/

ተጨማሪ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

Health Mበኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3645 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 429 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ15 እስከ 60 ዓመት የሆኑ 26 ወንዶችና 4 ሴቶች ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 9ኙ የውጭ የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 17ቱ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ 4ቱ ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው በመሆኑ ያላቸው ንክኪ በመጣራት ላይ ይገኛል።

በዚህም ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል18ቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 3ቱ ከአፋር ክልል፣ 4 ሰው ከኦሮሚያ ክልል፣ 3ቱ ከትግራይ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል 5 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 128 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ለ73 ሺህ 164 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 429ኙ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከ30 የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.