ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት የሚያስገድድ መመሪያ ጸደቀ

%name ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት የሚያስገድድ መመሪያ ጸደቀበኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቀ።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት ህይወት ለመታደግ ሲባል ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማድረግ ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቋል።

ወ/ሮ አዳነች እንዳሉት ከሌላው ስህተት መማር ብልህነት ነው !የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝን በተመለከተ ብራዚል ዉስጥ የነበረው መዘናጋት፣ ቸልተኝንት፣ የተላለፉትን ድንብ እና መመሪያዎችን አለማክበር ዛሬ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው።

ለእራሳችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለወገናችንና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ወረርሽኙን መከላከል አለብን ብለዋል። በመንግስት እና በባለሞያዎች የተላለፈውን የጥንቃቄ መመሪያዎችንም ችላ ሳንል እንተግበራቸው። ለህግ አስከባሪው አካል እንታዘዝ። ከማንም በላይ ጥቅሙ ለራስ ነው ሲሉ ጠቅላይ አቃቤ ህጓ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ኢፕድ)

1 Comment

  1. በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው ። በተለይ ለ ኢትዮጵያ እና ለ አላደጉ አገሮች ብቸኛው ኮሮናን መከላከያ ዘዴ ጭምብል ማድረግ ነው ። ጭምብል ማድረግን እንደ መከላከያ የተጠቀሙ አገሮች በ ኮሮና የደረሰባቸው ጥቃት አነስተኛ ነው ። በ ምሳሌነት የሚጠቀሱት አገሮች ደቡብ ኮሪያ ፣ ሲንጋፖር እና ቼክ ሪፓብሊክ ህዝቦቻቸውን የታደጉት በ ዋናነት ጭምብል መጠቀምን በ ማስገደዳቸው ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.