/

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ ተጨማሪ 35 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ታወቀ

Health Mተጨማሪ 35 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 352 ደርሷል።

የጤና ሚኒስትሯ እንዳስታወቁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው እድሜያቸው ከ18 እስከ 80 ዓመት የሆኑ 17 ወንድና 18 ሴት ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተለዩት 29 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) ፣ 4 ሰው ከሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ እንዲሁም 1 ሰው ከማራ ክልል አጣየ ለይቶ ማቆያ መሆናቸው ታውቋል።

ከነዚህ መካከልም 6ቱ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 24 በበሽታው ከተያዘው ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸውና 5 ሰዎች ደግሞ የወጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክክ እንደሌላቸው ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 229 ናቸው።
ተጨማሪ 3 ሰው ያገገመ ሲሆን እስካሁን 116 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እስካሁን አጠቃላይ 59, 029 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑን መረጃው ያሳያል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰንብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገበር አሳስበዋል።

1 Comment

  1. በጣም አስቸኳይ/Top Urgent/

    ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማሰሱ ስራ በደንብና በተቀናጀ ሁኔታ መቀጠል አለበት፡፡ አዳዲስ ሰዎች መገኘቱ ብዙ ጠቋሚ ነገር ስላለው ሰዎቹ የሚኖሩበት፣ የሚሰሩበት እና በወር ውስጥ የት የት አካባቢ እንደነበሩ በማጣራት በየቦታው የመርመር ስራ ጊዜ ሳይጠው ሊከናወን ይገባዋል፡፡
    የቅስቀሳ ስራው፣ መታጠቢያና ሳኒታይዘር የማቅረብ ስራ ቀድሞ ተጀምሮ ስለነበር በአሁኑ ጊዜ መሰላቸት ደረጃ ደርሶ የተወም ስላለ ክትትል የሚያደርግ ግብረ-ሃይል ከፖሊስ፣ ወረዳ እና ታዋቂ ግለሰቦችን ወይም አርቲስቶችን በማካተት በየሰፈሩና አካባቢው ሊሰራ ይገባል፡፡ መራራቅ እንዲከበር እና ማሰክ ማድረግ ግዴታ ሊሆን ይገባል፡፡ ህፃናት እንዳይወጡ መከልከልና ይህንን የማይፈፅሙ ላይ ጊዚያዊ እርምጃ መውሰድ ያስገባል፡፡ ይህ በአፋጣኝ ካልተደረገ ነገ የማይወጡት ችግር ላይ እንዳይደረሰ፡፡ እንደውጪዎቹ Lockdown ማድረግ ባይቻልም አስቸኳይ አዋጁን ያለአግባባ ሳይጠቀሙ /Abuse ሳይደረግ/ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል፡፡ ምግብ ቤቶችና ካፌዎች በሚኖራቸው የወንበር ብዛትና ስፋት ሊያስናግዱት የሚገባው ሰው ብዛት እየተወሰነ በአግባቡ እየፈፀሙ ለመሆኑ የህግ አካላት እየገቡ መቆጣጠር ይኖርባቸዋል/የእጅ መንሻ መፈለግ ቀርቶና የሚሰጡ ባለቤቶችም እንደሚጠየቁ በማሳሰብ/፡፡

    በየጤና ጣቢያዎችም አንድ ግለሰብ ቫይረሱ ተገኘበት ሲባል የሚደረግ ጥንቃቄና በአንቡላንስ መኪና የመውሰድ ስራ ላይ ብዙ ቸልተኛ ስራ እየተደረገ ስለሆን መስተካከል ይኖርበታል የሚቆጣጠራቸው አካልም ያስፈልጋል፡፡ በየሱቁና ንግድ ቦታዎች ከአስተናጋጆቹ ጀምሮ ድንቡን በማያከብሩ ላይ መጀመሪያ ባለንብረቶቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማደረግ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ስንት ደረሰ እያሉ surprise ከመሆን አሁኑኑ ሁሉንም ጥንቃቄዎች ማስተግበር ያስፈልጋል፡፡ በእምነት ተቋማት አካባቢም በሀይማኖት ሰዎች በደንብ ሊነገር ይገባል መተፋፈግ እንዳይፈጠር፡፡ ዘግይቶ ቫይረሱ የገባባቸው የደቡብ አሜሪካ አገሮች ላይ እያስከተለ ያለው ችግር እየታየ ስለሆነ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

    አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.