ህወሓት አሁን ትግራይ ክልል ውስጥ ባለው መነሳሳት ስለደነገጠች በደሕንነት ክፍሏ በኩል ዋና ዋና የሚባሉ የተቃዋሚ መሪዎችን የመግደል ሐሳብ ላይ ተወያይታለች

abrha destaፕላኑ እንዲህ ነው። ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ የህወሓት ተቃዋሚዎች ይለያሉ።
“የዐብይ አሕመድ መንግስት በሰብአዊ መብት ጥሰት ሰበብ የትግራይ ክልል መንግስትን በመወንጀል በክልላችን ጣልቃ ገብቶ ሊቆጣጠረን ስለፈለገ የህወሓት ተቃዋሚዎችን ለመግደል ፕላን አለው”
ተብሎ በሰፊው እንዲሰራጭ፣ እንዲነገርና እንዲፃፍ ይደረጋል።
“ዐብይ እኛን ለማስወንጀልና ለመከፋፈል ፈልጎ የኛን ተቃዋሚዎች ለመግደል አቅዷል”
እየተባለ ፕሮፓጋንዳ ይሰራል።
ህወሓት ተቃዋሚዎቿን ትገድላለች።
ራሷ ገድላ “ይሄው ያልነው አልቀረም፤ እኛን ለማስወንጀል ዐብይ አስገዳላቸው” ይባላል።
ከዛ ህዝብን ለመቀስቀስና ተቃውሞን ለማስቆም ይረዳታል።
ከነሱ ያገኘሁት ነው። በደሕንነት ክፍሉ ተወያይተውበት ለበላይ አካል ተልኳል።
ከትግራይ ክልል እንድወጣም ተነግሮኛል። ግን አልወጣም!
ህወሓት አብርሃ ደስታ “በሌላ አካል ሊገደል ይችላል” ብላ ካሰበች ጋርድ ቀጥራ ትጠብቀኝ። ካልሆነ ግን ከህወሓት ውጭ ማንም አይገድለኝም!
አብርሀ ደስታ

3 Comments

 1. ከዚች ጦሰኛ ሴትዮ ማነው ሕወሓት እንዴት እንደምንገላገል አንድዬ ይወቅ! ከጽንሰቷ ጀምሮ እሥከጅጅትናዋ ድረሥ በተንኮልና በሸር የተለከፈች፣ ካለግድያ ሌላ መፍትሔ የማታእቅ ጉድ በመሆኗ ለይቶላት ጉድጓድ እሥክትገባና መርዟም እሥኪረክሥ በጣም መጠንቀቅ ይገባል። እንደወያኔ የሰው ደም የሚጠማው የለም – ከነብርና አንበሣም በበለጠ ነው ደም የሚጠማቸው። ኧረ አሁንሥ እግዚኣብሔር ይራዳንና ይገላግለን! ሥንት ትውልድ በነዚህ ጅቦች ተበልቶ ይለቅ?

 2. Abreha Desta you have paid sacrifice for truth, justice and democracy. The old guards have missed the opportunity for pardon, and never admit they committed crimes you are a living witness. When the weyanes are desperate the think of disrupting the peace of Tigray and Ethiopia. Specially now there is no way they leave Mekelle and their days are numbered they plot destruction and we know if something bad happens to you we will notify the world criminal justice office to take care of them. they can kill an activist or fighter but that shortens their life span. I have great respect for all of you who are trying to liberate Tigray from those criminals and their cliques
  I have great respect for you, Sehoule, Aregawi Amdom, etc.,etc. I wish I can mention all the brave youth who stood for truth and justice.
  Hang on there is light at the end of the tunnel and you are very close to achieve you goals. The agony of Tigray will continue as long as the woyanes exist and hope the resurrection of Tigray is at the corner.
  God bless and protect those who stood for justice and truth.
  Muchfun.
  Canada.

 3. ተሞጋገሱብን እንጂ ለመሆኑ አብረሀ በላይ ከሌሎች ትግሬዎች የተለየ ነዉ?
  ጎበዝ የዚህን ሰዉ ትያትር ለምን እንደምታወጡለት አይገባኝም። ይንቁናል እኮ የጻፈዉን ጽሁፍ በሙሉ ፈልጉና አንብቡ ከዛ ማንነቱን ታዉቁታላችሁ ሰዉየዉ ከመለስ ዘራዊ ያነሰ ዘረኛ አይደለም። ንቃታቸዉ አነስተኛ ነዉ በሚል ግንዛቤ ሲያስፈልገዉ በየጊዜዉ የሚያፋጅ አጀንዳ እየሰጠን ይጠፋል። ሰዉየዉ አላስቆሙቱም፤ አላሰሩትም፤ሊገድሉትም ፈጽሞ አላሰቡም።

  ባለፈዉ ታሰረ የተባለዉም የራሱ የሆነ ትያትር አለዉ። ለጊዜዉ ሀሳቡን ነገር እስኪጠራ በትግራይ ኦን ላይ ሃሳቡን ይግለጽ አባ ዊርቱ እንዳሉት ኦፍ ላየን ካልሆነ።፡የነሱ አዲሱ ፕሮግራም ህወአት ወድቋል ጨርሶ ከመዉደቁ በፊት አረጋዊ በርሄ፤ግደይ ዘራጽዮን እና መሰሎቹን ይዘዉ ከመሀል ሊቦረቡሩ ነዉ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ለነሱ ምናቸዉም አይደለም። ሀቁን መቀበል የግድ ነዉ ከላይ እንዳልኩት ቀደም ብሎ የጻፈዉን ጽሁፎች ለማጣቃሻነት ማየት ይጠቅማል። እንደዚህ አይነት ሰዎች መጡም ቀሩም ጥቅም የለዉም በታሪክ ከኤርትራ የመጀመሪያዎቹ ሀገር ወዳዶችን የትም አይሄዱም በሚል መዘናጋት ባንዳ ጠንክሮ የሆነዉን እያየን ነዉ። ለጊዜዉ ከዛ አካባቢ ያሉን የታመኑ ሰዎች ክቡር ገ/መድህን አርአያና አቶ ጌታቸዉ ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) አዘጋጂ ብቻ ናቸዉ።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.