ሕወሓትን እየተጋፈጠ ካላው ከአምዶም ጎን እንቁም የወዳጆቹ ጥሪ! – አብርሃ በላይ

amdomየአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አንድም ገ/ሥላሴ ሰሞኑን ሕወሓት በትግራይ እየደረሰበት ካለው ተቃውሞ አንጻር ተጠያቂ በማድረግ ከኪራይ ቤት እስከ ማስወጣት ደርሰዋል። የሰዎቹን ጭካኔ ለሚያውቀው የቀረው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስም የፈጸሙትም ግድያ ገና ተጨማሪ ተቃውሞ ያስነሳብናል የሚል ሥጋት ላይ ወድቀዋል። ይህን ተቃውሞ ይመራሉ ብለው ከሚፈሩዋቸው አንዱ አንድም ነው። ዛሬ ቀርቶ አራት ህልም ስልጣን ላይ እያሉ በትግራይ ተቃውሞ ብርቅ በሆነበት ወቅት መቀሌ ሮማናት አደባባይ የከበቡትን የትግራይ ልዩ ሀይሎ ሳይፈራ ከአሥር የማይበልጡ ለተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት አፈና በቃኝ ብሎ በግልጽ ለወጣቱ አርአያ ሆኗል። ዛሬስ ወዳጆቹ ያቀረቡትን ከአምዶም ግን የመቆም ጥሪ ያንብቡት ይደግፉ

“ለፍትህና ለዴሞክራሲ መከበር በመጮሁ ብቻ አክቲቪስት አምዶም ገ/ስላሴ ትናንት ተከራይቶ ይኖርበት ከነበረው ቤት ለ2 አመት ህጻን ልጁን እንኳን ሳይራሩ አውጥተውታል። “ሳባ” ብሎ የሚጠራት ህፃን ልጁን ደግሞ በሀገሩ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ባንዴራ ስለሚያስጊጣት፣ ትህነጎች ይበልጥ ይቃጠላሉ። አከራዮችን ጠርተው፣ እሱን ካላባረርክ አንተ ትገባበታለሁ እያሉ አክቲቪስቶችን መኖሪያ ያሳጧቸዋል። ኢትዮጵያዊው ወገኔ የትግል አጋርነትህን በሞራል ይሁን በማተሪያል በቻልነው አቅም አምዶምን አይዞን ልንለው ይገባናል።”

አብርሃ በላይ

https://www.gofundme.com/f/Help-Amdom-and-His-Family?utm_source=customer&utm_medium=copy_link-tip&utm_campaign=p_cp+share-sheet&fbclid=IwAR0r_tLCQvhVatwNMzIHlWOFKulL7Azvqu1Vo75_RUOpqWM2Pv7Dd1hNQNM

ተጨማሪ ያንብቡ:  "በወያኔ ምክንያት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም" - አርበኞች ግንባር

2 Comments

  1. አበረሃ በላይ ነህ ደስታ ተዉ አትቀልዱብን በዛ መከራ ወቅት የት ነበራችሁ? ትግሬ ሲያኮላሺ አገር ሲያጠፋ የኢትዮጵያን አጥንት ሲግጥ። ስንት ወጣት ያንተን ልጂ የሚያህል በትግሬ ተኮላሸ፤ተገደለ፤ንበረቱን ተቀማ፤ ተሰደደ። ሌላዉ ጓደኛህ ስኡል ይሆን ሲኦል አላጣራሁም በጥቂት ህወአቶች ምክንያት ትግሬ አዲሰ አበባ አንገቱን አቀርቅሮ መሄድ የለበተም ብሎ ጽፎልሀል። የታክቲክ ለዉጥ መሰለኝ እናንተ ከዉጭ እኛ ከመሀል እንቦርቡር ብላችሁ። እስቲ አንተ ፍረደኝ 40 አመት ሙሉ ስታለቅስ ከበሮ የሚደልቅ ትግሬ ዛሬ በአንጻራዊ ሰላም ካላቀረቀረ መች ሊያቀረቅር ነዉ ይችን ቀልድ ተዉን። አንዶም ምን አጥቶ ነዉ እኔ የማዋጣለት አሜሪካና አዉሮፓ ምርጥ ትምህርት ቤት የሚማር ትግሬ ያዋጣለት እንጂ።

  2. አቶ አብረሃ በላይ የአምዶም ገ/ስላሴን መጉላላት ባሰማህን ማግስት ትግራይ “ተፈነቃቀለች” ። እስቲ ምን ይባላል ከተከራየበት ቤት ማውጣት ያውም በኮረና ጊዜ። እነዚህ ሰዎች በግዞትም ሆነው ለራሳቸው ወንድም እንኳ ያልሆኑ ህልማቸው ተሳክቶ ዳግም ስልጣን ቢመለሱ አለቀላት አገራችን። አቶ አብረሃ በላይ ያንተም ተጋድሎ ቀላል አልነበረም። በህብረታችን አገራችንን እንታደጋለን። ሰዎቹ ልባቸው አይሞት። በቀደም ደግሞ በቪኦ የሰማሁት ሳልሳዊ ወያኔ የሚሏቸው መጥተዋል። ትግራይን ነጻ ምርጫ በራሳችን እናደርጋለን እያሉ እየዛቱ ነው። እንደው በክራንችም ቢሆን እየተጎተትን እዛ ሄደን እናልቃታለን እንጅ በደም አጥንታችን ያቆየናትን ትግራይ እናስገነጥል ይመስላቸዋል እነዚህ ጨምላቆች? የኛው እኮ ናት ትግራይ። ስንቱን ወገኖቻችንን አጥተናል ትግራይ ላይ። እስቲ ይቺ መስከረም ትጥባና እንተያያለን ሲገነጥሉ ወይም ፌዴራል ያላወቀው ምርጫ ሲያደርጉ። ይልቅ በገዛ እጃቸው ከሞቀ ሆቴል አቢይ እንዳያሽቀነጥሯቸው በጊዜ መለማመጥ ቢጀምሩ ይሻላል። የወገን ምክር ቢሰሙ ብዬ ነው። በጣም በዛ። ለነገሩ እንደነፈንቅል አያያዝ መስከረምም ላንደርስ ይሆናል። ይልቅ ለነአምዶምና የፈንቅል ታጋዮች የምመክረው ቢኖር ይህን ትግላችሁን በጥንቃቄና በብልሀት ምሩት። ከተቀሩት ወገኖቻችሁም ተናበቡ። ወቅቱም እንደልብ የልብ ለማድረግ አያመችም በኮረና ምክንያት። ሌላው የምመክራችሁ ምን ቢነሽጣችሁ፣ ምን ቢያስቆጫችሁ እንዲህ ብላችሁ ከነዚህ ሰዎች እንዳትላተሙ። ሁሉን ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ አድርጉት። እልክም እንዳትጋቡ። ማስተዋል ያለባችሁ ለናንተ ጀምበሪቱ እየወጣች ስለሆነ የምትረግጧትን ምድር ሳይቀር እያስተዋላችሁ ርገጡ። ፈጣሪ አገራችንን በጋራ የምናበለጽግበትን እድል ያመቻችልን። ትግራይ ኦንላይኖች አሁን ኦፍላይን መሆን ጀምሩ።

    ብዙ መልካም ነገሮች ብቅ እያሉ ነው በኮረናው ምክንያት። ትላንት እንኳ በቪኦኤ ስሰማ አስደናቂ የሆኑ ስምንት የኢትዮጵያ የጆን ሆፕኪንስ ዶክተሮች፣ በዶር ሶስና ከበደ የተመራ ህብረት ፈጥረው በዚህ የኮረና መከራ ጊዜ የህዝባችንን የፐብሊክ ሄልዝ አቅምን ለመገንባት እየጣሩ ነው። እገራችን እነ ወያኔን የመሳሰሉ የስልጣን ጥመኞች ባይኖሯት በውጭው አለም ያሉን እንደነ ዶር ሶስና አይነቶች ሳይሳቀቁ ወደአገር ቢመለሱ ኢትዮጵያ በጥቂት አመታት ከባድ እርምጃ በሄደች። ያለን ብቃት ያለው የዳያስፖራ ሃይል የዋዛ አይደለም። ከናይጄርያ በሉት ከማንም የሚተናነስ አይደለም። እስቲ አስቡት ወያኔ ሀርነት ትግራይ ብሎ፣ የየብሄራት ነጻ አውጪ ብሎ ምን አይነት እድገትና ብልጽግና ይታሰባል በ ሀያአንደኛው ክፍለዘመን? ከመጠርያቸው ጀምሮ የህዝቡን ስሜትና አኗኗር የማይመጥን የደከመ ፍልስፍና። ዘመን ሲቀያየር እንኳ የማይቀየር ያረጀ መመርያ።

    በመጨረሻም ሳጠቃልል ምናልባት ይህ የትግራይ ልጆች “ፈንቅል” የኢትዮጵያን መጻኢ እድልና የዛሬውን የአገሪቱን ቁመና (ለምሳሌ የአባይን ሁኔታ) ወሳኝ ሚና ይጫወት ይሆናልና እያንዳንዱ አገርወዳድ ዜጋ በሁሉም መስክ ከነዚህ ትግራይ ወጣቶች መተባበር አለበት ባይ ነኝ። አመሰግናለሁ። እድገት የሚሰምረው በህብረት ነውና።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.