የአባትዮው ለገሰ ቦንድ ለህወሀት መርከብ እንደገዛው የጆሮ ጠቢ ልጁ ፈንድም ለወነግ ባቡር እንደሚገዛ ይጠበቃል! – በላይነህ አባተ

Tana 1በላይነህ አባተ ([email protected])

የቱሪዝም ኮሚሽንም ሆነ ሌላው የወሮ በሎች “አስተዳደር” ባለስልጣን ከጣና በሚገኘው ገቢ ሆዱን ሞልቶ እያደረ ጣና በምህረት የለሽ አረም ሲመጠጥ የአሳማን ያህል እንኳን ህሊናውን ሲቆጠቁጠው አይታይም፡፡ በመለኮት ስራ ገብቶ ይህ አድግ በቤተክርስቲያን መንበር እንደ ወፈጥ የጎለታቸው “ፕትሪያሪክ”ና ጳጳሳትም ስንቱን ገዳማት ታቅፎ ያለው ጣና ሲደርቅ የወፎችን ያህል ሲጨነቁ አይታይም፡፡

ቦንድ ቦንድዶ ባህር ለሸጠው ህወሀት መርከብ የገዛው በውጪ ያለው ላሜ ቦራም ለህወሀት የማደጎ ልጅና ጀሮ ጠቢ ፈንድ ፈንድዶ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ሐብት እንዳለው አስታውቋል፡፡ [1] እነዚህ ፈንድ ፈንዳጆች ጣናን ከሌላ አገር እንዳለ ሀይቅ ረስተውታል፡፡ ዶሮ ሳይጮህ ጀምረው ስለግድብ ሲጮሁ ግን ይሰማል፡፡ ምንጩ ከደረቀ ግድብም ሆነ ስለግድ መጮህ እንዳማይኖር ማሰብ ተስኗቸዋል፡፡ የፈነደዱትን ፈንድ ለወነግ ባቡርና ለነጃዋር ቪላ ተነመዋኛው ገዝተው እንደልማዳቸው እንደ ባህር ኩበት ተንከርፈው ለመቅረት የነሆለሉ ይመስላል፡፡

እኛ የዛሬ ኢትዮጵያውያን ተሩቅ ታሪካችን ቀርቶ ተቅርብ ልምዳችን መማር ያለመቻላችን ዝግመት ሰፊ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ባንዳ ተደብቆ ወይም አቀርቅሮ ተሚውልበት ባህል ወጥተን የባንዳዎችና የከሃዲዎች አድናቂና ተከታዮች የመሆናችን መርገምት ልባዊ ፀሎት ያሻዋል፡፡

ለገሰ ዜናዊ በወቅቱ በነበረው ያረቦች አመፅ መክንያት በእስራኤሎችና በምዕራባውያን ትዕዛዝ እንደዚሁም ሲወለድ በተነቀረበት የአማራ ጥላቻ የአማራን ጥቅም ለመንጠቅ ዓባይን ተሱዳን ደጃፍ ሊገድብ “ሕዳሴና ቦንድ” እያለ ቃዠ፡፡ የለገሰ ቅዥት እንደ ዛር ተኮፍሷቸው የሰይጣን ቁራጩ ለገሰ ቦንድ እንዲሳካ ስንቶች “ምሁራን” ስንክሳር እሚያካክል ጥሑፍ ጣፉ፡፡ ስንቶች ሆዳም ካድሬዎች የቦንድ ስብሰባዎችን ለማዘጋጀት መቀመጫቸውን ተወዲያ ወዲህ አማቱ፡፡ ስንቶች በሕዝባቸው መቃብር እንጀራ እሚጋግሩ ዘፋኞች ልማት፣ ህዳሴና ታድሶ እያሉ ዘፈኑ፡፡ ከሀዲዎችን እየተከተላችሁ ሕዝባችሁን አታስፈጁ ቢባሉም አልሰማ አሉ፡፡ በእነዚህ ህሊና ቢስ ጉዶች ተላላኪነት የተሰበሰበው የቦንድ ገንዘብ ወገኖቻችውን እንደ ደን ከማስጨፍጨፍ በተጨማሪ ለገዳዮቹ መሳከሚያ፣ ለሰርግ መደገሻ፣ ለግል መርከብና ለአውሮጵላን መግዣ መዋሉ  ገሃድ ሆነ፡፡ ብዙ ሰሚ አላገኘችም እንጂ ገሃድ ከመውጣቱም በፊት አንድ የሜቴክ ሰራተኛ አጋለጠች፡፡ [2] (ይኸንን ቆርጠውና አጣብቀው ይመልከቱ) https://ethsat.com/2017/08/esat-menalesh-meti-former-employee-metec-exposing-corruption-august-2017/

ከቦንድ መቦንደድ ውድቀት ትምህርት መውሰድ ያቃታቸው ጉዶች ዛሬ ደሞ ለገሰ በአማራ ጨቋኝነትና በብሔር ብሔረሰቦች ተጨቋኝነት ግሳንግስ ልብወለድ ዘፍቆ፣ በካድሬነት አስደቁኖና በጆሮ ጠቢነት አስቀስሶ ሕዝብ ለመፍጀት ለሃያ አመታት እንደ እቃ ሲጠቀምበት ለኖረው ተቅለስላሽ እባብ ፓስተር ፈንድ መፈንደድ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ፈንድ ፈንዳጆች አባ የሻነው ተሚተርኳት ትልም አነሱ፡፡

አባ የሻነው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትል ታሪክ ደጋግመው ይተርኩልን ነበር፡፡ አባ የሻነው “ተትሏ እንማር!” ይላሉ ራሳቸውንም እንደተማሪ በመቁጠር፡፡ “ትሏ ዛፍ ለመውጣት ስትሞክር ወደቀች፤ አንድ በሉ፡፡ እንደገና ሞክረች ግን ነጠረች፤ ሁለት በሉ፡፡ አሁንም እንደገና ስትንጠለጠል ዘች አለች፤ ሶስት ብሉ፡፡ ዘች ታለችበት ተነስታ እንደገና ተንጠለጠለች፤ ግን ተመልሳ እርፉቅ አለች፤ አራት በሉ፡፡ እርፉቅ ታለችበት ተነስታ አሁም ግንዱን በትንሹ ወጣች፤ ግን እንደገና ተንደባለለች፤ አምስት በሉ፡፡ ተተንደባለለችበት ተነስታ ተበፊቱ የበለጠ ርቀት ዛፉን ወጣች፤ ግን ተመልሳ ነጠረች፤ ስድስት በሉ፡፡ ተነጠረችበት ተነስታ ለሰባተኛ ጊዜ ስትሞክር ሰማይ የደረሰውን ዛፍ ምንም እንከን ሳይገጥማት ወጣችው” እያሉ ይተርካሉ ጨረቃ የመሰለ ፈገግታ እያሳዩና ሻሽ የመሰለ ጺማቸውን እያፍተለተሉ፡፡

ከትረካው በኋላም አባታችንና መምህራችን አባ የሻነው “በሰባተኛው ዙር ትሏ ለምን የተሳካላት ይመስላችኋል?” ብለው ሲጠይቁ “በሰባት ስላሴ ስለሚውል፣ ተስፋ ስላልቆረጠች …ወዘተርፈ” እያልን እንመልሳለን፡፡ እርሳቸውም “እርግጥ ነው ተስፋ ያልቆረጠን ስላሴም ይረዳል!” ብለው የምንሰጠውን መልስ ሳያጣጥሉ “ትሏ የተሰካላት ተእያንዳንዷ ልምድ ትምህርት በመውሰድዋና ያደናቀፏትን መንገዶች ትታ ሌላውን በመከተልዋ ነው” ብለው  ተልምድ የመማርንና የተለያዬ መንገድ የመከተልን ጠቀሜታ ያስተምራሉ፡፡

የአባ የሻነው ትል ያህል ተልምድ መማር ተስኗቸው ስለ ቦንድ እጃቸው ውሀ እስቲቋጥር የጣፉት፣ ላንቃቸው እስቲደርቅ የሰበኩት፣ ልሳናቸው ጥረቅም እስቲል የዘፈኑትና መቀመጫችርውን እስቲያልባቸው ያረጠረጡት ህሊናቸው የሸጡ አለዚያም የተንዘላዘሉ የለገሰ ቦንድ ካድሬዎች ነበሩ፡፡ አለዚያማ ሰይጣንና ለገሰን እንኳንስ ቆመው ሞተውስ ከዘልዛላ በቀር ማን ያምናቸዋል?

የሚያዝ የሚጨበጥ ጭራ የሌለው ለገሰ፤ የሰፈሩን ባንክ በመዝረፍ ውንብድናውን የጀመረው ለገሰ፤ በአስር ሺ የሚቆጠሩ የመንደሩን ጎረምሶችና ኮረዳዎች እንደ ሳር አሳጪዶ አገራችንን የባህር መተንፈሻ የነሳት ለገሰ፣ ኬሻ በአሸዋ እየሞላ በርሃብ ለረገፈው ሕዝብ እንደ ስንዴ የሸጠው ለገሰ፤ ለፖለቲካ ፍጆታ የቅዬውን ሕዝብ በቦንብ ያስጨረገደው ለገሰ፣ አማራን ለማዳከምና ለማጥፋት ድንጋዩን ብቻ ሳይሆን ጠጠሩን፣ አሸዋውንና አፈሩን የፈነቀለው ለገሰ፣ በአያቶቻችን ደምና አጥንት የከበረውን መሬታችንን ለሥጋና ለነፍስ አባቱ ሱዳን የሰጠው ለገሰ፣ ሕዝብን በቋንቋ ጎራዴ ያቃላው ለገሰ፤ ስንቱን ባልታወቀ ወህኒ ያሰቃየው ለገሰ፣ እልፍ አእላፍን እያሰደደ ባባህር ያስበላውና በጭራቆች ያሳረደው ለገሰ “ቦንድ” ብሎ ሲጮህ ቦንደኞቹም ተከትለው እንደ ገደል ማሚቶ “ቦኦ…ንድ…ቦኦ..ንድ” እያሉ አስተጋቡ፡፡ ሳጥናኤል የእግዚአብሔርን ቃል እየተናገረ እንደሚያታልለውም ለገሰ “ራዕይ፣ ታድሶ… ህዳሴ” እያለ ጫቱን እየቃመ ሲጀነጅን ቦንደኞቹም ተከትለው “አዎ ልማት፣ ታድሶ፤ ህዳሴ! ያገር ጉዳይ! የሕዝብ ጉዳይ!” እያሉ ተሽኮረመሙ፡፡

መሽኮርመሙ ከሞቀ ውሀ እንደ ገባ ጨው ፍርክስክስ አርጓቸው ነፈሰ-ገዳዩንና ከሀዲውን ለገሰን እንቃወማለን እሚሉት ሁሉ የቦንድ ካድሬ ሆነው ቁጭ አሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ሕዝብ እንደ ጫካ ሲጨፈጨፍ ድምፃቸው ተሰምቶ እማይታወቅ ተሽኮርማሚ ዲዳዎች በጥሑፍና በራዲዮ ቦንድ፤ ታሐድሶ፤ ህዳሴ በሚሉት ቃላት አፋቸውን ፈቱ፡፡ ስንቶቹ ከንቱ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ከስማቸው ዳር ፒኤች ዲ፣ ኤም ዲ፣ ፕሮፌሰርና ዶክተር  እሚሉ ማእረጎች እያስቀመጡ ድጓ እሚያካክል ዝባዝንኪ እየጣፉ አንባቢን አባተሉ፡፡ ስንቶች አቀንቃኞች “ህዳሴ፣ ራዕይ፣ ታድሶ፣ ልማት” እያሉ መስክ ግጦ እንደ ጠገበ አለሌ በየሜዳውና አዳራሹ አክላሉ፡፡ ስንቶቹ ዘፋኞች ሙሴ የተሻገረውን ባህር የሸጠውን ለገሰን “ባህር አሻጋሪው ሙሴ!” እያሉ በሌለ ባህር አፋቸውን እንደ ሰማይ ከፍተው ተሕዝብ፣ ተእግዚአብሔር፣ ተህሊና፣ ተእውነትና ተታሪክም እስከ መጨረሳው ተቀያየሙ፡፡ ስንቶች ከርሳሞች የለገሰን ቦንድ ለመግዛት እንደ ቡችላ ጅራታቸውን ወትፈው ተንጦሎጠሉ፡፡

ዛሬ ደግሞ በኸርማን ኮን ኃይል ወንበር የወጣው አባትዮው ለገሰ ሞቶ እባቡ ልጁ በኸርማን ኮን ተንኮል ወንበር ሲወጣ ለለገሰ የተዘፈነው ዘፈን ተደገመ፡፡ ባህር አሻጋሪው ሙሴ ተዘፈነ፡፡ “ምሁራን”፣ ካድሬዎች፣ ዘፋኞች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና እነዚህን የሚከተሉ መንጋዎች በመዝሙር፣ በዘፈን፣ በፌስ ቡክ፣ በትዊተር፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ ድጓ በሚያካክሉ ጽሑፎች ልሳናቸው እስቲዘጋና ኮቢያቸው እስቲደርቅ እባቡን ፓስተር አወደሱ፡፡ ፓስተሩ በካድሬነት፣ በጆሮ ጠቢነት፣ በኮሎኔልነት፣ በአስተዳዳሪነት፣ ከአባቱ ከለገሰ ጋር በገደላቸውና ባሰቃያቸው ዜጎች ጦር ሰደዱ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ከእግሩ ሥር እንደ አሽከር ተወሸቁ፤ ሌሎችም በፍቅር አብደው ከተኸሻውና ከደረቱ ወደቁ፡፡ አያሌ “ምሁራን” ለኮር አባሉ የኢህአዴግ ሊቀመንበር የሃያ አራት ሰዓት ካድሬ ሆኑና አረፉ፡፡ ካድሬነታቸው እየበረታ ሲሄድም ከመዝሙሩ፣ ከዘፈኑ፣ ከስግደቱ፣ በፍቅር ሙዝዝ ከማለቱም አልፈው ፈንድ ከፈቱና ቂሉን ሕዝብ ማለብ ጀመሩ፡፡

ተመምሩ ደቀመዝሙሩ እንደሚባለው አማራ ፈንድ የሚሰበሰብለት ፓስተር ግን ከአባቱ ለገሰም የበለጠ አማራን በአገሩ ስደተኛ ማድረጉን ቀጠለ፡፡ እንኳን ጉራፈርዳ ቤገምድር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋም አማራን ስደተኛ አደረገ፡፡ ለገሰ እንደ ጨንገር እየመለመለ ታማራ ጫንቃ የጎለታቸውን እርጉም ባዳንዳዎች እንደ ካርታ ተወንበር እየፐወዘ አማራን እርስ በርሱ ለማናከሰ እንደ አሳዳጊው ሰይጣን ድንጋዩን ብቻ ሳይሆን ጠጠሩን፣ አሸዋውንና አፈሩንም ፈነቀለ፡፡

ይኸ ሁሉ እየሆነ ሆዳሙ የምሁር ካድሬ ግን ተአባ የሻነው ትልም አነሰ፡፡ የአባ የሻነው ትል ተስድስት ልምዶች ስድስት ትምህርቶች ስትቀስም እኛ በወልቃይት አማሮች የተጀመረው መታረድ በደኖን፣ አርባ ጉጉን፣ ጉራፈርዳን፣ መተከልን፣ ጎንደርን፣ ኢሉባቦርን፣ ለገጣፎንና ሌሎችም አካባቢዎች ካዳረሰበት አርባ ዓመታት ልምዶች ስንት ትምህርት ቀሰምን? የአባ የሻነው ትል በሰባት ሙከራዎች ሰባት መንገዶችን ስትሞክር እኛ በአርባ ዓመታት  ስንት መንገዶችን ፈተሽን?

“የወንዝ ዳር ልማት፣ የብሔሮችና የሲኖዶስ እርቅ፣ አገራዊ ወይም ኤፍሬም ይሳቃዊ ሽምግልና” በሚሉ አቢይ ለገሰ ስብከቶች የተሽኮረመምን ስንት ዓርባ አመታት ተመሳሳይ መንገድ እንከተላለን? እስከ መቼስ አባትዮው ለገሰ ቦንድ ሲል ተቦንድደን ልጁ አብዮት ፈንድ ሲል ተፈንድደን እንዘልቀዋለን?

አላግባብ መቦንደድና መፈንደድ የማይሰለቸው ዘልዛላ በአባትዮው ለገሰ ቦንድ ለህወሀት መርከብ እንደገዛው በጆሮ ጠቢ ልጁ ፈንድም ለወነግ ባቡር እንደሚገዛ ይጠበቃል!

 

  1. የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ https://zehabesha.info/archives/105403
  2. ዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ (ምን አለሽ መቲ) እና ወ/ሮ ቤተልሄም ግርማ የቀድሞ የሜቴክ ሰራተኛ ድርጅቱ ውስጥ ስለሚካሄደው ሙስና አጋለጡ።https://ethsat.com/2017/08/esat-menalesh-meti-former-employee-metec-exposing-corruption-august-2017/

መጀመርያ ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም. እንደገና ግንቦት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

ተመሳሳይ ጽሑፎች

  1. እስከ መቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች? http://quatero.net/amharic1/archives/28589
  2. ምሁራን በእባብ ተሸውደው የዕፀ በለስ ፍሬ መግመጥ እሚያቆሙት መቼ ነው? https://www.satenaw.com/amharic/archives/37149

 

2 Comments

  1. The Nile Dam was conceived as a grand electrification project for the would be independent republic of Tigray. The TPLF territorial map drawn in secret shows that the Benishangul region where the daam is located is adjacent to Tigray. Future take over of the region by Tigray is part of the TPLF plan of greater Tigray. But the TPLF is now pushed out of power, has run away to Tigray and the nile dam meant for Tigray is out of its hands. The change in Ethiopia has destroyed the TPLF grand plan and mad the Nile dam a national Ethiopian issue and project. Tigray will not be the final sole owner of the Dam and beneficiary of the power generated.as conspired by the TPLF.

  2. The women diasporas donated the majority of the money to Abiy’s trust fund without their husbands
    approval , now the women diaspora who have given money to PP trust fund are spying conspiring with many of the Ethiopian embassies against their own husbands and family members because the women are blaming their husbands and brothers for the failure of the trust fund withtwith money being looted to buy bullets to kill poor Ethiopians.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.