ግብፅ የማያባራ ተንኮል !!!! – ተድላ አስፋው

ተድላ አስፋው
ተድላ አስፋው

ግብፅ ዛሬ እንደሰማነው ከኢትዮጵያ ጋር “ዉይይት” እንደምትቀጥል ነው በኅዳሴው ግድብ ላይ። የተባለዉ ዉይይት  በመጪው ሀምሌ የሚጀመረዉን የኅዳሴግድብ  ዉሀ ሙሌት ለማዘግየት በግብፅ በኩል ታስቦ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም።

ዉሀ ሙሌቱ በሀምሌ የማይጀመር ከሆነ ግብፅ አሸናፊ ትሆናለች ምክንያቱም በሚቀጥለው አንድ አመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚያመጣዉን ዉዝግብ ተንተርሶ ትርፍ በመመኘት።
 የአለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ከ Wuhan በተነሳው ተዉሀሲ ምክንያት ከፍተኛ ቀዉስ በመግባቱ በጠቅላላው አፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያ ከፍተኛ ማህበራዊ ቀዉስ ሊነሳ ይችላል። ግብፅ ጊዜ ለመግዛት የምታደርገዉ ተንኮል ግልፅ ይሁን።
የኢትዮጵያ ገዢዎች ይህን ዉሀ ሙሌት እንዳያደርጉ የሚከለክላቸው የዉጭ ሀይል ፍፁም የለም። የአሜሪካ መንግሥት እስከ መጪው ኅዳር ምርጫው ድረስ ያለው ተሰሚነት ዜሮ ገብትዋል በ Wuhan ምክንያት።
የተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካና ቻይና ጎራ መስርቶ አዲስ የአለም ዉዝግብ እየከፈተ ነው። ሆንግኮንግ ጥሩ ምሳሌ ነው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ ላይ ጦር ይዞ ዉሀ አትሙሉ የሚል የዉጭ ሀይል ሊመጣ አይችልም። በግብፅ በኩል የሚሰማው የጦር ድንፋታ በድንበርዋ ሊቢያ የመጣዉን አደጋ ለመከላከል ከማዋል አልፎ አገር አቛርጦ ሊመጣ አቅም የለዉም።
የኅዳሴ ግድቡን ዉሀ መሙላት አለመሙላት ያለው በገዢዎቻችን እጅ ነው። በስልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ይህን ሙሌት ካላስጀመረ ተጠያቂ መሆኑ ይሰመርበት።

1 Comment

  1. The Egyptians can not continue fooling and with the determination of Dr. Seleshe now that the EX-prime minister is leading the delegation and will say by hook or crook the filling will start in July this should be the opening of his mission, Otherwise they are betraying the Ethiopian dream and vision.
    Even Americans like Reverend Jesse Jackson said when Egypt built the Aswan Dam they did not consult Ethiopia why has Ethiopia has to consult and ask the permission of Egypt this is admitting that weakness and fear.
    God bless & protect Ethiopia.
    Mesfinachew.
    Ottawa, Canada.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.