አማራ ጉድህን ስማ! – በላይነህ አባተ

Harerበላይነህ አባተ ([email protected])

ሀረርና ድሬድዋ እንደ ኒው ዮርክና ለንደን የሰው ዘር በሙሉ የሚኖርባቸው የጦቢያ ከተማዎች ነበሩ፡፡ በአማራ መቃብር መንደር ለመመስረት በተነሱት ጭራቆች ለመሳሪያነት የተሰራው ይህ አድግ በኢትዮጵያ ምድር እንደ እሾህ ተተከሰከሰ ጊዜ ጀምሮ ግን ሀረርና ድሬዳዋ ለአማራ የምድር ሲዖል ሆነዋል፡፡ ይህ ሲዖል ተአማራ ተርፎ እንደ ጉራጌ ላሉ ሌሎች ያገራችን ዜጎችም ተርፏል፡፡ ይህ አማራና ሌሎችም የሚኖሩበት ሲዖል እንደ ሻማ እየበራች ባለችው የህግ ባለሙያ ኤልሳ ከበደ አደባባይ ውሏል፡፡ ይኸንን ይመልከቱ፡፡

https://youtu.be/8-pzzg4B_Og

በሀረር፣ በድሬዳዋና በሌሎችም እነዚህን በመሳሱት ከተሞች የአማራ ኑሮ በአስራ ስምንተኛውና አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ተነበሩት የአሜሪካና የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ከፍቷል፡፡ ቅድመ አያቶቻቸው ህይወታቸውን ገብረው ባቆሟት አገር አማሮች ተሌላ ዓለም እንደ መጡ ወራሪዎች ተቆጥረው ተምጣኔ ሐብትና ተውክልና መገለል ብቻ ሳይሆን ሰርተው እንዳይበሉም ተከልክለዋል፡፡ በአይምሯቸው እንዳያስቡ፣ በአፋቸው እንዳይናገሩና በእጃቸው እንዳይሰሩ ተከልክለው ሰው ሆነው የመኖር መብታቸው ተገፏል፡፡

በአፓርታይድ ዘመን በገዛ አገራቸው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት ተነፍጓቸው የነበሩት የደቡብ አፍሪቃ ጥቁሮች መምረጥ የተፈቀደላቸው ከሰባ ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በተሸጡበት አገር እንደ እቃ ይቆጠሩት የነበሩት የአሜሪካ ጥቁሮችም ከስንት ትግል በኋላ የመምረጥ ፈቃደ የተሰጣቸው ከሰባ ዓመታት በፊት ነበር፡፡ የሀረርና የድሬዳዋ አማራ ደግሞ በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን በራሱ አገር እንኳን የመመረጥና የመናገር እንደ ባርያ ሰርቶ የመኖር መብቱም ተነፍጓል፡፡

አማራ ጉድህ ስማ! አንተን በመምሰሉና ያንተን ቋንቋ በመናገሩ በሀረር፣ በድሬድዋና ሌሎችም ሥፍራዎች ወገንህ የእንሰሳ ያህል እንኳ ክብር ሲነፈገው “እኔ ጋ ታልደረሰ” ወይም አንድ እግሩን ጅብ ሲጎርሰው “ሁለተኛውን ታስበላኛለህ ሰጥ በል” እንዳለው ጅል ዝም ታልክ የተሸከምከው ሥጋ የአሳማ፤ በውስጥህ ያለችው ነገ በበሽታም ሆነ በእድሜ መግፋት ሲው የምትለው ነፍስም የቅንቡርስ መሆኗን ተረዳ፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! ወገንህ እንደ አረም እየተነቀለ በየ ስፍራው ሲጣል በአገርቤትም ሆነ በአውሮጳ፣ በአሜሪካና አውስትራሊያ በካሚዮን እየፈሰስክ ይኸንን ታይቶ የማይታወቅ ግፍ በሆዳምነትና በአድርባይነት ዝም ካልክ በምድር ለዘላለም በታሪክ የሚያስወቅስና በሰማይም ሲዖል የሚዶል ኃጥያት ተሸክመህ መሄድህን እወቅ፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! ሴት ተማሪዎችን በጅቦች አስበልትህ ፍትህ ሳትጠይቅ ማደሩ እንደ እሾህ የማይወጋህ እንደ ድንጋይ Cመቀመጫም እየቆየ የማይቆረቁርህ ተሆንክ ለእናትህ፣ ለልጅህ፣ ለእህትህና ዘጠኝ ወር ለኖርክበትን ማህፀን ደንታ የሌለህ ግሳንግስ እንደሆንክ ተረዳ፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! በምርጫ ሳይሆን በመለኮት ፈቃድ አንተን መስለው ስለተፈጠሩ ታሪካዊ የውጪ ጠላቶችህ ለወንበር ያበቋቸው እርጉሞች ወገኖችህን እንደ እባብ ቀጥቅጠው ሲገዟቸውና አፍነው ሲወስዷቸው ዝምብለህ አሁንም ተሙሴዎችህና ተሱሰኞችህ ጀርባ ተቀምጠህ የማያልቅ ድስኩርህን ተቀጠልክ ታስቆርቱ ይሁዳ የከፋህ  ከሀዲ መሆንህን እወቀው፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! በቅድመ አያቶችህ ተጋድሎ ተባርነት ብትድንም በስንፍናህና በቸልተኝነትህ ቅደመ አያቶችህ ተባርነት ያዳኗቸው ባንዶች በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ባርያ እያደረጉህ መሆኑን ተገንዘብ፡፡ ይኸንን ባርነት በአንድነት ታልመከትክ በአልበገር ባይነት ከራስ ካሳ እስከ ሞያሌ ጠላትን ተናንቀው የወደቁት የቅድመ አያቶችህ አጥንት እሾህ፤ ነፍሳቸውም ቅዠት ሆኖ ሊወጋህ እንደሚኖር አጢን፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን በገዛ አገርህ እንደ እቃ እየተቆጠርክ ያለኸው ብአዴን በሚባለው ተይሁዳ የባሰ ከሀዲ አሳልፎ ሰጪነት መሆኑን ረስትህ ተብአዴን የዝንጆሮ ቆንጆ ለመምረጥ ምድጃ ውስጥ እንደገባ ድንች ስትርመጠመጥ የምትውል የብአዴን ካድሬ ተሆንክ አንተም ወገንህንና ፍትሕ ፈላጊውን አምላክ የከዳህ ይሁዳን አፍቃሪ እርጉም ባንዳ መሆንህን ተረዳው፡፡

አማራ ጉድህን ስማ! የውጪ ኃያላን ደጋግመው ሞክረው ያልቻሉትን በቸልተኝነትህ፣ በትግስትህና በብአዴን እጀታነት ወይም ዛቢያነት የባንዳዎች ልጆች ባርያ እያደረጉህ መሆኑን ተረዳ፡፡ ይህቺ ከንቱ ዓለም ለገራምና ለደካማ የማትሆን መሆኗን ተሰላሳ ዓመት ታሪክህ ተገንዘብ፡፡ ብአዴን የሚባለውን አበጣባጪና ለባርነት የሚዳርግ ቃልቻ ተራስህ ዠልጠህ አውርደህ ክብርና የአገር ድንበርን በሚጠብቁ ፍትሀዊ ጎበዝ አለቆችና ጀግኖች ተካ፡፡

አማራ ሆይ ኤልሳ ከበደን አዳምጥና ጉድህን ስማ! ሰምተህም ቀበቶህን አጥብቀህ ፍትህን አስፍንና ወገንህን ተባርነት አውጣ! የግፉዐንና ለአገር ነፃነት ሲዋደቁ የወደቁት ቅደመ አያቶቻችን አምላክ ካንተ አይለይ፡፡ አሜን፡፡

 

End notes:

  1. History of Election in South Africa:  https://www.sahistory.org.za/article/history-elections-south-africa
  2. When Did African Americans Actually Get the Right to Vote? https://www.history.com/news/african-american-voting-right-15th-amendment

 

ግንቦት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

1 Comment

  1. Too much provocation and pocking others wound may bring adverse effect. I hope this women will not trigger the other side. For Example, The return of the mosque forcefully concerted to church; Ras Mokonin’s genocide etc. Reterning of Adul Sultanet etc. Assa Gorgari Zendo yawatal

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.