በትግራይ ባለሀብቶችም የተቃውሞ ጥያቄ አቅርበዋል የባለሃብቶችና ነጋዴዎች ጥያቄ !

am 2 በትግራይ ባለሀብቶችም የተቃውሞ ጥያቄ አቅርበዋል የባለሃብቶችና ነጋዴዎች ጥያቄ !ትግራይ የኣንድ ፊውዳል ስርዓት የሚከተል ቤተሰብ የግል ንብረት ሆና ቆይታለች።

ፖለቲካዊ ስልጣን ከቀበሌ እስከ ርእሰ መስተዳድር ፤ ከዋህዮ(ሴል) እስከ የህወሓት ስራ ኣስፈፃሚ ኣባላትና ሊቀ መንበር የኣንድ ቤተሰብ ርስት ሆና ቆይታለች ኣሁንም እዛው ናት። በማሕበራዊ ጉዳይም ከጫፍ እስከ ጫፍ በኣንድ ቤተሰብ ስር በመኖፖል የተያዘ ነው።

በምጣኔ ሃብት ከጫፍ እስከ ጫፍ ቤተሰቡና ኔትወርኩ ሙሉ በሙሉ ሊባል የሚችል በቁጥጥሩ ስር ኣውሎታል።

ይሄ ጉዳይ ኣስመልክቶ ኣቶ ገብሩ ኣስራት “መላ ቤተሰብ በመደራጀት ኣንዱ ፖለቲካዊው ስልጣን ሌላው ኢኮኖሚያዊ መስመሩ በመቆጣጠር ኣገሪቱን ዘርፋታል” ብሎ በሰርጌን መፅሄት ገልፆ ነበር።

ዛሬ በመሰቦ ስሚንቶ ኣጋጥሞ ያለው ችግር የዚሁ ኣካል ነው። እነ ኣቦ ስብሓት ከመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራ ኣስከያጅ እስከ ዘበኛ፤ ከዋና ስሚንቶ ኣከፋፋዩ ጉና ንግድ እስከ የቀበሌ ኣከፋፋዮች የራሳቸው ዘመድ ኣዝማድ በማሰማራት ገበያው እንደፈለጉ ይዘውሩታል።

እንደ ዳንጎቴ፣ ሓበሻ፣ ሙገር ወዘቱ ስሚንቶ ፋብሪካዎች ትግራይ እንዳይገቡና ህዝቡ ኣማራጭ እንዳያገኝ መንግስታዊ ስልጣን ተጠቅመው እገዳ በመጣል ሌላ የገበያ ኣማራጭ እንዳያገኝ ኣድርገዋል።

ዛሬ የትግራይ ባለሃብቶች ትዕግስት ተማጥጦ ዓመፅ ለማሰማት የገፋፋቸው ምክንያቶች

* በቂ የስሚንቶ ምርት እያለ የነሱ ተራ ለስብሓት ነጋ ዘመዶች እየተሰጠ ዋጋው በእጥፍ መጨመሩና ለኪሳራ መዳረጋቸው፣

* የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ ችግሩ ለመቅረፍ በተደጋጋሚ መግለጫ ቢሰጥም ምንም መፍትሄ ባለመገኘቱ፣

* ንግድ ቢሮ ስሚንቶ ለማከፋፈል ከነጋዴዎች ወደ ከተማ ኣስተዳደሮችና ቀበሌዎች እንደሚሰጥ የገለፀው ዋነኛ ተጠቃሚ የሚሆኑት ኣሁን ኔትወርክ ዘርግተው ስሚንቶ እየሸጡ ያሉትየ እነ ስብሓትን ቤተሰብ መሆኑ በመረዳታቸው(ከቀበሌ እስከ ክልል ያለው ኣስተዳደራዊ መዋቅር በነስብሓት እጅ መሆኑ ስለሚረዱ)፣

* ኣብዛኛዎቹ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ከባንክና ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ተበድረው ከኣረጣ የማይተናነስ ወለድ ከኣቅማቸው በላይ እየሆነ በመምጣቱ ነው።

የነጋዴዎቹ ዓመፅ በተጋሩ መሃል ኣንደኛና ሁለተኛ ዜጋ ቆጥሮ ተጠቃሚና ተጎጂ የሚያደርግ ኣሰራር ጉዳቱ ከሚቋቋሙት በላይ ስለሆነባቸው ነው።

ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልና ስርዓት የያዘ የንግድ ስርዓት እንዲኖረን ኣበክረን እንታገል !

ትግራይ ከኣንድ ኣምባገነን ቡዱን የኣገዛዝ ቀንበር ማላቀቅ የሁላችን ትግል ያስፈልጋል።

#ነፃነታችን_በእጃችን_ነው !
አምዶም ገ/ሥላሴ የአረና ሕዝብ ግንኙነት

2 Comments

  1. We liberated Tigrai from the Amara hegemony not to give our hard earned money to businesses outside . Tigrai is for Tigraians only .

  2. የወያኔ ውድቀትና መንኮታኮት የሚመጣው በትግራይ ህዝብ ነው። ለዘመናት በስሙ እየነገድ ራሳቸውንና ዘመዶቻቸውን ጠቅመው ሌላውን ህዝብ ራቁቱን ያስቀሩት እነዚህ አረመኔዎች ምንም ሃይል ቢጠቀሙ ቀኑ እንደመሸባቸው ልባቸው ይነግራቸዋል። ከጎረቤትና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አቃቅረውና አራርቀው አፍነው የያዙት የትግራይ ህዝብ መነሳቱ አይቀሬ ነው።እየተነሳም ነው! በመሰረቱ የትግራይ ህዝብ ጭቆና ሲበዛበት ሆ ብሎ መነሳቱ በወያኔ ዘመን የተጀመረ አይደለም። ያው ግን አለ አደል ጀግንነት፤ ሃገር ሌላውም ታሪክ የሚጀምረው ከወያኔ ነው እየተባለ ውሸት የሚጋተው ይህ ህዝብ አንገፍግፎታል። እነርሱ በውስኪ እየተራጩ ለጎረሱት እንጀራ ማወራረጃ የሃይላንድ ውሃ የሚቀርብላቸው እነዚህ የፓለቲካ ቀበጦች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት አንዴ ከዶ/ር አብይ ጋ ሌላ ጊዜ ከንስሃ አባታቸው ከሻቢያው አለቃ ጋ ሲላተሙ ማየት ወይ ጉድ ለካ የእሳት ራት እሳትን የምትዞረው እንዲሞቃት ሳይሆን ለማረፍ ፈልጋ ነው ያስብላል።
    ወያኔ አረመኔ ነው። ሌባ ነው፡ ከጣሊያኑ ግራዚያኒ ይከፋል ስንል በመረጃ እንጂ እንዲሁ በነሲብ ከሚያልፍ ውሃ ከተቀዳ ወሬ አይደለም። ፕ/ሩ በውሸት ማህተም በተመታ ክስ ዘብጥያ ወርደዋል። ከዚያም አጋቾቻቸው ቀስ በቀስ መርዛማ ነገር ከምግብ ጋር እያቀመሱ ወደ ሞት አፋፍ አድርሰዋቸዋል። ከዚያም የማይተርፉ መሆናቸውን የተረዳው የወያኔው ዶክተር ዶክተሩ ውጭ እንዲሄድና እዚያው ሞታቸውን እንዲረድ ያመቻቻል። ፕ/ሩ በአንዲት የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ህክምና ተከታትለው አረፉና አስከሬናቸው ሃገር ቤት ይላካል። በቀብራቸው ላይ ወያኔ ሳይለንሰር የተገጠመበት ሽጉጥ አስታጥቆ ሰላዪችና ገዳዪቹን ያሰማራል። ቁጥሩ ትዝ ባይለኝም ካልቃሽ መካከል ሰው ተዝለፍልፎ ሲወድቅና ደም ሲፈሰው ማየት ግራ ያጋባ ነበር። ቆይቶ ግን ጭብል አጥላቂዎች የሰው ነፍስ ቀጣፊዎች ወያኔዎች ሰዎችን እየመረጡ እየገደሉ እንደሆነ ሰው ይነቃል። በእንባ መካከል ደም በደም መካከል እንባ። ቀብሩ ሊፈጸም ሲል እዚህ አይቀበሩም ተብሎ ሌላ ቦታ ተወስደው አረፉ። ይህ ሰው ፕ/ር አስራት ወ/የስ ናቸው። በፕ/ሩ ላይ የተሰራው ደባና ሴራ ከጓዳቸው ይጀምራል የሚሉም ነበሩ። ከጓዳ ሆነ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ሃገሪቱ የገደላትና የሸጣት የሚፈላሰስባት ሃገሬ ያለው ደግሞ በግፈኞች አፈር የሚመለስባት ለመሆኑ የአሁንና ያለፈ ታሪካችን ምስክር ነው። ወያኔ ስብዕና የለም። ሃዘን ቤት ተቀምጦ የሃዘን ንፍሮ እየበላ ንፍሮው ላይ መርዝ የሚጨምር የማፊያ ድርጅት ነው። አሁን ሱፍና ገበርዲን ለብሰው በከረባት ታንቀው ሰው መስለው የሚታዪት አቶ መስፍን ስዪም ስንት ግፍ እንደሰሩ የሥራ ባልደረቦቻቸው ይናገሩ። ከወያኔ ወያኔ የሚሻል የለውም። ሁሉም ደም አፍሳሾችና ዘራፊዎች ናቸው። ለምሳሌ እንውሰድ አምባሳደር ብርሃኔ ገ/ክርስቶ በብራስለስ የሰራው ግፍና የዝርፊያ ጥልፍልፍ አዲስ አበባ ቤ/መንግሥት ድረስ ነው። ያልተሰራ ግፍ የለም። የሰው አንገት ቀልተው አዲስ አበባ ውስጥ ከቤተ መንግሥቱ ውጭ አንጠልጥለዋል።
    የትግራይ ህዝብ እነዚህን አረመኔዎች ከራሱ መንጥሮ ህዝቡ በመረጠውና ለህዝብ በሚያስቡ እስካልተካቸው ድረስ ወያኔ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት ጦርነት መክፈት፤ ተወረራችሁ ማለት፤ ተከባችሁሃል እያለ ማስፈራራት ሌላም ክክፋት ጆንያቸው ውስጥ በየጊዜው የመከራ ዶሴ እያወጡ ለመሰንበት መጣራቸው አያቋርጥም። ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ላፍታም ሆነ እፎይ ለማለት ወያኔን ከሥር መሰረቱ መንጥሮ በአዲስና አርቆ በሚያይ ትውልድ ሊተካው ያስፈልጋል። ያለዚያ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሁሉጊዜ ሲያለቅስ ይኖራል እንደሚሉት ነው። 45 ዓመት በወያኔ ሥር በቂ ነው። ለዛቸው ተሟጦ የሞት ሽታ ብቻ ሆነዋልና ይብቃ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.