በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ወሰን የማካለል ተግባር ያለቀለት እና ችካል የመትከል ጉዳይ አለመሆኑ ተሰምሮበታል – ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን

Demekeበኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ወሰን የማካለል ጉዳይ ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ፤ ወቅታዊ ሁኔታውን ባገናዘበ፣ “ያገባኛል” የሚሉ አካላት ሙሉ ተሳትፎ ባካተተ እና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ አግባብ የሚከወን እንጂ፤ ወሰን የማካለል ተግባር ያለቀለት እና ችካል የመትከል ጉዳይ አለመሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ-ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ስብሰባ ከግንቦት 8-10 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ተገናኝቶ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው፣ በድንበር ጉዳዮች እና አዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ እና ደህነንት ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል።

የፖለቲካ ውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል መልካም ግንኙነትን፣ ሰላምን፣ አብሮ መኖርን እና በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ የረጅም ጊዜ ግንኙነቶችን በሚያጠናክር መንፈስ መካሄዱን ም/ጠ/ሚ/ር አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ በሁለቱ አገራት አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታዩ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፤ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ አፈናና የመሳሰሉ ህገ ወጥ ድርጊቶችን በጋራ ለመከላከልና መፍትሄ ለመሻት የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል።

የወሰን መካለል ጉዳይ በተመለከተ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያሻግር እና የአካባቢውን ሕዝቦች ዘላቂ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መወሰድ እንዳለበት ግንዛቤ ተፈጥሯል ሲሉ ተናግረዋል።

የሁለቱ አገራት አጎራባች የአስተዳደር አካላትም በየጊዜው እየተገናኙ ልዩነቶችን በማጥበብ በጋራ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ መምከር እንዳለባቸውም መግባባት ላይ ተደርሷል።

ሁለቱ ወገኖች ቀጣዩን የኢትዮ-ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ስብሰባ በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም አጋማሽ በካርቱም ለማድረግ መስማማታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

2 Comments

  1. As long as the two regions Oromia and Tigrai keep widening the Ethiopian defense forces will stay put taking no military actions , actually the Ethiopian Defense high ranking officials currently are busy land grabbing the fertile farm lands of Gambella getting ready to monopolize the farming industry .
    There is a huge military / Oromo farmers camp being built in Gambella right now.

  2. አቶ ደመቀ ወይ ካነበቡት ወይ ሰዉ ሹክ ብሎት ጆሮዎ ቢደርስ ደስ ይለኛል። ሱዳን በግብጽ ግፊት ኢትዮጵያን ለጥጣ መያዝ ትፈልጋለች ሁኔታዉ ሊያጋድል የችላል ብለዉ ስምምነት ያልሆነ ስምምነት አትፈርሙ።፡በተለይም እርሶና አቶ ገዱ የአማራን መሬት በዲፕሎማሲ ሰጥቶ መቀበል በሚባል ተረት አሳልፋችሁ ከሰጣችሁ አካባቢዉ ላይ ስማችሁ ከመጥፋቱም በላይ ተወላጆቻችሁም ትልቅ መከራ እንደሚገጥማቸዉ አስቡበት ይህ ሁኔታ ከማንም ባለስልጣን በላይ እናንተን ይመለከታል።
    የኢትዮጵያ ልጆች በራሳቸዉ ተነሳሺነት ከየቦታዉ ብቅ ብቅ እያሉ ተአምር እየሰሩ ስለሆነ የግብጽ ጉዳይ ሊያሳስባችሁ አይገባም ሱዳን አለኝ የምተለዉ መሬትም ጊዜ አይታ ነዉ ። ትግሬዎችም ኢትዮጵያዊ እንዲሆኑ የበጀቱን ሸምቀቆ መሳብ ነዉ ሌላዉን ጊዜዉ ሲደርስ እንመክራለን። ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለመበተን ካላችሁ እቅድ የተነሳ ሰሜኑን ለሻቢያ ምእራቡን ለሱዳን ኬንያ አልጠየቀም እንጂ ከትግሬ ክልል በስተቀር ሁሉንም ይሰጡት ነበር ታዲያ ጥጋባቸዉን አይቶ ያዘነዉ የኢትዮጵያ አምላክ የምጽአት ጊዜ እስኪሰባሰቡ በትኗቸዋል በዉኑ አለም የሉም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.