/

“ግብፅ የራሷ አስዋን ግድብን ስትሰራ የኢትዮጵያን አስተያየት አልጠየቀችም ነበር” አሜሪካዊው የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን

Jessie


“ግብፅ ለፀጥታው ምክር ቤት የላከችው ደብዳቤ ላይ ከጠቀሰችው ጉዳይ አንዱ ኢትዮጵያ ግድቧን መሙላት እንዳትጀምር የሚያሳስብ ነው። ይህ የግብፅን ሀፍረተቢስ አካሄድ የሚያሳይ ነው። ራሷ የአስዋን ግድብን ስትሰራ የኢትዮጵያን አስተያየት አልጠየቀችም ነበር። ኢትዮጵያ እና ግብፅ በተለያዩ አለም አቀፍ ህጎች ይዳኛሉ ካልተባለ በቀር ግብፅ በፊት ያላደረገችውን ኢትዮጵያ አሁን አድርጊ ልትባል አይገባም”— ጄሲ ጃክሰን ከፃፉት ደብዳቤ የተወሰደ


አሜሪካዊው የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን ግብፅ ሰሞኑን ለተ.መ.ድ የፀጥታው ምክር ቤት ያስገባችው ደብዳቤ ላይ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ (Congressional Black Caucus) ተቃውሞ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቧል!

ዛሬ ማምሻውን የደረሰኝ ይህ በጄሲ ጃክሰን የተፃፈ ደብዳቤ እንደሚለው ግብፅ የአሜሪካ መንግስትን፣ የአለም ባንክን እንዲሁም ተ.መ.ድን በመጠቀም የቅኝ ግዛት ውል በ11 የአፍሪካ ሀገራት ላይ ለመጫን እየሞከረች ነው።

“መንግስታችንም ሆነ የአለም ባንክ የአደራዳሪ ሚና እንደሌላቸው ግልፅ ሊደረግ ይገባል… አሜሪካ አረብ ሊግ እና ግብፅ ከወጠኑት የቅኝ ግዛት ውልን በጥቁር አፍሪካውያን ላይ ከመጫን እቅድ ራሱን ሊነጥል ይገባል” የሚለው ደብዳቤው ለጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ መሪ ካረን ባስ የተፃፈ ነው።

ኤልያስ መሰረት

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

[pdf-embedder url=”https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2020/05/Rev.-Jacksons-letter-to-Bass-May-19-2020-4.pdf” title=”Rev. Jackson’s letter to Bass – May 19, 2020 (4)”]

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ... ይነጋል ጨለማው ... !

8 Comments

 1. የገዛ ከሃዲ ልጆቿ ከውስጥ ሲገዘግዙዋት ፣ እነ አልሲሲ ጋር የሚያሽቃብጡትን የአገር ከሃዲዎችን ሳይሆን ከነ አልሩሲ ጋር የሚያብሩትን እነ ጀሲ ጃክሰንን የሰጠን አምላክ ያውቃል። እንዲህ ነው ጀሲ ጃክሰን። እውነቱንም ነው የአልጀዚራው አልሩሲ። አገርበቀል ሚዲያዎች እንደምን ድምጻችሁን በዚህ አባይ ጉዳይ ከፍ እንደማታደርጉ አይገባኝም። እነ የዛ ቱልቱላ ጁዋርን ሚዲያ ማለቴ አይደለም፣ ሌሎቻችሁ እልፍ አደላችሁ እንዴ? ወገኖች የአባይ ጉዳይ እኮ ነው፣ የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ እኮ ነው። ይህ ፕሮጀክት እንዴት ተጀመረ ስህተቱ ሳይሆን አቢይ ምን ላይ አድርሰውታል ፣ አለምስ ምን እያለ ነው ነው መታየት ያለበት። ይቺ በውስጥ እንዲህ እርቃናችንን መሆናችንን አይቼ ነበር አቢይ የሙሌቱን ጉዳይ እስከ አሜሪካ ምርጫ እያስታመሙ ይሂዱ ብዬም የተማለድኩት። እነሆ የጀሲ ጃክሰኑን አይነት በሰፊው ለመሸመት ከትራምፕ ውድቀት በሁዋላ ያመቻል ከሚል ነበር። ፈጣሪ አሁኑኑ እደጃችን ሲያመጣቸው የአገሬ ህዝብ በዚህ ጉዳይ በጣም መምከር አለበት። በተለይ ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ አገሩን ለውስጥና ውጭ ባንዳ ያሰረከበው ብዙሃኑ ወገን ያነዳል፣ ያስቆጫልም። የሚያወሩትና የሚሰብኩት በህይወታቸው ሙሉ ከወሬና መኮፈስ በቀር በግል እንኳ ዬትም ፈቀቅ ማለት ያልቻሉ ፖለቲሻን/አክቲቪስት ተብዬዎች ናቸው። አቢይ አህመድ ካጠፉት ትልቁ ስህተት ያኔ ከውጭ በገፍ ምድረ ተቃዋሚ “በድልአድራጊነት” መጋበዛቸው ሳይሆን ከገቡ በሁዋላ አስቤዛና መጠለያ ማቅረባቸው ነው። ለጁዋር አይነቱ የአገር ከሃዲ ደግሞ ከአስቤዛና መጠለያ አልፎም ዘበኛም ተቀጥሮለታል። ትልቅ ስህተት። ፖለቲሻን ለአቢይ ብለው ሳይሆን ለአገራቸው እስከሆነ ድረስ ለምን ተብሎ ነው ከደሃው ጉሮሮ ተነጥቆ የእነርሱን ከርስ የሚሞላው? ያውም ዛሬ ለአገሪቱ እንዲህ ጠላት ሊሆኑ። ለምንድነው አቢይ የታዬ ደንደአን አይነት ቆራጥነት የማላይባቸው? ፍርጥ አድርገው ቢያፈርጧቸው ኖሮ እንዲህ የማንም ጨምላቃ ግብጽ ትሁን ወያኔ መቀለጃ አንሆንም ነበር። ልደቱ አያሌው እንኳ እንዲህ እስኪኮፈስብን ድረስ? መቼስ እነዛኑ የመቀሌን ግዞተኞች ተማምኖ እንጅ በምኑ ነው አሁን እሱ በአገሬ ላይ ዛቻው? ብዙ ያስቆጫል ያገራችን ጉዳይ።

 2. So truthfully and realistically and straightforwardly powerful !!!

  Thank you so and so much for standing
  by the side of those who deserve the right to use their natural resources fairly and equally!!!

 3. ብርሀኑ ነጋ/ጁዋር መሀመድ/አንዳርጋቸዉ ጽጌ/ዳዉድ ኢብሳ/መራራ ጉዲና/ሌንጮ ለታ/ልደቱ አያሌዉ/ጁነዲን ሳዶ/አረጋዊ በርሄ…. እንደዉ ተሳስተዉ ስለ አባይና ሱዳን አሰፍስፎ ሊበላዉ ለደረሰዉ የኢትዮጵያ መሬት አልሰሙ ይሆን? ደ/ር አብይስ ምን ነካዉ ሐ/ማርያምን የመሰለ ቤቱን ማስተዳደር የማይችል ሰዉ እሳት ከበሉ ከግብጽ ተደራዳሪዎች ዉስጥ መመደቡ እንቅልፍ እንዲተኛ ነዉ ወይስ ተደራዳሪዎችን እንዲያግዝ እሱን ማካተቱ? እነ ሺመልስ አብዲሳ በአክሊሉ ሐብተወልድ/ይልማ ዴሬሳ/ከተማ ይፍሩ መቀመጫ ትቀመጡ? እንደዉ ምን ብንበድልን ነዉ? እግዚኦ የዘረኛዉ ብዛት ከትላንት አይማር። ዶ/ር አብይ አንድ ወንጀለኛ በስልጣን ዘመኑ ላያስር ቃል ገብቶላቸዋል ማለት ነዉ? እዉነትም ሐ/ማርያም እንዳለዉ ማንኛዉም ወንጀል ዉስጥ እጁ አለበት ያለዉ ነገር እዉነት ይሆን? ለማንኛዉም ከሐ/ማርያም አንደበት ስሙት። አፍሪካዉያን ጥቁር አሜሪካኖች በችግራችሁ ጊዜ ደርሰናል በችግራችን ጊዜ ድረሱልን። ጄሲ ጃክሰን እናመሰግናለን የእኛ መሪዎች መናገር ያልደፈሩትን እርሶ ተናገሩልን።
  በኢትዮጵያ አምላክ ሐይለ ማርያም ሲለበለብ ስሙት ከ ቲም ሰባስትያን ጋር ኢትዮጵያ የወደቀችዉ እንዲህ ያለ ጉድ ላይ ነበር? አያፍርም መቶ ጊዜ መንግስቴ መንግስቴ ይላል አክብረዉ እንደያዙት ሁሉ። ቤተሰብ ባይኖርህ ሌላ ልትባል ይገባ ነበር ማፈሪያ https://www.yout ኢትዮጵያ ዉስጥ አመራሩ ሃላፊነት ሲጎድለዉ ሀገር ወዳዱ በግሉ ትንቅንቅ ይዟል የአንድነት ሐይሎች በርቱ ቀኑ ለዘረኛዉ ሲጨልም የአንድነት ሐይሉ ገና ያብባል።

 4. Thank you, Rev. Jesse Jackson, for being the voice for my old country Ethiopia. I hope the Black Caucus will speak up against the unprecedented miscarriage of justice by the US Government and World Bank on Ethiopia.
  Whatever happens in the Security Council, Ethiopia must proceed according to plan and the generation of hydroelectric power a reality for its more than 60% citizens without electricity.

 5. African Union AU should provide a verification to Ethiopia stating Ethiopia needs both the GERD powerplant and the Nile water , a similar type of verification to the verification Ethiopia recently got from European Union EU.

  Abawirtu
  Please provide us voting Ethiopians the exact informations evidences about Lidetu’s , Jawar’s treason actions of helping Alsisi so we Ethiopians will reconsider our choice of political parties who to vote for at the next elections according to the substantiated informations we get . So far all the information we got from PM Abiy is ” there are traitors” but no names were provided so thank you for telling us the names but names are not enough we need more details.

 6. Ethiopians in USA should change their attitudes towards Black African Americans completely by studying the term “GO BACK TO AFRICA” in the Urban Dictionary .

  Skift › 2020/01/22 › provocativ…
  Provocative ‘Go Back to Africa’ Travel Campaign Sees Early Success in … – Skift

 7. Great job by Jacksons!!

  This is a surprise & wonderful narratives is being done by Jackson that someone can understand what a gap is seen even if there are so many Ethiopian scholars & experts on water resource managements in Ethiopia & abroad (on finding out what Egypt had been done before & Great countries; like UK & others have been imposed their colonization & neo-colonization power in Ethiopia).

  All in all, it shows Ethiopia’s weaknesses on foreign diplomatic arena. Just like Jacksons requested for Africa- Americans, Ethiopians opposition parties; Balderase (lead by Eskinder Nega) who have a great stake on future development of the country shall collect “petition” from all Ethiopians for full right of using Nile water by Ethiopians, instead of focusing them on political conflicts.

  Let’s vow for our right & long live to Ethiopia!!

 8. Jesse Jackson was a shining star in the US politics. He could not make it to the top for a well known reason. Now we see the man standing on the side of people that deserve the dam more than any other country. We are grateful for his firm stand. I would like to see very much a letter of thanks from our Prime Minister. Ambassador Alemayehu Abebe

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.