‹‹ኢትዮጵያ ነባር ዲፕሎማቶቿን በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በማሰማራት ዘመቻ ብታካሂድ ይመረጣል›› -ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ

100744537 1649475885203753 3895345134845296640 nአዲስ አበባ፡- መንግስት ነባርና በጡረታ የተገለሉ ዲፕሎማቶቿን በማሰባሰቡ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሰፊ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ የቀድሞው የ16ኛ ሰንጥቅ ሜካናይዝድ ብርጌድና በኋላም የሶስተኛው ሜካናይዝድ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ገለጹ፡፡
ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ መንግስት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋናነት የዲፕሎማሲ ስራውን በከፍተኛ ደረጃ ማካሄድ ይጠበቅበታል፡፡ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ረገድ የበቁ ሰዎች አሏት፡፡ ዘመን ሲቀየርና ፈተናዎች ሲያጋጥሙ ወደኋላ በመሄድ በዘርፉ ካሉት ዲፕሎማቶች በተጨማሪ ነባርና በጡረታ የተገለሉ ዲፕሎማቶችን በማምጣት ምክራቸውንና አስተያየታቸውን መቀበል መልካም ነው:: እነርሱ የሀገር ሀብት ናቸው፡፡
በዚህ ረገድ ከድሮ ጀምሮ የራሳችንን በየመስኩ የነበሩ ብቁ ባለሙያ ዜጎች ያላቸውን አቅም በሚገባ ያለመጠቀም ችግር አለብን ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ፣ ነባርና አንደበተ ርቱእ እንዲሁም የሰከኑ ዲፕሎማቶች ስላሉኝ ያላቸውን እውቀት መጠቀም ብልህነት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም በርካቶችንም መጥቀስ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ አይደለም እውቀታቸውን ሕይወታቸውን ለሀገራቸው የማይሰስቱ ብዙ ሚሊዮን ልጆች ያሏት ሀገር ነች ያሉት ጀነራሉ ፣ እነዚህንና ሌሎችንም በጡረታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ጠርቶ ተወያይቶ ለዲፕሎማሲው ስራ በአለም ዙሪያ ማሰማራት ተገቢ ነው ብለዋል:: እድሜ ዘመናቸውን ግብጽንና ሴራዋን ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ በምእራቡ አለም ዲፕሎማሲ ውስጥ የኖሩ ነባር ዲፕሎማቶች በአለም ዙሪያ ተሰማርተው ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንዲሁም የኢትዮጵያን
ሕጋዊ የመልማት መብትን ለአለም በማስረዳቱ በኩል ከፍተኛ ድጋፍ ሊያበረክቱ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አሁን ካሉት ጋር ተነጋግሮ መጀመሪያ አንድ የልኡካን ቡድን ወደ ተፋሰሱ ሀገሮች፣ ሁለተኛውን ደግሞ ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲሁም ሶስተኛውን ወደ አውሮፓ ህብረትና ወደተቀረው ዓለም በመላክ ወዳጆቻችን በሆኑ ሀገሮች ሁሉ ላይ ጭምር ሰፊና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ፤ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያሉበት
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ለሀገራቸው ዲፕሎማት ሆኖ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል ፡፡
የነባር አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እውቀትና ልምዳቸው ለሀገር ይጠቅማል፡፡ እነሱን አሰባስቦ መንግስትን እንዲያግዙ፣ እንዲያማክሩና አስተያየት እንዲሰጡ ማድረግ ለሀገርም ለመንግስትም ይጠቅማል:: እነርሱ የሀገር ሀብት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባዎች በዓለም ሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች

አዲስ ዘመን ግንቦት 18/2012
ወንድወሰን መኮንን

1 Comment

  1. It is too late now to bring these capable diplomats , capable engineers , capable environmentalists , capable military officers into this discussion.
    All that should have been done before Ethiopia went to USA to sign declaring the three countries will reach an agreement by January the 15th 2020.

    Now the solution is for PM Abiy and Gedu Andargachew to publicly admit their faults and to resign ,then Ethiopia can start a brand new diplomatic effort by notifyig all involved
    that Ethiopia is voiding the USA brokered negotiation outcomes since Ethiopia was under siege by PP TPLF and is about to enter a transitional period.This resignations should be done soon before it is too late because time is running out for diplomatic efforts.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.