ከስምንት መቶ ግራም በላይ ወርቅ እየመዘኑ ሲከፋፈሉ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ

98354129 2849393251796643 7029888838143049728 n e1589912590548ከ 800 ግራም በላይ ወርቅ በተሸከርካሪ ውስጥ ሆነው እየመዘኑ ሲከፋፈሉ የተገኙ 3 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የሳሪስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ፡፡

ግለሰቦቹ ቀደም ሲል በአንድ የወርቅ መሸጫ ሱቅ ላይ የስርቆት ወንጀል ስለመፈፀማቸው ማስረጃ መገኘቱንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ዳማ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የወርቅ መሸጫ ሱቅ ላይ 60 ሺ ብር ግምት ያላቸው የጣት ቀለበቶች ገዢ መስለው በገቡ ግለሰቦች መሰረቃቸውን እና ፖሊስ የፈፃሚዎቹን ማንነት በማወቅ ለመያዝ ክትትል እያደረገ ባለበት ሁኔታ ግንቦት 6 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 6 ሰዓት ተኩል ገደማ በክፍለ ከተማው ወረዳ 9 ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 3 ግለሰቦች በተሽከርካሪ ውስጥ ሆነው ባለ 14፣ ባለ 18፣ እና ባለ 21፣ ካራት በአጠቃላይ 886 ግራም ወርቅ ይዘው እየመዘኑ ሲከፋፈሉ በክትትል ፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ሊያዙ መቻላቸው ተገልጿል።

አንደኛው ግለሰብ እጅ ላይ በወቅቱ 80 ሺ ብር እንደተገኘ ምክትል ኢንስፔክተር አበራ አስረድተዋል።

ቀደም ሲል ሳሪስ ዳማ ሆቴል አካባቢ የስርቆት ወንጀል በተፈፀመበት የወርቅ መሸጫ ሱቅ ውስጥ የተገጠመው የደህንነት ካሜራ የፈፃሚዎቹን ማንነት ቀርፆ እንደነበረ ያስረዱት መርማሪው የተጠርጣሪዎቹ ምስል ሲታይ ወንጀሉን የፈፀሙት ወርቅ ሲከፋፈሉ የተያዙት የ ሶስቱ ግለሰቦች ምስል መገኘቱን እና የግል ተበዳዮችም ከሌሎች ተጠርጣሪዎች መሃል በምስሉ ላይ ያሉትን ሶስቱን ግለሰቦች መርጠው መለየታቸውን ገለፀዋል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ነው ያሉት መርማሪው ገዢ መስለው የሚመጡ ሁሉ ገዢ ስላልሆኑ በተለይም የወርቅ ጌጣ ጌጦች በቀላሉ ሊያዙና ሊደበቁ የሚችሉ በመሆኑ በጌጣ ጌጥ መሸጫ ሱቆች ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች እስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ኢ ፕ ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.