ፈንቅል የሕወሓት ጭቆና ብሶት የወለደው ህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ አራማጅ ነው

ህሊና ዓወት ( አባል እንቅስቃሴ ፈንቅል አውሮፓ አሜሪካ )
5/27/2020.

Fenkelየትግራይ ህዝብ ከሰው አራጅ ፣ ጥፍር ነቃይ የሕወሓት አገዛዝ ለማውጣት የትግራይ ወጣት ለነፃነቱ መነሳት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ። ሕወሓት የጥቂት ማፍያ ፣ ሰው ገዳይ ፣ ዘራፊ እና ጨቃኝ ስብሰብ ነው ። የሕወሓት ስርአት ማብቃት አለበት ። ይህ ማፍያ ቡድን የትግራይ ወጣቶች ሲያፍን ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል የነበረ ነው ። ለአስረጅነት ያህል ለመጥቀስ በ1968 ዓ.ም በኤርትራ እና ኢትዮጵያ አዋሳኝ ቦታ ልዩ ሰሙ ዘገብላ በረሃ ላይ በረካታ የትግራይ ሓርነት ታጋዮች በለሊት ረሸነዋል ። ይህ የማፍያ ሰብሰብ በለሰ ቀንቶት በ1983 ዓ.ም ቤተመንግስት የመግባት እድል ሲያጋጥመውም ድመት መንኩሳ ነውና ሰውን የማፈንና የመግደል ተግባር ከቤተመንግስት እሰኪወገድ ሲፈፅም ቆይተዋል ። የሕወሓት ሀላፊዎች ላላፉት ሃያ ሰባት የአገዛዝ ዘመን ለፈፀሙት የሰበአዊ ሆነ ቁሳዊ ወንጀል በህግ መጠየቅ አለባቸው ። ትግራይ እና የትግራይ ህዝብ የወንጀለኞች መደበቂያ ምሸግ ሊይሆን አይገባም ። ወንጀል ተፈፃሚ ዘር የለውም ። የትግራይ ህዝብ የአገዛዝ ጭቆና ለማሰወገድ ደም የሰጠ ህዝብ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው ። ህዝቡ ለፈፀመው የአርበኝነት ተግባር ቢመሰገን እንጂ ዳግም የጭቆና አገዛዝ ቀንበር እንዲጫንበት አይፈቀድም ። ጥቂት የስብሃት ነጋ ማፍያ በዘረፋ ሲበለፅግ አብዛኛው የትግራይ ግን ሥራ ለምግብ ኑሮ ይኖራል ። በተለይ ከሕወሓት ያልተጠጋ የትግራይ ወጣት በከፋ ደህንነት ውሰጥ ነው ።

የሕወሓት የጭቆና አገዛዝ ከቤተመንግስት በሐይል ከተወገደ እንሆ ሁለት አመት አለፈው ። ሆኖም የዚህ ዘራፊ እና ወንጀለኛ ቡድን ከቤተመንግስት ተወገደ እንጂ ከትግራይ ገና አልተወገደም ። ይህ ድርጅት ከመንግስት አገዘዝ ወደ አሸባሪነት አገዘዝ በሽግግር ላይ ነው ። ትግራይ ውሰጥ ወጣቶች እየታፈኑ የሕወሓት እስርቤት ዜሮ ሰድሰት እየተሰቃዩ ይገኛሉ ። ይህ ኢፍትሐዊ አገዛዝ እንዲቆም የትግራይ ወጣት የእምቢተኝነት እንቅስቃሴ መጀመር ያሰፈልጋል ። የሕወሓት የአገዛዝ ጭቆና ከተቻለ በህግ ልዕልና በሐይል መወገድ አለበት ። የትግራይ እናቶች ዘላለም ስቆቃ እና ሰቃይ ውሰጥ መኖር የለባቸውም ። የሕወሓት ሀላፊዎች መላ ቤተሰብ በውጭ አገራት ተንደላቀው የሚኖሩ ይኖራሉ ። ጭቁን የትግራይ ህዝብ ግን ሰንዴ እና በቆሎ በጣሳ እየተሰፈረለት ይኖራል ። ይህ ደግሞ ፍትሐዊነት የጎደለው ተግባር ነው ። ሰፊው የትግራይ አርሶ እና አርብቶ አደር ህዝብ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ እጥቶ ሲቸገር የሕወሓት ድርጅት አመራሮች ልጆቻቸው በውጭ አለም ፣ ራሳቸው በአገር ውሰጥ ከህዝብ በዘረፉት ገንዘብ በድሎት ይኖራሉ ። ሰፊው የትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚ ፣ የፍትህ ፣ የመልካም አሰተዳደር ችግር ፣ የሥራ አጥነት ችግር ፣ እንዲሁም የአፈና ችግር ያለበት ህዝብ ነው ። ህዝቡ በተደጋጋሚ ብሶቱን ሲያሰተጋባ የቆየ ቢሆንም አድማጭ አልነበረም ።

ፈንቅል በትግራይ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ ፣ እንዲሁም የህግ ልዕልና በህግ እንዲረጋገጥ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ የተመሰረተ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው ። ህዝባዊ እምቢተኝነት በህዝባዊ አድማ ላይ አስፍቶ ይሰራል ። የሥራ አድማ ማድረግ ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ፣ እና ህገ መንግሰታዊ የህዝብ መብቶች እንዲከበሩ ፣ አጥብቆ ይሰራል ። የሕወሓት አገዛዝ የትግራይ ህዝብ ሰላማዊ ጥያቄዎች በሰላማዊ እና በህግ ልዕልና የማያሰተናግድ ከሆነ አገዛዙ ከሥሩ ለመንቀል ሙሉ መሰዋእትነት ለመክፈል የሚያሰችል የተግባር ስልት ይዘጋጃል ፣ ተግባራዊም ይሆናል ። የሕወሓት አገዛዝ በፈንቅል አባላት ላይ የሚወሰደው የሃይል እርምጃ ፈፅሞ ተቀባይነት አይኖረውም ። ይልቁንም ትግሉ ያንረዋል ። የፈንቅል አደረጃጀት በአገር ውስጥ እና ብውጭ የሚደግፍ ሲሆን የትግሉ ማዕከል ትግራይ ውሰጥ ነው ። የፈንቅል እንቅስቃሴ በከፍተኛ ተልዕኮ የሚመራው የትግራይ ወጣት ሲሆን ሁሉም የማህበረሰብ ድጋፍ ያካተተ ነው ። በኢትዮጵያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አውታሮች የፈንቅል እንቅስቃሴ ሀላፊነት በተሞላው ሁኔታ ይዘጉቡታል የሚል እምነት ይኖራል ። የፈነቅል እምቢተኝነት እንቅስቃሴ የትግራይ ህዝብ አይንና ጀሮ እንዲሁም የህልውና ዋስትና ሆኖ ይንቀሳቀሳል ። ውጤት ተኮር የሥራ ተግባራት ላይ አትኩሮት ያደርጋል ።

የፈንቅል ስልታዊ እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ ትግል እና ህገ መንግሰታዊ የመብት ጥያቄዎች መሰረት ያደረገ ነው ። የፈንቅል እንቅስቃሴ የመብት ፣ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ ፣ የፍትህ ፣ የህግ ልዕልና ፣ የመልካም አሰተዳደር ጥየቄ በመሆኑ መላ የትግራይ ህዝብ ከፈንቅል ጎን ሆኖ ለመብቱ እንዲታገል ጥሪ ለማድረግ እንፈልጋለን ። በተለይ የትግራይ ወጣት ሀላፊነት በተሞላው ተግባር ውስጣዊ አደረጃጀቱ እንዲያጠናክር ፣ ከሕወሓት ገዳዮች ራሱን እየተከላከለ የአፋኙ የሕወሓት ተግባር ለህዝብ እንዲያጋልጥ ታሪካዊ ሀላፊነት አለበት ። የትግራይ ወጣት ከሕወሓት በጎ ለውጥ እንዳማይገኝ ተገንዝቦ ለቀጣይ ሰላማዊ ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ ይጠየቃል ። የፈንቅል እንቅስቃሴ በጥልቀት መገንዘብ ፣ ተገንዝቦም ለተግባራዊነቱ መሰለፍ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ። ወጣቱ በውስጥ መሰመር በሚገኘው የተግባር እንቅስቃሴ በጥሞና እንዲከታተል መልዕክት ተላልፈዋል ። ተከታታይ የተግባር ትግል ስልቶች በውስጥ መሰመር የሚላኩ ይሆናሉ ። አመችነት እየተመዘነ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይደረግባቸዋል ። ከፊል የፈንቅል ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በሕወሓት ግብረ መልስ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ሕወሓት ሰላማዊ ለውጥ ለማድረግ ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል ። በፈንቅል እንቅስቃሴ እምነት አፈና ፣ እሰራት ፣ ግድያ ፣ እንዲሁም ግጭት ምክንያታዊ አይደሉም ፣ ተቀባይነትም ያላቸው አይመስሉም ። ፈንቅል ራሱን ሲያደራጅ የቆየ ፣ የሕወሓት አፈና የፈጠረው የሁለንተናዊ ለውጦች እንቅስቃሴ መሪ ነው ። በፈንቅል እንቅሰቃሴ እምነት የፌዴራል መንግስት ትግራይ ላይ በሕወሓት የሚፈፀመው የሰበአዊ ጥሰት በዝምታ ማለፍ የለበትም ። የፌዴራል መንግስት ህገ መንግስት የማክበር ህገ መንግሰታዊ ግዴታ አለበት ። በዚህ አጋጣሚ በመላው አለም የምትገኙ የፈንቅል አባላትና ደጋፊዎች ሁለንተናዊ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ በፈንቅል የትግል እንቅስቃሴ ሰም መልዕክት ለማስተላለፍ እንወዳለን ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.