ዛሬ በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት የሞከሩ 12 አባላት ያለ መክሰስ መብታቸው ተነሳ

Mustefe e1590112449605በሶማሌ ክልል በዛሬው ዕለት ተደርጎ በነበረው ልዩ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከተያዘው አጀንዳ ውጭ ስብሰባው እንዲሰረዝ፣ብጥብጥ በማንሳት፣የቀሩት የምክር ቤት አባላት ጭምር ስብሰባውን ረግጠው እንዲወጡ እና የክልሉን ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ባለስልጣናትን ሲዘልፉ ቆይተው ስብሰባውን ጥላው የወጡት እና ከምክር ቤቱ ውጭም ሁከት ለመፍጠር የሞከሩ 12 የምክር ቤት አባላት ያለ መክሰስ መብታቸው የተነሳ ሲሆን በሌሎች ወንጀሎችም የሚያስጠይቅ ወንጀል መጠርጠራቸው ተገለጸ።

ማምሻውን ጉባኤውን ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “ሁከት በመፍጠር፣ በሥርዐት አልበኝነትና እንዲሁም በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረዋል” ያላቸውን 12 የምክር ቤቱ አባላት ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን ሲያስታውቅ ማንነታቸውንም በስም ዘርዝሯል

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ አባላት

አህመድ መሀመድ ላይሊ
አህመድ አዳን አህመድ
አብዲወሊ መሀመድ ፋራህ
አህመሀድ ሀሰን መሀመድ
ሻፊ አሺር
ነዲር ዩሱፍ ኣደም
አብዲረሳቅ አብዱላሂ በይሌ
ዩሱፍ ኢልሚ ኢሳቅ
አህመድ ሀሰን ኑር
ዩሱፍ አህመድ ሂርሲ
ኒምዓን አብዱላሂ ሀመሬ እና
አብዱራህማን ኡራግቴ መሆናቸው ታውቋል።

ህብር ራዲዮ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርበኞች ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ሲሉ ማይካንድራ ላይ ተይዘዋል ተብለው የተከሰሱት 3 ወጣቶች ጥፋተኛ ተባሉ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.