸክሞ ቤተመንግስት ያስገባውን ሻዕብያ ክዶ ……..ትላለህ

   ሁለቱ ሀሳቦች እርስ በርስ የሚጋጩ ናቸው፡፡ ደርኝ ከገረሰሰ የሻቢያ ትከሻ ለምን አስፈለገው፡፡ ይህ እነ ብርሀኑ ነጋን የመሰሉ የሻቢያ ኩሊዎች ቱልቱላ ነው፡፡ ለሻቢያ ክሬዲት መስጠ ፈልገህ ይመስላል የመደመር/መቀነስ ካድሬዎች የወቅቱ መመሪያ መሆኑ ነው ብቻ መጽፍህ ካልቀረ ቀዳዳህን መሽፈን አትርሳ ለማለት ነው፡፡ ደርግን የገረሰሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው፡፡ የአቢይም ወያኔ በህዝባችን ትግል እንደማንኛውም አምባ ገነን አረመኔ ስርአት ይደመሰሳል፡፡

 2. መብት የሚገኘው ወይም የሚከበረው በ ሃይል ብቻ ነው። በ ሃዘኔታ ወይም በ ጸሎት አይገኝም። ስለዚህ መብቱን የሚፈልግ ህዝብ ለ መብቱ የሚያስፈልገውን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል አለበት። እኛም ኢትዮጵያዊያን መብታችንን ልናስከብር የምንችለው ተደራጅተን የ ሞት እና ሽረት ትግል ከ አካሄድን ብቻ ነው። ሌላ አማራጭ የለም።

 3. አቡጊዳ የተሻለ bloggers ድረገፅ ነበረ፣ ብቻ አንድ ስህተት ስላደረገ ጥፋቱን አስከተለ ፣ በእኔ አባባሎች ላይ ፊደሎችን መሰረዝና መደለዝን ሲያሰኘውም በገዛ ራሱው ፊደልን ጨመር በማድረግ አባባሎቼን ማወላገድ::

  አሁን ደግሞ እናንተ ዘ-ሓበሻዎች አባባሎቼን መደበቅና መወሸቅን አብዝታችኋል፣ ይሄ ተግባራችሁ እድሜያችሁን አሳጣሪ ይሆናል!

  ለምሳሌ እዚህ አርእስት ላይ 5 COMMENTS እንዳሉ ያመልክትና የሚነበቡት ግን 3 ብቻ ናቸው፣ ሌሎቹ ሁለቱ የማይነበቡት የእኔ ናቸው::
  እንዲሁም ቀደም ብዬ እነ ጌታቸው ሃይሌን ያስተማርኩበት በሙሉን አጥፍታችኋል፣

  በእናንተ ዘንዳ “ተወዳጅ” ለመሆን ስል ብቻ በፈረንጅ 1974 የተገረሰሰውን ፊውዳሊዝም እና ጭሰኝነት ይታደስ ይመለስ ብዬ አልሰብክ እንግዲህ….!

  ለወደፊት የሚያገለግለው Unity in diversity ብቻ ነውና ከታሪካዊ ሂደት ጋራ ራሳችሁን አዋህዱ፣ ካልሆነላችሁ ግን ዋልድባ መግባት የተሻለ ይሆናል………………!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.