/

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የታየው የኮቪድ-19 ስርጭት በሁለቱ ወራት ውስጥ ከነበረው ይበልጥ አሳሳቢ ነው – የጤና ሚኒስቴር

Health Mባለፉት ሁለት ሳምንታት የታየው የኮቪድ-19 ስርጭት በሁለቱ ወራት ውስጥ ከነበረው ይበልጥ አሳሳቢ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

እንደ ሃገርና እንደ አዲስ አበባ ከተማ ባለው የቫይረሱ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የየዕለት ቁጥሩ ቢለያይም ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ ብቻ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ተነጥሎ ሲታይ 230 መሆኑ የቫይረሱን የስርጭት ሁኔታ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል።

ይበልጡንም ደግሞ ባለፉት 2 ቀናት ቫይረሱ በ49 ሰዎች ላይ መገኘቱን እንደ አብነት በማንሳት የቫይረሱ ስርጭት መጠናከር ከህብረተሰቡ የጥንቃቄ ጉድለትና መዘናጋት የመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በበኩላቸው፥ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 365 ሰዎች 56ቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ከበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጋር ንክኪ ያልነበራቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውስም 48 በመቶ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

የቫይረሱ ስርጭት እንደየክፍለ ከተሞቹ የሚለያይ ቢሆንም ቀደም ሲል የተጠቀሰው ታሪክ ከሌላቸው ታማሚዎች ውስጥ 45ቱ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ቫይረሱ ከሰው ወደሰው እየተዛመተ የሚገኝበትን ፍጥነት ለማሳየትም በልደታ ክፍለ ከተማ በአንድ ሰው አማካይነት 32 ሰዎች መያዛቸውን አንስተዋል ዶክተር ኤባ፡፡

በሌላ በኩል በፖሊስ ጣቢያ በህግ ታራሚዎችና ጉዳያቸውን በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንኪኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት ሌሎች 66 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮኃንስ ጫላ እንደተናገሩት፥ የሃገሪቱም ሆነ የአፍሪካ ትልቁ የመገበያያ ስፍራ የሆነው መርካቶ ገበያን በያዘው አዲስ ክፍለ ከተማም ቁጥሮች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸውን ነው የተናገሩት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  In Dexter's laboratory lives the smartest boy you've ever seen

በመሆኑም ከፍተኛ ጥግግትና ጥንቃቄ አልባ እንቅስቃሴን ማስቀረት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ ሁለተኛው የቤት ለቤት ልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ያመላከቱት ሃላፊው፥ በልየታ ስራ ወቅትም ተመሳሳይ የጉዞም ሆነ የንክኪ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች መገኘታቸውን በማንሳት አሳሳቢነቱን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በመግለጫው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በተለይ በመዲናዋ ስጋትነቱ እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን በ7 ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተከሰተውን ይሄው የቫይረስ የስርጭት አድማሱን በክልሎች በተለይም ከአጎራባች ሃገራት ወደ ሃገር በሚገቡ ታማሚዎች አማካይነት ይበልጥ እንዳይስፋፋ የክትትል ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑም ተነስቷል፡፡

በቀጣይ ቀናትም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩት የኢድ-አልፈጥር በአል ስለሚመጣ በግብይትና በበአሉ አከባበር ወቅት ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዳይለየው መልዕክት ተላልፏል፡፡

በሶዶ ለማ/ኤፍ.ቢ.ሲ

 

1 Comment

  1. በጣም አስቸኳይ/Top Urgent/

    ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማሰሱ ስራ በደንብና በተቀናጀ ሁኔታ መቀጠል አለበት፡፡ አዳዲስ ሰዎች መገኘቱ ብዙ ጠቋሚ ነገር ስላለው ሰዎቹ የሚኖሩበት፣ የሚሰሩበት እና በወር ውስጥ የት የት አካባቢ እንደነበሩ በማጣራት በየቦታው የመርመር ስራ ጊዜ ሳይጠው ሊከናወን ይገባዋል፡፡
    የቅስቀሳ ስራው፣ መታጠቢያና ሳኒታይዘር የማቅረብ ስራ ቀድሞ ተጀምሮ ስለነበር በአሁኑ ጊዜ መሰላቸት ደረጃ ደርሶ የተወም ስላለ ክትትል የሚያደርግ ግብረ-ሃይል ከፖሊስ፣ ወረዳ እና ታዋቂ ግለሰቦችን ወይም አርቲስቶችን በማካተት በየሰፈሩና አካባቢው ሊሰራ ይገባል፡፡ መራራቅ እንዲከበር እና ማሰክ ማድረግ ግዴታ ሊሆን ይገባል፡፡ ህፃናት እንዳይወጡ መከልከልና ይህንን የማይፈፅሙ ላይ ጊዚያዊ እርምጃ መውሰድ ያስገባል፡፡ ይህ በአፋጣኝ ካልተደረገ ነገ የማይወጡት ችግር ላይ እንዳይደረሰ፡፡ እንደውጪዎቹ Lockdown ማድረግ ባይቻልም አስቸኳይ አዋጁን ያለአግባባ ሳይጠቀሙ /Abuse ሳይደረግ/ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል፡፡ ምግብ ቤቶችና ካፌዎች በሚኖራቸው የወንበር ብዛትና ስፋት ሊያስናግዱት የሚገባው ሰው ብዛት እየተወሰነ በአግባቡ እየፈፀሙ ለመሆኑ የህግ አካላት እየገቡ መቆጣጠር ይኖርባቸዋል/የእጅ መንሻ መፈለግ ቀርቶና የሚሰጡ ባለቤቶችም እንደሚጠየቁ በማሳሰብ/፡፡

    የጤና ጣቢያዎችም አንድ ግለሰብ ቫይረሱ ተገኘበት ሲባል የሚደረግ ጥንቃቄና በአንቡላንስ መኪና የመውሰድ ስራ ላይ ብዙ ቸልተኛ ስራ እየተደረገ ስለሆን መስተካከል ይኖርበታል የሚቆጣጠራቸው አካልም ያስፈልጋል፡፡ በየሱቁና ንግድ ቦታዎች ከአስተናጋጆቹ ጀምሮ ድንቡን በማያከብሩ ላይ መጀመሪያ ባለንብረቶቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማደረግ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ስንት ደረሰ እያሉ surprise ከመሆን አሁኑኑ ሁሉንም ጥንቃቄዎች ማስተግበር ያስፈልጋል፡፡ በእምነት ተቋማት አካባቢም በሀይማኖት ሰዎች በደንብ ሊነገር ይገባል መተፋፈግ እንዳይፈጠር፡፡ ዘግይቶ ቫይረሱ የገባባቸው የደቡብ አሜሪካ አገሮች ላይ እያስከተለ ያለው ችግር እየታየ ስለሆነ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

    አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.