ከታሪክ መጥፎ ጠባሣ ያልተማረ ፣የበለጠ ጉዳት ይደርስበታል ና የኢትዮጵያ መንግሥት በአባይ ጉዳይ ፣ከታሪክ ማመር ይጠበቅበታል። – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Nile 1የታላቁን ህዳሴ ግድብ በተመለከተ የግብፅ መንግሥት ፍላጎት ድብቅ አይደለም።ግልፅ ነው።ፍላጎቱ የህዳሴው ግድብ ወድሞ ማየት ነው።ይህ የዛሬው የግብፅ መንግሥት ብርቱ ፍላጎት ነው።ይህንን ፍላጎቱንም የሚያሣኩለት የተደራጁ  ፀረ -ኢትዮጵያ ኃይሎች በሀገራችን ውሥጥ እና በውጪ በህቡ አደራጅቷል።የትላንትናዎቹ  የግብፅ መንግሥታት እንዳደረጉት ሁሉ ፣ የዛሬውም የግብፅ መንግሥት በኢትዮጵያ የተረጋጋ መንግሥት እንዳይኖር ብርቱ ጥረትም እንደሚያደርግ ይታወቃል።
የትላንትናዎቹ የግብፅ መንግሥታት ፣ይህንኑ  ሲያደርጉ ነበር።በዚህ አድራጎታቸውም፣ የኢትዮጵያን ታሪክ የጦርነት ታሪክ ካደረጉት መንግሥታቶች መካከል ቀንደኞቹ  መሆናቸውን ታሪክ ዘግቦታል።
ከቅኝ ገዢዎቹ አወሮፖውያን ቀጠሎ ግምባር ቀደም ወራሪዎች እነሱ ነበሩ። በልጆቿ መሥዋትነት ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ሀገራችንን  ደጋግመው ወረዋል።ደጋግሞም በሰሜን የሚኖረው፣ የኢትዮጵያ  ህዝብ  ፣በጀግንነት ተጋድሎ ከሀገራችን ፣አፈሯን አራግፈው እንዲወጡ አድርጓቸዋል።

በኃይል የወረሩን ግን ፣ሊያወድሙን እንጂ ሊያለሙን ወይም  ሊያሥቀድሙን አልነበረም።  የወረራና የውጊያቸው ዓላማ ግልፅ ነበር። “ኢትዮጵያን በማዳከም የአባይ ውሃ ለልማት እንዳይውል ማድረግ።” የሚሰኝ ነው። በዚህ የአውዳሚነትና የአቆርቋዥነት ዓላማ  ፣በዲፕሎማሲያዊ  መንገድ በአዞ እንባ አንቢነት ይንቀሳቀሳሉ።

አንዳንዴም በዲፕሎማሲው መንገድ፣ የአዞ እንባ ከማንባት ባሻገር፣  አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆነውም እናገኛቸዋለን።   ኢትዮጵያን ለማዳከም፣ለማቆርቆዝና ለማውደም፣ እንዲረዷቸውም ፣ዘረኛና ሀገር ገንጣይ ድርጅቶችን ፣በተለይም ” የኦሮምኛ ፣ የትግሪኛ ፣ የሱማሊኛ ቋንቋ ተናጋሪ ምሁራንን ፣በጭቆና ሥም ትላንት ሲያደራጁ እንደነበር እና ዛሬም እንደቀጠሉበት  የማናውቅ ይመሥላቸዋል ።
ይሁን እንጂ፣ ትላንት በጭቆና በብሶት ለመታገል ከቤታቸው ጫካና በርሃ የወጡትን “ታጋዮች” በመደለል እና  የነገን ሥልጣን በማሣየት እንዲሁም በአውሮፖና አሜሪካ የነፃ አውጪ ሥምና ዝና እንዲኖራቸው በማድረግ፣ወታደራዊ ሥልጠና በመሥጠት፤በሥንቅና ትጥቅም በመደገፍ ያደረሱብንን ከባድ ውድመት እኛም ሆነ ታሪክ ከቶም አይረሳውም።…
የግብፅ መንግሥት ና አንዳንድ የአረብ መንግሥታት  በኤርትራ በቅድሚያ ጀብሃን በማቋቋም ፣የባህረ ነጋሽ(የኤርትራ ) ህዝብ አረባዊ እንዲሆን በብርቱ ጥረዋል።  ኢትዮጵያን ወደብ አልባ በማድረግ ፣ከድህነት የመላቀቅ ትግሏን አድካሚ እና በእንቅፋት የተሞላ እንዲሆን ሳያሰልሱ ፣ለተገንጣይ ቡድኖች ብርቱ ድጋፍ አድርገዋል። ዳሩ ግን በመገንጠላቸው ተጎጂ የሆኑት፣  የኢትዮጵያዊያን ወገን የሆኑት የኤርትራ ህዝቦችም እንደሆኑ ዛሬ ላይ በቅጡ ግንዛቤ ያገኘ ይመሥላል።

ኤርትራውያኑን ወደ በረሃ ያሶጣቸው   እሥከ ንጉሥ  ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ” ቀኃሥ ” መውደቅ ድረሥ ያለው፣ጭቆና እና በቀኃሥ የራሥ ገዝ አሥተዳዳራቸውን መነጠቅ እንደሆነ ልብ ይሏል።ይሁን እንጂ የውጪ ኃይሎች ለራሳቸው ከበርቴዎች እና ሀገር ጥቅም ሲሉ ትልቅ ድጋፍ በማድረግ ኤርትራ ከአካሏ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል ማድረጋቸው ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ተገቢ ባልሆነ ” የጭቡ ፍትህ” የኤርትራ ህዝብ ሥለተለየው ቢያዝንም፣ከአሶሳ   እሥከ ዶሎመና ያለው ኦሮምኛ ቋንቃ ተናጋሪ ህዝብ ግን ከየካቲት 1966 ዓብዮት በኋላ ፣ ባገኘው የመሬት ባለቤትነት መብት እና እኩልነት ጥያቄዎቹ ሙሉ ለሙሉ ሥለተመለሰለት ተገንጣይ ቡድኖቹ ራሳቸውን ያከሥማሉ ብሎ አሥቦ ነበር።ይሁን እንጂ በዛው “በነፃ አውጪ ” ሥማቸው ጥቂቶቹ ቀጠሉ።
ብዙሃኑ የኦሮሞ ህዝብ፣ከቀኃሥ ንጉሥዊ ሥርዓት መገርስስ በኋላ ከባርነት ነፃ በመውጣቱ ነፃ አውጪ አያሥፈልገውም ነበር። ብዙሃኑም  የአሁኗ ኢትዮጵያ ቅርፅ ብቻ ሣይሆን ኤርትራን(ባህረ ነጋሽን)ጨምሮ የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነ የሚያምን ኩሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ላለፉት 1000 ዓመታት ያረጋገጠ ህዝብ ነው። በደረግ የወታደራዊ አገዛዝ ዘመንም፣ከመላ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ፣ ለሀገር ዳር ድንበር ና ለህዝቧ ክብር  ሠላም ና ነፃነት    ደሙን በኤርትራ ተራሮች ላይ በጀግንነት  ማፍሰሱን ።አጥንቱንም መከሥከሱን ታሪክ በወርቅ ቀለም ፅፎታል።
እናም ፣ ዛሬም በታላቅ ኩራት ኢትዮጵያ፣ “በዛ ሰንሰለታማ ተራራ የወደቁት  ፣አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ህያው ጀግኖች ናቸው ትላለች።እንዲህም ሥትል። የወለጋው ጀግና ህያው ነው።የነጆው፣የደቢዶለው፣የአሶሳው ጀግና ህያው ነው።የአምቦው፣የግንደበረት፣የአዲስ ዓለም፣የሆለታው ጀግና ህያው ነው።የጅማው፣የአጋሮው (ከፋ) ጀግና ህያው ነው።የኢሉአባቦር ጀግና ህያው ነው።የሸዋው ጀግና ህያው ነው።የወሊሶው ፣የሰላሌው፣ ጀግና ህያው ነው።የአርሲው ጀግና ህያው ነው።የባሌው ጀግና ህያው ነው። …” ማለቷ ነው። በጥቅሉ፣የኢትዮጵያ ህዝብ ህያው ታሪክ እንዳለው ዛሬም በዓለም የሚዘነጋ ከቶም አይደለምናና!!!..ደም ና አጥንቱ ዛሬም ከኤርትራ ምድር ጋር ተቀላቅሎ ህያው ሆኖ እንደሚኖርም  ታሪክ ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ያሥታውሳል።…

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያን ፍላጎት ያልተረዳ መንግስት ኢትዮጵያን ሊመራ አይችልም - ገለታው ዘለቀ

ይህች የኩሩ ህዝብ ባለቤት፣ ገናና ሀገር ፣እንድትኮሰምን

ኃያላኑ ሀገራት ያደረጉትን ደባ ሁሉ በየትውልዱ እንዲታወስ ማድረጉን ታሪክ ይቀጥላል ።የከበርቴዎቹን ሀገራት መንግሥታትንም ሤራም እግረ መንገዱን ያጋልጣል።  እንዲህ  እያለ።
” ቅኝ ገዢዎቹ  ከአደዋ ሽንፈታቸው በኋላ፣ ኢትዮጵያን መመዝበር የምንችለው ህዝቡን በዘር እና በቋንቋ በመከፋፈል እንጂ በቀጥታ ጦርነት አይደለም።ህዝቡ ለወራሪ ጦር የማየበገር ነው።ከውጪ የሚመጣበትን ጠላት ተባብሮ ድል የማድረግ ከደሙ ጋር የተዋህደ ልምድ ያለው ነው።ሥለሆነም ይህንን ልምዱን በፕሮፓጋንዳ እንዲለውጥ  ማድረግ ሥለማንችል፣ሌላ ዘዴ መፈለገ አለብን።” በማለት ፣ ሌላ ዘዴ ቀይሰውለታል።ዘዲያቸውም ይህ ነው።

” በኢትዮጵያ የተለያየ ዘር፣ቋንቋ እና ኃይማኖት ሥላለ ለምን በቋንቋ አንለየውም ? ለምን አንዱን ዘር ከሌላው በቋንቋ ከፋፍለን አናጋጨውም? …ለምን ለአንደኛው ገንዘብና መሣሪያ በመሥጠት ሌላውን ቋንቋ ና ዘር እንዲወጋ ወይም የጠረፍ ኗሪው ላይ ግፍ እንዲሰራ በማድረግ መንግሥት አልጠበቀኝም ብሎ እንዲያኮርፍ፣ አድርገን ወደ አቋቋምንለት ዘረኛ ድርጅት እንዲቀላቀል አናደርግም?ግባችን ይህቺ ሀገር አቅመ ቢሥ ሆና በእኛ ድጋፍና እርዳታ ተንጠላጥላ እንድትኖር በማደረግ ሀገሪቱን መበዝበዝ አይደለምን ?በረጅም ሂደትም በዘር እና በጎሣ ሰበብ፣ ‘እኔ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ያለኝ ነኝና  የሀገሪቱ መሪ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ። ‘ ሌለው ደግሞ፣ ‘ እንዲህ ዓይነቱ የተረኝነት ፓለቲካ አጥፊያችን ነው።የመንግሥት ሥልጣን መያዝ ያለበት   በህዝብ  ግልፅ የአደባባይ  ውሳኔ በምርጫ መሆን አለበት። ‘ እየተባባሉ ወደ እርሥ በእርሥ ጦርነት ሲያመሩ እኛም ቢላዋ ለሁለቱም እናሥጨብጣቸዋለን ።እንዲተራረዱም እንገፋፋለን ።ህዝቡ እርሥ በእርሱ ተጋድሎ ቢያልቅ  ጉዳያችን አይደለም።የምንፈልገው መሬቱን ነው።የሀገሪቱን ሀብት። ….።”

ይህ ነው፤ ታራክ መዝግቦት ያለ ፣ለልጆቻችን የምንተርከው እውነት።ታሪክ መዝግቦ ያሥቀመጠው የገብፅም ሆነ የቀድሞ የቅኝ ገዢዎችን ሃሳብ የሚያራምዱ አመለካከት ፣እና ተግባር ዛሬም ይኸው ነው።ዛሬም አፍሪካዊያንን አያከብሩም።ለአፍሪካ ህዝብ ከፍተኛ ንቀት አላቸው።
አንዳንዶቹማ ያላቸው ንቀት ከጣራ በላይ ነው።ደሞ የሚገርመው፣ የሥልጡን ሀገር መሪዎች ነን ማለታቸው ነው።ህዝብን እየናቁ ሥልጣኔ በበኩሌ አይገባኝም።  ሆኖም  ለአፍሪካ ህዝብ ያላቸውን ከእሥከ የማይባል ንቀት ሳይ ይገርመኛል። በእዚህ ንቀታቸው የተነሳም አፍሪካዊያን “በሴራ ፓለቲካ ” ቢያልቁ ጉዳያቸው አይደለም።እናም በህቡ ለጥፋት ይንቀሳቀሳሉ።
ይህንን ፍላጎታቸውን ለማሳካትም  በዕቅድ ይንቀሳቀሳሉ።በመረጃ ላይ የተመሠረተ፣በማሥረጃ የተረጋገጠ የማባላት ሥራ ይሰራሉ።በአንዳንድ አፍሪካ ሀገራትም መንግሥትን የመሾምና የማውረድ ሥልጣን እና ችሎታ ከብቃት ጋር እንዳላቸው ደጋግመው አሣይተዋል።እነሱ ያሻቸውን ለማድረግ የሚያሥችል ከብረት የጠነከረ ረዢም እጅ እንዳላቸው እያሳዩ ና ቴክኖሎጂ በጎናፀፋቸው ” በእሥፓይደር ማን” እና “ባት ማን” ዓይነት  የኃይል ጥበብ እያሥፈራሩ ፣ በእጅ አዙር ለእነሱ ከበርቴዎች ጥቅም የሚቆም አሻንጉሊት መንግሥት(puppet state )በየሀገሩ ያቋቁማሉ።  ቅን አሥተሳሰብ ያላቸው የአውሮፖና ኢሲያ መንግሥታት እንዳሉ ቢታወቅም ፣እኩይ አሥተሣሠብ የሠፈረባቸው ፍላጎታቸው የአፍሪካን ህዝብ መጨረሰ የሆነ ከበርቴ የአውሮፓ፣የኢሲያ፣የአሜሪካ መንግሥታት መኖራቸውን ማንም ማሥተባበል ከቶም አይችልም።
ታሪክ ትላንት ና ታሪክ ዛሬ የሚያሳየን እውነት ይኸው ነው።በሀገራችን ብቻ የተፈፀመውን የእነሱን ተንኳል ዘርዝረን ለመጨረሥ ቀናቶች አይበቁንም።
የቅርቡን የደርግ የሶሻሊዝም ሥርዓት  እና ወድቀቱን ብናሥታውሥ የአውሮፓና አሜሪካን ጠንካራ ትብብር፣ከአረብ ሀገራት ጋር ተደምሮ እንደነበር እንገነዘባለን።
ምንም እንኳን ለሶሻሊዝም ሞት ፣በወቅቱ የሩሲያ መሪ የነበሩት  ጎርቫቾቭ “ፕሮስቶሪካ” እና “ግላሥኖሥት “(ታሐድሶ እና ግልፅነት) ቢያግዟቸውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መለስን ቅበሩት! - ተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ጎርቫቾቫ ፣  ሶሻሊዝም በፍጥነት እንዲሞት እና እንዲቀበር አድርገዋል።አሜሪካና አጋሮቿ ለሶሻሊዝም ሞት ያደረጉትን ያላሰለሰ በሴራ የተሞላ ጥረትና ያገኙትን ሥኬት ታሪክ መዝግቦላቸዋል።
ከዚህ በታሪክ ከተመዘገበው  የሶሻሊዝም ሞት በኋላ ነበር የደርግ ውድቀት የተከተለው። እናም በወታደሩ ውሥጥ ሠርገው በመግባት ፣ጦሩ አቅም እንዲያጣ የሀገሪቱ ዐይን የሆኑ የጦር መኮንኖችን በግንቦት  8/1981 ያልተቀናጀ፣ግብታዊ  መፈንቅለ መንግሥት እንዲያደርጉ ገፋፍተው በኮ/ሌ መንግሥቱ እንደሥፈጇቸው ታሪክ ዘግቦታል።
ቀሥ፣በቀሥም ኢትዮጵያን በማዳከም ና አቅመ ቢሥ በማድረግ ፣ እሳቸውንም  በዘዴ ከነቤተሰባቸው ወደ  ሐራሬ(ዙምባቡዌ ) ግንቦት 13 እንዲኮበልሉ  አደረገዋቸዋል። በዙም  ሳይቆይ  ግንቦት 20/1983 ዓ/ም ወያኔ አዲስ አበባ ገባ ።
አዲስ አበባ  የገባው ወያኔ የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ፣ሚኒልክ ቤተመንግሥት ያሥገቡትን አሜሪካኖች “አፍንጫችሁን ላሱ” ብሎ፣ፊቱን ወደ ቻይና አዞረ። በዚህ መከዳትም አሜሪካኖች አዘኑ።ተቆጩ። የአሜሪካኖቹ ቁጭት የዋዛ አይደለምና ሴራቸውን በረቀቀ መንገድ በመዘርጋት እሥካሁን ግልፅ ባልሆነ ሤራ የወያኔ ግዙፍ ጭንቅላት ( Master  mind )  የሆኑትን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን  በድንገት  አሳጧቸው። ከመለስ ሞት በኋላ ፣ ሌብነትን በግልፅና በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሥፋፉ እና በዝሙት እንዲጨማለቁ አደረጓቸው።ሀገርን በንፅህና ማገልገልም ሆነ “ከእኔ በፊት ወያኔ ይቅደም!!” ማለት ተቀበረ።በዚህ ሰበብም የዘር ቡድኖች በየአቅጣጫው አመፅ አሥነሱ።ወያኔም አጣብቂኝ ውሥጥ ሆኖ ሥልጣኑን ለቀቀ።አሜሪካኖችም ቀዝቃዛ በቀላቸውን በከፊል ፈፀሙ።ሆኖም እንደ ሶሪያ ኢትዮጵያን የማድረግ ህልማቸው መክሸፉን በመገንዘባቸው ሳይቆጩ አልቀሩም።ምክንያቱም ያልተጠበቀ መሪ ሥልጣን ላይ በመውጣቱና ህዝቡ እንደ ጥንት አባቶቹ በኢትዮጵያ ሀገሩ ድርድር እንደማያውቅ በሰኔ 15 /2010 ዓ/ም ለዶ/ር አብይ አመራር  ባደረገው ደጋፍ ሲያሳይ አሥተውለዋልና!!!
አሜሪካ ለቱጃሮቿ ጥቅም ሥትል ፤ ግብፅ ደግሞ ” ኢትዮጵያ ከበለፀገች ከእኔ ጋር እኩል የመደራደር መብት ይኖራታል።ሀብታም ሀገር ከሆነች ሳልወድ በግድ አክብርያት እኖራለሁ። …”ብላ፣በመፍራት ብቻ ሣይሆን የግብፅ ህዝብ ፣ከኢትዮጵያ  ዴሞክራሲያዊነት  በመማር፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመራትን ሥለሚሻ  ፣የእኛ ሀብትና ንብረት ነገ ትልቅ አደጋ ያጋጥመዋል ” በሚል ፍራቻ፣ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ውድመት ይመኛሉ።
ግብፅ በአሜሪካ እንደምትደገፍ፣የግብፅ መንግሥትም ወታደራዊ መንግሥት መሆኑን እና የአሜሪካንን ፈቃድ ፈፃሚነቱ ያየለ መንግሥት መሆኑንም አትርሱ ።  “ከዚህ አንፃርም የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው።” (enemy of my enemy is my friend .) ማለት ይኽ መሆኑንም ተገነዘቡ።ይሁን እንጂ ጠላትነቱን በግልፅ ላያሳይ ይችላል።የኢትዮጵያን መንግሥት በተለሳለሰ ዲፕሎማሲ በልጦ ለመገኘት፣አልያም በእጅ ጥምዘዛ የተሻለ ነጥብ ለማሥቆጠር እንደሚጥር ግን ይታወቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና የብዕር ጀግኖቿ ጦርነት

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.